TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Turkey #Ethiopia የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ አካሂዶት በነበረው 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ከቱርክ ሪፐብሊክ ጋር የተደረጉ ወታደራዊ የትብብር ስምምነቶችን ላይ ውይይት አድርጓል። ምክር ቤቱ ፤ ቱርክና ኢትዮጵያ ዘመናትን የተሻገረ ጥብቅ ወዳጅነት ያላቸው መሆኑን በማስታወስ ቱርክ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን አጋር መሆኗን በተደጋጋሚ ያረጋገጠች አገር ናት ብሏል። በዚህ መነሻነት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ…
#Ethiopia #Turkey

የኢትዮጵያ ፓርላማ በ #ኢትዮጵያ እና #ቱርክ መካከል የተደረጉ ወታደራዊ ስምምነቶችን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

ፓርላማው ስምምነቱን ያፀደቀው ባካሄደው ሰባተኛ መደበኛ ስብሰባው ነው።

ኢትዮጵያ እና ቱርክ ወታደራዊ ትብብሮችን ለማድረግ የሚያስችላቸውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ነሃሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም በቱርክ አንካራ መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

ከስምምነቱ መካከል በጥቂቱ ፦

(የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት)

➡️ ዓላማ፦ በ2ቱ አገሮች መካከል በመከላከያ ዘርፍ የሚደረገው ግንኙነት የሚመራበትን ግልጽ ማዕቀፍ ለመፍጠር ነው።

➡️ የስምምነቱ ይዘት ፦ በሁለቱ ሀገራት በትምህርት እና ስልጠና በተናጠልና በጋራ በሚዘጋጁ ወታደራዊ ልምምዶች ስለመካፈል፣ በመከላከያ ኢንዱስትሪ፣ የመረጃ ልውውጥ፣ የሎጅስቲክ፣ የጤና አገልግሎት፣ የመረጃ ስርአት እና የሳይበር ጥቃትን መከላከልና በሌሎች ተያያዥ መስኮች ፣ ከመደበኛ ጦርነት ውጭ ባሉ የሰላም ማስከበር ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ድንጋጌዎችን ያካተተ ነው።

➡️ በኢትዮጵያ ላይ የሚጥለው ግዴታ ፦ ሚስጥራዊ መረጃዎች፣ ሰነዶች እና ማቴሪያሎች ፣ አእምሮአዊ ንብረቶችን አስፈላጊውን ጥበቃ የማድረግ ኢትዮጵያ ለትምህርት እና ስልጠና ወደ ቱርክ ለምትልካቸው የመከላከያ አባላት እና ተማሪዎች በተቀባይ ሀገር የማይሸፈኑትን የህክምና ወጪዎችን ፣ ሌሎችንም የትምህርት እና ስልጠና ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ ይጥላል።

➡️ ከዚህ ስምምነት ኢትዮጵያ የምታገኘው ጥቅም ፦ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ፣ የሎጅስቲክ አቅርቦቶችን እና ድጋፎችን ለማግኘት የሰራዊት ትጥቆችን እንዲሁም በሰው ኃይል እና አስተዳደር ዙሪያ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ፣ የትምህርትና ስልጠና እድሎችን ለማግኘት ያስችላል።

(የወታደራዊ ፋይናንስ ትብብር ስምምነት)

➡️ ዓላማው ፦ በሁለቱ ሀገራት መካከል በመከላከያ ዘርፍ የሚደረገው ግንኙነት የሚመራበት ግልፅ የህግ ማዕቀፍ በመፍጠር የቱርክ መንግስት 100 ሚሊዮን የቱርክ ሊሬ ተመጣጣኝ የሆነ የአሜሪካ ዶላር ለኢትዮጵያ መንግስት ፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ለመከላከያ ዓላማ የሚውል 100% በቱርክ ሀገር የተመረቱ የመከላከያ ቁሳቁሶችን እና አገልግሎቶችን መግዛት የሚችልበትን መርዕ ለመወሰን ነው።

➡️ የስምምነቱ ይዘት ፦ የቱርክ መንግስት 100 ሊሬ ተመጣጣኝ የአሜሪካ ዶላር ለኢትዮጵያ መንግስት ስለሚሰጥበት ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት በዋናነት በቱርክ ከሚገኙ ኩባንያዎች 100% በቱርክ የተመረቱ የመከላከያ ቁሳቁሶችንና አገልግሎቶችን መግዛት የሚችልበትን መርህ ይደነግጋል።

➡️ በኢትዮጵያ ላይ የሚጥለው ግዴታ ፦ በሁለቱ ሀገራት የመረጃ ልውውጥ የተገኙ እና ሚስጥራዊ ተብለው የተለዩ መረጃዎችን ከሌላኛው ወገን የፅሁፍ ፍቃድ ሳይገኝ ለሌላ ሶስተኛ ወገን ያለ መግለፅ እና ሚስጥራዊ መረጃዎችን መጠበቅ እንዲሁም ከቱርክ መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት የተላለፈ ሀብት ፣ እቃ ወይም አገልግሎት ያለ ቱርክ መንግስት የፅሁፍ ፍቃድ ለሌላ ሀገር ወይም ሶስተኛ ወገን እንዳይተላለፍ ወይም ጥቅም ላይ እንዳይውል የማድረግ ግዴታን ይጥላል።

➡️ ከስምምነቱ ኢትዮጵያ የምታገኘው ጥቅም ፦ ኢትዮጵያ ከቱርክ መንግስት የምታገኘው 100 ሚሊዮን የቱርክ ሊሬ ተመጣጣኝ የአሜሪካ ዶላር ወታደራዊ ቁሳቁስ እና አገልግሎት ከቱርክ ድርጅቶች በመግዛት ለአስፈላጊ አገልግሎት ማዋል እንድትችል ያደርጋታል።

#Ethiopia_Turkey
#ኢትዮጵያ_ቱርክ #ወታደራዊ_ስምምነቶች

@tikvahethiopia
Addis Ababa University- Cisco Network Academy, @CiscoExams www.netacad.com

Cisco CCNA and CCNP Professional Network Engineering Training & Certification Preparation.

Class start date: June 18, 2022.

CCNA trainees will receive 3 international certificate of training completion, digital badge & 58% discount voucher for the international exam.

Phone #: 0902-340070 OR 0935-602563 OR 0945-039478:

Follow our telegram channel: @CiscoExams
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ፊንላንድ #ስውዲን #ሩስያ #NATO ➡️ የስዊድን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አን ሊንዴ ሀገራቸው የNATO አባል እንድትሆን ማመልከቻ መፈራረማቸው ተነግሯል። ሚኒስትሯ የፈረመት የአባልነት ጥያቄ ማማልከቻ ከፊንላንድ የNATO ማመልከቻ ጋር አብሮ ይቀርባል ሲሉ የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ➡️ ዛሬ የፊንላንድ ፓርላማ የNATO ወታደራዊ ጥምረት አባል ለመሆን የቀረበውን ሀሳብ በ188 ድምጽ…
#Update

#ፊንላንድ #ስውዲን #ሩስያ #NATO

➡️ ፊንላንድ እና ስዊድን NATOን ለመቀላቀል በይፋ የማመልከቻ ደብዳቤያቸውን ለNATO አስገብተዋል።

➡️ የNATO ዋና ፀሃፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ፊንላንድ እና ስዊድን የዓለም ትልቁን ወታደራዊ ህብረት ለመቀላቀል በይፋ ጥያቄ ማቅረባቸውን አረጋግጠዋል። ዋና ፀሀፊው 2ቱ ሀገራት የNATO አባል ለመሆን ያቀረቡትን ጥያቄ በከፍተኛ ደስታ መቀበላቸውን ገልፀዋል።

➡️ ፊንላንድ እና ስዊድን የNATO ጥምረት አባል ለመሆን ያቀረቡት ማመልከቻ በ30ዎቹ አባል አገራት የሚታይ ሲሆን ሂደቱ ሁለት ሳምንታትን ሊፈጅ እንደሚችል ተነግሯል። ቱርክ ሀገራቱን የአሸባሪዎች ማረፊያ ናቸው በማለት NATOን ለመቀላቀል የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ደጋግማ መቃወሟ ይታወቃል።

➡️ ነገ ሀሙስ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን የስውዲን ጠቅላይ ሚኒስትር እና የፊንላንድ ፕሬዜዳንት በዋይትሀውስ ተቀብለው ያነጋግራሉ፤ የ2ቱ ሀገራት መሪዎች NATOን ለመቀለቀል እያደረጉት ስለለው ሂደት ከባይደን ጋር ይወያያሉ ተብሏል። አሜሪካ ሀገረቱ የNATO አባል እንዲሆኑ ከፍተኛ ድጋፍን እየሰጠች ከምትገኝ ሀገር አንዷ ናት።

➡️ NATOን መቀላቀል በማሰቧ ከዩክሬን ጋር ጦርነት ውስጥ የምትገኘው ሩስያ አሁንም ወታደራዊ ኦፕሬሽኖችን እያካሄደች ነው። ሩስያ
በዶኔትስክ እና ሉሃንስክ የምድር ላይ ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች መቀጠሏ ተነግሯል።

➡️ ሩስያ፤ ፊንላንድና ስዊድን NATO የሚቀላቀሉ ከሆነ አፀፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ እየዛተች ነው ይህን ተከትሎ ፊንላንዳውያን በገፍ ወታደራዊ ስልጠናዎችን እየወሰዱ ነው። እንደ ዩክሬን ልንወረር እንችላል በሚል የሃገሪቱን ጦር በመቀላቀል በፈቃደኝነት ወታደራዊ ስልጠናዎች እየወሰዱ ይገኛሉ።

#አልጀዚራ #አፒ #አልአይን #ቲአርቲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሀገር እንደ ልብስ አትበጣጠስም " - ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ዛሬ የ2014 ዓ/ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የመክፈቻ ጸሎት መርሐ ግብር በአዲስ አበባ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተካሂዷል። በዚሁ መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ስለ #ሰላም መልዕክት አስተላልፈዋል። ብፁዕነታቸው ፥ " በአሁን ጊዜ በቤተክርስቲያናችን በኩል ያለው ከሚመጣው መከራ የተነሳ…
#UPDATE

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዓመት ሁለት ጊዜያት ከሚካሄዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤያት አንዱ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ (የ2014 ዓ/ም) መካሄድ ጀምሯል።

ጉባኤውን አስመልክቶ ፥ አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸው ፤ ጉባኤው ራሱን ከማናቸውም አደረጃጀት ነጻ አድርጎ የሰላም ጥሪን በማሰማት ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ሰላም መረጋገጥ ለሰላም በሰላም መሥራት መጣርና ውጤት ማምጣት እንደሚጠበቅበት ገልፀው በዚህ ዙርያ ይህ ዓቢይ ጉባኤው በስፋት ተወያይቶ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቀል ብለዋል።

አክለውም ፤ " ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ልጆቻችን እና ወገኖቻቻችን የምናስተላልፈው መልእክት ሰላምንና አንድነትን ለማረጋገጥ ጕልበትን እንደ አማራጭ መውሰድ አቁመን የተከሠቱብንን ችግሮች በውይይትና በድርድር ለመፍታት ለሚደረገው ጥረት የላቀ ድጋፍ በመስጠት በጦርነትና በረኃብ፣ በድርቅና በበሽታ እያለቁ ያሉ ልጆቻችንንና ወገኖቻችንን እንድንታደግ በእግዚአብሔር ስም በመማፀን መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን " ብለዋል።

(የአባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#Update

በዛሬው ዕለት Oxfam እና Save the Children ባወጡት ሪፖርት በድርቅ በተጠቁት፦
➡️ #ኢትዮጵያ
➡️ ኬንያ
➡️ ሶማሊያ በየ48 ሰከንዱ አንድ ሰው በረሃብ የመሞት አደጋ ተጋርጦበታል ብለዋል።

ሪፖርቱ ዓለም መከላከል የሚቻላቸውን ተደጋጋሚ አደጋዎች መከላከል አለመቻሉን አጉልቶ ያሳያል ተብሏል።

Jameel Observatory ከተሰኘ ድርጅት ጋር በጥምረት የተሠራው ሪፖርት ዓለም ዳግም ከፍተኛ የረሃብ አደጋን ችላ ብሏል ሲል አስጠንቅቋል።

እ.አ.አ በ2011 በሶማሊያ ከ260,000 በላይ ሰዎችን (ከግማሽ በላይ ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው) ከገደለው ረሃብ ጋር ተመሳሳይ አደጋ እንዳይከሰት ሪፖርቱ ስጋቱን አስቀምጧል።

በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ረሃብ በሚመስል ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ የተባለ ሲሆን በኬንያ 3.5 ሚሊዮን ሰዎች በከፍተኛ ረሃብ እየተሰቃዩ ነው።

በ3ቱ ሀገራት ለከፍተኛ ረሃብ የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ባለፈው ዓመት ከነበረበት ከ10 ሚሊዮን ወደ23 ሚሊዮን አድጓል።

በተደጋጋሚ ለቀረበው አስቸኳይ ድጋፍ " በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ " የተገኘው የገንዘብ ድጋፍ ዝቅተኛ ነው ተብሏል።

እንደሪፖርቱ ከሆነ፦

➡️ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በተከሰተ ድርቅ

➡️ በግጭቶች ምክንያት ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው

➡️ የኮቪድ-19 ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ምክንያት ሰዎች ችግሩን እንዳይቋቋሙ አድርጓል።

የዩክሬን ጦርነት እየጨመረ የመጣውን የምግብ ዋጋ በማናር ችግሩን አወሳስቦታል።

በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ምልክቶች ቢሰጡም የዓለም መሪዎች በጣም ከመዘግየታቸው ሌላ የሰጡት ምላሽ አነስተኛ ነው።

በዚህም በሚሊዮን ሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ እንደሚጋለጡ ማስጠነቀቂያ መሰጠቱን ቢቢስ ዘግቧል።

[ ሙሉ ሪፖርት ]

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ኩባንያ የአክሲዮን ገበያ የመመስረት ኃላፊነትን ተረክቧል።

የአክሲዮን ገበያ የመመስረት ኃላፊነት ለብሔራዊ ባንክ ተሰጥቶ የነበረ ሲሆን አሁን ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ተላልፎ ተሠጥቷል።

በዚህም መሠረት ብሔራዊ ባንክ የአክሲዮን ገበያ የማቋቋም ስራ ሲያከናውን የነበረው ቡድን ስራውን ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ኩባንያ በዛሬው እለት አስረክቧል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ኩባንያ ከኤፍ ኤስ ዲ አፍሪካ ጋር የትብብር ስምምነት ማድረጉም ሪፖርተር አስነብቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

➡️ ፈረንሳይ ፣ ጣልያን እና ስፔን 85 የሩሲያ ዲፕሎማቶችን ማባረራቸውን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ዲፕሎማቶቹ ሀገራቱን ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት በስለላ ስራ ላይ ተሰማርተዋል በሚል ተከሰው ሲሆን፤ ሩስያ ክሱ ሀሰት ነው ብላለች፤ የዩክሬን ጦርነት ከጀምረ ጊዜ አንስቶ 300 የሩሲያ ዲፕሎማቶች ከተለያዩ ሀገራት ተባረዋል።

➡️ ሩስያ ዛሬ የስፔን እና የፈረንሳይ ዲፕሎማቶችን አባረረች። እስካሁን 27 የስፔን፣ 34 የፈረንሳይ ያባረረች ሲሆን 24 የጣልያን ዲፕሎማቶችን ልታባርር እንደሆነ ተሰምቷል።

➡️ የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን የNATO አባላት ሀገራቸው ፊንላንድ እና ስዊድን ወደ ህብረቱ አባልነት እንዳይገቡ ያደረባትን ስጋት እንዲያከብሩ ጠየቀዋል። ኤርዶጋን ፊንላንድ እና ስውዲን የNATO አባል ሀገር እንዲሆኑ ሀገራቸው ድጋፏን እንደማትሰጥ በተደጋጋሚ ገልፀዋል።

➡️ የዩክሬን ጦርነትን ለማስቆም በዩክሬን እና ሩሲያ መካከል ሲደረግ የነበረው ድርድር ቆሟል። ሁለቱም ወገኖች ለድርድሩ መደናቀፍ አንዱ ሌላውን እየወነጀለ ነው።

➡️ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን የፊንላንድ እና ስዊድን ለNATO አባልነት ያቀረሹትን ታሪካዊ ያሉትን ማመልከቻ ባደስታ እንደሚቀበሉትና አጥብቀው እንደሚደግፉ አስታውቀዋል። ፕሬዜዳንቱ ዛሬ ባወጡት ተግለጫ ከUS ኮንግረስ እና ከNATO አጋሮች ጋር በመሆን በፍጥነት ፊንላንድ እና ስዊድን ወደ ጠንካራው የመከላከያ ህብረት (NATO) ለማምጣት እሰራለሁ ብለዋል።

➡️ ፊንላንድ NATO ለመቀላቀል ባሳለፈችው ውሳኔ ላይ የሩሲያ ምላሽ ድንገተኛ ቢሆንም እርምጃዎቹ ግን ወታደራዊ ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

#አልጀዚራ #ኤኤፍፒ #ዘኪየቭ_ኢንዲፔንደንት #አልአይን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ባለቤት ወ/ሮ መነን ኃይሌ ምን አሉ ? ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ በአዲስ አበባ ከቤታቸው እንደወጡ እስካሁን አልተመለሱም። ይህን ተከትሎ ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል በሰጠቱ ቃል የሚከተለውን ብለዋል ፦ " ትናንት ሰኞ ግንቦት 08/2014 ዓ/ም ከቤታቸው 5፡15 አካባቢ የወጣው ከጓደኛው (አቶ ዮሐንስ ቧያለው) ጋር ቀጠሮ እንደነበረው…
#Update

ብርጋዴር ጄነራሉ ባሕር ዳር ናቸው ተብሏል።

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የደረሱበት ሳይታወቅ ከቆዩ ከ2 ቀናት በኋላ ባሕር ዳር እንዳሉና ደህና መሆናቸውን የሚገልጽ መልዕክት እንደደረሳቸው ባለቤታቸው ተናግረዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ሰኞ ግንቦት 08/2014 ዓ.ም. ከቤታቸው ረፋድ ላይ ከወጡ በኋላ የደረሱበት ሳይታወቅ እስከ ረቡዕ አመሻሽ ድረስ ቆይተዋል።

ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ዛሬ ምሽት ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል፤ የጄነራል ተፈራ ጠበቃና የሚያውቋቸው ሰዎች ባለቤታቸው ባሕር ዳር ውስጥ በሚገኘው ዘጠነኛ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንዳሉ እንደነገሯቸው ገልፀዋል።

ወ/ሮ መነን ባለቤታቸው በላኩት መልዕክት ደህና መሆናቸውን እና አሁን ያሉበት ቦታ በመግለጽ ቤተሰባቸው እንዲረጋጋ መልዕክት ልከዋል ብለዋል።

ከአማራ ክልል የፀጥታ እና ደኅንነት እንዲሁም ከፖሊስ ማብራሪያ ለመጠየቅ የተደረገው ሙከራ ለጊዜው አለመሳካቱን ቢቢሲ ጨምሮ አስነብቧል።

@tikvahethiopia