TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

የመጅሊሱ ቅሬታ ምንድነው ?

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ህዝበ ሙስሊሙ ሀገራዊ ምክክሩን እጅግ እንደሚደግፈው ነገር ግን ከምክክሩ ተሳታፊዎች ጋር በተያያዘ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እንዳልተሰጠው በዚህም ምክንያት ቅሬታ እንዳደረበት ገልጿል።

ም/ቤቱ ያደረበት ቅሬታ " በምክክሩ ላይ የሙስሊሞች ውክልና አነስተኛ ነው ፤ ይህ ደግሞ በምክክር ውጤቱ ላይ ተጽእኖ እንዳያሳድር ስጋት አለኝ " የሚል ነው።

" #ከወረዳ እስከ #ክልል ድረስ የሚሳተፉት ተወካይ ሙስሊሞች ቁጥር እጅግ አነስተኛ ነው " የሚለው ም/ቤቱ ፥ " እንደ ሙስሊም በጋራ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ መግባባት ላይ ለመድረስ በቂ ተወካዮች አልተወከሉም " ብሏል።

የምክር ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ከማል ሀሩን ምን አሉ ? (ለሃሩን ሚዲያ)

- ሙስሊሙ ከምንም በላይ ምክክሩን ይፈልገዋል።

- ሙስሊሙ የቆዩ ችግሮች ስላሉበት ይሄን ምክክር እንዲሳካ በጣም ከሚደግፉት ማህበረሰብ ክፍሎች ዋነኛው ነው።

- ከሌሎች እምነቶች ሲነጻጸር ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለዚህ ምክክር ያለው ድጋፍ ፈጽሞ ሊወዳደር የሚችል አይደለም። ሙስሊሙ ይህንን ምክክር የሚፈልገው ያልተመለሱለት ጥያቄዎቹ እንዲመለሱለት ነው።

- ተወካዮች ከታች ሲመረጡ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ተሳታፊ እንዲሆን ያስፈልጋል። ኮሚሽኑም check and balance ማድረግ አለበት ፤ በትክክልም የዚህን ማህበረሰብ ጥያቄዎች የሚያነሱ ተወካዮች ተወክለዋል የሚለውን።

- የተሳታፊዎች ልየታ ከታች ጀምሮ ሲመጣ በትክክል ሁሉም ማህበረሰብ መወከሉን ማረጋገጥ ይገባል። ኮሚሽኑም ከሌሎች እምነቶች ጋር balance የማድረግ ስራ ይጠበቅበታል።

- ተሳትፎ ላይ ቁጥሩ የተዛባ ከሆነ፣ በጣም አነስተኛ ከሆነ ቅሬታ ስለሚያስከትል ጥንቃቄ ያስፈልጋል።

- ኮሚሽኑ አካሄድ የነበረው ሲቪል ማህበራት፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ መምህራን ፣ አርብቶ አደሮች፣ እድሮች፣ የፍትህ አካላት፣ የመንግሥት ሰራተኞች፣ ፖለቲከኞች የያዘ ነው በሃይማኖት መልክ ግን የቀረበ ነገር የለም። እነዚህ አደረጃጀቶች ምን ያህል ሙስሊሙ ተሳትፎ አለው ? የሚለው ያሳስበናል፤ ስጋትም አድሮብናል።

- የተነሱ ጥያቄዎችን እና ያሉትን ስጋቶች በተደጋጋሚ ለኮሚሽኑ ቀርበው የጋራ ኮሚቴ ጭምር እንዲቋቋም መረጃዎችም እንዲሰጡ ተጠይቆ በተለያየ ምክንያት ሊሳካ አልቻለም።

- ውይይቶች አድርገናል በተደጋጋሚ ፤ በውጤቱ ላይ የሙስሊሙን ተሳትፎ የሚያሳዩ መረጃዎች (ዳታ) ማግኘት አልተቻለንም።

- እንደ አጀንዳ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄዎች በ9 አጀንዳዎች ተካተው ፣ በ47 ጥያቄ ቀርቦ የካቲት 2 ላይ ለኮሚሽኑ ቀርቧል። መጨረሻ ላይ ኮሚሽኑ ያንን የማስፈጸም ኃላፊት አለበት።

- ታች ያለው የማህበረሰቡ ውክልና በተሻለ ሁኔታ ሁሉ የሃይማኖት ተቋማት ባገናዘበ፣ ሃይማኖት ተቋማትን balanced ባደረገ ሁኔታ መታየት አለበት ቁጥሩ። ለምሳሌ ፦ ከ12 ሺህ ምን ያህል ሙስሊም ተካቷል ፤ ከአዲስ አበባም ከ2500 ተሳታፊ ካለ ምን ያህል ሙስሊም ተሳታፊ ነው ? የሚለው ነው የማህበረሰቡ ጥያቄ።

- እኛ በቂ መረጃዎች የሉንም ለማህበረሰቡ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት አስቸጋሪ ነው። በአንዳንድ ሁኔታ ስናጣራ በጣም አነስተኛ ቁጥር ያለበት ስለሆነ የተሻለ ውጤት እንዲገኝ ጥያቄ በማያስነሳ መንገድ እንዲሄድ ማድረግ ይገባል።

- የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተሳታፊ ቁጥር አነስተኛ ከሆነ የሚቀርበው አጀንዳ ይቀራል ፤ ያ ደግሞ እጅጉን ያሳስበናል።

- በእኛ በኩል አሁንም ምላሽ እየጠበቅን ነው።

#EthiopianMuslims
#HarunMedia
#NationalDialogue

@tikvahethiopia
" የተፈጸመው ወንጀል ጭካኔ የተሞላበት አረመኔያዊ ወንጀል ነው " - ፖሊስ

በጫጉላ ምሽት ሚስቱን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን የሃላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ሟች ሪባቴ ትባላለች።

ሟች እና ወንድሟ በግድያ ተጠርጣሪው ግለሰብ አማካኝነች ቁርዓን እንደሚቀሩ ከሟች እህት አመደልሃዲ አንደበት ለመስማት ተችሏል።

ተጠርጣሪው ሟችን ማግባት እንደሚፈልግና ለሟች ወንድም በጓደኛው አማካኝነት ሃሳቡን ይገልጽለታል።

የሟች ወንድም አብዱልሃዲም ሟች እህቱን " ተስማምተሻል ወይ ? " በሚል መጠየቁንና ከሀፍረት መግለጽ ብትፈራም እንደተስማማች በመረዳቱ ወደ ጋብቻ ቅድመ ሁኔታው ማለፋቸውን ይገልጻል።

ከዚያም ወደ ጥሎሽና ኒካህ ተኪዷል።

ኒካህ ከታሰረ በኃላ ከለሊቱ 10 ሰዓት ገደማ ስልክ ተደወለልኝ የሚለው ወንድሟ " ሪባቴ ታማለች ና " ተብሎ ተነገረኝ ሲል ሁኔታውን አስታውሷል።

ወደ ቤታቸው ሲሄድ ግን ቤቱ በፖሊስ ተከቦ ነበር።

ሌላኛው የሟች ወንድም በርገና  " አባቴ ኒካህ እሰር ብሎ ከወከለኝ ቀን ጀምሮ ያለው ነገር ብቻ ነው ማውቀው ከዚያም ወንድሜን ወከልኩት ኒካሀው ታሰረ አለኝ ከዛ ለሊት 10 ሰዓት ስልክ ተደወለልኝ ቦታው ስንደርስ ቤቱ በፖሊስ ተከቧል " ሲል ገልጿል።

" በጭራሽ ያልገመትነው ነገር ሆኖ አገኘን " የሚለው የሟች ወንድም " ፖሊሶች እኛ ወደ አስክሬኑ እንዳንጠጋ አድርገው አስክሬኑን ወደ ሆስፒታል ወስደው እሱን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስዱት " በማለት አስረድቷል።

" ለሟች እህታችን ተገቢው ፍትህ ተሰጥቶን ተጠርጣሪው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኝ እንፈልጋለን " ብሏል።

የሃላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ በበኩሉ ድርጊቱ ከተፈጸመበት ሰዓት አንስቶ ተጠርጣሪውን በህግ ጥላ ስር አውሎ 5 አባላት ያለው መርማሪ ቡድን በማዋቀር ምርመራ እያካሄደ መሆኑን አመልክቷል።

የተፈጸመው ወንጀል " ጭካኔ የተሞላበት አረመኔያዊ ወንጀል ነው " ሲል ገልጿል።

ፖሊስ የተጠርጣሪውን የእምነት ክህደት ቃል እንደተቀበለና በአጭር ጊዜ ውስጥ ምርመራው አልቆ  ውሳኔ እንዲያገኝ እንደሚሰራ አመልክቷታ።

የሃላባ ህዝብ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል እና መረጃ በመስጠት ላደረገው ርብርብ ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሀሩን ሚዲያ ነው። #HarunMedia

@tikvahethiopia