TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#PMOEthiopia

ዛሬ ማክሰኞ የሚኒስትሮች ምክር ቤት 18ኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂዶ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

ም/ቤቱ ከተወያየባቸው ጉዳዮች አንዱ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ ደንብ ለማሻሻል በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው።

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የተፈቀደ እና የተከፈለ ካፒታል በማሻሻል የተቋቋመበትን ዓላማና ተልዕኮ ለማሳካት እንዲችል በተለይ ፦

- በግንባታ ላይ ያሉ የባቡር መሰረተ ልማቶች እንዲጠናቀቁ የተጠናቀቁትም ወደ ስራ እንዲገቡ፤

- በቀጣይ ለሚገነቡ የባቡር መሠረተ- ልማቶች የተሻለ አቅም እንዲኖረው የተፈቀደ ካፒታሉ ወደ ብር 221 ቢሊዮን ከፍ እንዲል በጥሬ ገንዘብና በአይነት የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ ብር 120 ቢሊዮን እንዲሆን ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ መቅረቡ ተገልጿል።

ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

(ተጨማሪ የዛሬ የምክር ቤቱን ወሳኔዎች ከላይ ያገኛሉ)

@tikvahethiopia
#ቭላድሚር_ፑቲን

የሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አገራቸው ሩስያ ከአፍሪካ ጋር ላላት ግንኙነት ቅድሚያ እንደምትሰጥ ተናገሩ።

ይህን ያሉት ትናንት ሰኞ ሞስኮ ውስጥ መካሄድ በጀመረውና ከ40 በላይ የአፍሪካ ሀገራት ልዑካን እየተካፈሉበት እንዳሆነ በተነገረው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ነው።

ፕሬዜዳንት ፑቲን ምን አሉ ?

" አገራችን ከአፍሪካ አገራት ጋር ለመተባበር ቅድሚያ እንደምትሰጥ እና በዚህም እንደምትቀጥል አጽንኦት መስጠት እፈልጋለሁ።

ከዩክሬን በሚቀርበው እህል ላይ የተደረሰው ስምምነት ካልታደሰ ሩሲያ ለተቸገሩ የአፍሪካ አገራት #በነጻ እህል ታቀርባለች።

በባለፉት ዓመታት ሲላክ የነበረውን የእህል መጠን ለአፍሪካ አገራት በተለይም ከሩሲያ ለሚፈልጉ በነጻ ለማቅረብ ዝግጁ ነን።

ሩሲያ የደረሰችባቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለአፍሪካ አገራት ታካፍላለች ፤ የኤሌክትሪክ ሀይል እንዲያመርቱ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች።

አፍሪካ እያቆጠቆጠ ባለው የብዝኃ የዓለም ስርዓት ላይ ስልጣኗን እና ሚናዋን ማሳደግ እንደምትቀጥል አምናለሁ። "

#BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አፋልጉን በአዲስ አበባ ሳሪስ አዲስ ሰፈር በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ትሰራ የነበረች " ቤዛዊት በቀለ " የምትባል ሞግዚት / ግለሰብ ከምትሰራበት ቤት የ2 ዓመት ህጻን የሆነችውን ሶልያና ዳንኤልን (ከላይ በፎቶ ተያይዟል) ከቤት ይዛት መሰወሯን ቤተሰቦቿ ገልጸውልናል። እናት እና አባትን ጨምሮ መላው ቤተሰብ ጭነቅት ላይ የሚገኙ ሲሆን የንፋስ ስልክ ፖሊስ መምሪያ ጉዳዩን እንዲያውቀው ተደርጓል። ህፃን…
#Update

ህፃን ሶሊያን ዳንኤል ተገኝታለች።

• " 40 ሺህ ብር ይከፈልሻል ብለው ሰዎች ስላግባቧት ህፃኗን ሰርቃ ልትሰወር መቻሏል ተጠርጣሪዋ ገልጻለች " - የአዲስ አበባ ፖሊስ

ከቀናት በፊት በሞግዚቷ ተሰርቃ የተወሰደችው የ2 ዓመቷ ህፃን ሶሊያና ዳንኤል ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር ባደረገው ጠንካራ ክትትል ሱሉልታ ከተማ ላይ መገኘቷን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

የሁለት (2) ዓመት ዕድሜ ያላት ህፃን ሶሊያና ዳንኤል ሳሪስ አዲስ ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሃሙስ መጋቢት 7 ቀን 2015 ዓ/ም ረፋድ ላይ ቤዛ በቀለ በተባለችው የቤት ሰራተኛቸው ተሰርቃ ስለመወሰዷ ይህን ተከትሎ የወላጆቿ የአፋልጉን ጥሪ ሲሰራጭ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ በህፃኗ ወላጆች የቀረበለትን አቤቱታ ተቀብሎ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀትና ከአዲስ አበባ ውጪ ወደተለያዩ የሃገራችን ከተሞች እና አካባቢዎች በመሄድ ጭምር አስፈላጊ መረጃዎችን በፖሊሳዊ ጥበብ በማሰባሰብ ከፍተኛ ጥረትን የጠየቀ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

" የክትትል ስራው ቀንና ሌሊት ደጅ ውሎ ማደርን የግድ የሚል እጅግ አድካሚ  ነበር " ያለው ፖሊስ " በስተመጨረሻም ቤዛ በቀለ ዛሬ መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ/ም ሱሉልታ ከተማ "ኖኖ መና አቢቹ" ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ህፃን ሶሊያና ዳንኤልን ሸሽጋ በተቀመጠችበት  በቁጥጥር ስር መዋሏን አሳውቋል።

ተጠርጣሪዋ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለች በኋላ እንደተናገረቸው 40 ሺህ ብር ይከፈልሻል ብለው ሰዎች ስላግባቧት ህፃኗን ሰርቃ ልትሰወር ችላለች፡፡

በወንጀሉ ላይ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ምርመራው መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#መቐለ

" የተለያዩ በደሎች እየደረሱብን ነው " ያሉ በትግራይ የሚገኙ የጦር ጉዳተኞች ዛሬ በመቐለ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ከመቐለ ዘግቧል።

ፖሊስ ሰልፉ ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ተኩሷል ተብሏል።

የጦር ጉዳተኛ ሰልፈኞቹ ከመቐለ ከተማ ወጣ ብሎ ከሚገኘው " መለስ ካምፓስ የጦር ጉዳተኞች ማእከል " በመነሳት እስከ የትግራይ ክልል አስተዳደር መሥርያ ቤት የተለያዩ መፈክሮች እያሰሙ ነበር የተጓዙት።

ሰልፍ የወጡት በአብዛኛው #ወጣቶች የጦር ጉዳተኞች ፦

- «እየደረሰብን ያለውን አስተዳደራዊ በደል ሕዝብ ይስማልን፣ ይወቅልን»

- «በኛ ስም ከሕዝብ የሚሰበሰብ መዋጮ እኛጋ እየደረሰ አይደለም፤ በተደጋጋሚ ጥያቄ ብናቀርብም ምላሽ አጥተናል»

- «በቂ ምግብና ውኃ እንኳን አጥተን የከፋ ሁኔታ ላይ ነን»

- «የታጋዮች ድምፅ ይሰማ»

- «ትኩረት ለጦር ጉዳተኞች»

- «ተክደናል» የሚሉና ሌሎች ብልሹ አሠራሮች የሚያወግዙ መፈክሮችን ያሰሙ እንደነበር ሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።

ሰልፈኞቹ " ድምፃችንን ለማሰማት ወደ ከተማ እንዳንገባ መቐለ ዩኒቨርስቲ አሪድ ካምፓስ አካባቢ አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ጭምር እንድንበተን ሙከራ ተደርጓል "  ሲሉም ተናግረዋል።

ዶቼ ቨለ ሬድዮ ፤ የጦር ጉዳተኞቹ ሰልፍ ከፍተኛ የቁጣ ስሜት ይታይበት ነበር ያለ ሲሆን ሁኔታው በሃይማኖት አባቶች ሸምጋይነት እንዲረጋጋ ተደርጓል ብሏል።

ሰልፈኞቹ የክልሉ አስተዳደር መ/ቤት በሆነው ደጀን ቢሮ በር  ቆይታ የነበራቸው ሲሆን የሕወሓት ከፍተኛ አመራር አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ከሌሎች ወታደራዊ መሪዎች ጋር በችግሮቻቸው ዙርያ መወያየታቸውን ሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።

#ዶቼቨለ_ሬድዮ

@tikvahethiopia
#ረመዷን

የረመዷን ወር መግቢያ ጨረቃ ዛሬ ባለመታየቷ ምክንያት ታላቁ የረመዷን ጾም ሀሙስ መጋቢት 14 ይጀምራል።

እንኳን ለታላቁ የረመዷን ጾም በሰላም አድረሳችሁ።

ረመዷን የፍቅር፣ የአንድነት፣ የሰላም፣ የመተሳሰብ እና የአብሮነት ወር እንዲሆንልን ከልብ እንመኛለን።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና 

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) አረፉ።

በቀድሞ ስማቸው አባ ኃይለማርያም መለሰ (ዶ/ር) በጵጵስና ስማቸው ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ ዕድ የሾሙት ጳጳሳት 14 ኤጲስ ቆጶሳት መካከል አንዱ ነበሩ።

ብፁዕነታቸው ለረጅም ጊዜ ከሀገር ውጪ እና በሀገር ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ሳይችል ቀርቶ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ  ተለይተዋል።

ምንጭ፦ EOTC TV

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

ለግብይትዎ የብርሃን ኤቲኤም ካርድን በመጠቀም ጊዜዎን ይቆጥቡ፤ ድካምዎን ያቅልሉ!

አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !

Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://publielectoral.lat/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ

@berhanbanksc
TIKVAH-ETHIOPIA
የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 'ህወሓት' እና ሸኔ' ን በሽብርተኝነት ፈረጀ። 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛው መደበኛ ስብሰባ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ ም/ቤቱ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሚያካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ "ህዝባዊ…
#TPLF

የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአሸባሪነት የሰየመውን ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የሽብርተኝነት ስያሜ #ይነሳ #አይነሳ በሚለው ጉዳይ ላይ ዛሬ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

በምክር ቤቱ ውስጥ የብልፅና አባላት ሕወሓትን ከአሸባሪነት ለመሰረዝ ያለመ ዝግ ስብሰባ ትናንት መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔን ጨምሮ፣ የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር)፣ እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በተገኙበት ሲያካሂድ እንደዋለና በውይይቱም በርካታ መግባባት ያላስቻሉ ጠንካራ ሐሳቦች መሰንዘራቸውን ጋዜጣው ከምንጮቼ  ሰምቻለሁ ብሏል።

ይሁን እንጂ በፓርላማው የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲን የ2014 በጀት ዓመት የፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲት ላይ ለመምከር ለመጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ለጠዋት ጠርቶት የነበረውን ስብሰባ ወደ ከሰዓት በማጠፍ፣ በዚሁ ቀን ጠዋት አስቸኳይ ስብሰባ ለፓርላማ አባለቱ መላኩ ተገልጿል፡፡

ፓርላማው ሕወሓትንና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ድርጅት ወይም በመንግሥት ‹" ሸኔ "  ተብሎ የሚጠራውን ታጣቂ ቡድን በአሸባሪነት የፈረጀው በሚያዚያ በ2013 ዓ.ም. ነበር፡፡

#ሪፖርተር_ጋዜጣ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ምዕራባውያን እንግዳ የሆነ ባህል (የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት) እንድንፈቅድ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " - ፕሬዜዳንት ሙሴቬኒ የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች በአፍሪካ አገራት ላይ በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ሲሉ ወቅሰዋል። ሙሴቬኒ ይህን ያሉት አገራቸው የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በተመለከተ አዲስ ሕግ እያረቀቀች ባለችበት ወቅት ነው።…
#Update

የኡጋንዳ ፓርላማ በአገሪቱ ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ #ወንጀል እንዲሆን የሚያደርገውን ረቂቅ ሕግ አጸደቀ።

ሕጉ ምን ይዟል ?

- ማንኛውንም ራሱን በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አፍቃሪነት የመደበ፣ ወይም የጾታ ለውጥ ያስደረገ እንዲሁም በእንግሊዝኛ ምሕጻራቸው ኤል-ጂ-ቢ-ቲ-ኪው ዝርዝር ውስጥ የሚካተት የጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋን ሁሉ ወንጀለኛ ያደርጋል።

- በጸደቀው አዲሱ ሕግ መሠረት የተመሳሳይ ጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋ #የረጅም_ጊዜ_እስር ይጠብቀዋል።

- የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን በጉያው ያቀፈ ፣ በቤተሰብ ደረጃ #ያስጠለለ ፣ ወዳጃቸው የሆነ ወይም አብሯቸው ያለ ሰው “እከሌ እና እከሌ” ብሎ ለሕግ አካላት ማንነታቸውን የማጋለጥ ግዴታን በሌሎች ላይ ይጥላል።

- በዚህ ሕግ ልጆችን ለዚሁ ለተመሳሳይ ጸታ ያጨ ወይም ያስተላለፈ #የእድሜ_ይፍታህ ፍርድ ይጸናበታል።

- " በተመሳሳይ ጸታ መብት " ዙርያ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ግንኙነቱን የሚያበረታታ ማንኛውንም የሕትመት ውጤት ማተም አልያም በሌሎች የመገናኛ ብዙኃን ማሠራጨት አይችሉም። ይህን ካደረጉ በሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ።

በምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ የተመሳሳይ ጾታ ቀድሞም ሕገ ወጥ ተደርጎ ነው የቆየው።

ይህ ሕግ ከሕገ ወጥነቱ አልፎ ነገሩን ወንጀልና በተራዘመ እስር የሚያስቀጣ ያደርገዋል።

በዚህ ወር መጀመርያ ለፓርላማ የቀረበው ይህ ሕግ በከፍተኛ ድምጽ ነው ትናንት ማክሰኞ የጸደቀው።

ከዚህ በኋላ ሕጉን የመሻር ብቸኛ ሥልጣን ያላቸው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ሲሆኑ ሕጉ ላይ በፈረሙ ቅጽበት ተፈጻሚነቱ ይረጋገጣል።

ከቀናት በፊት የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ #ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች #በአፍሪካ አገራት ላይ በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ማለታቸው ይታወሳል።

ፕሬዝዳንቱ በአገሪቱ ፓርላማ ቀርበው ንግግር ሲያደርጉ " እንግዳ የሆነ ባህል / ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንድንፈቅድ ምዕራባዊያኑ ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " ብለዋል።

" ምዕራባውያን የራሳቸውን አሠራር በሌሎች ላይ ለመጫን የሚያባክኑትን ጊዜ ማቆም አለባቸው " ሲሉ አሳስበው ነበር።

#BBC

@tikvahethiopia