TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥቆማ

ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት (3) ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ኤግዚቡሽን ማዕከል " የልጆች ንባብ ፌስቲቫል " ተዘጋጅቷል።

በፌስቲቫሉ ላይ ለልጆች የሚሆኑ መጽሐፍቶችና የእረፍት ጊዜያቸውን በደስታ የሚያሳልፉበት መርሐግብር መዘጋጀቱን አዘጋጆቹ አሳውቀውናል።

ይኸው የንባብ ፌስቲቫል መግቢያ ያለው ሲሆን ለ3 ሰው 250 ብር ለአንድ ሰው 100 ብር መሆኑ ተገልጿል።

የቲክቫህ ቤተሰቦችም ፤ በሀገራችን በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ለተጎዱ አከባቢዎች ላሉ ትምህርት ቤቶች የሚውል  የመጽሐፍት ማሰባሰብ ዘመቻ በዚሁ ፌስቲቫል ላይ ያከናውናሉ።

ለፌስቲቫሉ የምትመጡ ቤተሰቦች ቤት ካሏችሁ መጽሐፍ መለገስ የምትችሉ ሲሆን በዕለቱ የሚገኙ ተሳታፊዎች መጽሐፍ ለመለገስ መመዝገብ ይችላሉ፤ ምዝገባውን ተከትሎ በቀጣይ ሳምንታት በየቤታችሁ በመገኘት መረከብ እንችላለን።

በዚህ ልዩ የህጻናት ፌስቲቫል ላይ ከልጆት ጋር ለመሳተፍ ሲመጡ ፦
- ከ9-12 ማንኛውም መፅሀፍ፣
- ከ1-8 አጋዥ መፅሀፍ ብቻ
- ማንኛውም አይነት ያገለገሉ ኮምፒዩተሮች፣ ታብሌቶች፣ ፕሪንተር፣ የፕሪንተር ቀለም፣ ነጭ ወረቀት ማበርከት ይቻላል።

ዛሬ በይፋ የተጀመረው ፌስቲቫሉ ቅዳሜ እና እሁድ ይቀጥላል።

@tikvahethiopia
" መረጃ ለሰጠኝ እስከ 10,000,000 ዶላር ወሮታ እከፍላለሁ " - አሜሪካ

አሜሪካ ፤ የአልሸባብ የሽብር ቡድን መሪ ነው ያለችው ሞሐሙድ አብዲ አደንን በተመለከተ መረጃ ለሰጣት እስከ 10,000,000 ዶላር (አስር ሚሊዮን ዶላር) / 540,000,000 ብር ወሮታ እንደምትከፍል አስታወቀች።

ሞሃሙድ እ.ኤ.አ. በ2019 አልሸባብ በኬንያ፣ ናይሮቢ ዱሲትዲ2 ሆቴል በፈፀመው እና 22 ንፁሃን ዜጎች በተገደሉበት ጥቃት ውስጥ እጁ እንዳለበት አሜሪካ ገልፃለች።

አሜሪካ ይህን ግለሰብ በተመለከተ መረጃ ለሰጣት እስከ 10,000,000 ዶላር የሚደርስ ወሮታ እከፍላለሁ ብላለች።

እ.አ.አ በ2019 አልሸባብ በጎረቤታችን ኬንያ ናይሮቢ፤ ቅንጡ ከሚባሉት ሆቴሎች አንዱ በሆነው ዱሲትዲ2 የሽብር ጥቃት ፈፅሞ 22 ንፁሃን ተገድለዋል።

ከተገደሉት መካከል አንድ የአሜሪካ ዜጋ ነበር።

በወቅቱ የአልሸባብ ቡድን ቃል አቀባይ ፤ በናይሮቢ ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ ገልፆ ነበር።

@tikvahethiopia
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 16ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

(ዝርዝሩን ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ኤክሳይዝታክስ ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ማሻሻይ ተደርጎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል። ማሻሻያው ቴሌቪዥን እና ቪድዮ ካሜራ ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ እንዲሆኑ፤ ተሽከርካሪዎች ላይም የኤክሳይዝ ታክስ እንዲቀንስ ያደርጋል። የገንዘብ ሚኒስቴር ለሁለት ዓመታት እና ከዛ በላይ ሲተገበር የቆየው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ አዳዲስ ማሻሻይ አደርጎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ማቅረቡ ተሰምቷል። ማሻሻያ ተድርጎ…
#UPDATE #ኤክሳይዝ_ታክስ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅን ለማሻሻል በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ምክር ቤቱ ፤ " ከየካቲት 2012 ዓ/ም ጀምሮ ስራ ላይ በዋለው የኤክሳስ ታክስ አዋጅ ያስገኘውን ጠቀሜታ እንዲሁም የታዩትን ክፍተቶች በመገምገም በአንዳንድ ምርቶች ላይ የተጣለውን የማስከፈያ ምጣኔ ማስተካከል ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ የአዋጁ ማሻሻያ ተዘጋጅቶ ቀርቧል " ብሏል።

ምክር ቤቱ በቀረበው ረቂቅ የማሻሻያ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላም ግብዓቶችን በማከል ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።

#ማስታወሻ

የገንዘብ ሚኒስቴር ለሁለት ዓመታት እና ከዛ በላይ ሲተገበር የቆየው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ አዳዲስ ማሻሻይ አደርጎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ማቅረቡ አይዘነጋም።

ማሻሻያ ተድርጎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ የነበረው ረቂቅ የኤክሳይዝ ታክስ የያዛቸው አዳዲስ ጉዳዮች ፦

- በተሽከርካሪ ላይ ይጣል የነበረው የኤክሳይዝ ታክስ መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል ፤
- ከ3000 ሲሲ ባላይ  ጉለበት ባላቸው ተሽከርካሪዎች ላይ ይጣል የነበረው 240 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ በረቂቅ አዋጁ 120 አካባቢ ዝቅ እንዲል ይላል ፤
- ከ2501 እስከ 3000 ሲሲ 106 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ፤
- ከ1501 እስከ 2500 ሲሲ 90 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ፤
- ከ1500 ሲሲ በታች 66 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ፤ እንዲጣልባቸው ይላል ረቂቅ አዋጁ።

ከዚህ በተጨማሪ ማሻሻያው ቴሌቪዥን እና ቪድዮ ካሜራ ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ እንዲሆኑ ያደርጋል።

@tikvahethiopia
ሚኒስትሮቹ ወዴት ነው የተሸኙት ?

ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፦

- የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞግስ፤
- የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ፤
- የግብርና ሚኒስትር አቶ ኡመር ሁሴን፤
- የጠ/ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ተፈሪ ፍቅሬን ዛሬ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት መሸኛታቸውን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አሳውቋል።

ፅ/ቤቱ ሚኒስትሮቹ / የምክር ቤቱ አባላት በ " ክብር ተሸኙ " እና " ቀጣይ ጉዟቸው ስኬታማ እንዲሆንላቸው ይመኛል " ከማለት የዘለለ ዝርዝር ጉዳይ አላብራራም።

የምክር ቤቱ አባላት ለምን ? በምን ምክንያት ? ወዴት ? እንደተሸኙ በዝርዝር ያልገለፀው የፅ/ቤቱ መረጃን በርካታ ትልልቅ ሚዲያዎች ቀጥታ በመውሰድ እየተቀባበሉት ይገኛሉ።

መረጃው በርካቶችንም ያወዛገበ ሲሆን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች " ለምን እና ወዴት እንደተሸኙ ? " የሚለውን መረጃውን ባሰራጨው የፅ/ቤቱ የማህበራዊ ትስስር ገፅ እና በሚዲያዎች ትስስር ገፅ ላይ በመግባት እየጠየቁ ነው።

ዛሬ ሽኝት ተደርጎላቸው ከተባሉት መካከል አቶ ኡመር ሁሴን ኦባ እና አቶ ተፈሪ ፍቅሬ ቡሳ በቅርቡ በፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአምባሳደርነት መሾማቸውን ወደ ፕ/ት ፅ/ቤት የማህበራዊ ትስስር ገፅ ተመልሰን በመመልከት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ወ/ሮ ዳግማዊት እና ኢ/ር ታከለ ለሌላ ስልጣን ታጭተው ይሁን አይሁን የሚታወቅ ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የ4ቱን የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ሽኝት በተመለከተ ከጠ/ሚ ፅ/ቤት መረጃ ለማግኘት ጥረት ያደርጋል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

በቅርቡ አዲስ ነገር በእጅዎ ! ከሚገምቱት በላይ ፈጣን፣ ቀላል እና ዘመናዊ ።
ዝግጁ ይሁኑ!
#Apollo #OurNewProduct #ProductLaunch
#selfie #BankofAbyssinia #DigitalEthiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#መግለጫ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ፤ በተቋሙ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ላይ የተፈጸመውን ህገ-ወጥ እስር አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

ኢሰመጉ በመግለጫው ፥ መንግስት በአራት የኢሰመጉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ላይ ህገ-ወጥ እስር የፈጸሙ፣ እንዲፈጸም ትዕዛዝ በሰጡ እና በአስቸኳይ ከእስር እንዳይለቀቁ ባደረጉ የፖሊስ አባላት እና አመራሮች ላይ ተገቢውን ምርመራ በማድረግ በህግ ተጠያቂ እንዲያደርግ አሳስቧል።

በተጨማሪ መንግስት ተቀዳሚ ሃላፊነቱ ሰብዓዊ መብቶችን ማክበር፣ ማስከበር እና ማሟላት አንደሆነ በመረዳት በተቃራኒው ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ በሚሰሩ አንደ ኢሰመጉ ባሉ ተቋማት ላይ የሚፈጽማቸውን ጫናዎች፣ ዛቻዎች፤ ማስፈራራቶች፣ ማንገላታቶች፣ ማዋከቦች፣ እስሮችና መሰል ጥሰቶችን መፈጸም እንዲያቆም አስገንዝቧል።

ኢሰመጉ ከባለሙያዎቹ ተወስደው በፖሊስ እጅ የሚገኙ የተለያዩ ሰነዶች መኖራቸውን አመልክቶ ይህ በፖሊስ እጅ ላይ የሚገኙ ሰነዶች ጉዳይ እደሚያሳስበው ገልጿል።

መንግስት ወደፊት መሰል ከህግ አግባብ ውጪ የሆኑ አስሮች እና “ጫናዎችን እንዳይፈጽም ይህንን ድርጊት በሚያደርጉ ስልጣናቸውን አላግባብ በሚጠቀሙ አካላት ላይ ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድም ኢሰመጉ በመግለጫው አሳስቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia