TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጋምቤላ

ጋምቤላ ዩኒቨርስቲ አንድ ተማሪው እንዲሁም አንድ መምህሩ ህይወታቸው ማለፉን አሳወቀ።

የዩኒቨርሲቲው የ2ኛ ዓመት የአካውንቲንግ ተማሪ የነበረው ኡጁሉ ቲሞቲ ቱትላም ሐምሌ 9/2015 ዓ.ም ህይወቱ ማለፉን ተቋሙ ገልጿል።

ተቋሙ የተማሪውን ህልፈት በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።

በሌላ በኩል ፤  በተቋሙ የሳይኮሎጅ ትምህርት ክፍል መምህር የነበሩት ኳንግ ኒያል ፖች ሀምሌ 11/2015 ዓ.ም ህይወታቸው ማለፉን ጠቁሟል።

በመምህሩ ህልፈት ላይም ዩኒቨርሲቲው ዝርዝር መረጃ ይፋ አላደረገም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Addis lissan .pdf
#AddisAbaba

የ 'ሊዝ ጨረታ አሸናፊ' ሆነው ባልቀረቡ ተጫራቾች ምትክ ዕድል የተሰጣቸው የሁለተኛ አሸናፊዎች በተሰጠው ዕድል የማይጠቀሙ ከሆነ ጨረታው ተሰርዞ መሬቱ ወደ መሬት ባንክ ሊገባ እንደሚችል ተጠቁሟል።

የአ/አ ከተማ አስተዳደር ከሳምንታት በፊት ባወጣው የመሬት ሊዝ ጨረታ ተወዳድረው በአንደኛ ደረጃ ካሸነፉ 287 ተጫራቾች መካከል 156 የሚሆኑ አሸናፊዎች በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው የሊዝ ውሉን ባለመዋዋላቸው፣ ሁለተኛ ለወጡ ተጫራቾች ጥሪ አቅርቧል።

ነገር ግን የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ባቀረበው ጥሪ በሁለተኛ ደረጃ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ሳይሆን፣ አንደኛ የወጡ ተጫራቾች ያቀረቡትን ዋጋ ከፍለው የሊዝ ውል እንዲዋዋሉ መባሉ ቅሬታ ፈጥሯል፡፡

ምንድነው ቅሬታው ?

ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ 2ኛ ደረጃ አሸናፊ ፦

" ሁለተኛ አሸናፊዎች በሰጠነው ዋጋ ውል እንዋዋል የሚል መከራከሪያ ሐሳብ ቢያቀርቡም የከተማ አስተዳደሩ አይሆንም የሚል አቋም ይዟል፡፡

የጨረታ ሰነዱ ላይ እንደቀረበው፣ አንደኛው ተጫራች በሌላኛው ዋጋ ላይ ተመሥርቶ ዋጋ መስጠት አይችልም፤ ይህም የአንድን ተጫራች ዋጋ ማስተላለፍ (Reshuffle) አይችልም የሚል አንድምታ ያለው ነው።

አስተዳደሩ በሁለተኛው አሸናፊ ውል እንዳይገባ ከተደረገበት ምክንያት ውስጥ ተጫራቾች ተመሳጥረው አሻጥር ለመሥራት ነው ከሚል ዕሳቤ የመነጨ ነው ቢባል እንኳን፣ በአንደኛ አሸናፊ ዝርዝር ላይ የቀረበው ከፍተኛ የዋጋ ልዩነት ይህንን ለማለት የሚያስደፍር አይደለም።

አንደኛ አሸናፊዎች ባቀረቡት ዋጋ መዋዋል አዳጋች ነው። አሸናፊዎቹ ያቀረቡት ዋጋ የመሬት ሊዝ ጨረታው ከረዥም ጊዜ በዃላ የወጣ በመሆኑ በሽሚያ የተደረገና ምናልባት አዋጪ ሆኖ ቢሆን ኖሮ፣ ቢያንስ ግማሽ የሚሆኑት አንደኛ አሸናፊዎች ይካፈሉበት ነበር። "

ሌላ ስማቸው እንዲገለፅ ያልደለጉ 2ኛ ደረጃ አሸናፊ ፦

" በአንደኛ አሸናፊዎች የቀረበው ዋጋ መሬት በግለሰብ ደረጃ ከሚተላለፍበት ዋጋ በጣም ከፍተኛ የሆነና የተጋነነ ነው።

በመመርያ ላይ የተቀመጠ አሠራር ቢሆንም ዳግም ሊጤን የሚገባው ነው። "

ስለ ጉዳዩ የተጠየቁ አንድ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የሥራ ኃላፊ ፦

" በመሬት ሊዝ ጨረታው በአንደኛ ደረጃ የተገለጸ አሸናፊ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ቀርቦ ውል ካልተዋዋለ ሁለተኛ የወጡት ተጫራቾች የሚስተናገዱት አንደኛ የወጡት ተጫራቾቹ መሬቱን እንወስድበታለን ብለው ባቀረቡት ዋጋ ከቀረቡ ብቻ ነው።

ለጨረታ የቀረበው ቦታው ዋጋ ወጥቶለታል የሚለው ከመታወቁ አንፃር መሬቱን መውሰድ የፈለገ በቀረበው ዋጋ መውሰድ የሚችል ሲሆን፣ ካልሆነ ደግሞ መሬቱ ወደ መሬት ባንክ የሚገባበት አሠራር አለ።
ይህም አዲስ ያልሆነ ነባርና ቋሚ አሠራር ነው።

ለሁለተኛ አሸናፊዎች የተሰጠው ዕድል አንደኛ አሸናፊዎች መሬቱን ስላልወሰዱ የተሰጠና ለሌላ ለሦስተኛ የማይተላለፍና ለተጫራቾቹ የመውሰድ ጥቅም የሚሰጥ ነው ከዚህ በኋላ የሊዝ ዋጋ ሲሰላ የጨረታው ዋጋ ታሳቢ ተደርጎ የሚሠራ ነው። "

ማስታወሻ፦ የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ  ግንቦት 7 ቀን 2015 ዓ.ም.፣ በከተማዋ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች 297 ይዞታዎችን ለተጠቃሚዎች በሊዝ ለማስተላለፍ ጨረታ ማውጣቱ የሚታወስ ነው፡፡ በሊዝ ጨረታ እንዲተላለፉ የተዘጋጁት 297 ይዞታዎች አጠቃላይ ካሬ ሜትር 143 ሺሕ (14.3 ሔክታር) ሲሆኑ፣ ይዞታዎቹ በአሥራ አንዱም ክፍላተ ከተሞች የሚገኙ መሆናቸው ናቸው። የሊዝ ጨረታ የአሸናፊዎችም ታውቀው ስም ዝርዝራቸው ይፋ ተደርጓል።

Credit : Ethiopian Reporter

@tikvahethiopia
#ሳፋሪኮም_ኢትዮጵያ

አዲሱን የሳፋሪኮም የጽሁፍ መልዕክት ጥቅልን ገዝተን ከወዳጅ ዘመዶቻችን ጋር ደስታችንን እንጋራ። ወደ *777# በመደወል የመልዕክት ጥቅል እንግዛ

አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://publielectoral.lat/Safaricom_Ethiopia_PLC

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
#ጋሹና_ቡና ☕️

የተፈጥሮን ጣዕም ይቅመሱ፤ ምርታችን በተለያዩ አማራጮች የቀረበ ፦
✔️ በ 1ኪሎ
✔️ በ 500 ግራም
✔️በ 250 ግራም
✔️በ 50 ግራም

📍 አድራሻ ፡ ኮተቤ ካራ ዞብል ፓርክ ፊት ለፊት

ስልክ +251-9-03-91-92-93 | +251-9-79-18-15-56 | +251-9-88-80-82-42

ቴሌግራም - https://publielectoral.lat/gashunacoffe
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/gashunacoffee/
ይዘዙን ካሉበት በፍጥነት እናደርሳለን::
#NationalExam

የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ።

ተቋማቱ አጠቃላይ ያሉበትን ደረጃ እየገመገሙ ናቸው።

ፈተናው የተሳለጠ እንዲሆን ተቋማት በዚህ ሳምንት ተመራቂ ተማሪዎቻቸውን በማስመረቅ በቶሎ ይሸኟቸዋል።

ከሐምሌ 16 ጀምሮ ተቋማት ለ12ኛ ክፍል ፈተና #ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ማሳሰቡ አይዘነጋም።

ከትምህርት ምዘናና ፋተናዎች አገልግሎት ባገኘነው መረጃ መሰረት ፤ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሐምሌ 16 -17 / 2015 ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ ፤ ሐምሌ 18 የፈተና ኦረንቴሽን ይሰጣቸዋል፤  ከሐምሌ ከ19 - 21/2015 ፈተናው ለ 3ት ቀናት ይሰጣቸዋል ፤ ሐምሌ 22-23/2015 ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ይመለሳሉ።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ ሐምሌ 22 -23/2015 ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ፤ ሐምሌ 24/2015 የፈተና ኦረንቴሽን ይሰጣል ፤ ከሐምሌ 25 -28/2015 ፈተናው ለአራት ቀናት ይወስዳሉ ሐምሌ 29-30/2015 ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
" ዘንድሮ በመደበኛው 667 ሺህ 483 ፤ በግል፣ በማታ እና በርቀት 200 ሺህ 691 ተፈታኞች ፈተና ይወስዳሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ከ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ ባለፈው ዓመት የተስተዋሉ የተለያዩ እንከኖች በዚህኛው ዓመት መስተካከላቸውን የትምሕርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

ምዝገባው በማንዋል በመሆኑ ተፈጥሮ የነበረውን የተፈታኞች መረጃ አያያዝ ጥራት ጉድለት ለማረም ዘንድሮ ምዝገባው በበይነ መረብ መካሄዱን አገልግሎቱ ገልጿል።

በተጨማሪም ከዩኒቨርሲቲ ድልድል፣ ዝግጅት እና አቀባበል ጋር በተያያዘ እክሎች የነበሩ ሲሆን ዘንድሮ ችግሩ መቀረፉን አረጋግጧል።

አምና ካጋጠመው ጉድለት በመማር የፈተና ማስፈጸሚያ ማንዋል እና መመሪያውን በማዘጋጀት እና በመከለስ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደርጓል።

ባለፈው ፈተና ወቅት ተፈታኞችን ማዘጋጀት አለመቻሉ ዋና ችግር እንደነበር የጠቀሰው አገልግሎቱ በዚህ ዓመት በቂ ዝግጅት ስለመደረጉ ገልጿል።

በዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡት 869 ሺህ 802 ትክክለኛውን የምዝገባ ሂደት ያላሟሉ 1 ሺህ 213 ተፈታኞች ምዝገባ መሠረዙንም ተገልጿል።

ዘንድሮ ፦

- በመደበኛ 667 ሺህ 483
- በግል፣ በማታ እና በርቀት 200 ሺህ 691 ተፈታኞች ፈተና ይወስዳሉ።

ፈተናው በሁለት ዙር በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ይሳጣል።

የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 21 ቀን፤ ሁለተኛው ዙር ፈተና ደግሞ ከሐምሌ 25 እስከ 28 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ አገልግሎቱ አረጋግጧል።

የማኅበራዊ ሣይንስ ተፈታኞች ከሐምሌ 16 እስከ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እ
የሚገቡ ሲሆን ሐምሌ 18 ገለጻ ይሰጣቸዋል።

የተፈጥሮ ሣይንስ ተፈታኞች ደግሞ ከሐምሌ 22 እስከ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ገብተው ሐምሌ 24 ቀን ገለጻ ይሰጣቸዋል።

ተፈታኞች ፈተናውን በራሳቸው ጥረት እንዲሠሩ አሳስበው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባለፈው ዓመት የፈተና ደንብ ጥሰት የፈጸሙ 17 ሺህ ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ መሠረዙን አስታውሷል።

Credit : #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ምርቃት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከነገ ረቡዕ ጀምሮ ተማሪዎቻቸውን ያስመርቃሉ። ተቋማት ለዓመታት ያስተማሯቸውን ተማሪዎች ቤተሰቦቻቸው ፣ የክብር እንግዶች በተገኙበት ነው የሚያስመርቋቸው። ዘንድሮ ከተሰጠው የመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ በምርቃት መርሃግብር ላይ ከመሳተፍ ጋር በተገናኘ በተመራቂዎች ዘንድ ጥያቄዎች የነበሩ ቢሆንም ትምህርት ሚኒስቴር ይህ ጉዳይ የተቋማቱ #የሴኔት ውሳኔ ጉዳይ መሆኑን ገልጾ…
ከ20 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው።

በዛሬው ዕለት በርካታ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ።

ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ/ም ፦

- ጅማ ዩኒቨርሲቲ
- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ ካምፓስ)
- ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (በዋናው ግቢ)
- አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ (ዋናው ግቢ)
- ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ
- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ
- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
- ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
- ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ
- ዲላ ዩኒቨርሲቲ
- እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
- ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ (በዋናው ግቢ) 
- መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ
- ቀብሪ ድሃር ዩኒቨርሲቲ
- ወራቤ ዩኒቨርሲቲ
- ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ
- ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ
- መቱ ዩኒቨርሲቲ
- አምቦ ዩኒቨርሲቲ
- ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ
- ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ
- ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
- ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ
- ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ
- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ።

ተጨማሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መረጃዎች በ @tikvahuniversity በኩል ማግኘት ትችላላችሁ።

ተመራቂዎች እና መላው ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ !!

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከ20 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው። በዛሬው ዕለት በርካታ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ። ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ/ም ፦ - ጅማ ዩኒቨርሲቲ - ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ ካምፓስ) - ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (በዋናው ግቢ) - አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ (ዋናው ግቢ) - ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ - ጂንካ ዩኒቨርሲቲ - ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ…
አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመቄዶንያ መስራች አቶ ቢንያም በለጠ እና ለአርቲስት ደበበ እሸቱ ፤ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ለተወዳጇ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ( #ጂጂ ) የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አበርክተዋል።

አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራች አቶ ቢንያም በለጠ ላከናወኗቸው በጎ ስራዎች የክብር ዶክትሬት አበርክቶላቸዋል። በሰሩት ስራ በሰው ልጆች ደህንነት ላይ ለሀገር የማይተካ አስተዋፅኦ ማበርከታቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው አርቲስት ደበበ እሸቱ በኪነጥበብ ዘርፍ ላበረከቱት ውለታ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷል።

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ለድምጻዊት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።

ዕውቅናው ሁለገቧ አርቲስት #የኢትዮጵያን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም በማስተዋወቅ እንዲሁም በኪነ ጥበብ #የአዊን_ሕዝብ_ቋንቋ እና #ባህል በማሳደግ ላበረከተችው አስተዋፅኦ ነው የክብር ዶክትሬት የተበረከተላት።

የክብር ዶክትሬቱን የእጅጋየሁ ሽባባው ወላጅ እናት ተቀብለዋል።

@tikvahethiopia