TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update! " መሬቱ ጭራሽ በNGO እጅ ገብቶ አያውቅም ከመጀመሪያው ጀምሮ የቤተ ክርስቲያኗ እጅ የነበረ ነው " - ቤተ ክርስቲያኗ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን 40 በመቶ የሚሆነው የኩሪፍቱ ማዕከል ይዞታዋን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር " በጉልበት ሊወስደው ነው " ስትል በተደጋጋሚ መግለጿ ይታወቃል። ለቤተ ክርስቲያኗ ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጥ ቲክቫህ ትላንት የጠየቅነው የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር…
" የሚዲያ ዘመቻችሁን እንድታቆሙ እንጠይቃለን " - የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር

የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ፥ " በሕገ-ወጥ መንገድ ረዘም ላለ ጊዜ ሳይለማ የቆየ 280,000 ካሬ ሜትር ለልማት እንዲውል ማድረግ ሕገ- መንግስትን ማስከበር እና ማክበር እንጂ የሚያስወቅስ ጉዳይ አይደለም " አለ።

ይህን ያለው ዛሬ ባወጣው ማሳሰቢያ ነው።

አስተዳደሩ ፥ " ሕግ እና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ማስከበር የአንድ የመንግስት አካል ሃላፊነት ሆኖ እያለ ለ40 ዓመታት ያለ ልማት ( ያለ ህዝብ ጥቅም) የቆየ 280,000 ካሬ ሜትር ስኩዌር (የህዝብ እና የቀጣይ ትውልድ ውስን ሐብትን በሕገ -ወጥ መንገድ በየትኛውም መንገድ በሚዲያ ጫናም ሆነ በጉልበት ይዞ መገኘት ወንጀል ነው " ብሎታል።

" በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ኩሪፍቱ ሃይቅ ዙርያ የሆነው እንደሱ ነው " ሲል አክሏል።

ከተማ አስተዳደሩ ፥ " የመንግስት እና የሀዝብ ውስን ሃብትን የመጠበቅ ፥የማስተዳደር እና ለልማት እንዲዉል የማድረግ ህዝባዊ ፣ መንግስታዊ ግዴታ እና ተጠያቂነት አለበት " ያለ ሲሆን " ተደጋግሞ የሚደረግብን የሚዲያ ጥላቻ እና ዘመቻ የህዝብን ጥቅም ከማረጋጋጥ ጉዞዋችን ቅንጣት የማይገታን መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን " ብሏል።

" የከ/መስተዳድሩ ይህን መሬት ለልማት እንዳያውል በሃይማኖት ሽፋን ሕገ- ወጥ ሁከት እና ዘመቻ እያደረጋችሁ ያላችሁ አካላት በሙሉ ከድርጊታቸሁ እንድትታቀቡ " ሲልም አሳስቧል።

" ከዚህ ውጪ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ላይ የሕግ-የበላይነት ለማስከበር እንገደዳለን " ሲልም አስጠንቅቋል።

" የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ይህንን ተረድተዉ የተጀመረውን ሃገራዊ እና የሕዝቦችን ተጠቃሚነት ጉዞ የሚያደናቅፍ የሚዲያ ዘመቻውን እንድያቆምልን እንጠይቃለን " ብሏል።

#Bishoftu

@tikvahethiopia