TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አሳዛኝ_ዜና

በካይሮ ብሄራዊ የካንሰር ማእከል አቅራቢያ የደረሰው የመኪና ግጭት ባስከተለው ፍንዳታ 19 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 30 መቁሰላቸውን ነው የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ያስታወቀው፡፡

የሃገር ውስጥ ሚኒስቴር በበኩሉ አንድ በፍጥነት የሚሄድ መኪና ከሌላው ጋር በመጋጨቱ ፍንዳታውን አስከትሏል ብሏል፡፡ ነገር ግን ግጭቱ ብቻውን ትልቅ ፍንዳታ ለምን እንዳስከተለ እስካሁን ግልፅ አለመሆኑንም ተናግረው አደጋው በመኪኖቹ ግጭት ብቻ መድረሱም አለመታወቁን ገልፀዋል፡፡

አደጋውን ተከትሎ የተለቀቁ ቪዲዮዎች እንደሚያሳዩት በርካታ መኪኖችን ሲያቀጣጥል የነበረውን መጠነ ሰፊ እሳት የአደጋ ግዜ ሰራተኞች ሊቆጣጠሩት ሲሞክሩ ተስተውለዋል፡፡ የካንሰር ህክምና ማእከል ውስጥ ያሉ ለቀው የወጡ ሲሆን በታዋቂው አደባባይ ታኺር አቅራቢያም መሆኑ ታውቋል፡፡

ከሆስፒታሉ በተቃራኒ ጎን የሚገኙት የባንክ ጥበቃ አብድል ራህማን ሞሃመድ እንዳሉት” በአካባቢው ፍንዳታውን ሰምተናል በአፋጣኝም መግቢያ በሮቹን ዘግተናል” ብለዋል፡፡

የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር የቆሰሉ ሰዎች ወደ ህክምና መወሰዳቸውንም ገልጿል፡፡ የግብፅ አቃቤ ህግ የአደጋውን መንስኤ በመመርመር ላይ ሲሆን ለሮይተርስ የዜና ወኪል የተናገሩ ምንጮች ከመንግስት አካል ፍንዳታው ጥቃት መሆኑን አለመገለፁን ተናግረዋል፡፡ መርማሪዎች፣የወንጀል መርማሪ ላብራቶሪ እና የቦምብ ኤክስፐርቶች ፍንዳታው የደረሰበት ቦታ መገኘታቸውን ምንጮች ለአልጀዚራ ተናግረዋል፡፡

በግብፅ የመኪና አደጋ የተለመደ እንደሆነ የገለፀው የአልጀዚራ ዘገባ 8 ሺህ ግጭቶች ባለፈው አመት መመዝገባቸውንና ይህም ለ3 ሺህ ሰዎች ሞትና ለ12 ሺህ ሰዎች መቁሰል ምክንያት መሆኑን አስነብቧል፡፡

Via አልጀዚራ/ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

16 ኢትዮጵያውያን ህይወታቸው አለፈ!

ከሊቢያ ወደ ጣሊያን በባህር ሲጓዝ በነበረ #ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ የ16 ኢትዮጵያውን ዜጎች ህይወት አለፈ። ሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ባጋጠመው በዚህ አደጋ 16 የትግራይ ተወላጆች ህይወት ማለፉን የክልሉ የህዝብና መንግስት ግንኙነት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው በዛሬው ዕለት በሰጠው የሀዘን መግለጫ ከሊቢያ ወደ ጣሊያን ሲጓዝ በነበረ ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ ህይወታቸው ካለፉት ዜጎች ውስጥ 10ሩ ሴቶች መሆናቸውን ገልጿል። በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት ዜጎችም በክልሉ ኢሮብ ተብሎ የሚጠራው ወረዳ ተወላጆች መሆናቸው ታውቋል።

የክልሉ መንግስት በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ፥ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን ተመኝቷል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የአፈር መደርመስ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የመረጃ ኢንተለጀንስ ቡድን መሪ ሳጅን ጌታሁን ተስፋዬ እንደተናገሩት፥ አደጋው የተከሰተው በወረዳው ጋንታ ካንቻሜ ቀበሌ ልዩ ስሙ “መርከብ ጣቢያ” በሚባል ስፍራ ነው። አደጋው በአንድ ብሎኬት ማምረቻ ድርጅት ውስጥ መድረሱንም ተናግረዋል።

የአደጋው መንስኤ የብሎኬት ማምረቻ ሰራተኞች አፈር በመቆፈር ላይ እያሉ በዙሪያው ከፍተኛ መጠን ያለው አፈር መደርመሱ መሆኑንም አስታውቀዋል ፡፡ሳጅን ጌታሁን እንዳሉት በአደጋው በአፈር ቁፋሮ ላይ የነበሩ አራት ሰዎች ወድያውኑ ሕይወታቸው አልፏል። ከሟቾች መካከል ሁለቱ ወንድማማቾች መሆናቸውም ነው የተገለጸው። በቁፋሮ የወጣው የሟቾች አስክሬን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ምርመራ ተደርጎለት ለቤተሰቦቻቸው መሰጠቱ ተዘግቧል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና | አርቲስት ጫንያለሁ ወልደጊዮርጊስ ከዚህ አለም በሞት መለየቱን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ዘግቧል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia