TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Amhara

" ከ7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ነው እቅድ የተያዘው ከነሐሴ 20/2016 ዓ/ም ጀምሮ የተመዘገቡት ግን 1.7 ሚሊዮን ናቸው - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

በመንግስት የጸጥታ ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በየጊዜው የተኩስ ልውውጥ የሚስተዋልበት አማራ ክልል በ2017 የትምህርት ዘመን ከ7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዘገብ እንዳቀደ፣ ከነሐሴ 20 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ የተመዘገቡት ግን 1.7 ሚሊዮን ተማሪዎች መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ፣ " ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 292 ሺሕ በላይ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 1.2 ሚሊዮን በላይ፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወደ 180 ሺሕ ተማሪዎች ተመዝግበዋል " ብሏል፡፡

" በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምዝገባው እየተካሄደ ነው፡፡ ትንሽ እሱ ላይ መዘግየት ይታያል፡፡ እስካሁን በጠቅላላ ወደ 1.7 ሚሊዮን ተማሪዎች ናቸው የተመዘገቡት የእቅዱን ወደ 24 ፐርሰንት አካባቢ " ነው ያለው፡፡

በጸጥታው ችግር ባለፈው ዓመት በርካታ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ይታወቃል፡፡  በ2017 የትምህርት ዘመንስ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች እጣ ፈንታቸው ምንድን ነው ? እውነት ተመዝግበውስ ለመማር አስቻይ ሁኔታ አላቸው ወይ ? ከዚህ አኳያ ቢሮው ምን አቅዷል ? ምንስ እየሰራ ነው? ስንል ቢሮውን ጠይቀናል፡፡

የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን " በክልሉ ከ10 ሺሕ 874 በላይ ትምህርት ቤቶች አሉ፡፡ በአዲሱ የትምህርት ዘመን የእኛ ፍላጎት እነዚህ ሁሉም ትምህርት ቤቶች 7 ሚሊዮን ተማሪዎች እንዲያስተምሩ፣ መማር ማስተማሩ እንዲጀምር/እንዲቀጥል ነው " ብለዋል፡፡

" በተለይ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የጸጥታ ችግር ስላለ የትምህርት ሥራን ከዚህ በፊት እንደምናደርገው ሁሉ የምዝገባ ሥራን ለመስራት እንቅፋቶች ቢኖሩም ምዝገባ ተጀምሯል፡፡ የምዝገባ አፈጸጻሙ በምንጠብቀው ልክ ባይሆንም ምዝገባ እየተካሄደ ነው " ሲሉ አቶ ጌታው ተናግረዋል፡፡

የመማር ማስተማር ሂደቱ እዳይደነቃቀፍ በትጥቅ ትግል ላይ ያሉትን ጨምሮ ሁሉም ሰው ኃላፊነት መውሰድ እንዳለበት ቢሮው አስምሮበታል።

" አንድንድ ቦታ ላይ ትላንት ትምህርት ሲጅሩ ልንማር ይገባል የሚል ሞቶ ሁሉ ይዘው የወጡ ተማሪዎች አሉ፡፡ ይሄ በጣም ልብ ይብራል ሰው ሆኖ ለተፈጠረ ሁሉ፡፡ ምሁራን፣ የኃይማኖት አባቶች፣ በዛኛው ወገን ያሉ ወንድሞቻችንም ጭምር ይህን ተረድተው ትምህርትን ነጻ ሆነን እንድንስራ በጎ ሚናቸውን መጫወት አለባቸው " ሲሉ አስገንዝበዋል።

" በ2016 ዓ/ም በተለያየ ምክንያት ትምህርት ተቋርጦባቸው የቆዩ አካባቢዎች፤ ሳይማሩ የቆዩ ተማሪዎች፤ ተዘግተው የቆዩ ትምህርት ቤቶች አሉ " ሲልም ቢሮው ገልጿል፡፡

ከውድመት ጋር በተያያዘም አቶ ጌታቸው በሰጡት ቃል፣ " በክልሉ ካለው የጸጥታ ችግር ወይም ግጭት ጋር በተያያዘ ከፍተኛም መካከለኛም ጉዳት የደረሰባቸው ወደ 1115 ትምህርት ቤቶች አሉ " ነው ያሉት፡፡

" እነዚህን ትምህርት ቤቶች መልሶ ግብዓታቸውን በማሟላት ረገድ አንደኛ በአካባቢው ማህበረሰብ የሚሸፈን በዚያው ነው የሚሸፈኑት " ብለዋል፡፡

" የእኛን የክልሉን ኢንተርቬንሽን ሚጠይቁት ደግሞ አጋር አካላትን እያሳተፍን እቅድ አቅደን እያነጋገርን ነው፡፡ ከነርሱ ሀብት እያፈላለግን ትምህርት ቤቶች እንደገና ቁስቁሳቸው እንዲሟላ፣ እንዲገነቡ የማድረጉን ሥራ ወደፊት የምንስራ ነው የሚሆነው " ሲሉ አክለዋል፡፡

በክልሉ በ2016 ዓ/ም መመዘገብ ከነበረባቸው 6.2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከ2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት እንዳልተመዘገቡ ተገልጾ የነበረ ሲሆን፣ በ2017 ትምህርት ዘመን ደግሞ ቢሮው ለመመዝገብ ካቀደው ከ7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ ተመዘገቡ የተባለው 1.7 ተማሪዎች ናቸው፡፡

#TIKvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
🔈 #የወላጆችድምፅ

“ ወደ ባሕር ዳር ከተማ ልጆቻችንን ለማስመዘገብ ስንሄድ ለሚቀመጡበት ወንበር 6 ሺሕ ብር ክፈሉ እያሉን ነው ” - የተማሪ ወላጆች

“ እኔ የማውቀው ችግር የለም ” - የባሕር ዳር ከተማ ትምህርት መምሪያ

በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ዙሪያ የሚገኙ ወላጆች በጸጥታው ችግር በአካባቢያቸው መማር ያልቻሉ ልጆቻቸውን በባህር ዳር ከተማ ከፍተኛ ትምህርት ቤቶች ለማስመዝገብ ሲሄዱ ከአቅማቸው በላይ የሆነ ገንዘብ ክፈሉ እየተባሉ መሆኑን ለቲካቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

የተማሪ ወላጆች በዝርዝር ምን አሉ ?

“ በጸጥታው ችግር ምክንያት በባህር ዳር ዙሪያ ያሉ ወረዳዎች ትምህርት መቀጠል አልቻሉም፡፡

ጫናውን ተቋቁመን አንጻራዊ ሰላም ወዳለበት ወደ ባህር ዳር ልጆቻችንን ለማስመዘገብ መሸኛ ይዘን ስንሄድ ተማሪዎቹ የሚቀመጡበት አንድ ወንበር ለሦስት ይዛችሁ ስትመጡ ብቻ ነው የሚመዘገቡት እያሉን ነው።

በወላጅ ተለምነው በድርድር ወደ ገንዘብ ይቀይሩታል፡፡

አንድን ሰው 2 ሺሕ ብር፣ ለአንድ ወንበር 6 ሺሕ ብር ይጠይቃሉ፡፡ ልጆቻችን በጭንቀት ውስጥ ስለሆኑ ገንዘቡን በመክፈል ምዝገባ አካሂደናል፡፡

ተማሪዎቹ ቤተሰቦቻቸው በሚገብሩት ግብር የተሰሩ ትምህርት ቤቶች ነበሯቸው ፤ በጦርነቱ ምክንያት ስላልቻሉ ነው የመጡት። ከዚሁ ክልል ውስጥ ነው፡፡

ችግሩ ደግሞ የመጣው እራሳቸው መቆጣጠር ባለመቻላቸው ነው መስዋዕትነት እየከፈልን ያለነው። ችግሩን ተቋቁመን ስንሄድ አበረታትተው መቀበል ሲገባቸው ገንዘብ ያስከፍላሉ፡፡

ገንዘቡን ወንበር ይገዙበታል ወይ የሚለውም አጠያያቂ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ገንዘቡን ስንከፍል ደረሰኝ እንኳ አይሰጡንም፡፡

ክፍያውን የሚቀበሉት ለመመዝገብ የተወከሉ ሰዎች ናቸው፡፡ እንዲህ የሚደረገውም በባህር ዳር በሚገኙ ሃይስኩል ትምህርት ቤቶች ነው፡፡ ዞረን በጠየቅንባው ትምህርት ቤቶች ተመሳሳይ አሰራር ገጥሞናል፡፡

በጸጥታ ችግር መማር ሳይችሉ ከሚቀሩ አንጻራዊ ሰላም ወዳለበት አጎራባች ቦታ ሲሄዱ መባል የነበረበት ' እንኳን ደኀና መጣችሁ ' ነበር፡፡ ነገር ግን ተማሪዎቹ ሲሄዱ ሌላ ጫና እየተፈጠረ ነው፡፡

የወንበር ችግር ገጥሟቸውም አይመስለንም፡፡ ወላጅ ላይ የተለዬ ምሬትና ጫና ከመፍጠር በመተዛዘን ተማሪዎቹን ቢያስተናግዷቸው መልካም ነው፡፡ ገንዘቡን መክፈል ያልቻሉ መመዘገብ አልቻሉም። ” ብለዋል።

ለተነሳው ለዚህ ቅሬታ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የባሕር ዳር ከተማ ትምህርት መምሪያን ጠይቋል።

ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አንድ ኃላፊ በሰጡት ቃል፣ “ ባሕር ዳር ዙሪያ ከባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ሊመዘገብ መጥቶ ሁሉም ትምህርት ቤት ጋር ' ለሦስት፤ ለሦስት አንድ ወንበር አምጡ ወይም ወንበር ይዛችሁ ካልመጣችሁ አላስተናግድም ' ያለ ትምህርት ቤት የለም። ” ብለዋል።

“ እኛ ጋ ' ችግር ደረሰብኝ ' ብሎ የመጣም የለም፡፡ ' ወንበር አምጣ ተብያለሁ ' ብሎ መጥቶ የጠየቀኝ ተማሪም የለም፡፡ ሁሉንም ትምህርት ቤት እየዞርኩ እያየሁ ነው፡፡ የትኛውም ትምህርት ቤት ላይ እየተመዘገቡ ነው። ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ አልፎ አልፎ አንመዘግብም ያሏቸውን እራሴ እየመራሁ ነው ያስመዘገብኳቸው፡፡ ትምህርት ቤቱ የማህበረሰብ ተሳትፎ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ግን አግሪመንት ወስዶ ማህበረሰቡ የፈረመውን ነው እያስከፈለ ያለው። ” ሲሉ አክለዋል።

“ እኔ የማውቀው ችግር የለም ” ያለው ትምህርት መምሪያው፣ እንዲህ የሚያደርጉ ትምህርት ቤቶች ካሉ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ቢያሳውቁት ታች ድረስ ወርዶ እርማት እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡

ወላጆች መሰል ችግር ያለባቸውን ቦታዎች ለትምህርት መምሪያ መጠቆም እንደሚችሉ ተመላክቷል።

#TikvahethiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" ወደ ፖለቲካ ፈጽሞ መመለስ አልፈልግም ! " - የእናት ፓርቲው አቶ ዳዊት ብርሃኑ

የእናት ፓርቲ አባል፣ አመራርና የሕዝብ ግንኙነት ሆነው ያገለገሉት አቶ ዳዊት ብርሃኑ ከዛሬ (መስከረም 10 ቀን 2017 ዓ/ም) ጀምሮ በፈቃዳቸው ሥራ መልቀቃቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

" በተለይም ፓርቲው አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን መጋቢት 30 ቀን 2015  ዓ/ም ባከናወነበት ወቅት በጠቅላላ ጉባኤው በሕዝብ ግንኙነት ከተመረጥኩ በኋላ የተሰጠኝን ኃላፊነት በአግባቡ ስወጣ ቆይቻለሁ " ብለዋል።

" በትብብር ፓርቲዎችም ዘንድ ባለኝ የፀሐፊነት ሚና የበኩሌን ድርሻ ስወጣ ነበር " ነው ያሉት።

" ምንም እንኳ ፓርቲው ከተመሠረተ ያስቆጠረው እድሜ አጭር ቢሆንም የቆየሁባቸው አራት አመታት በሀሳብ ልዕልና እና በሰለጠነ የሀሳብ ጉርብትና ብቻ ፖለቲካ መስራት የሚችሉ አባላትን ያፈራንበትም ወቅት ነበር " ሲሉም አክለዋል።

ከፓርቲው የለቀቁት በምን ምክንያት ነው? በሥራ? ባለመግባባት? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ በምላሻቸው፣ " ከፓርቲው የለቀቁት በግል ውሳኔ ነው " ብለዋል።

በተለይ የፓለቲካ ምህዳሩ እንደ ጠበበ በሚገለጽበት በአሁን ወቅት በፓርቲ ሥራ ውስጥ መቆዬት ተግዳሮቱ ምንድን ነው ? ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ፣ " ከባድ ነው። የአገርና ሕዝብን አደራ መሸከም እጅግ በጣም ከባድ ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ተፎካካሪ ፓርቲዎችና ገዢው ብልጽግና ለሻከረ ግንኙነታቸው መፍትሄው ምንድነው ይላሉ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ ምላቸው፣ " ሀቀኛ፣ ሁሉን አቀፍ፣ በአግባቡ የሚመራና ግልጽ የሆነ የፓለቲካ ድርድር ማድረግ " የሚል ነው።

የፓርቲ የሕዝብ ግንኙት አገልግሎትዎ ምን ይመስል ነበር? ለሚለው ጥያቄ ደግሞ፣ " አስቸጋሪ፣ ፈታኝ እንዲሁም ከፊል ስኬታማ ነበር " ብለዋል።

ካሁን ወዲያ በሌላ ፓርቲ እንጠብቀዎት ወይስ በፓርቲ ሥራ እስከወዲያኛው እየወጡ ነው? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ "ወደ ፓለቲካ ፈጽሞ መመለስ አልፈልግም" ነው ያሉት።

እናት ፓርቲ ለወደፊት ምን ያስተካክል? ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ አቶ ዳዊት አጭር ምላሻቸው፣ "መሠረቱን" የሚል ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara " ከ7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ነው እቅድ የተያዘው ከነሐሴ 20/2016 ዓ/ም ጀምሮ የተመዘገቡት ግን 1.7 ሚሊዮን ናቸው - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በየጊዜው የተኩስ ልውውጥ የሚስተዋልበት አማራ ክልል በ2017 የትምህርት ዘመን ከ7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዘገብ እንዳቀደ፣ ከነሐሴ 20 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ…
#Amhara

“ የእኛ አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶቻችን ደረጃ 2 ላይ ያሉ ናቸው፡፡ ደረጃቸው ዝቅተኛ ግን መማር ማስተማሩን ማስኬድ የሚችሉ እንደማለት ነው ” - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

በአማራ ክልል በተለይ በጸጥታ ችግር ሳቢያ የግብዓት እጥረት ያለባቸው ትምህርት ቤቶች እንዳሉ፣ ይህም ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ማነቆ እንደሆነባቸው ወላጆች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገጸዋል፡፡

ለአብነትም እንደ መጽሐፍት፣ ወንበር መሰል ቁሳቁሶች እንደሌሉ፣ የወደሙ ትምህርት ቤቶች አለመጠገን፣ በግጭት የቀጠና ውስጥ የሆኑ አቅመ ደካማ ወላጆች ደግሞ ለልጆቻቸው እንኳ የትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዳልቻሉ ነው ያስረዱት፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጥ የክልሉን ትምህርት ቢሮ ጠይቋል፡፡

ቢሮው ምን ምላሽ ሰጠ ?

“ የግብዓት እጥረት አለብን ያሉ ትምህርት ቤቶች ይኖራሉ፡፡ ትክክል ነው፡፡ የግብዓት እጥረታቸው በሁለት መንገድ ነው የሚፈታው፡፡

አንደኛ የአካባቢውን ማህበረሰብ በማሳተፍ ነው፡፡ ሁለተኛ ደግሞ በክልል ደረጃ ደግሞ የሚሟሉ አሉ፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍት በክልል ነው የምናሟላው፡፡

ከ14 ሚሊዮን በላይ መጽሐፍት ታትመው ስርጭት ተደርጓል፡፡ አሁንም በቀጣይ የሚሰራጩ አሉ፤ ከ1 ቢሊዮን በላይ በጀት የክልሉ መንግስት መድቦ አሁንም የሚታተሙ መጽፍት አሉ፡፡

እነርሱን አሳትመን እናሰራጫለን፡፡ የመምህራን ቅጥርም እናሟላለን፣ ትክክል ነው፡፡

የእኛ ክልል ትምህርት ቤቶች ሙሉ ግብዓት የተሟላላቸው፣ ስንታንዳርዳቸውን ያሟሉ አይደሉም፡፡

ትምህርት ቤቶች በ4 ደረጃ ይከፈላሉ፡፡ ደረጃ 1፣ 2፣ 3 እና ደረጃ 4 ተብለው፡፡ ደረጃ 4 የሚባል ትምህርት ቤት በክልሉ የለንም፡፡

ደረጃውን ያሟላ በጣም ኢንተርናሽናል እንደማለት ነው፡፡ ደረጃ 3 የሚባለው ደግሞ ለተማሪዎች መማር ማስተማር የተሻለ የሆነ ትምህርት ቤት ማለት ነው፡፡

የእኛ አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶቻችን ደረጃ 2 ላይ ያሉ ናቸው፡፡ ደረጃቸው ዝቅተኛ ግን መማር ማስተማሩን ማስኬድ የሚችሉ እንደማለት ነው፡፡ ይሄ ማለት ብዙ ግብዓት የሚጎድላቸው ናቸው፡፡

ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 3ቱም ሳይንስ ቤተ ሙከራ እንዲሟላ፣ ደረጃውን የጠበቀ የኳስ ሜዳ እንዲኖረው፣ አጥር እንዲኖረው፣ ስታንዳርዱን እንዲያሟላ፣ ፋሲሊቲውን በማሟላት ረገድ መስራት የሚጠይቀን ሥራ አለ፡፡

እሱን በእቅድ ለመምራት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ ግን ሙሉ የሕብረተሰቡን ተሳትፎ የሚጠይቅ ሥራ ነው፡፡

የእኛን ትምህርት ቤቶች በስንት ዓመት እንቀይራቸዋለን ደረጃቸውን ለማሻሻል ብለን አንድ በጣም ትልቅ የለውጥ እቅድ አቅደን ወደ ሥራ በገባን ማግስት ነው የጸጥታው ችግር የተፈጠረው፡፡

በዚህ ዓመት ውስጥ ትምህርት ቤቶቹን እንቀይራለን ብለን ነበር ዞሮ ዞሮ ወደ ሥራ መግባት አልተቻለም ”
ብሏል፡፡

የግብዓት እጥረት ላለባቸው ከባለሀብቶችና ባለንብረቶች ድጋፍ የማሰብሰብ ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ቢሮው ገልጿል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ጠቅላላ የአካል ጉዳተኞች ሕግ ከሁለት ዓመት በላይ የተስፋ እንጀራ ብቻ ሆኖብናል " - አቶ አባይነህ ጉጆ

የአካል ጉዳተኞችን ዘርፈ ብዙ የሆኑ ችግሮች ይፈታል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል የተባለው " ጠቅላላ የአካል ጉዳተኞች ሕግ " በታቀደለት ወቅት አለመውጣቱ አካል ጉዳተኞችን ዋጋ እያስከፈለ መሆኑን የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበር ፌደሬሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የማኅበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይነህ ጉጆ  ምን አሉ?

“የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ሲነሳ በርካታ ችግሮች አሉ፡፡ ሆኖም ብዙ ችግሮቻችንን ሊቀርፍልን ይችላል ብለን እየጠበቅን ያለነው ጠቃላላ የአካል ጉዳተኞች ሕግ ይወጣል ብሎ መንግስት ተስፋ ሰጥቶናል።

በተስፋ ብቻ አላበቃም ሕጉ ድራፍት ተደርጎ የጋራ ምክክር ሕጉ ላይ አካል ጉዳተኞችም ተሳትፎ ከተረጋገጠበት በኋላ ለፍትህ ሚኒስቴር ሂዶ ነበር።

ፍትህ ሚኒስቴር አንዳንድ በእኛ በኩልም ተቀባይነት የሌላቸውን ኮመንቶች በመስጠት ወደኋላ መልሶታል። ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው ሕጉን በባለቤትነት የሚያረቀው።

ጠቅላላ የአካል ጉዳተኞች ሕግ ከሁለት ዓመት በላይ የተስፋ እንጀራ ብቻ ሆኖብናል፡፡

እሱ ሕግ ቢወጣ የተሻለ ነገር ሊያመጣ ይችላል።

ሕጉ ቢወጣ እውነት ለመናገር በርካታ ችግሮቻችንን ይቀርፋል ብለን እናምናለን"
ብለዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-09-24

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ወደ 28 ሰዎች ናቸው የሞቱት፡፡ በአጠቃላይ 47 ሰዎች ላይ ሞት፤ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል፡፡ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል " - የዞኑ ፖሊስ መምሪያ

በወላይታ ሶዶ ዞን ዛሬ (ረቡዕ መስከረም 15 ቀን 2017 ዓ/ም) ከቀኑ 7 ሰዓት ደረሰ በተባለ የትራፊክ አደጋ የበርካቶች ሕይወት ሲያልፍ በ47 ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡

አደጋው የደረሰው መነሻውን ከወላይታ አድረጎ ወደ ዳውሮ ዞን ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ፓፓታ ቀበሌ ሲደርስ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል፡፡

በአደጋው የሞቱትና የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ምን ያክል ናቸው ? ስንል የጠየቅናቸው የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ንጋቱ በሰጡን ምላሽ፣ " በወደ 28 ሰዎች ናቸው የሞቱት፡፡ በ14 ሰዎች ከባድ፣ በ5 ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሷል " ብለዋል።

" አጠቃላይ ወደ 47 ሰዎች ላይ ሞት፤ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል " ብለዋል፡፡

" ከሕጻን እስከ አዋቂ ድረስ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ነው ጉዳት የደረሰባቸው " ነው ያሉት፡፡

" የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል፡፡ አሁን ወደ 8 ሰዎችም ወደ ከፍተኛ ህክምና ሪፈር እየተላኩ ስለሆነ ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል " ሲሉ ኮማንደሩ ተናግረዋል፡፡

አደጋው የደረሰበት ምክንያት ታውቋል ? ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ " የቴክኒክ ምርመራ ተደርጎ ወደፊት ነው የሚገለጸው፡፡ ለአሁን ግን ዳገት ተሽከርካሪው ዳገት እየወጣ እስክራፕ ነው የገጠመው፡፡ ከትልቅ ዳገት ላይ ወደ ቁልቁለትና ርቀት ባለው ወንዝ ውስጥ ነው አጠቃለይ ተሳፋሪዎችን ይዞ የገባው " ሲሉ መልሰዋል።

ተሽከርካሪው ስንት ሰዎችን ነበር ያሳፈረው ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ፣ " አጠቃላይ ቁጥሩን እየመዘገብን ነው፡፡ እስካሁን ባለው መረጃ በ47 ሰዎች ላይ ነው ሞትና ጉዳት የደረሰው፡፡ ጉዳት ሳይደርስባቸው የተረፉ ወደ 6 ሰዎች አሉ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

" ጠቅላላ ተሳፋሪዎቹ ከ56 እስከ 60 ሰዎች ይደርሳል የሚል ግምት አለን " ነው ያሉት፡፡

" ቦታው ወንዝ ውስጥ ነው፡፡ የአካባቢው ማህበረሰብም የጸጥታ ኃይልም ተረባርቦ ጉዳት የደረሰባቸውን የማንሳት፣ የተጎዱ በፍጥነት ወደ ህክምና እንዲደርሱ እየተደረገበት ያለ ሁኔታ አለ " ነው የተባለው፡፡

ምን ያክል ሰዎች ናቸው ወደ ሕክምና የተላኩት ? ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ፣ " ጠቅላላ ወደ 21 ሰዎች ወደ ወደ ሆስፒታሎች ተልከዋል፡፡ 8 ሰዎች ከሆስፒታል ሪፈር ተብለው ወደ ክርስቲያን ሆስፒታል ተጭነው እየወጡ ያሉት ሁኔታ ነው ያለው " ተብሏል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ወደ 28 ሰዎች ናቸው የሞቱት፡፡ በአጠቃላይ 47 ሰዎች ላይ ሞት፤ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል፡፡ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል " - የዞኑ ፖሊስ መምሪያ በወላይታ ሶዶ ዞን ዛሬ (ረቡዕ መስከረም 15 ቀን 2017 ዓ/ም) ከቀኑ 7 ሰዓት ደረሰ በተባለ የትራፊክ አደጋ የበርካቶች ሕይወት ሲያልፍ በ47 ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡ አደጋው…
#Update!

“ ከባድ ሁኔታ ላይ ያሉ ተጎጅዎች አሉ፡፡ የ26 ሰዎች አስከሬን ተለይቶ ወደ ዳውሮ ዞን፣ የሁለት ሰዎች ደግሞ ወደ ወላይታ ዞን ተሸኝቷል ” - ወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ

ከወላይታ ዞን ወደ ዳውሮ ዞን እየተጓዘ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ዲዳዬ ወረዳ ፓፓታ ቀበሌ ሲድረስ ትላንት በደረሰበት ድንገተኛ አደጋ በ48 ተሳፋሪዎች ላይ ሞት፣ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹን ነግረናችሁ ነበር፡፡

ፖሊስ፣ አስክሬን የመፈልግ ሥራው እንደቀጠለ፣ በተለይ በ8 ተሳፋሪዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ስለደረሰ ሪፈር እንደተባሉና በዚህም የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ነበር የገለጸው፡፡

ሪፈር የተባሉት ተጎጅዎች እንዴት ሆነው ይሆን ? ስንል ዛሬ በድጋሚ የጠየቅናቸው የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ንጋቱ ጌታቸው ምላሻቸው፣ “ ተጎጅዎች ሕክምና እየተከታተሉ ናቸው፡፡ ጉዳቱ ከባድ ስለሆነ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ” ብለዋል።

“ በክርቲያን ሆስፒታል፤ ኦቶና ሆስፒታልም ሕክምና እየተከታተሉ ነው፡፡ አንዳንድ ከባድ ሁኔታ ላይ ያሉ ተጎጅዎች አሉ ” ብለዋል፡፡

ኮማንደሩ የደረሰውን አደጋ ሂደት በተመለከተም፣ “ አስከሬን ወደ ቤተሰብ የመሸኘት ሥራ ተሰርቷል፡፡ የ26 ሰዎች አስከሬን ማንነታቸው ተለይቶ ወደ ዳውሮ ዞን፣ ሁለት ሰዎች ደግሞ ወደ ወላይታ ዞን ተሸኝቷል ” ነው ያሉት፡፡

“ ቀሪ ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው 22 ተሳፋሪዎች በኦቶና ወላይታ ሶዶ ሆስፒታል እየታከሙ ነው ” ሲሉ ገልጸዋል።

“ አስክሬን የማውጣት፣ ምርመራ የማድረግ ሥራ ሌሊቱን ጭምር እስከ 11 ሰዓት ድረስ ወስዷል፡፡ ሕዝቡ፣ አመራሩ፣ የጸጥታ ኃይሉ፣ ሙያተኞች ሁሉ ተረባርበዋል” ብለው፣ በዛ በአስቸጋሪ ቦታ ርብርብ ላደረጉት የወገን ደራሾች ምስጋና አቅርበዋል።

° አሽከርካሪው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር እንደዋለ፣
° ቀላል ጉዳት እንደደረሰበት፣ ከሆስፒታል ክትትል አድረጎ እንደወጣ፣
° አሽከርካሪው ቃሉን ሲሰጥ የተለዬ መረጃ ካልተገኘ በቀር እስከሁን ባለው መረጃ በተሽከርካሪው ተሳፍረው የነበሩት ወደ 56 ሰዎች እንደነበሩ፣
° 6ቱ ተሳፋሪዎችም አደጋ ሳይደረስርባቸው እንደተረፉ አስረድተዋል።

“ የትራፊክ አደጋ ከገዳይ በሽታም በበለጠ የአገር ተረካቢ ትውልድን ጭምር እየጨረሰ፤ መተኪያ የሌለውን ሕይወትም እየቀጠፈ ነው " ብለዋል

" አሽከርካሪዎ፤ ባለንብረቶች፣ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ የትራፊክ ደንብና ሕግን አክብረው እንዲሽከረክሩ ጥሪ አቀርባለሁ ” ሲሉ ኮማንደሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የተሳፋሪዎች ቁጥር ከ56ም ሊጨምር ይችላል የሚል ግምት እንዳለ፣ የአደጋው ቴክኒካል ምክንያት ገና በምርመራ ላይ እንደሆነ የተመላከተ ሲሆን፣ በህክምና ላይ ያሉት ተጎጅዎችን ሁኔታ ጭምር ተከታትለን መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ተከፍቷል

በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ከተከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ጋር በተያያዘ  ተዘግተው የነበሩ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ክፍት ተደርገዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ

“ የኢትዮ ቴሌኮም ነጻ ዳታ ሽልማት ለሁሉም አሮጌ ሲም ካርድ ተጠቃሚዎች ” በሚል ሰሞኑን ነጻ ሜጋ ባይት ለማግኘት “ ሊንክ ጠቅ ያድርጉ ” የሚል መልዕክት በማኅበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት ወደተለያዩ ግለሰቦች እየተላከና እየተዘዋወረ ነው፡፡

ይሄው ከሥሩ ሊንክ የተቀመጠበት የሚዘዋወረው መልዕክት ፡-
➡️ 6 ወር ለቆየ ሲም፣ 10GB
➡️ 1 ዓመትና ከዚያ በላይ፣ 20GB
➡️ ከ5 አመት በላይ ለቆየ ሲም፣ 50GB ነጻ ሽልማት ኢትዮ ቴሌኮም እየሰጠ መሆኑን የሚገልጽ ነው፡፡

አንዳንድ ሊንኩን የከፈቱ ሰዎችም፣ “ ስንከፍተው መረጃዎት እየተበረበረ ነው ይላል፡፡ ጉድ ተሰርተናል ” ሲሉ የተስተዋሉ ሲሆን፣ ብዙዎች ደግሞ ይህን ጉዳይ ኢትዮ ቴሌኮም ያውቀዋል ? በማለት እየጠየቁ ነው፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የሚዘዋወረውን መልዕክት ተቋሙ ያውቀዋል? ትክክለኛስ ነው? ሲል ኢትዮ ቴሌኮምን ጠይቋል፡፡

የተቋሙ ቺፍ ኮሚዩኒኬሽን ኢፊሰር አቶ መሳይ ውብሸት ምን ምላሽ ሰጡ ?

“ የኛ ቲምም ቼክ አድርጎታል፡፡ Phishing የሚሉት የማጭበርበር መልዕክቶችን የሚልኩ ናቸው፡፡

ታማኝ ከሆኑ ካምፓኒዎች የሚላኩ መልዕክቶችን በማስመስልና የሰዎችን መረጃ የሚወስዱ Phishing  ብለን የምንጠራቸው የሳይበር ጥቃት መንገዶች ናቸው፡፡

እኛ ያስቀመጥነውም እንሰጣለን ያልነው ሽልማትም የለም፡፡ የላክነውም መልዕክት የለም፡፡ የኛ የሴኩሪቲ ቲምም እየተከታተለ ነው፡፡

ሊንክ ልከው እርሱን ንኩ ነው ‘ንኩ’ የሚሉት የእድሉ ተጠቃሚ ለመሆን፡፡ ግን ፐርሰናል መረጃዎችን የመውሰድና ላልተገባ ነገር ሰዎችን ለመዳረግ የሚያደርጉት ጥረት ነው፡፡

ዌብሳይቶቹን የኛ ቲሞች ሞኒተር እያደረጉ ሰዎች ላይ ጥቃት እንዳይደርስ ቁጥጥር እያደረጉ ነው፡፡

ሳይቶቹን የመዝጋት ሥራዎች እየተሰሩ ነው በቅንጅት፡፡ ስህተት እንደሆነ፣ የኛ እንዳልሆነ ሰው እንዲያውቅ እናደርጋለን፡፡

ይኛው መልኩን ቀይሮ የሰውን መረጃ ለመውሰድ ሆነ እንጂ ብዙ ጊዜ በተለይ ቴሌግራም አካባቢ ላይ ተከታይ ለማግኘት በኢትዮ ቴሌኮም፣ በቴሌ ብር እየተከፈቱ ደንበኛ ለማብዛት የሚደረጉ ጥረቶች አሉ፡፡

ይሄም ኢንቴንሽኑ ሌላ ቢሆንም ያው ነው፡፡ ከእኛም ብቻ አይደለም ምንጩን ስናጣራው ከሌላ አገር ውስጥ የሚመጣ፣ ወደ ሌላ አገር ሪፈር የሚያደርግ ነው ሊንኩ፡፡

የትልልቅ ተቋማት መልዕክት በማስመስል ሊንኮችን አስቀምጠው አጓጊ ሽልማቶችን እየሰጡ የሰዎችን መረጃ የማጭበበርበር ነገር ነው የሚፈጠረውና Phishing በተለያዬ በኢሜይል፣ በቴክስት፣ በጥሪ መልክም ሊመጣ ይችላል፡፡

ሰዎች ሊንኩን ባለመንካት ከእንደዚህ አይነት አሳሳች መልዕክቶች ራሳቸውን ይጠብቁ፡፡ እንዲህ አይነት ጉዳይ ሲገጥማቸውም በ9090 በነጻ ደውለው በዚያ እንዲያሳውቁንም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ”
ብለዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) በበኩሉ፣  “ የኢትዮ ቴሌኮም ነጻ ዳታ ስልማት ለሁሉም አሮጌ ሲም ካርድ ተጠቃሚዎች ” በሚል መልዕክቶች ወደ ተለያዩ ግለሰቦች እየተላኩ መሆኑን እንዳረጋገጠ አስታውቋል፡፡

አስተዳደሩ፣ “ መልዕክቱ የግለሰቦችን ሚስጥራዊ መረጃዎችን የማጥመድ ጥቃት (Phishing Attack) መሆኑን ማረግገጥ ችያለሁ ” ብሎ፣ ግለሰቦች ሊንኩን ባለመክፈት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሪልስቴት #Update " ቤት ገብተው የሚኖሩ ሰዎች አሉ በጣም ነው የሚያሳዝኑት መብራትና ውሃ ስለሌለ እንጀራ ጋግረው አያውቁም እሱን እያየን ለመግባት ተቸግረል " - የኖህ ሪልስቴት ቤት ገዢዎች "...ለፕሬስ መግለጫ አልሰጥም  " - ኖህ ሪልስቴት የኖህ ሪልስቴት ሀያት ግሪን ቤት ገዢዎች ድርጅቱ በውሉ መሠረት የቤቱን መሠረተ ልማት እንዳላሟላላቸው በድጋሚ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታ አቀረቡ፡፡…
#Update

" በድጋሚ ቢሮ ሂደን ጠየቅናቸው ግን የተስፋ ቃል ከመስጠት ውጪ መሬት ላይ ምንም ተጨባጭ ነገር አይሰሩም  " - ቤት ገዢዎች

ከ600 በላይ የሚሆኑ የአያት ግሪን ኖህ ሪልስቴት ቤት ገዢዎች፣ በውላቸው መሠረት ድርጅቱ የመብራት፣ የውሃ፣ የታንከር መሠረተ ልማቶችን ባለሟማላቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከፍለው ከገዙት ቤታቸው መግባት እንዳልቻሉ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል እሮሮ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

በወቅቱ ለጉዳዩ ምላሽ የጠየቅነው ኖህ ሪልስቴት በበኩሉ፣ አንድ ጊዜ በሰጠን ምላሽ የመብራት፣ ውሃ፣ የታንከር ችግር እንዳለና መሠረተ ልማቶቹን ለማሟላት የዘገየው ችግር ገጥሞት እንደሆነ ገልጾ፣ " በጣም በአጠረ ጊዜ ውስጥ ለመስራት እየሞከርን ነው " ሲል ቃል ገብቶ ነበር፡፡

ይሁን እንጅ ቅሬታቸው ባለመፈታቱ ገዢዎቹ ከወራት በኋላ በድጋሚ ቅሬታ አቅርበዋል፡፡

ድርጅቱን በድጋሚ ጥያቄ ስናቀርብለት ግን፣ " በጠበቃቸው አማካኝነት እየተከታተሉ ስለሆነና ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት የመሄድ እድል ስላለው የድርጅቱን የመከራከር መብት የሚያጣብብ ስለሚሆን ለፕሬስ መግለጫ አልሰጥም " ከማለት ውጪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጠቧል፡፡

ገዢዎቹ አሁንስ ዝርዝር ምን አሉ ?

" ምን ማድረግ እንዳለብን ጨነቀን፡፡ በገንዘባችን ቤት ገዝተን መሠረተ ልማቱ እንዲሟላ ለዓመታት እየለመንን እንገኛለን፡፡ እኛ ዋናው ጥያቄያችን ቤታችን ተጠናቆልን እንድንገባ ነው፡፡

በድጋሚ ቢሮ ሂደን ጠየቅናቸው ግን የተስፋ ቃል ከመስጠት ውጪ መሬት ላይ ምንም ተጨባጭ ነገር አይሰሩም፡፡ ማጭበርብር ማታለል ነው የተያያዙት፡፡ የሚነግሩን ነገር በብዙ ውሸት ታጀበ ነው፡፡

እየሄድን ስንጠይቅ በቃ መጫወቻ ነው የሚያደርጉን ንቀት ያለበት ቃላት ከመስጠት ውጪ ምንም የሚሰሩልን ነገር የለም፡፡

20፣ 30 እየሆንን እየተሰበሰብን እየሄድን ስድስት፣ ሰባት ጊዜ በአካል ቢሯቸው ሂደን ጠየቅናቸው ግን ቃል ከመግባት ውጪ የሚያደርጉት ነገር የለም፡፡

ስለዚህ ጠበቃ ወክለን በጠበቃችን አማካኝነት ያለበትን ፕሮጀክት ሂደት ስጡን፣ መቼ ትጨርሳላችሁ? ብለን ጠየቅናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድርም ተሰብስብን ሂደን ጠየቅን ግን ይህንን የሚከታተል አካል የለም፡፡ ሌላው የሚገርመው ነገር ደግሞ ይሄ ነው፡፡

በሌላ በኩል ግን ቤቱ ሳይጠናቀቅ የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ራሱ ሳይቱን ሂዳ መርቃለች፡፡

እኛን ብቻ ሳይሆን እሷንም ሸውደዋታል፡፡ ኤሌክትሪክ ጠልፈው፣ ኤሊቬተሩን አሰርተው፣ ፊኒሽንጉን የጨረሰ አንድ የቤት ባለቤት አለ እርሱን ለምነው ያንን ቤት ነው ያሳዩዋት (ለከንቲባዋ ማለታቸው ነው)፡፡

ከተማ አስተዳደሩም ያለውን እውነታ እንዲያውቅልን እንወዳለን፡፡ ቤቱ ተጠናቀቀ ብለው እኛ ላይ ዜና፤ ፕሮሞሽን ሰርተውብናል፡፡ ቤቱ ግን የውሃና የጋራ መሠረተ ልማቱ ምንም አላለቀም፡፡

አሁንም በውላችን መሠረት የውሃ፣ መብራት፣ ኢሊቬተር መሠረተ ልማቶች እንደሚሟሉልን እንጠይልን " ብለዋል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia