TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#HawassaUniversity

በህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተለጠፈው ማስታወቂያ ምንድነው ? ዩኒቨርሲቲውስ ምን ምላሽ ሰጠ ?

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚማሩ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲልኩ ነበር።

ለዚህ ቅሬታ መነሻቸውም አንድ ተለጥፎ ያዩት ማስታወቂያ ነው።

ማስተወቂያው ፦

° በ12ኛ ክፍል ፈተና ምክንያት ተማሪዎች ወደቤት መሄዳቸውን ይጠቁማል።

° የገበያው አለመረጋጋት አቅራቢዎች ላይ በፈጠረው ከፍተኛ ጫና እና በቀን ለ1 ተማሪ የተወሰነው 22 ብር ዕለታዊ ወጪ ጋር ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ላልተወሰነ ጊዜ የመግቢያ ቀን መራዘሙን ያሳያል።

° ኢንተርን ሽፕ ላይ ያሉ እና ካፌ ተጠቃሚ የነበሩ እጩ ዶክተሮች በምግብ ምትክ የሚሰጠውን የነን ካፌ ፎግም ሞልተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይላል።

° የተማሪዎች መግቢያ እስኪገለጽ ከቀን 29 /11/ 2016 ዓ/ም ጀምሮ የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ በመቋረጡ በተለያዩ ምክንያቶች ግቢ ያሉ ተማሪዎች በ4 ቀን ለቀው እንዲወጡ ይላል።

የተማሪዎች ቅሬታስ ምንድነው ?

መልክዕታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ ተማሪዎች ትልቅ ቅሬታ እንዳላቸው ይገልጻሉ።

ቅሬታቸው ፦

- ላለፉት ስምንት ዓመታት ትምህርት ላይ ብንሆንም አሁንም በተለያየ መልኩ ጊዜያችን እየተቃጠለ ነው።
- የመመረቂያ ጊዜያችን አሳሳቢ ሆኗል።
- መግቢያችን ለሁለተኛ ጊዜ መራዘሙ ትክክል አይደለም።
- በኮቪድ-19 ለአስር ወራት እንዲሁም በ12ኛ ክፍል ፈተና ምክንያት የትምህርት ጊዚያችን ተቃጥሏል። ወሁን የመመረቂያ ጊዚያችን ተራዝሟል።
- በዚህ ዓመት ለ12ኛ ክፍል ፈተና እንድንወጣ ተደርገን ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም ነው የተጠራነው። በኋላም ወደ ሐምሌ 25/2016 ዓ.ም ተገፋ። አሁን ደግሞ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ሰማን። ይህ ትክክል አይደለም።
- የሚመለከተው አካል መፍትሔ ይስጠን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተማሪዎች ቅሬታን እንዲሁም የተለጠፈውን ማስታወቂያ ይዞ ዩኒቨርሲቲው አለኝ የሚለውን ማብራሪያ ለተማሪ እንዲሰጥ ጠይቋል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ  ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ተባባሪ  ፕሮፌሰር አለሙ ጣሚሶ ምን አሉ ?

የቀረበዉ መረጃ ትክክል አይደለም።

ኢንተርን ሀኪሞች ከግቢ አይወጡም። ዶርማቸውንም አይለቁም። ይልቁንም ለተወሰነ ጊዜ የዩኒቨርስቲው የምግብ አገልግሎት በመቋረጡ በጀታቸዉን እንዲጠቀሙ ነው የተገለጸው።

ይህ የሆነው አሁን ላይ ለ3 አመት ውል የገቡ ነጋዴዎች በእቃ መወደድ ምክኒያት ምንም አይነት የምግብ ግብአት ሊያቀርቡልን ባለመቻላቸዉና ይህን ችግር  ተወያይተን መፍትሄ እስክንሰጠዉ ነው።

ሌሎች ተማሪዎች ቅድመ ዝግጅት ከተጠናቀቀ በቅርቡ ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሳሉ። ትክክለኛ ቀኑንም  ለተማሪዎች በይፋ ይነገራቸዋል።

ተማሪዎችን አሁን ላይ መቀበል ያልተቻለው ከምግብ አቅርቦትና አንዳንድ ማስተካከያ የሚፈልጉ ጉዳዮች ስላሉ ነው።

በየጊዜዉ ለ12ኛ ክፍል ፈተና ሲባል ከግቢ መውጣታቸውን ሆነ አሁን ላይ በቶሎ አለመግባታቸው የሚወስድባቸውን ጊዜ  ለማካካስ ዩኒቨርሲቲው መፍትሄዎችን አስቀምጧል። በዛ ይሄዳል።

ተማሪውን የሚያደናግር ማስታወቂያ ያወጣዉ አካል ከኛ እውቅና ዉጭ በመሆኑ ማንነቱን አጣርተን እርምጃ የምንወስድ ይሆናል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ሳይንስ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝደንቱ ተማሪ ደረጀ መንገሻ ምን አለ ?

👉 ኢንተርን ዶክተሮች ከግቢ ባለመውጣታቸዉ እስካሁን መጉላላት አልደረሰባቸውም። ማስታወቂያውም ያለኛ እውቅና ነው የተለጠፈው።

👉 ተማሪውን ሳይፈልግ ወደነን ካፌ መቀየር አግባብ ስላልሆነ ለዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች ውሳኔዉ ልክ አለመሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ አስገብተን ምላሽ እየጠበቅን ነው።

👉 ተማሪዎች ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ/ም ያልገቡበት ምክኒያት ዩኒቨርሲቲዉ ከበጀት ማስተካከያና ካምፓስ ውስጥ ከሚያስተካክላቸው አንዳንድ ነገሮች ጋር በተያያዘ ምክኒያት ነው።

👉 ተማሪዎች በጊዜ ወደ ግቢ ባለመግባታቸው በቀጣይ ተማሪዎች ላይ የሚከሰተዉን ጫና በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው እንዲያስብበት ተነጋግረናል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

More - @tikvahuniversity

@tikvahethiopia