TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አሜሪካ

ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ ፤ በሉዊዚያና ግዛት ከታች አንስቶ እስከ ዩኒቨርሲቲ ባሉ በሁሉም የመማሪያ ክፍሎች ውስጥ አስርቱ ትዕዛዛት እንዲለጥፉ ታዟል።

ትላንት ደግሞ የኦክላሆማ ግዛት በአስቸኳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እንዲጀመር አዟል።

የግዛቱ ትምህርት ቢሮ በግዛቱ ያሉ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች መጽሐፍ ቅዱስን በትምህርት ስርዓታቸው በአስቸኳይ እንዲያካትቱና እንዲያስተምሩ መመሪያ አስትላልፏል።

በግዛቱ የትምህርት የበላይ ተቆጣጣሪ ሪያን ዋልተርስ የተላከ መመሪያ " አፋጣኝ እና ጥብቅ ተፈጻሚነትን " የሚፈልግ አስገዳጅ ድንብ ነው ይላል።

ዋልተርስ " መጽሐፍ ቅዱስ ታሪካዊና ባህላዊ መሠረት ነው "  ብለዋል።

" ያለ መጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ እውቀት የኦክላሆማ ተማሪዎች የአገራችንን መሠረት በትክክል መረዳት አይችሉም " በማለት ነው በአስቸኳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እንዲሰጥ መታዘዙን ያመለከቱት።

በግዛቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ይተገበራል።

ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ እያንዳንዱ ክፍል መጽሐፍ ቅዱስ ሊኖረው ይገባል ተብሏል። ሁሉም አስተማሪዎች በክፍሉ ውስጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ማስተማር እንዳለባቸው ታዟል።

የሲቪል መብት ተሟጋች ድርጅቶች ግን ይህንን ውሳኔ ተቃውመዋል።

ሃይማኖት እና መንግሥት መለያየት አለባቸው ብለዋል።

አንድ መንግሥትን ከሃይማኖት መለያየት እንዳለበት የሚሰራ ተቋም ፥ " የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ሰንበት ትምህርት ቤቶች አይደሉም " ብሏል።

" ሪያን ዋልተርስ የተሰጠውን የመንግሥት ስልጣንን አላግባብ በመጠቀም ሃይማኖታዊ እምነቱን በሌሎች ላይ ለመጫን እየተጠቀመበት ነው። ይህ እኛ ባለንበት ሊሳካ አይገባም " ብሏል ተቋሙ።

በአሜሪካ የሃይማኖት ነፃነትን ለማስጠበቅ የሚሰራው ኢንተርፌይዝ አሊያንስ ፤ " መመሪያው ግልጽ በሆነ መልኩ ሃይማኖትን መጫን ነው " ሲል ገልጾታል።

" እውነተኛ የእምነት ነፃነት ማለት የትኛውም የሃይማኖት ቡድን አመለካከቱን በሁሉም አሜሪካውያን ላይ እንዳይጭን መከላከል ነው " ብሏል።

#BBC #CNN

@tikvahethiopia