TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኮሜዲን ወንዶሰን አልሞተም፤ ወሬው ሀሰት ነው!

"ከኮሜዲያን ወንዶሰን መሸሻ (ደኩሌ) ጋር በተያያዘ የሚነዛው ወሬ ውሸት መሆኑን ማረጋገጥ ችያለሁ። ኮሜድያን ደኩሌ በህይወት አለ።" - ጋዜጠኛ ተቦርነ በየነ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ እውቅና [የሶስት ወር] የሰጣቸው 11 ፓርቲዎች፦

- ኤጀቲማ ፌደራሊስ ፓርቲ /ኤፌፓ/
- ሱማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ
- የካፋ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ህብረት/ካህዴህ/
- የፊንፊኔ ህዝቦች ለፍትህ እና ለዴሞክራሲ ፓርቲ /ፊህዴ/
- የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
- ኅብረት ለዲሞክራሲና ለነፃነት ፓርቲ/ኅዴነፓ/
- የሲዳማ አንድነት ፓርቲ /ሲአፓ/
- ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ፓርቲ
- የሶማሌ ብሄራዊ ፓርቲ /ሶብፓ/
- የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር /ኢአአግ/
- የወለኔ አርሶአደር ህብረት

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የአቶ አሸብር ባልቻ ሹመት...

ከግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ በዓለምአቀፍ ቢዝነስ የማስተርስ ዲግሪያቸውን ያገኙት አቶ አሸብር ባልቻ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ፡፡

አቶ አሸብር ከስዊዲን ሀገር ኬ. ቲ. ኤች ዩኒቨርሲቲ በዘላቂ ኢነርጂ ምህንድስና ዘርፍ ተጨማሪ ኮርሶችን ወስደዋል፡፡

አቶ አሸብር በበደሌ ቢራ ፋብሪካ፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ በተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት፣ የገባ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ በመሆን ካገለገሉ በኋላ ከጥቅምት 2012 ዓ.ም ጀምሮ ይህን ኃላፊነት እስከተቀበሉበት ቀን ድረስ የኃይል ማመንጫዎች ግንባታ ስራ አስፈፃሚ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

አቶ አሸብር ባልቻ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን በተለያዩ የስራ መደቦች በባለሙያነትና በኃላፊነት ለ16 ዓመታት አገልግለው ከየካቲት 09 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተቋሙን በዋና ስራ አስፈፃሚነት እንዲመሩ በተቋሙ የሥራ አመራር ቦርድ መሾማቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡

[የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬም የቀጠሉት የድጋፍ ሰልፎች...

ከሰሞኑን በተለያዩ ከተሞች ሲካሄዱ የነበሩ የድጋፍ ሰልፎች ዛሬም ቀጥለዋል። በዛሬው ዕለት የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አመራርን የሚደግፍ ሰልፍ በሀዋሳ፣ በቢሾፍቱ፣ እንዲሁም በፊቼ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልፆልናል።

የሰልፉ ተሳታፊ የሆኑ የተወሰኑ ሰዎችን ያነጋገርን ሲሆን "ሀገር በስድብ እና በጥላቻ አይገነባም፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰሩትን ስራ ከማንቋሸሽ እና የፌስቡክ ዘመቻ ከማካሄድ ለህዝቡ አማራጫ ሀሳብ ማቅረብ ይቻላል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ እስካሁን ላደረጉት አስተዋፆ ምስጋና እንጂ ስድብ አይገባቸውም" ብለዋል።

PHOTO : SOCIAL MEDIA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HAWASSA

ዛሬ ማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ በሀዋሳ እየተደረገ ያለው ሰልፍ ላይ ከሲዳማ አስተዳደርና ከ36 ወረዳዎች የተውጣጡ የሲዳማ ብሄር ተወካዮች ፣ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች እና የመንግስት ሰራተኞችን ያሳተፈ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መስፈርት የማያሟሉት የግል ትምህርት ቤቶች...

- 1615 የግል ትምህርት ቤቶች ለመኖሪያ ቤት ታስበው የተሰሩ ናቸው

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች በተማሪ ብዛት 52 በመቶ ድርሻ ቢኖራቸውም አብዛኞቹ የትምህርት ሚኒስቴርን መስፈርት እንደማያሟሉ ተገለጸ።

አንድ ሺህ 615 የግል ትምህርት ቤቶች ለመኖሪያ ቤት ታስበው በተሰሩ ቤቶች ተማሪዎችን በተጨናነቀ ሁኔታ እያስተማሩ እንደሚገኙ መሆኑም ታውቋል።

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የግል ትምህርት ቤቶች የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ...

የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን በአዲስ አበባ ከተማ የግል ትምህርት ቤቶች የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ በሕብረተሰቡ ላይ ጫና እየፈጠሩ መሆኑን በጥናት ማረጋገጡን ገለጸ።

የአዲስ አበባ የግል ትምህርት ቤቶች ማህበር በበኩሉ ጥናቱ ሁሉን ያላሳተፈና ሚዛናዊነት የጎደለው ነው ብሏል።

ባለስልጣኑ የገበያ ነጻነትን ያለአግባብ በመጠቀም ጸረ ውድድር ስምምነትና የተከለከሉ የንግድ አሰራሮች በተስተዋለባቸው የትምህርት ተቋምት ላይ ጥናት አድርጓል።

በተመረጡ 100 የግል ትምህርት ቤቶች በተካሄደው ጥናት ላይ የተገኘውን ውጤት አስመልክቶ ባለስልጣኑ ከባለድርሻ ተቋማት ጋር ውይይት አድርጓል።

በጥናቱ መሰረትም በትምህርት ቤቶቹ የትምህርት ተቋማቱ መጻህፍትን አሳትመው መሸጥና የደንብ ልብስ ከተወሰኑ ተቋማት ብቻ እንዲገዙ የማስገደድ ሁኔታ ተስተውሏል።

በተጨማሪም ”ፈተና የሚመጣው ከማጠናከሪያ ትምህርት ነው” በሚል አስገዳጅ በሆነ መልኩ ተማሪዎች ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍሉ ማድረግ፣ ለተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ተወዳዳሪነት በሌለው መልኩ በከፍተኛ ዋጋ የማቅረብ ሁኔታ እንደሚስተዋል በጥናቱ ተመልክቷል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት...

መንግስት የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ የሚገድቡ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን እንዲያስቆም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አሳሰበ።

ምክር ቤቱ በአገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫው ላይ እንደተገለጸው መንግስት በተለያዩ አካባቢዎች የተነሱ የፓርቲዎችን ነጻ እንቅስቃሴ የሚገድቡ የህግ የበላይነት ጥያቄዎች በወቅቱ ምላሽ እንዲሰጣቸው አሳስቧል።

ኢዜማ ፣ ኦፌኮ ፣ አረና፣ ኦነግ እና ለሎች አገራዊና ክልላዊ ፓርቲዎች የፖለቲካ እንቅስቃሴያቸውን በፈለጉት ቦታ ለማካሄድ ሲሞክሩ በተለያዩ ቡድኖች እና ተቋማት የፖለቲካ እንቅስቃሴያችንን እንዳናካሂድ እክል ፈጥረውብናል ማለታቸው ይታወሳል።

የጀመርነው የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የሚሳካው የህግ የበላይነት ሲረጋገጥ ብቻ ነው ያለው የምክር ቤቱ መግለጫ ህብረተሰቡ እና ማህበራዊ ተቋማት ለህግ የበላይነት ቅድሚያ እንዲሰጡም ጠይቋል።

ምርጫ ቦርድም የጀመረውን ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ጤናማ ግንኙነት እንዲኖረው የሚያስችሉ ስራዎቹን አጠናክሮ እንዲቀጥል ምክር ቤቱ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ጠይቋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE - የሟቾች ቁጥር 2,120 ደርሷል - በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 75,730 በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,120 የደረሰ ሲሆን 75,730 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 16,155 መድረሳቸውን ተመልክተናል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

- የሟቾች ቁጥር 2,247 ደርሷል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 76,790

በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እንዲሁም በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከባለፉት ቀናት ጋር ሲተያያ እየቀነሰ እንደሆነ እየተገለፀ ይገኛል።

ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,247 የደረሰ ሲሆን 76,790 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 18,590 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ በመከላከያ ዘርፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ!

በኢፌዴሪ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን በሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ የሥራ ጉብኝት አድርጓል፡፡

የልኡካን ቡድኑ በቆይታው ከሳዑዲ ዓረቢያ የጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ፈያድ ቢን ሃመድ አል-ሩዋሊ እና የሳዑዲ ዓረቢያ የመከላከያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በመገናኘት በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይቶችን አካሂዷል፡፡

በውይይቶቹ በኢትዮጵያ እና ሳዑዲ ዓረቢያ መካከል በመከላከያ ዘርፍ ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር እና በሌሎች ቀጠናዊ የጋራ ስጋቶች ዙሪያ በትብብር መሥራት እና የልምድ ልውውጥ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክርና የሐሳብ ልውውጦች ተደርገዋል፡፡

#FDREDefenseForce
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዘረፋ ወንጀል የተጠረጠሩ 16 ሰዎች ተያዙ...

በአሶሳ ከተማ በምሽት የዘረፋ ወንጀል የተጠረጠሩ 16 ባጃጆች ከእነ አሽከርካሪዎቻቸው በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የከተማው ፖሊስ ፅሀፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በፅሀፈት ቤቱ የወንጀል መከላከል ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት ኢንስፔክተር ደረጃ ኢታና እንደገለፁት በከተማው የሚፈፀም የዘረፋና ስርቆት ወንጀል እየተበራከተ መጥቷል፡፡ ችግሩን ለማስቆም ፖሊስና ህብረተሰቡን ያቀፈ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ከየካቲት 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ሥራ ተገብቷል ብለዋል፡፡

ግብረ ኃይሉ ከህብረተሰቡ የደረሰውን ጥቆማ መሠረት በማድረግ እስከ አሁን ድረስ 16 ባጀጆችን ከእነ አሽከርካሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስረድተዋል፡፡

አሽከርካሪዎቹ በእኩለ ለሊት እየተዘዋወሩ ዘረፋ ለሚፈፅሙ ግለሰቦች የትራንስፖርት አገልግሎቱን በመስጠት ወንጀል የተጠረጠሩ ናቸው ብለዋል። ካናቢስ የተባለ አደንዛዝ እፅ በማዘዋወር የተጠረጠሩ ሌሎች ስምንት ግለሰቦችንም ግብረ ኃይሉ በቁጥጥር ሥራ እንዲውሉ አድርጓል።

#ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JawarMohammed

ወደወለጋ፣ወደኢሉባቦር ኦፌኮ ድጋፍ የለውም፤መሪዎቹም [ጃዋርን ጨምሮ] ወደዛ ላይሄዱ ይችላሉ የሚሉ ስጋቶች አሉ ተብለው 'ኬላ' በተሰኘ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ የተጠየቁት አቶ ጃዋር መሃመድ የሰጡት ምላሽ፦

ምንሄደው ድጋፍ ያለን ቦታ ብቻ አይደለም። ምንሄደው ድጋፍ ለማጠናከር ነው። እኛ በሁሉም ወረዳ ላይ ህዝባችንን ማነጋገር እንፈልጋለን። ግን ሰዉ ይረሳል እንጂ በጣም ነገሮች በተጧጧፉበት እና መንግስት በጣም በተዳከመበት፣ በሌለበት ወቅት እኔና በቀለ እስከ አሶሳ ድረስ ሰው ማንም በማይሄድበት፣ የመንግስት ባለስልጣን ሀገር ጥሎ በጠፋበት ወቅትም ስንሄድ ነበር። አሁንም ወደምዕራብ እንሄዳለን።

ምዕራብና ደቡብ እንደሚታወቀው ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ ህጋዊ ያልሆነ ኮማንድ ፖስት አለ። ያ ኮማንድ ፖስት እንዲነሳ በህጉ challenge እናደርጋለን። እኛ ብቻ አይደለንም ጥምረት ፈጥረን እየሰራን ነው ያለነው ከኦነግ ጋር፣ ከኦብፓ ጋር አብረን ወደፊት የምናደርገው እንቅስቃሴ ይኖራል።

የማንሄድበት ዞን አይኖርም። ኦሮሚያ ውስጥ ብቻ አይደለም ወደ ተለያዩ ክልሎች የመሄድ እቅድ አለን። ደፍሮ ለሚለውም የተያያዝነው ትግል እንጂ ዳንስ አይደለም። ስለዚህ ሁሉም ቦታ እንሄዳለን። ስንሄድ ደግሞ በተጨባጭ ይታያል።

#TikvahFamily
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስለታሰሩ ኮድ 2 VAN መኪናዎች ጉዳይ፦

አቶ ደበሌ ቀበታ [ከጉሙሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር] ለፋና የተናገሩት፦

አስመጪዎቹ አድርገው የነበረው ፤ እነዚህ ተሽከርካሪዎች ለግል መገልገያ የሚውሉ አይደሉም ይሉና ዲክላር ያደርጉ ነበር። በዚህ ልክ ዲክላር ካደራረጉ በኃላ ኤክሳዝ ታክስ ሳይከፍሉ ለግል መገልገያ እቃ ነው ወይም ለህዝብ ማመላለሻ ነው ብለው በግልፅም ለጉሙሩክ ሳይገልፁ በተጭበረበረ መልክ ይጠቀሙበት እንደነበረ ጥናቱ አሳየ።
.
.
ስለዚህ በዚህ ምክንያት መንግስት መሰብሰብ ይገባ የነበረው ኤክሳይዝ ታክስ ከነዚህ ተሽከርካሪዎች ያጣል። አገልግሎቱን ህብረተሰቡ ያግኝ በሚል ውሳኔ ነው መንግስት ከነዚህ ተሽከርካሪዎች ኤክሳይዝ ታክስ አልሰበስብም ያለው።
.
.
ኦፊሻል የሆነ ውሳኔ መወሰን ቢሆንም፤ አንዱ የንግድ ፍቃድ አውጥተው እነዚህን ተሽከርካሪዎች ወይም ኮድ 1 ወይም ወደ ኮድ 3 መቀየር ይገባቸዋል። ውሳኔዎቹ ጉዳት የማያደርሱ ሆኖ በምርጫው ላይ የተመሰረተ አይ እና ለታክሲ አገልግሎት እናውለው ወይም ለህዝብ ማመላለሻነት እናውለው ፤ ኮድ ሁለት የሚለው ይመክናል፤ ትራንስፖርት ባለስልጣን ሄደው ያመክኑትና ተሸከርካሪው ኤክሳይዝ ታክስ ለተተወላቸው አላማ ማዋል አለባቸው።

📹5 MB
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአብን ህዝባዊ ውይይት...

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የአዲስ አበባ ማስተበባበሪያ ፅ/ቤት በመጪው እሁድ የካቲት 15 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ አባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር አልማዝዬ ሜዳ አጠገብ በሚገኘው በቄራ ወረዳ 5 ሸማቾች ማኅበር አዳራሽ በንቅናቄው የማታግያ አጀንዳዎች እና በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ዙሪያ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ሕዝባዊ ውይይት እንደሚያካሂድ አሳውቋል።

ምንጭ፦ አብን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሌላ መረጃ፦

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን/ የምስራቅ ጎጃም ዞን የአዋበል ወረዳ ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤት በስኩት እነጋትራ ቀበሌ ከሚገኙ አባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር በእነጋትራ ፍልቅልቅ ከተማ እሁድ የካቲት 15 ከጠዋቱ 4:30 ጀምሮ ውይይት እንደሚያደርግ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HAWASSA

የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ ዛሬ ሀዋሳ ከተማ በነበረ የድጋፍ ሰልፍ ላይ "የሲዳማ ህዝብ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር ባደረገው ትግል ለዘመናት ሲገደል እና ሲታሰር ቆይቶ ፤ የህዝቡ የረጅም ጊዜ ጥያቄ «ተገቢ» መልስ ያገኘዉ በለውጡ ነዉ ተደምጠዋል።

አስተዳዳሪው "አካባቢያችንን የትርምስ እና የግጭት ቀጠና በማድረግ ለውጡን ለማደናቀፍ የቋመጣችሁ ከእንግዲህ ጊዜ እና ገንዘባችሁን በማጥፋት ባትደክሙ ይሻላችኋል" ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia