TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" እኔ የማውቃቸው ብቻ 6 ሰዎች ተገድለዋል " -  የዕድሜ ባለፀጋ

በአጣዬ ከተማ እና በሰንበቴ ዙሪያ የታጠቁ ኃይሎች ሰሞኑን ከፈተቱት በተባለ ተኩስ ንጹሐን መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

አንድ የአካባቢው ነዋሪ የእድሜ ባለፀጋ ፤  “እኔ የማውቃቸው ብቻ 6 ሰዎች ተገድለዋል። ወደ ደብረ ብርሃን የተላከ ቁስለኛም አለ ” ብለዋል።

ይህ መረጃ የአንድ አካባቢ ብቻ እንደሆነ ነው ያስገነዘቡት።

“ ካራ ለጉማ አዲስ አበባ መርካቶን ነው የሚመስለው ከአጣዬ በመጡ ተፈናቃዮች። ከዛፍ ስር፣ ት/ቤት ነው የተጠለሉት ” ብለዋል።

" አጣዬ 01 ቀበሌ ዘረፋ ነበር ፤ ሰንበቴም በተመሳሳይ ፤ አጣዬ ከተማ በጣም ወድሟል” ሲሉ አስረድተዋል።

ከኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አንድ የሰንበቴ ነዋሪ በበኩላቸው ሰሞኑን የተኩስ ጥቃት እንደነበር ተናግረው  “ የኦሮሞ ተወላጆችም በ ' ፋኖ ' ታጣቂዎች ተገድለዋል። በእኛ አካባቢ ከ5 በላይ ሰዎች ተገድለዋል ” ሲሉ ተናገረዋል።

“ በተለይ ከሳምንታት ጀምሮ ግድያ፣ ቃጠሎ ነው የሚስተዋለው። በርካታ ንጹሐን ቆስለዋል” ሲሉ ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ በአካባቢው ያለውን ሁኔታ በተመለከተ " ህዝቡ አለቀ፣ ወደ ማን አቤት እንበል ? " ሲሉ  ጠይቀዋል።

የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ ተመስገን ተስፋ ከቀናት በፊት ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፣ " ሰውም አልቋል፣ ሚሊሻውም የሚችለውን ያህል ሞከረ አለቀ " ብለው ለጥቃቱ " ሸኔ" ን ተጠያቂ ሲያደርጉ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ደግሞ ለጥቃቱ " ፋኖ " ን ተጠያቂ ሲያደርግ ተስተውሏል።

ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ መካሻው፣ ስልክ ባያነሱም “ ስብሰባ ላይ ሆኘ ነው ” ያሉ ሲሆን፣ የሚመቻቸውን ወቅት ስንጠይቃቸው “ አሚኮ  ላይ መግለጫ ስለሰጠን ከዛ ማግኘት ይችላሉ ” ከማለት ውጪ በድጋሚ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

በሰሜን ሸዋ ዞንና ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አጎራባች ስፍራዎች በሚገኙ የአማራና የኦሮሚያ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ነው የተባለውን ጥቃት በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው በበኩላቸው፣ “ ስብሰባ ላይ ነኝ ” ብለዋል።

የኢፌደሪ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ፣ የኦሮሚያ ክልል ሰላምና ጸጥታና ኮሚዩኒኬሽን ቢሮዎች በተመሳሳይ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

በማንኛውም ሰዓት ማብራሪያ ከተገኘ ይቀርባል።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ምዕመናን #ክርስቲያናዊ_አለባበስ ለብሳችሁ እንድትገኙ እና የአቅማችሁን ያህል እድትለግሱ ጥሪ እናቀርባለን " - ማህበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን " ኑ ቸርነትን  እናድርግ " በሚል መሪ ቃል ነገ እሁድ ከቀኑ 7:00 ላይ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በሚሊኒየም አዳራሽ ያካሂዳል። ገቢ ማሰባሰቢያው…
#Update

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን " ኑ ቸርነትን  እናድርግ " በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

ገቢ ማሰባሰቢያው በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን ፣ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶችን ለመደገፍ የሚውል እንደሆነ ተገልጿል።

በመርሃግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት  የማኅበሩ ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም ፤ " የመርሃ ግብሩ ዋነኛ ዓላማ ባለን አቅም ሁሉ ለወገን መድረስ ነው " ብለዋል።

" ረሃብ ጊዜ አይሰጥም " ያሉት የማህበሩ ሰብሳቢ " በውጭ ድርጅቶች ፣ በመንግስትና በሌሎችም የተለያዩ አካላት ብዙ እርዳታዎች ይደረጋሉ (የምግብም የአይነትም) በተለይ ግን ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ብዙ ጊዜ ትኩረት አያገኙም " ብለዋል።

" እነዚህን ክፍተቶች እና ጉድለቶች መሙላት አለብን " ሲሉ አስገንዝበዋል።

" አሁን ላይ በየቦታው ያሉት መፈናቀሎች ፣ በየቦታው ያሉ የረሃብ ችግሮችን በማሰብ ማህበረ ቅዱሳን ሌሎች አገልግሎቶችን ገቶ መጀመሪያ ነፍስን የማዳን፤ ህይወትን የመታደግ ስራ ይቀድማል ብሎ እየሰራ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ሁሉን ማድረግ የምንችለው ስንኖር ነው " ያሉት ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ " እኛ በልተን እያደርን ሌሎች ወገኖቻችን በረሃብ እና ጥማት መሞት ስለሌለባቸው ' ኑ ቸርነትን እናድርግ ! ' በሚል በዚህ በታላቁ ዐብይ ጾም ወቅት ዝግጅቱ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

ዛሬ ሚሊኒየም አዳራሽ መገኘት ያልቻሉ ምዕመናን በየቤታቸው ሆነው በማህበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም የሂሳብ ቁጥሮች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000309803648 ፣ አሃዱ ባንክ 0025393810901 ፣ ወጋገን ባንክ 0837331610101 ፣ አቢሲንያ ባንክ 37235458 ፣ አዋሽ ባንክ 01329817420400 ድጋፍ ማድረግ ይቻላሉ ተብሏል።

ፎቶ ፦ ከማኅበረ ቅዱሳ ቴሌቪዥን

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሊዝ #አዲስአበባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ መሬትን በሊዝ ለማስተላለፍ 2ኛ ዙር ጨረታ አውጥቷል። መሬትን በሊዝ የማስተላለፍ ተግባር ለአራት ዓመታት ከተቋረጠ በኋላ ግንቦት 5 ቀን 2015 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል፡፡ 2ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታም ረቡዕ ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም መውጣቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቢሮና ከአዲስ ልሳን ጋዜጣ መረጃውን አግኝቷል። …
በአዲስ_አበባ_2ኛው_ዙር_የመሬት_ሊዝ_ጨረታ.pdf
5.3 MB
በአዲስ አበባ ከተማ የ2ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክ/ ከተማ (ፒያሳ) በዓድዋ ድል መታሰቢያ አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ ፦
- በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣
- በኮልፌ ቀራንዮ፣
- በአራዳ፣
- በአቃቂ ቃሊቲ፣
- በየካ፣
- በቦሌ፣
- በአዲስ ከተማ፣
- በቂርቆስ፣
- በጉለሌ
- በልደታ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ እንደሚፈልግ አሳውቋል።

(ዝርዝር የጨረታው መረጃ በPDF ተያይዟል - ይመልከቱ)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ የጨረታ መረጃ ባለቤት አዲስ ልሳን መሆኑን ያሳውቃል።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

አዋኪ ድርጊት በሚፈፀምባቸው ንግድ ቤቶች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

ሰሞኑን በቦሌ ክፍለ ከተማ ከ3 ሺህ 80 የሺሻ ዕቃ እና 80 ኪሎ ግራም አደንዛዥ ዕፅ ተይዞ መወገዱን ገልጿል።

በህጋዊ ንግድ ሽፋን ሺሻ እና አደንዛዥ ዕፅ ሲጨስባቸው ከተገኙ ቤቶች ነው ይሄ የተያዘው።

ፖሊስ በሰጠው መረጃ በድንገተኛ ቁጥጥር ከተደረገባቸው መካከል ፦
- መኖሪያ ቤቶች
-  ፔንሲዮኖች፣
- ማሳጅ ቤቶች እና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ይገኙበታል፡፡

ይህ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለይም በአዲስ አበባ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ያለው አዋኪ ድርጊት እጅግ ትኩረት የሚሻ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ የደረሰው መልዕክት ያስረዳል።

በተለይ ተማሪዎች፣ ህፃናት፣ የወለዱ እናቶች፣ ቀን ስራ ደክመው የሚገቡ በርካታ ዜጎች ባሉባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ብዙ አዋኪ ድርጊቶች በመኖራቸው ትኩረትን ያሻል።

የግል መኖሪያ ቤቶች ለሺሻ ማጬሻ ፣ ለመጠጥ መጠቻ፣ ለሲጋራ ማጬሻ እየዋሉ ማህበረሰቡ እንደሚታወክ ተጠቁሟል።

ምሽት ላይም ቢሆን ከጭፈራ ቤቶች የሚወጣው ድምጽ ማህበረሰቡን ሰላም የሚነሳ በመሆኑ ቁጥጥር እንዲደረግ ተጠይቋል።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia