TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

የመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአፋጣኝ ስራ እንዲጀምር ለማድረግ እንደሚሰራ የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ አመራሮች ማረጋገጫ ሰጡ።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አመራሮች ዛሬ በትግራይ ክልል ጉብኝት አድርገዋል።

አመራሮቹ ጉብኝት ያደረጉት በመዲናዋ መቐለ እና አካባቢው ሲሆን #ዓላማው ፦ በጦርነት ምክንያት በአምራች ዘርፎች ላይ የደረሰውን ውድመት ማእከል ያደረገ እቅድ ለማዘጋጀት እና በፍጥነት ስራ የሚጀምሩበትን ሁኔታ ለመፍጠር እንደሆነ ተነግሯል።

ሚኒስቴሩ ፤ ጉብኝቱ ውድመት የደረሰባቸው እና በግብአት አቅርቦት እጥረት ስራ ያቆሙ አምራች ተቋማትን ስራ ለማስጀመር ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ማድረግ የሚያስችል መሆኑን ገልጿል።

በዚሁ ጉብኝት በመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክ አስፈላጊ የግብአት አቅርቦት እንደሚሟሉ እና በአፋጣኝ ስራ እንደሚጀምር አመራሮቹ ማረጋገጫ መስጠታቸው ተነግሯል።

በተመሳሳይ አመራሮቹ በውቅሮ ከተማ የሚገኙ ሸባ ሌዘር ኢንዱስትሪ እና ሰማያታ እምነ በረድ ፋብሪካ የደረሰውን ውድመት በአካል ተገኝተው መመልከታቸውንና ውድመቱ እንዳሳዘናቸው ድምፂ ወያነ ዘግቧል።

Photo Credit : Demtsi Woyane

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የአዲስ- አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ መሆኑን የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ አስታውቋል፡፡

መንገዱ የተዘጋው ትላንት ምሽት ከደረሰ አደጋ ጋር በተያያዘ ነው።

ኢንተርፕራይዙ ባወጣው መግለጫ ትላንት ሰኞ ምሽት 4:45 ላይ ወደ አዳማ አረቄ ጭኖ እየተጓዘ ክፍያ በር ላይ በተገለበጠ ተሽከርካሪ ምክንያት ባጋጠመ የእሳት አደጋ በህይወትና ንብረትላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

ይህን ተከትሎም የአዲስ- አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ስለሆነም ደንበኞች በሞጆ 52 ኪሎ ሜትር፣ 56 ኪሎ ሜትር እንዲሁም በ60 ኪሎ ሜትር አማራጭ የጉዞ መስመሮችን እንዲጠቀሙ ኢንተርፕራይዙ አሳስቧል፡፡

ትላንት ምሽት ምን ተፈጠረ ?

- በትናትናው ዕለት ምሽት የሐበሻ አረቄ ጭኖ እየተጓዘ የነበረ ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ የእሳት አደጋ ደርሶበታል።

- አደጋው የደረሰው አዳማ መዉጫ የመጨረሻ ክፍያ ጣቢያ ሲደርስ ሲሆን ሰዓቱ ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ 45 ነበር።

- በተሽከርካሪዎች ውስጥ የነበሩ ሶስት ሰዎች እና አንድ #የክፍያ_ጣቢያ_ትኬት ቆራጭ ሰራተኛ ወዲያው በቃጠሎው ህይወታቸው አልፏል።

- አራት ሰዎች ከባድ የቃጠሎ አደጋ ደርሶባቸው በአዳማ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው።

- አረቄ ጭኖ ሲጓዝ የነበረው ተሽከርካሪና ሌሎች 3 ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል።

- 10 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።

Credit : #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
በ1.3 ቢሊዮን ብር የሚገነባው " ለሚ ፓርክ " !

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛው መስቀል አደባባይ ሲል የጠራው " ለሚ ፓርክ " የተሰኘ ግዙፍ ግንባታ ዛሬ በይፋ መጀመሩን አሳውቋል።

ግንባታውን ያስጀመሩት የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ናቸው።

አስተዳደሩ ፕሮጀክቱ " ብቸኛ የህዝብ አደባባይ የነበረውን የመስቀል አደባባይ የሚደግም ሁለተኛ ታላቅ ፕሮጀክት ነው " ብሏል።

ፕሮጀክቱን በተመለከተ ይፋ በተደረገ መረጃ ፦

- ለግንባታው 1.3 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዞለታል።

- ግንባታው 14 ሺህ 400 ካሬሜትር ላይ የሚያርፍ ይሆናል።

ምን ይኖሩታል ?

👉 የህዝብ ስፍራ አደባባይ (public space) የመኪና ማቆምያ፣
👉 የመዝናኛ ስፍራዎች፣
👉 ጂምናዝየሞችን፣
👉 የስብሰባ አዳራሽ፣
👉 የህዝብ መሰባሰቢያ ስፍራ (public space)፣
👉 የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራ፣
👉 የሰርግና ሌሎች አገልግሎቶች የሚውል መናፈሻ፣
👉 ሱፐርማርኬት፣
👉 የቢሮ አገልግሎት የሚሰጡ ቦታዎች፣
👉 መጽሀፍት የማንበቢያ ስፍራና የመሳሰሉት ይኖሩታል፡፡

- በግንባታው ወቅት እስከ 1100 ያህል ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሏል። በቀጣይ በቋሚነት ለ400 ዜጎች የስራ ቦታቸው ይሆናል።

- ፕሮጀክቱ በ10 ወራት ተገንብቶ የሚጠናቀቅ መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት የአዲስ- አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ መሆኑን የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ አስታውቋል፡፡ መንገዱ የተዘጋው ትላንት ምሽት ከደረሰ አደጋ ጋር በተያያዘ ነው። ኢንተርፕራይዙ ባወጣው መግለጫ ትላንት ሰኞ ምሽት 4:45 ላይ ወደ አዳማ አረቄ ጭኖ እየተጓዘ ክፍያ በር ላይ በተገለበጠ ተሽከርካሪ ምክንያት ባጋጠመ የእሳት አደጋ በህይወትና ንብረትላይ…
ፎቶ ፦ ትላንት ሰኞ ፤ ምሽት 4 : 45 በአዲስ አበባ - አዳማ የፍጥነት መንገድ ላይ የ " ሐበሻ አረቄ " ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ ላይ የደረሰው አደጋ ለአራት ሰዎች ህይወት ማለፍ እና አስር / 10 ሚሊዮን ብር ለሚገመት ንብረት ውድመት ምክንያት ሆኗል።

ይህን አደጋ ተክትሎ የአዲስ - አዳማ ዋና መውጫ ላልተወሰነ ጊዜ ተዘግቷል።

Photo Credit : OBN

@tikvahethiopia
" የወይብላ ቅድስት ማርያምና ቅዱስ ሚካኤል የጥምቀት በዓል በተለመደው ቦታ ይከበራል " - ብፁዕ አቡነ ሄኖክ

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስና የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የበላይ ጠባቂ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል "እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ" ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸው፤ የጥምቀት በዓል በአደባባይ ሲከበር 1500 ዓመታትን አስቆጥሯል ብለዋል።

ብፁዕነታቸው፤ በአዲስ አበባ ደረጃ ከጃንሜዳ በተጨማሪ 83 የጥምቀተ ባሕረ ማክበሪያ ቦታዎች መኖራቸውን ገልጸው ጥር 10 ቀን ታቦታቱ ከመንበረ ክብራቸው ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በመውረድ ቃና ዘገሊላን ጨምሮ ለ3 ቀናት በየባሕረ ጥምቀቱ እንደሚከበር ተናግረዋል።

በ2014 ዓ.ም የጥምቀት በዓል የወይብላ ማኅደረ መለኮት ቅድስት ማርያም እና ቅዱስ ሚካኤል ታቦታት ከኦሮሚያ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ከሌሎች ታቦታት ጋር አድሮ ሲመለስ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የሰው ሕይወት የመጥፋትና የአካል መጉደል አደጋ በዚህ ዓመት አይደገምም ብለዋል።

በዚህ ዓመት በአደባባይ የሚከበረውን የጥምቀት በዓል ሰላማዊ ለማድረግ ከኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ባለሥልጣናትና ከአዲስ አበባ መስተዳድር ኃላፊዎች ጋር ስለበዓሉ አከባበር ሰፊ ሥራ መሠራቱን አውስተው የማኅደረ መለኮት ወይብላ ማርያም በዓልም በዚያው በተለመደው የማክበሪያ ቦታ እንደሚከበር ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው፤ መላው ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን በተለይ በልዩ ልዩ መልክ የተደራጁ የወጣት ማኅበራት ኅብረት፣ ለበዓሉ ድምቀት በሁለንተናዊ ሥራ እየተሳተፉ የሚገኙ ወጣቶችና የሰ/ት/ቤት አባላት ከጸጥታ አካላት ጋር በመናበብና በጋራ በመሥራት " የክብረ በዓሉን መንፈሳዊ ድባብ እናስጠብቅ " ሲሉ አሳስበዋል።

ምንጭ፦ አ/አ ሀገረ ስብከት

@tikvahethiopia
ዛሬ እነማን ይሾሙ ይሆን ?

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በሚያደርገው ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀረቡ ሹመቶችን መርምሮ ያፀድቃል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን የሚያካሂደው ዛሬ ከቀኑ 7:30 ጀምሮ እንደሆነ ተጠቁሟል።

በስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርቡ ሹመቶችን ከማፅደቅ ባለፈ የም/ቤቱን 2ኛ አመት የስራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ፦ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በቅርቡ ለተሾሙ 14 ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደሮች እና 7 አምባሳደሮች በብሔራዊ ቤተ መንግስት በተካሄደ ስነ-ስርዓት የሹመት ደብዳቤ ሰጥተዋል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።

ተሿሚ አምባሳደሮች በጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ አማካኝነት ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል።

ፎቶ፦ የፕ/ት ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ እነማን ይሾሙ ይሆን ? የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በሚያደርገው ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀረቡ ሹመቶችን መርምሮ ያፀድቃል፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን የሚያካሂደው ዛሬ ከቀኑ 7:30 ጀምሮ እንደሆነ ተጠቁሟል። በስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርቡ ሹመቶችን ከማፅደቅ ባለፈ የም/ቤቱን…
#Update

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ እና ምክትላቸው አቶ ሰለሞን አረዳ " #በፍቃዳቸው ከስራቸው መልቀቃቸው " ተገለጸ።

ይህ የተገለጸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።

ምክር ቤቱ በዛሬው ስብሰባው ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንትነት የቀረቡ ዕጩዎችን መርምሮ ሹመታቸውን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@tikvahethiopia