TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሪልስቴት #Update " ቤት ገብተው የሚኖሩ ሰዎች አሉ በጣም ነው የሚያሳዝኑት መብራትና ውሃ ስለሌለ እንጀራ ጋግረው አያውቁም እሱን እያየን ለመግባት ተቸግረል " - የኖህ ሪልስቴት ቤት ገዢዎች "...ለፕሬስ መግለጫ አልሰጥም  " - ኖህ ሪልስቴት የኖህ ሪልስቴት ሀያት ግሪን ቤት ገዢዎች ድርጅቱ በውሉ መሠረት የቤቱን መሠረተ ልማት እንዳላሟላላቸው በድጋሚ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታ አቀረቡ፡፡…
#Update

" በድጋሚ ቢሮ ሂደን ጠየቅናቸው ግን የተስፋ ቃል ከመስጠት ውጪ መሬት ላይ ምንም ተጨባጭ ነገር አይሰሩም  " - ቤት ገዢዎች

ከ600 በላይ የሚሆኑ የአያት ግሪን ኖህ ሪልስቴት ቤት ገዢዎች፣ በውላቸው መሠረት ድርጅቱ የመብራት፣ የውሃ፣ የታንከር መሠረተ ልማቶችን ባለሟማላቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከፍለው ከገዙት ቤታቸው መግባት እንዳልቻሉ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል እሮሮ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

በወቅቱ ለጉዳዩ ምላሽ የጠየቅነው ኖህ ሪልስቴት በበኩሉ፣ አንድ ጊዜ በሰጠን ምላሽ የመብራት፣ ውሃ፣ የታንከር ችግር እንዳለና መሠረተ ልማቶቹን ለማሟላት የዘገየው ችግር ገጥሞት እንደሆነ ገልጾ፣ " በጣም በአጠረ ጊዜ ውስጥ ለመስራት እየሞከርን ነው " ሲል ቃል ገብቶ ነበር፡፡

ይሁን እንጅ ቅሬታቸው ባለመፈታቱ ገዢዎቹ ከወራት በኋላ በድጋሚ ቅሬታ አቅርበዋል፡፡

ድርጅቱን በድጋሚ ጥያቄ ስናቀርብለት ግን፣ " በጠበቃቸው አማካኝነት እየተከታተሉ ስለሆነና ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት የመሄድ እድል ስላለው የድርጅቱን የመከራከር መብት የሚያጣብብ ስለሚሆን ለፕሬስ መግለጫ አልሰጥም " ከማለት ውጪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጠቧል፡፡

ገዢዎቹ አሁንስ ዝርዝር ምን አሉ ?

" ምን ማድረግ እንዳለብን ጨነቀን፡፡ በገንዘባችን ቤት ገዝተን መሠረተ ልማቱ እንዲሟላ ለዓመታት እየለመንን እንገኛለን፡፡ እኛ ዋናው ጥያቄያችን ቤታችን ተጠናቆልን እንድንገባ ነው፡፡

በድጋሚ ቢሮ ሂደን ጠየቅናቸው ግን የተስፋ ቃል ከመስጠት ውጪ መሬት ላይ ምንም ተጨባጭ ነገር አይሰሩም፡፡ ማጭበርብር ማታለል ነው የተያያዙት፡፡ የሚነግሩን ነገር በብዙ ውሸት ታጀበ ነው፡፡

እየሄድን ስንጠይቅ በቃ መጫወቻ ነው የሚያደርጉን ንቀት ያለበት ቃላት ከመስጠት ውጪ ምንም የሚሰሩልን ነገር የለም፡፡

20፣ 30 እየሆንን እየተሰበሰብን እየሄድን ስድስት፣ ሰባት ጊዜ በአካል ቢሯቸው ሂደን ጠየቅናቸው ግን ቃል ከመግባት ውጪ የሚያደርጉት ነገር የለም፡፡

ስለዚህ ጠበቃ ወክለን በጠበቃችን አማካኝነት ያለበትን ፕሮጀክት ሂደት ስጡን፣ መቼ ትጨርሳላችሁ? ብለን ጠየቅናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድርም ተሰብስብን ሂደን ጠየቅን ግን ይህንን የሚከታተል አካል የለም፡፡ ሌላው የሚገርመው ነገር ደግሞ ይሄ ነው፡፡

በሌላ በኩል ግን ቤቱ ሳይጠናቀቅ የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ራሱ ሳይቱን ሂዳ መርቃለች፡፡

እኛን ብቻ ሳይሆን እሷንም ሸውደዋታል፡፡ ኤሌክትሪክ ጠልፈው፣ ኤሊቬተሩን አሰርተው፣ ፊኒሽንጉን የጨረሰ አንድ የቤት ባለቤት አለ እርሱን ለምነው ያንን ቤት ነው ያሳዩዋት (ለከንቲባዋ ማለታቸው ነው)፡፡

ከተማ አስተዳደሩም ያለውን እውነታ እንዲያውቅልን እንወዳለን፡፡ ቤቱ ተጠናቀቀ ብለው እኛ ላይ ዜና፤ ፕሮሞሽን ሰርተውብናል፡፡ ቤቱ ግን የውሃና የጋራ መሠረተ ልማቱ ምንም አላለቀም፡፡

አሁንም በውላችን መሠረት የውሃ፣ መብራት፣ ኢሊቬተር መሠረተ ልማቶች እንደሚሟሉልን እንጠይልን " ብለዋል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

በምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት " አስቸኳይ " ያለውን ሰብሰባ ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።

ዛሬ መሰከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም በመቐለ በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅ/ቤት አዳራሽ መካሄድ በጀመረው ስብሰባ በሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራውን ህወሓት በይፋ የተቃወሙ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ከፍተኛ ካድሬዎች ተገኝተዋል። 

አቶ ጌታቸው በሰብሰባው መክፈቻ " ፓለቲካዊና ሰላማዊ ትግል በማጠንከር በብቃት በመምራት ወደፊት የሚያራምድ አመራር መፍጠር ልዩ ትኩረት  ያሻዋል " ብለዋል። 

ህወሓት ያጋጠመው ችግርና መፍትሄዎቹ አልሞ መካሄድ በጀመረው ስብሰባ በድርጅቱ ወስጥ የተፈጠረው ችግር ተገንዝቦ ውስብስቡን በማቅለል ተገቢ የፓለቲካ መፍትሄና አቅጣጫ የሚሰጥ አመራር የሚያስፈልግበት ወቅት አሁን ነው ተብሏል። 

" የፕሪቶሪ ስምምነት ህዝብን ከተጨማሪ እልቂት የታደገ ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው " ስምምነቱ ያሰገኘው ሰላም ማስቀጠል ቁልፍ ጉዳይ ነው " ብለዋል።

" በምክትል ሊቀመንበር የተመራው ማእከላይ ኮሚቴና የከፍተኛ ካድሬዎች ስበሰባ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል " ሲል ድምፂ ወያነ ጠቅሶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#VisitAmhara

ግሸን ደብረ ከርቤ !

ግሸን ደብረ ከርቤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በአንጋፋነታቸው ከሚታወቁት ቅዱሳን ሥፍራዎች አንዷ ናት፡፡

የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም ሌሎች የገዳሟን ታሪክ ማወቅ የሚፈልጉ ሰዎች በየጊዜው ወደ ግሸን ይጓዛሉ፡፡

በተለይ ከመስቀል በዓል እስከ መስከረም 21፣ ጥር 21 እንዲሁም መጋቢት 10 ወደ ግሸን የሚጓዘው ሕዝብ በመቶ ሽዎች ይቆጠራል፡፡

በረከት ለማግኘት፣ ታሪክ ለማወቅ እና ለመፈወስ ግሸን ለእምነቱ ተከታዮች ቀዳሚ መዳረሻ ናት፡፡

በኢትዮጵያ የሀይማኖት ቱሪዝም ታሪክ ብዙ እንግዶችን በማስተናገድ ግሸን ከቀዳሚዎች መካከል ትገኛለች፡፡

ነገ መስከረም 21 ታላቁ የግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ክብረ በዓል ይከበራል፡፡

እንኳን አደረሳችሁ !

(Vist Amhara)

#TourismAndPeace  #GishenDebreKerbe #SouthWollo #ReligiousFestival #Ethiopia #LandOfOrigins

@tikvahethiopia
" ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥምቅት 30/2017 ወደ ቤታችሁ ግቡ ፤ ይህ ካልሆነ የሽያጭ ውሉ እንዲቋረጥ ተደርጎ ቤቱን ለሌላ ዕድለኛ እናስተላልፋለን " - የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እየገነባ ለቤት ተጠቃሚዎች በዕጣና በጨረታ የሚያስተላልፈው የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን " በሽያጭ ከተላለፉና ውል ከተፈጸመባቸው ቤቶች መካከል የቤት ባለቤቶች ወደ ቤታቸው ገብተው እየኖሩ አለመሆኑን አረጋግጫለሁ " ብሏል።

" በህጋዊ መንገድ ውል የተያዘባቸው ቤቶች ለህገወጥ ተግባር እየዋሉ ነው " ያለው ኮርፖሬሽኑ ፥ የቤት ባለቤቶች ከኮርፖሬሽኑ ጋር በያዙት የሽያጭ ውል ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ወደ ቤታቸው እንዲገቡ አስጠንቅቋል።

" በተባለው ጊዜ ውስጥ ወደ ቤቱ የማይገባ የቤት ባለቤት የሽያጭ ውሉ በህግ አግባብ እንዲቋረጥ ተደርጎ ቤቱን ለሌላ ዕድለኛ እናስተላልፋለን " ሲልም ገልጿል።

#AddisAbaba

@tikvahethiopia
#CBE🚨

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት ክፍያ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ ተጨመረ።

መንግስት በቅርቡ ባወጣው አዲስ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሕግ መስረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚያቀርባቸው ምርት እና አገልግሎቶች ላይ በነበረው የአገልግሎት ክፍያ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲከፈልባቸው መወሰኑን ገልጿል።

በዚህም ከነገ መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ. ም ጀምሮ የባንኩ ምርትና የአገልግሎት ዓይነቶች ላይ በሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ የተጨመረባቸው መሆኑን ባንኩ አሳውቋል።

@tikvahethiopia