TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ? ዛሬ መቐለ ሁለት ስብሰባ ሲካሄድ ውሏል። አንዱ የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚገኙበት 14ኛ የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ሲሆን ሌላኛው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ጉባኤውም የተቃወሙ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በርካታ የክልል፣ የዞን እና ወረዳ አመራሮች የተገኙበት…
#Update

በህወሓት ምትክል ሊቀመንበር እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራው የዛሬው የመቐለው ስብሰባ ቁጥራቸው አንድ ሺህ መሆኑ የህወሓት አባላትና አመራሮች ተገኝተው እንደነበር ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት የአንድ ቀን ስብሰባቸውን ከምሽቱ 2:30 አጠናቀዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ካወጡዋቸው ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አራቱ ነጥቦች የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የፈጠረው አንፃራዊ ምቹ ሁኔታ እንዲቀጥል የሚያስታውስ ነው።

" ሰላም አማራጭ የሌለው አማራጭ መሆኑ በመቀበልና በመረዳት ማንኛውም ወደ ግጭትና ጦርነት የሚመራ የውስጥና የውጭ ተንኮል በፅኑ እንቃወማለን " ይላል።

በአቋም መግለጫው ከተገለፁ አራት ነጥቦች  በህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የ14ኛው ጉባኤ ኢ-ህጋዊነት የሚያትት ሆኖ " ተደናግረው በጉባኤው በመሳተፍ ላይ የሚገኙት የህወሓት አባላት ወደ ቀልባቸው በመመለስ ከህዝባቸው ጎን እንዲሰለፉ " ሲል ያሳስባል።

ዘጠነኛው ነጥብ ደግሞ በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኘው የክልሉ ተወላጅ ፣ የድርጅቱ አባልና ደጋፊ ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ፣ ማህበራት ፣ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ምርጫ ተካሂዶ መንግስት እስኪቋቋም ድረስ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ደግፈው እንዲቆሙ ጥሪ ያቀርባል።

" የተከበራችሁ የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች በድርጅታችን ውስጥ የተፈጠረው የሃሳብ ልዩነት እንደ ሁሉ ጊዜ በጥሞና በማየት በማያዳላ መንገድ የህዝቡ ፀጥታና ሰላም ማስከበር ይገባል " ያለው የውይይቱ ተሳታፊዎች አስረኛ ነጥብ የአቋም መግለጫ የፀጥታ ሃይሎች አሁን የያዙት የማያዳላ አቋም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቀርበዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

Via @tikvahethiopiatigrigna

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF በሊቀመንበሩ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የተመራው የህወሓት ጉባኤ አቶ ጌታቸው ረዳን ከምክትል ሊቀመንበርነት አነሳ። ዶ/ር ደብረጽዮን በድጋሚ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ተነግሯል። በአቶ ጌታቸው ረዳ ምትክ አቶ አማኑኤል አሰፋ ምክትል ሊመንበር ሆነው ተመርጠዋል። ሌሎች የስራ አስፈጻሚና የማእከላይ ኮሚቴ ሆነው የተመረጡ የድርጅቱ አባላት ከላይ ስማቸው ተያይዟል። ምርጫ ቦርድ ከጉባኤው ቀደም…
#TPLF

በሊቀ-መንበር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በተመራውና ለ7 ቀናት በቆየው የህወሓት 14ኛው ጉባኤ አዳዲስ የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት ተመርጠዋል።

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር እና ጉባኤውን ሲቃወሙ የቆዩትን አቶ ተኽለብርሃን ኣርኣያ ተነስተው አቶ ገብረ ካሕሳይ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

አሁን ከሊቀመንበር ቦታቸው ተነስተው በአቶ ገብረ የተተኩት አቶ ተኽለብርሃን ይመሩት የነበረው የቁጥጥር ኮሚሽን ፤ የቁጥጥር ኮሚሽን ፥ " ጤናማ ያልሆነ ሂደት ውጤታማና መልካም ጉባኤ መፍጠር ስለማይችል የሚያስከትለው አደጋ የከፋ ነው " በማለት ከጉባኤው ራሱን ማግለሉን ይታወሳል።

በሌላ በኩል ፥ በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የተመራው የህወሓት ጉባኤ ፤ በጉባኤው ላይ ያልተሳተፉ አባላትን አግዷል።

" ጉባኤው እንዳይካሄድ እንቅፋት ፈጥሯል " ያለውን ቡድን ነው ያገደው።

ያታገዱት አባላት ጥያቄቸውን በጹሁፍ የሚያቀርቡ ከሆነ ወደ አባልነታቸው ሊመለሱ ይችላሉ ብሏል።

ቀደም ብሎ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ያሉበት 14 የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ጉባኤውን እንደማይሳተፉ ማሳወቃቸው ፤ የቁጥጥር ኮሚሽን አባላትም ራሳቸውን ማግለላቸው ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
" ከተያዘው እቅድ ውጭ እኛ የማናቀውን ስብሰባ ማካሄድ አይቻልም " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር

በትግራይ ክልል ፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ጊዚያዊ አስተዳደሩ የማያውቀው ማንኛውም ሰብሰባ ማካሄድ የሚከልክል የስራ መመሪያ ይፋ ተደረገ።

ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅህፈት ቤት በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ፊርማ ለሁሉም
-  የዞን አስተዳደሮች
- ለወረዳ አስተዳደሮች
- የክፍለ ከተማ አስተዳደሮችና
- የወረዳ ምክር ቤቶች 
የተላከው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፈቀደው ውጪ ሌላ ስብሰባ ማካሄድ አይቻልም ይላል።

➡️ የኮሌራ በሽታ መከላከል
➡️ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስና የክልሉን ግዛታዊ አንድነት ማስከበር
➡️ የ2016 ዓ.ም በጀት መዝጋትና የ2017 ዓ.ም በጀት ማዘጋጀት ... ሌሎች ህዝባዊና መንግስታዊ እቅዶች የጊዚያዊ አስተዳደሩ መሆናቸው የጠቀሰው የስራ መመሪያው ፤ " ከዚህ ውጪ የሚደረጉ ሰብሰባዎች የተያዘው እቅድ ስለሚጎዱ አይፈቀዱም " ብሏል።

ከላይ ከተጠቀሱት እቅዶች ውጪ ማሰተናገድ የጊዚያዊ አስተዳደሩን ስራ በማደናቀፍ #ተጠያቂነት_የሚያስከተል መሆኑን  በመግለጽ አስጠንቅቋል።

የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትም ይህኑን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥብቅ መመሪያ ሰጥቷል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF #Tigray የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለመምራት ህወሓት " የራሱን ሰዎች መመደብ ይችላል " ሲሉ የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ። አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ቡድን " አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም ” ብለዋል። ሊቀመንበሩ ፤ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት ትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር " ህወሓትን ወክሎ ነው የገባው። አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም…
#Tigray

የትግራይ ጊዜያዊ አስተደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የስልጣን ሽምሹር አደረጉ።

ፕሬዜዳንቱ በህወሓት የፓሊት ቢሮ አባልዋ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ምትክ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ክርስቶስ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ በማድረግ ሾመዋል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ ተፈርሞ ነሃሴ 14/2016 ዓ.ም የወጣው ደብዳቤ ፤ ፀጋይ ገብረተኽለ የዞኑ አስተዳዳሪ በመሆን የሚገባቸው ጥቅም ተጠብቆላቸው ሃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጡ አደራ በማለት ያሳስባል።

አዲሱ ተሿሚ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ኽርስቶስ ቀደም ሲል በዞኑ የእንደርታ ወረዳ አስተዳዳሪ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል። 

ወ/ሮ ሊያ ከቀናት በፊት የህወሓት ስራ አስፈጻሚ በመሆን መመረጣቸው ይታወሳል።

ህወሓት ባካሄደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ያልሰጠው ፤ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር የሚገኙባቸው 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን " ህጋዊ አይደለም " ያሉት ጉባኤ ካልተሳተፉት መካከል  ፦
- የምዕራባዊ
- የማእከላዊ
- የምስራቃዊ
- የደቡበዊ ዞኖች አስተዳዳሪዎች ይገኙበታል። 

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው የስልጣን ሹምሽር ያደረጉበት የደቡባዊ ምስራቅ ዞን ኣስተዳዳሪ ፀጋይ ገ/ተኽለ ህወሓት ባካሄደው ጉባኤ የፓሊት ቢሮ አባል ሆነው የተሸሙት ወ/ሮ ሊያ ካሳ የተኩት አምስተኛ የእነ ዶ/ር ደብረፂዮን አካሄድ የሚቃወሙ የዞን አስተዳዳሪ ናቸው።

በትግራይ ካሉ 7 የዞን አስተዳደሮች አምስቱ የእነ ዶ/ር ደብረፂዮን አካሄድ በሚቃወሙ የሚመሩ ሲሆኑ ሁለት ዞኖች ማለትም የሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በተካሄደው ጉባኤ የፓሊት ቢሮ አባል ሆነው በተመረጡት  ተኽላይ ገ/መድህን የመቐለ ከተማ ደግሞ በተካሄደው ጉባኤ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ሆኖው በተመረጡት ይትባረክ ኣማሃና ኤልያስ ካሕሳይ ዋናና ምክትል በመሆን በመመራት ላይ ይገኛሉ።

ቀሪዎቹ የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን አካሄድ የሚደግፉ የሁለት ዞን አስተዳዳሪዎች በያዙት ሃላፊነት የቆዩ ይሆን ? የብዙዎች ጥያቄ ነው። 

የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከቀናት በፊት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን ለመምራት ህወሓት " የራሱን ሰዎች መመደብ ይችላል " ሲሉ ተናግረው ነበር።

ሊቀመንበሩ ፤ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር " ህወሓትን ወክሎ ነው የገባው። አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም " ነበር ያሉት።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ጊዜያዊ አስተደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የስልጣን ሽምሹር አደረጉ። ፕሬዜዳንቱ በህወሓት የፓሊት ቢሮ አባልዋ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ምትክ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ክርስቶስ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ በማድረግ ሾመዋል። በአቶ ጌታቸው ረዳ ተፈርሞ ነሃሴ 14/2016 ዓ.ም የወጣው ደብዳቤ ፤ ፀጋይ ገብረተኽለ የዞኑ አስተዳዳሪ በመሆን የሚገባቸው ጥቅም ተጠብቆላቸው ሃላፊነቱን በአግባቡ…
#TPLF #Tigray

በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ማንኛውም አይነት የስልጣን ሹምሽር አልቀበልም አለ።

በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " በማንኛው የሃላፊነት እርከን በራስ ፍላጎት የሚደረግ የስራ ምደባና ሹምሽር ተቀባይነት የለውም " ብሏል።

የእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ለሁሉም የዞንና የወረዳ የድርጅቱ ፅህፈት ጠቅሶ ባሰራጨው ደብዳቤ ፥ " ከሰርዓታዊና ተቋማዊ አሰራር ውጪ የሚካሄዱ የስራ ምደባዎች ኢህጋዊ ብቻ ሳይሆኑ ተጠያቂነትን ያስከትላሉ " ሲል አስጠንቅቋል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ነሃሴ 17/2016 ዓ.ም በህወሓት የፓሊት ቢሮ አባልዋ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ምትክ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ክርስቶስ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ በማድረግ መሾማቸው ዘግበናል።

ነሃሴ 18/2016 ዓ.ም የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ደግሞ በሰሜናዊ ምዕራብ ዋና አስተዳዳሪና በቅርቡ ህወሓት ባካሄደው ጉባኤ የፓሊት ቢሮ አባል ሆነው በተመረጡት ተክላይ ገ/መድህን ምትክ የክልሉ የስፓርት ኮሚሽን ኮምሽነር የነበሩት ተኽላይ ፍቓዱ ተሹመዋል።

ትግራይ ካሉዋት ሰባት የዞን አስተዳደሮች በአሁኑ ጊዜ ስድስቱ የእነ ዶ/ር ደብረፂዮን አካሄድ በሚቃወሙ የሚመሩ ሲሆኑ የመቐለ ከተማ ብቻ በቅርቡ  በተካሄደ ጉባኤ  የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ሆኖው በተመረጡት ይመራል። 

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF #Tigray በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ማንኛውም አይነት የስልጣን ሹምሽር አልቀበልም አለ። በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " በማንኛው የሃላፊነት እርከን በራስ ፍላጎት የሚደረግ የስራ ምደባና ሹምሽር ተቀባይነት የለውም " ብሏል። የእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ለሁሉም የዞንና የወረዳ የድርጅቱ ፅህፈት ጠቅሶ ባሰራጨው ደብዳቤ…
#Tigray

" በቅርቡ ሁሉም ተቀባይነት ያላቸው ህጎችና አሰራሮች በመጣስ ጉባኤ አድርጊያሎህ የሚለው ህገ-ወጥ ቡድን በትግራይ ስርአት አልበኝነት እንዲስፋፋ እየሰራ ነው " ሲል የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሷል።

አስተዳደሩ ፥ ህዝብ ለማገልገል የሚያካሂዳቸው የመዋቅራዊ አደረጃጀት ማስተካከያዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

የመንግስት ውሳኔና ተግባር የሚያደናቅፍ ማንኛውም አካል ሆነ ሃይል አልታገስም ብሏል።

" ህግና ስርዓት የሚጥስ አካል ሆነ ሃይል ህጋዊ አሰራር የተከተለ ተጠያቂነትና እርምጃ እንደሚወሰድበት ሊታወቅ ይገባል " ሲል አስጠንቅቋል።

በአሁኑ ወቅት ማንኛውም የስልጣን ጥያቄ አለኝ የሚል ቡድን በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ጠያቄውን ለሚመለከተው አደራዳሪ አካል   በሰላማዊ አግባብ የማቅረብ መብቱ ዝግ እንዳልሆነ ጠቁሟል።

" ጊዚያዊ አስተዳደሩ እንዲዳከም ሳያለሰልስ የሰራ ቡድን አሁን የሚደረጉት የስራ ምደባዎች ' ህጋዊ አይደሉም ' ብሎ በመቃወም ለዓመታት እስከ ታች በሰፋው ኔትወርክ እንቅፋት እየፈጠረ ይገኛል " ብሏል።

" ቡድኑ በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተመደቡ አመራሮች ህጋዊ አይደሉም ተቀባይነት የላቸውም ' ከማለት አልፎ ባደራጀው ኔትወርክ እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ በመውረድ ' እንዳትቀበሉዋቸው ' በማለት ህግ አልበኝነት እንዲነግስ በመንቀሳቀስ ላይ ነው " ሲል ከሷል።

" ህዝቡ ህገ-ወጥቶች ሃይ ሊላቸው ሊያስታግሳቸው ይገባል " ሲል አስገንዝቧክ።  

" ህዝቡ ተገቢውን  መንግስታዊ አገልግሎት እንዲያገኝ አልሞ የሚከናወነው የመዋቅር ማስተካከያ እርምጃ ተጠናክረው ይቀጥላሉ ፤ መንግስታዊ የመዋቅር ማስተካከያ እርምጃ በሚቃደናቅፍ አካል ሆነ ሃይል እርምጃ እንደሚወሰድ ህዝባችን ሊያውቀው ይገባል "  ሲል በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚመራስ ጊዜዊ አስተዳደር አሳውቋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia 
#Tigray

ዛሬ በአክሱም ከተማ የብዙዎች መነጋገሪየ የሆነ ፓለቲካዊ ክስተት ተከስቷል።

በመካከላቸው በተፈጠረው ፓለቲካዊ ልዩነት በርቀት በመግለጫዎች ሲጎነታተሉ የከረሙት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እና የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በዓመታዊው አክሱም ከተማ የዓይኒ ዋሪ በዓል አከባበር ላይ ተገናኝተዋል።

በመድረኩ በቅደም ተከተል ንግግር ያደረጉት ሁለቱ መሪዎች ከምር ይሁን ከአንገት በላይ በማይታወቅ የእጅ ሰላምታ ተጨባብጠዋል።

ከአክሱም ከተማ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከንግግራቸው በላይ አነጋገሪ የሆነው " በዓሉ ላይ እኔ ነኝ መገኘትና መሳተፍ ያለብኝ " የሚል ክርክርና ሰጣ ገባ መነሳቱ ነው።

ክርክርና ሰጣ ገባቸው የሃይማኖት አባቶች መሃል ገብተው አስማምተው ሁለቱም በመድረኩ እንዲገኙና ንግግር እንዲያደርጉ ለማሳመን የወሰደው ጊዜ ፕሮግራሙ ሳይጀመር ለሰዓታት እንዲራዘም ሆኗል።

ሁለቱ መሪዎች ያደረጉት ሰጣ ገባ ደጋፊዎቻቸው ደረስ ዘልቆ እስከ አሁን ድረስ በማህበራዊ የትስስር ገፆ እያከራከረ ይገኛል።

ቀድመው ንግግር ያደረጉት ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ድርጅታቸው በቅርቡ ባካሄደው 14ኛው ጉባኤ ያሳለፋቸው ውሳኔዎችና አተገባበራቸው ያተኮረ ሲሆን ቀጥለው የተናገሩት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በንግግራቸው የጊዚያዊ  አስተዳደሩ የስራ አቅዶችና አንድነትን የሚመለከት ነበር። 

ፕሬዜዳንት ጌታቸው በስም ያልገለፁዋቸው " የውጭ  ጠላቶች " የሚያደርጉት ሙከራ ከትግራይ አቅም በላይ አይደለም ፤ ስለሆነም ከጨለማ ለመውጣት በአንድነት መጓዝ አለብን ብለዋል።

ለሦስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ትግራይ የነበሩት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በህወሓትና በጊዚያዊ አስተዳደሩ መካከል የተፈጠረው ውጥረት መርገብ እንዳለበት ማሳሰባቸው መዘገባችን ይታወሳል። 

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

" በችግር ላይ ሌላ ችግር  በህዝቡ ላይ የመጫን ፍላጎት የለንም ፤ አሁን የገጠመን ፈተና እናልፈዋለን። አባቶች በፀሎትና ምክር አግዙን !! " - ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)

የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) ነሃሴ 24 ቀን 2016 ዓ/ም ከአበው ጳጳሳት እና የአገር ሽማግሌዎች ጋር በኣክሱም ከተማ መወያየታቸውን የሚገልጽና አንድ ንግግር ሲያደርጉ የሚታይበት ቪድዮ ተሰራጭቷል።

ቪድዮው በትግራይ ፐብሊክ ሚዲያ (TPM) የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ነው የተሰራጨው።

ሊቀመንበሩ የ5 ደቂቃ ርዝማኔ ባለው ንግግራቸው  ፥ " እኔ ለድርጅትና ለህዝብ ደህንነት ስል ብዙ ታግሻለሁ ፤ ትዕግስትና ዝምታዬ ግን መልካም ነገር ሳይሆን አደጋ ነው ያስከተለው ፤ ስለሆነም ከአሁን በኋላ መታገስ ሳይሆን ተመጣጣኝ ሰላማዊ ትግል ነው የሚያዋጣው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" እኛ የውጭ ጠላት አለብን የውስጥ ጉዳይ አናቆየው በማለታችን በውስጣችን ብዙ ችግሮች እንዲፈጠሩ ሆኗል " ያሉት ደብረፅዮን (ዶ/ር) ፥ " ከአሁን በኋላ የጎራ መደበላለቅ አይኖርም አቋማችን በግልፅ በማንፀባረቅ ሰላማዊ ትግል ማካሄዳችን እንቀጥላለን " ብለዋል።

" በሃይል ፍላጎቴን አሳካለሁ የሚል አካል ሃይ ሊባል ይገባዋል ፥ በትግራይ በጉልበት እሰራለሁ ማለት አያዋጣም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከአሁን በኋላ ከህዝብ የሚደበቅ ሚስጥር አይኖርም " በማለትም ተናግረዋል።

ሊቀመንበሩ ፤ " የተፈጠረውን ልዩነት በሰላም እንጨርሰው ፤ የማይሳካ ከሆነ ግን ሉአላዊነታችንን አሳልፈን አንሰጥም ፤ አቋማችን ግልፅ በማድረግ እንታገላለን " ብለዋል።

" አንድ በማያደርገን አንድ ሁኑ አትበሉን  በፓለቲካ አንድ በማያደርግህ አቋም አንድ መሆን አይቻልም ፤ ተከባብሮ በሰላም መስራት ግን ይቻላል ፤ ትግራይ ለሁሉም በቂ ናት " ሲሉም ደብረጽዮን (ዶ/ር) አክለዋል።

ህዝቡ ላይ በችግር ላይ ሌላ ችግር መጫን  እንደማይፈልጉ የተናገሩት ሊቀመንበሩ ፥ የተፈጠረው ሁኔታ ተስፋ የሚያስቆርጥ እንዳልሆነና በሰላማዊ አግባብ እንደሚፈታ በማመላከት የሃይማኖት አባቶች በፀሎትና በምክር እንዲረዱዋቸው ጠይቀዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያመቐለ #TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TIGRAY

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በዓዲግራት ምን አሉ ?

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዋና ከተማ ዓዲግራት ህዝባዊ ውይይት አካሂደዋል።

" ህዝቡ ስጋት ላይ የሚጥል ሁኔታ ለመቅረፍ ከናንተ መሃል ተገናኝተናል " ብለዋል።

" የትግራይ መልሶ ግንባታ ጋሃድ እንዲሆን በመደጋገፍ መስራት ይገባናል " ሲሉ አስገንዝበዋል።

" በውስጣች በተፈጠረው መፎካከር መስራት የሚገቡን አልሰራንም " ያሉት አቶ ጌታቸው " አብዛኛው ጊዚያችን በጭቅጭቅና በጎሪጥ በመተያየት ነው ያሳለፍነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ በማህበራዊ አገልግሎት መልሶ ግንባታ ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገናል ፤ ጅምሮቻችን ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በውስጣችን የታዩ ድክመቶችን ማረምና የጋራ መፍትሄ ለመሻት መስራት ይጠበቅብናል " ብለዋል።

" በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ሁሉም በጠላት ስር የሚገኙ አከባቢዎች  ወደ ነባር አስተዳደራቸው መመለስ አለባቸው ብለን እየሰራን ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው " የሰላም ስምምነቱ በተሟላ መልኩ እንዲተገበር እንደ መንግስት ጠንክረን እንሰራለን " ሲሉ ተናግረዋል።

" የህዝባችን ሰላም በማረጋገጥ በኩል ዓለም ከኛ ጋር ናት ይህንን እንዲቀጥል ግን ውስጣዊ አንድነታችን እንዳይላላ ያለማቋረጥ መስራት አለብንም " ብለዋል።

በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ዓዲግራት ሲደርሱ በልዩ አጀብ በፈረሰኞች የተደገፈ አቀባበል ነበር የተደረገላቸው።

በአቀባበሉ የተገኙ የዓዲግራት ከተማ ወጣቶች ፦
👉 የጥይት ድምፅ እንጠየፍ !! 
👉 መሰረታዊ ለውጥ እንፈልጋለን !!" 
👉 ተፈናቃዮች ይመለሱ ግዛታዊ አንድነት ይከበር !!
👉 ትግራይ በሳይንስና ጥበብ እንጂ በጥይት አፈሙዝ አትመራም !!
👉 ጊዚያዊ አስተዳደሩ እንደግፋለን !!
የሚሉና ልሎች መፈክሮች በመያዝ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በተመራ የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች ቡድን ምክትል ፕሬዜዳንት ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ ነበሩበት።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ምን አሉ ?

የትግራይ ጊዜዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩትና ም/ፕሬዜዳንት ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ የሚገኙበት የአመራሮች ቡድን ከሰሞኑን ህዝባዊ ውይይቶችን እያደረገ ነው።

ትላንት ማይጨው ላይ በነበረ ውይይት ጀነራል ፃድቃን ስለ ፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ዙሪያ ሃሳቦች ሰጥተዋል።

" የሚታየውን ዋናው የልዩነት ነጥብ በፕሪቶሪያ ውል ላይ ያለ የአመለካለት ልዩነት ነው " ብለዋል።

" ስምምነቱ ዓለም አቀፍ ውል ነው መከበር አለበት " ሲሉም በቅርቡ እኔ ነኝ ህጋዊ ህወሓት የሚለው የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ሃይል ሲሸነቆጥ አድርገዋል።

ፕሬዜዳንቱ ጌታቸው ረዳ ደግሞ ሃሳቡ አጠናክረዋል።

"  የፕሪቶሪያ ውል ለማፍረስ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ጦርነትን መጥራት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል " በማለት አስጠንቅቀዋል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንትና ምክትላቸው በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትና አመለካከትና አተገባበር  ዙሪያ የሰነዙሩዋቸው ጥንካራ ትችቶች ተከተሎ የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ሃይል መልስ ሰጥቷል።

የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ሃይል በመወከል መልስ የሰጡት የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድና በህወሓት ምክትል ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚመሩ በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት " ህጋዊ ጉባኤ አይደለም " ባሉት 14ኛው ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ አባል ሆነው የተመረጡና በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ህወሓት ወክለው ከተደራደሩትና ውሉ ከፈረሙት አንዱ ፍስሃ ሃፍተፅዮን (ዶ/ር) ናቸው ። 

ፍስሃ (ዶ/ር) " ህወሓት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት እንደማይደግፍ ተደርጎ እየቀረበ ያለው ሃሳብ ስም ማጥፋት ነው " ሲሉ ኮንነዋብ።

" ህወሓት በፕሪቶሪያ ስምምነትና አተገባበር የፀና አቋም አለው " ሲሉ ተናግዋል።

የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በደቡብ አፍሪካ በሚፈፀምበት ወቅት ትግራይን ወክለው በተሳተፉ ተደራዳሪዎች መካከል ልዩነት ተፈጥሮ እንደነበረ አስታውሰዋል።

ጊዚያዊ መንግስት ማቋቋም አለመቋቋም በተደራዳሪዎች መካከል ከነበሩት የሃሳብ ልዩነት እንድ አንድ ነጥብ ጠቅሰውታል።   

" በፕሪቶሪያ ተስማምተን መፈረማችን አንድ ፀጋ ሆኖ የቀሩት ጉድለቶች በሂደት እንፈታቸዋለን ብለን አምነን ነው የተመለስነው " ሲሉ ፍስሃ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ሌላው " ህወሓት ከሻዕብያ ጋር ግንኙነት አለው የሚለው ወሬ ነጭ ውሸት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

የፕሪቶሪያ ስምምነት ተደራዳሪና ፈራሚ ቡድን አባል የሆኑት ፍስሃ (ዶ/ር) " በውስጣችን ያሉ ግን መሬታችን ወረው ለያዙ ያግዛሉ " በማለት በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ጊዚያዊ አስተዳደር ወቅሰዋል። 

" ወደ ጦርነት የሚያስገባ አንድም ምክንያት የለም " ያሉ ሲሆን በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አፈፃፀምና አተገባበር እሳቸውን ያቀፈው የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ሃይል ትክክለኛ እንደሆነ ሞግተዋል።

የአሜሪካው የፕሪቶሪያ የሰላም አደራዳሪ ማይክ ሃመር ውሉና አተገባበሩ የሚመለከት ጉብኝት ለማድረግ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ፓለቲካዊ ልዩነት ግን አሁንም አልበረደም።

የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ሃይል " ህጋዊ  አይደለም " የተባለ 14ኛ ጉባኤ ካካሄደ በኋላ የእነ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ሃይል ፥
- ደርጅታዊ ስብሰባዎች በመንግስት የስራ ሰአት እንዳይካሄዱ የሚከለክል የስራ መመሪያ ፣
- ላልተወሰነ ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ የሚከለክል ማስጠንቀቅያ ፣
- የዞን አስተዳደሪዎች ሹምሹር ያካሄደ ሲሆን በክልሉ የዞኑ ትልልቅ ከተሞች በመዘዋወርም ህዝባዊ ውይይቶች በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ባለፈው ሳምንት በተምቤን ፣ በዓዲግራትና በማይጨው ህዝባዊ ውይይቶች አካሂዷል።

በቀጣይ የጳጉሜን ቀናትም ኣክሱምና እንዳስላሰ ሽረ እንደሚያቀና እየተነገረ ነው።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ምን አሉ ? የትግራይ ጊዜዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩትና ም/ፕሬዜዳንት ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ የሚገኙበት የአመራሮች ቡድን ከሰሞኑን ህዝባዊ ውይይቶችን እያደረገ ነው። ትላንት ማይጨው ላይ በነበረ ውይይት ጀነራል ፃድቃን ስለ ፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ዙሪያ ሃሳቦች ሰጥተዋል። " የሚታየውን ዋናው የልዩነት ነጥብ በፕሪቶሪያ ውል ላይ ያለ የአመለካለት…
#Tigray

አቶ ጌታቸው ረዳ የጤና አክል ገጥሟቸዋል።

ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ዛሬ ጳጉሜን 2/2016 ዓ.ም የወጣ መግለጫ እንዳመለከተው ፥ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ዛሬ በአክሱም ሊካሄድ የታቀደው ህዝባዊ ውይይት ተሰርዟል።

ፅ/ቤቱ ፕሬዜዳንቱ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ከአክሱም ከተማና አከባቢዋ ነዋሪዎች ጋር ሊካሄድ እቅድ የተያዘለት ህዝባዊ ውይይት ሳይካሄድ በመቅረቱ ይቅርታ ጠይቋል።

ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ያጋጠማቸው የጤና እክል ቀላል ይሁን ከባድ በመግለጫው የተጠቀሰ የለም ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

ከሰሞኑን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ምክትላቸው ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ያሉበት የአመራሮች ቡድን በየከተማው ህዝባዊ ምክክር እያደረገ እንደነበር ይታወቃል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray አቶ ጌታቸው ረዳ የጤና አክል ገጥሟቸዋል። ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ዛሬ ጳጉሜን 2/2016 ዓ.ም የወጣ መግለጫ እንዳመለከተው ፥ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ዛሬ በአክሱም ሊካሄድ የታቀደው ህዝባዊ ውይይት ተሰርዟል። ፅ/ቤቱ ፕሬዜዳንቱ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ከአክሱም ከተማና አከባቢዋ ነዋሪዎች ጋር ሊካሄድ እቅድ የተያዘለት…
#UPDATE

" የጤናዬ ሁኔታ ብዙ የሚያሳስብ አይደለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ 

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ጳጉሜን 2/2016 ዓ.ም በ X ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሑፍ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት በማስቀደም " የጤንነት ሁኔታየና ድህንነቴ ያሳሰባችሁና ያስጨነቃችሁ ሁላችሁም ደህና ነኝ " ብለዋል። 

" ተደጋጋሚ ረጅም መንገድ በመኪና መጓዝና ደካም ተደራርቦ የፈጠረው ጊዚያዊ ችግር እንጂ በሚያሳስብ ሁኔታ እንዳልሆንኩ በፈጣሪና በፅዮን ማርያም ስም እገልፅላችኃለሁ " ሲሉ ፅፈዋል።   

ቀጣይ ህዝባዊ መድረኮች ከተወሰኑ ቀናት በኋላ እንደሚቀጥሉ የገለፁት አቶ ጌታቸው " በመድረኩ ለመሳተፍ አክሱም ድረስ ለተንገላቱ ተሳታፊዎች ደግሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ " በማለት አክለዋል።   

ዛሬ ጳጉሜን 2/2016 ዓ.ም ከጊዚያዊ  አስተዳደሩ የፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት የወጣ መግለጫ ፕሬዜዳንቱ የጤና እከለ እንደገጠማቸው በመግለፅ በአክሱም ከተማ ሊካሄድ እቅድ የተያዘለት ህዝባዊ ውይይት ለሌላ ጊዜ መተላለፉና ይቅርታ መጠየቁን መዘገባችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia            
#TPLF #እንዳስላሰሽረ

በሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ተከለከለ።

ህወሓት ሰላማዊ ስልፍ ለማካሄድ ከጳጉሜን 3 - 5 ባሉት ቀናት የጠየቀ ሲሆን ሰልፉ የሚካሄድበት ቦታ ደግሞ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ ሽረ ከተማ ነው።

የህወሓት ፅህፈት ቤት እንዳስላሰ ሽረ ቅርንጫፍ ነሃሴ 29/2016 ዓ.ም በፃፈው የሰላማዊ ሰልፍ የፍቃድ ደብዳቤ በክልሉ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ በሰላማዊ መንገድ ድምፁ ለማሰማት መፈለጉ ያትታል።

ቅርንጫፍ ፅህፈቱ ፍቃድ በጠየቀበት ሰላማዊ ሰልፍ ፦

"
- ከባቢያዊ መለያየትና አገር የሚበትኑ ተግባራት ይቁሙ !
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ !!
- የፀለምቲና ራያ ተመላሽ ተፈናቃዮች ድህንነታቸው ይጠበቅ !
- የህዝበኝነት ፓለቲካ በትግራይ እንቃወማለን !
- የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ይተግበር !
- ጊዚያዊ አስተዳደር የተቋቋመለት ዓላማ ይተግብር !
- ህወሓትን ለማፍረስ የሚደረግ እንቅስቃሴ ይቁም !
- ህወሓት ሰላምን ይደግፋል !
- ጦርነት የሚናፍቅ የህወሓት መሪ የለም ! "

የሚሉና ሌሎች መፈክሮች እንደሚያሰማ በፍቃድ መጠየቂያ ደብዳቤው ላይ ገልጿል።

ቅርንጫፍ ፅህፈቱ ለጠየቀው ' ሰላማዊ ሰልፍ ' የማካሄድ ጥያቄ መልስ የሰጠው የእንዳስላሰ ሽረ ከተማ አስተዳደር በወቅቱ ባለው የፓለቲካ ትኩሳት እና የአዲስ ዓመት መለወጫ በመሆኑ ምክንያት የፀጥታ ሃይሉ የተደራረቡ ስራዎች ስላሉበት ሰላማዊ ስልፉ እንዳልተፈቀደ አሳውቋል።

በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ልኡክ በተምቤን ዓብዩ ዓዲ ዓዲግራትን ማይጨው ካካሄዳቸው ህዝባዊ ውይይቶች በመቀጠል በአክሱምና በእንዳስላሰ ሽረ ከተማዎች ለማካሄድ አቅዶ የነበረ ቢሆንም አቶ ጌታቸው ባጋጣመቸው የጤና እክል ምክንያቱ ውይይቱ ለሌላ ጊዜ መዛወሩን የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል መዘገቡ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
#ትንሳኤ70እንደርታ

" የመቐለ ከተማ አስተዳደር የፈቀድልን ህዝባዊ ስብሰባ ተከለከልን " ሲል ትንሳኤ 70 እንደርታ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታውን አሰማ።

የፓርቲው ሊቀመንበር ከበደ አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በሰጡት ቃል ፥ _ እሁድ ጳጉሜን 3/2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ አስተዳደር ግቢ በሚገኘው አግኣዚ የስብሰባ አዳራሽ ህዝባዊ ስብሰባ ለማካሄድ ተፈቕዶልን አባልና ደጋፊዎቻችን ጠርተን ስናበቃ አዳራሽ እንዳንገባ በታጣቂዎች ተከልክለናል " ብለዋል።

" በህጋዊ መንገድ የተፈቀደ ህዝባዊ ውይይት መከልከልና ታዳሚዎች ማንገላታት ኢ-ዴሞክራሲያዊ ነው " ያሉት የፓርቲው ሊቀመንበር በተግባሩ ማዘናቸው በመግለፅ ከሚመለከተው አካል ግልፅ ማብራርያ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ተናግረዋል።

" የመቐለ ከተማ ፀጥታ ፅ/ቤት በፃፈልን ደብዳቤ መሰረት ስብሰባውን የፀጥታ ጥበቃ ለማድረግ ፓሊስ መድቦ በቦታው የተገኙ ሲሆን ማንነታቸውና ተጠሪነታቸው የማይታወቁ ሌሎች ሃይሎች ተሳብሳቢው ወደ ግቢ እንዳናሰግባ የአዳራሹ ሰራተኞች ሳይቀር እንዳይገቡ በር ላይ ለነበሩ የጥበቃ ሰራተኞች ትእዛዝ በመሰጠቱ ምክንያት ስብሰባው ሳይደረግ ቀርተዋል " ሲሉ አስረድተዋል።

" እንደምክንያት ያቀረቡትም የከንቲባ ፅ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ለጋስ ማርያም ' እኔ ካልደወልኩኝ እንዳይገቡ ብለዋል ' የሚል ሲሆን ግለሰብዋ በደብዳቤ የፈቀዱትን ስብሰባ በዚህ መንገድ የከለከሉበት ምክንያት ለመጠየቅ ስልካቸው ላይ በተደጋጋሚ ብንደውልም ስላካቸውን በመዝጋታቸው ምክንያት ልናገኛቸው አልቻልንም " በማለት ገልጸዋል።

የመቐለ ከተማ ፀጥታ ዘርፍና ፓሊስ መንግስታዊ ሃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት መሞከሩን አመልክተው " ምስጋና ይገባዋል " ብለዋል።

የመቐለ ከተማ አስተዳደርና ፓሊስ እስከ አሁን ሰዓት ስለ ክልከላው የሰጠው ይፋዊ ማብራርያም ሆነ መግለጫ የለም። 

ትንሳኤ 70 እንደርታ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ከአንድ ዓመት በፊት ሰላማዊ ፓለቲካዊ ትግል ለማካሄድ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና አግኝቶ መመስረቱ ይታወቃል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
#Tigray

ባጋጠመ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ከ10 በላይ ተሳፋሪዎች ህይወታቸው ተቀጠፈ።

የትራፊክ አደጋው ዛሬ  ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ከቀኑ 5:00 ሰዓት አከባቢ የተከሰተ ሲሆን የሰሌዳ ቁጥር TG - 04539 የሆነ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከዓድዋ ወደ መቐለ ሲጓዝ ወርዒ ልዩ ቦታ  እንዳፈላሲ ቁልቁለት ሲወርድ ወደ ገደል በመግባቱ ነው አደጋው ያጋጠመው።

በውስጥ ከተሳፈሩ ሰዎች ከ10 በላይ ወድያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ 5 ሰዎች በፅኑ ተጎድተዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የደረሰው መረጃ እንደሚያመላክተው 48 ሰዎች የመጫን አቅም ያለው መለስተኛ አውቶቡስ በአጋጣሚ 20 ሰዎች ብቻ አሳፍሮ መጓዙ ለሟችና ቁስለኞች መቀነስ ምክንያት ሆኗል።

የአደጋው ምክንያት ገና በመጣራት ላይ ነው።

ይህ ወር በርካታ በዓላት የሚከበሩበት በመሆኑ ብዙ የትራፊክ እንቅስቃሴ ይኖራል ፤ በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ አይለያችሁ።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia 
" 60 ሰዎችን አግተው ወስደዋል ፤ 369 ከብቶች ተዘርፈዋል ፤ 19 ቤቶችን አቃጥለዋል " - በትግራይ ክልል የምስራቃዊ ዞን

የኤርትራ መንግስት ወታደሮች 60 ሰዎች አግተው መውሰዳቸው 369 ከብቶችን በመዝረፍ 19 ቤት ማቃጠላቸው ተገልጿል።

የኤርትራ መንግስት ወታደሮች የእገታ የዝርፍያና ቤቶች የማቃጠል ተግባር የፈፀሙት በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የኢሮብና ጉሎመኸዳ ወረዳዎች እንደሆነ የዞኑ የኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት አሳውቋል።

ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ፅሕፈት ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ፥ ታግተው ከተወሱዱት 60 ሰዎች ሁለቱ ሴቶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ወጣቶችና የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ናቸው።

የኢሮብና የጉመኸዳ ወረዳዎች 8 የቀበሌ ገበሬ ማህበራት የትግራይ ጦርነት ከተጀመረበት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ወዲህ ሙሉ በሙሉና በከፊል በኤርትራ መንግስት ቁጥጥር ስር ይገኛሉ።

ለድህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉት የጉሎመኸዳ ወረዳ ቀበሌ ገበሬ ማህበራት አርሶ አደሮች በሰጡት አስተያየት ፥ ባሳለፍነው ዓመት መጨረሻ በዜጎች ላይ ያነጣጠረ አፈና ተባብሶ መቀጠሉ አመልክተዋል።

" በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የትግራይ ክልል ግዛታዊ አንድነት ወደነበረበት ባለመመለሱና የኤርትራ ሰራዊት ከአከባቢያቸው ሙሉ በሙሉ ባለመውጣቱ ለአፈናና ለከባድ የፀጥታ ስጋት አደጋ ተጋልጠናል " ብለዋል።

የጉሎመኸዳ ወረዳ የሰላምና የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ ነብዩ ስዩም በበኩላቸው " በሙሉና በከፊል በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ከሚገኙ የወረዳው 4 ቀበሌ ገበሬ ማህበራት አስከአሁን 52 ወገኖች ታፍነው መወሰዳቸው እረጋግጠናል " ብለዋል።

" ማርታ ፣ አዲስ ተስፋ ፣ አዲስ ዓለም ሙሉ በሙሉ ሸዊት ለምለም በከፊል በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ይገኛሉ " ያሉት ሃላፊው " የኢትዮጵያ የአገር መከላከያ ሰራዊት በአከባቢው የለም " ሲሉ ገልፀዋል።

በተያያዘ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ከተለያዩ የኢሮብ ወረዳ ቀበሌ ገበሬ ማህበራት 8 ሰዎች ታፍነው 222 ከብት፣ 157 ፍየልና በጎች ሲዘረፉ 19 ቤቶች በኤርትራ መንግስት መቃጠላቸው የዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ዓዴፓ) ሊቀ-መንበር ዶሪ አስገዶም አስታውቀዋል። 

የወረዳው የኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት እንደገለፀው አራት ቀበሌ ገበሬ ማህበራት በሙሉና በከፊል በኤርትራ መንግስት ወታደሮች ቁጥጥር ስር ይገኛሉ።

በኤርትራ መንግስት ወታደሮች ቁጥጥር ስር የሚገኘው የአከባቢው ማህበረሰብ ለአራት ዓመታት በከፍተኛ የፀጥታ አደጋ ስጋትና ተስፋ መቁረጥ ስሜት እንደሚገኝ የገለፁት የወረዳዎች ነዋሪና የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ገልጸዋል።

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተተግብሮ የኤርትራ ጦር ከያዘው አካባቢ እንዲወጣ ፣ የህዝብ ደህንነት እንዲጠበው፣ ተፈናቃዮች ወደ ቂያቸው እንዲመለሱ ተጠይቋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

በእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ቡድን የሚመራው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 16 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ማባረሩና ከነበራቸው ድርጅታዊ ሃላፊነት ማንሳቱን አስታወቀ።

ድርጅቱ መስከረም 6/2017 ዓ.ም አካሄድኩት ያለውን ስብሰባ አስመልክቶ ባወጣው ባለ ሦስት ገፅ መግለጫ :- 

1. አቶ ጌታቸው ረዳ 
2. አቶ በየነ ምክሩ
3. ፕ/ር ክንደያ ገ/ሂወት
4. ዶ/ር ሓጎስ ጎዲፈይ
5. ወ/ሮ ኣልማዝ ገ/ፃዲቕ
6. አቶ ረዳኢ ሓለፎም
7. ወ/ሮ ሰብለ ካሕሳይ
8. አቶ ኢሳያስ ታደሰ
9. አቶ ሰለሞን መዓሾ
10. አቶ ሺሻይ መረሳ
11. ዶ/ር ገ/ሂወት ገ/ሄር 
12. አቶ ርስቁ አለማው
13. አቶ ሃፍቱ ኪሮስ
14. አቶ ብርሃነ ገ/የሱስ
15. አቶ ሩፋኤል ሽፋረ 
16. አቶ ነጋ ኣሰፋ 

ከአባልነትና ከድርጅት ሃላፊነት " አባርሪያችኃለሁ " ብሏል።

የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ህወሓት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና የነፈገውና የድርጅቱ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ጌታቸው ረዳና በርካታ የማእከለዊ ኮሚቴ አባላት " ህገወጥ " ያሉትን 14ኛ ጉባኤ በማካሄድ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል መልሶ የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle  

@tikvahethiopia