TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
10ኛው የኢትዮጵያ ክልል 'ሲዳማ ክልል' ! የደቡብ ክልልና አዲሱ የሲዳማ ክልል በዛሬው ዕለት በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ፊት ቀርበው የስልጣን ርክክብ አካሂደዋል። ይህን ተከትሎ ሲዳማ በሀገሪቱ 10ኛው ክልል የሚሆን ሲሆን ፥ የምክር ቤቱ አባላት ለሲዳማ ክልል ህዝብ 'እንኳን ደስ አላችሁ' ብለዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
10ኛው የኢትዮጵያ ክልል!

(በኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

በዛሬው የሲዳማ የስልጣን ርክክብ ስነ ስርዓት የታደሙ የሲዳማ ተወላጅ የዞን እና የፌደራል ባለስልጣናት ደስታቸውን በተለያዩ መልኩ ሲገልጹ እንደነበር ኢትዮጵያ ኢንሳይደር በፎቶ ዘገባው አሳይቷል።

ባለስልጣናቱ እግዚያብሔርን ደጋግመው ሲያመሰግኑ መደመጣቸውንና፤ በይፋዊ ንግግራቸውም ሆነ በስልክ ቃለ ምልልሳቸው ይህንኑ ሲያስተጋቡ እንደነበር ተገልጿል።

በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ደስታቸውን በመተቃቀፍ አሊያም በመጨባበጥ መግለጽ ያልቻሉት ባለስልጣናቱ፤ ክርኖቻቸውን በማጋጨት “የእንኳን ደስ አላችሁ” መልዕክት ሲለዋወጡ ታይተዋል።

በዛሬው ስነ ስርዓት ላይ የቀድሞዎቹ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ደሴ ዳልኬ እና ሚሊዮን ማቲዮስ፣ የቀድሞው እና የአሁኑ የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪዎች ቃሬ ጫዊቻ እና ደስታ ሌዳሞ እንዲሁም የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ጥራቱ በየነ ተገኝተዋል።

#EthiopiaInsider

@tikvahethtikvahethiopia @tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ዛሬ ማምሻውን የአሜሪካ መንግስት ባወጣው መግለጫ ከምርጫ በኋላ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያን የወደፊት አካሔድ ለመወሰን እና የአገሪቱን ዴሞክራሲ እና ብሔራዊ አንድነት ለማጠናከር ጠ/ ሚ ዐቢይ አህመድ የሚመሩት መንግሥት እና መላ ኢትዮጵያውያን ከምርጫ በኋላ ለሚካሔድ አካታች የፖለቲካ ብሔራዊ ውይይት ቁርጠኛ እንዲሆኑ ነው የባይደን አስተሳደር ጥሪ ያቀረበው።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሚመሩት የአሜሪካ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለሠራተኞቹ ጥረቶች እውቅና ቢሰጥም ፤ 6ኛው አገራዊ ምርጫ የሚካሔድበት ከባቢ “አሳሳቢ ነው” ብሏል። 

የአሜሪካ መንግስትን አቋም የሚያንጸባርቀው መግለጫ ዛሬ ማምሻውን አንቶኒ ብሊንከን በሚመሩት የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በኩል ነው የወጣው።

የባይደን አስተዳደር የኢትዮጵያ ምርጫ አሉበት ያላቸው ፈተናዎች ፦
- የተቃዋሚ ፖለቲከኞች እስር፣
- የገለልተኛ ሚዲያ መዋከብ፣
- የአካባቢያዊ እና ክልላዊ መንግሥታት ወገንተኝነት እንዲሁም በመላ ኢትዮጵያ በብሔሮች እና በማህበረሰቦች መካከል የተቀሰቀሱ ግጭቶች ለነፃ እና ፍትሐዊ ምርጫ እንቅፋት ናቸው ብሏል።

"በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች በክልሎች እና ብሔሮች መካከል ያለው ልዩነት መካረር የአገሪቱን አንድነት እና የግዛት ሉዓላዊነት ያሰጋል” ያለው የአሜሪካ መንግስት #ከምርጫው_በኋላ መፍትሔ ሊፈለግ እንደሚገባ አሳስቧል።

የአሜሪካ መንግስት ፥ “ከምርጫው በኋላ ያለው ጊዜ #ኢትዮጵያውያን ተባብረው እነዚህን ልዩነቶች ለመጋፈጥ ኹነኛ ወቅት ነው” ብሏል።

የአሜሪካ መግለጫ : www.state.gov/elections-in-ethiopia/

#EthiopiaInsider #SpokespersonNedPrice #Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ የቱርክ የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደሀገር ተመለሱ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት መልዕክት ፥ "ከተከበሩ የቱርክ ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጋር የነበረንን ውድ ጊዜ አጠናቀን ወደ ሀገር ተመልሰናል።" ብለዋል። አክለውም ፥ "የቱርክ መንግስት እና ህዝብ ያደረገልንን የወሳኝ ጊዜ ትብብር ሀገራችን…
#Turkey #Ethiopia #Sudan

የቱርክ ፕሬዝዳንት ረጂብ ጣይብ ኤርዶጋን በኢትዮ - ሱዳን ድንበር ጉዳን ኢትዮጵያ እና ሱዳን ለሸማገላችሁ ሲሉ ሀሳብ አቅርበዋል።

ኤርዶሃን ሃሳቡን ያቀረቡት፤ ከጠ/ሚ አብይ አህመድ ጋር ትላንት በአንካራ በሰጡት መግለጫ ነው።

በትላትናው የዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ሪሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን መግለጫ ወቅት የትግራይ እና የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳዮች ተነስተዋል።

ኤርዶጋን ሀገራቸው ቱርክ ኢትዮጵያ እና ሱዳን የሚወዛገቡበትን የድንበር ጉዳይ ለማደራደር ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል።

ኤርዶጋን “ውዝግቡ በ2ቱ አገሮች መካከል በሚደረግ ውይይት በመልካም ጉርብትና ላይ በመመስረት እንዲፈታ የልብ ፍላጎቴ መሆኑን ገልጫለሁ ፤ ቱርክ ጉዳዩ በሰላም እልባት እንዲያገኝ ሽምግልናን ጨምሮ ማናቸውንም አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ ናት" ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ኤርዶጋን በሰሜን ኢትዮጵያ ስለተፈጠረው ጦርነት ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አላት ያሉትን ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ እና ጠቀሜታ ጠቅሰው ለሀገሪቱ ሰላም፣ ጸጥታ እና አንድነት ትኩረት እንደሚሰጡ ገልጸዋል። 

“የቀጠናውን ሰላም እና መረጋጋት ከመጠበቅ አኳያ ለወቅታዊው ችግር በለዘብተኛ አካሄድ መፍትሔ ማበጀት ያስፈልጋል ብለን እናምናለን” ብለዋል።

አክለውም 9 ወራት በላይ ያስቆጠረው ውጊያ ከተባባሰ ዳፋው በአካባቢው አገራት ሊዳረስ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።  

#EthiopiaInsider #Anadolu

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #Ethiopia አሜሪካ በአማራ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ያለቻቸው የፋኖ ኃይሎች " ውይይትን አልቀበልም " ማለታቸውን በመግለጽ ይህ " ለራሳቸውም አይጠቅማቸውም " አለች። ሀገሪቱ ይህን ያለችው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በሆኑት ኢርቪን ማሲንጋ አማካኝነት ነው። አምባሳደሩ ፤ " በአማራ ክልል ውስጥ ውጊያ እያደረጉ የሚገኙት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ኃይሎች ' ውይይትን አንቀበልም…
#የአሜሪካ_አቋም!

" ግጭት የኢትዮጵያውያንን #ስቃይ_ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የለውም " - አሜሪካ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ አሜሪካ ስለ ኢትዮጵያ ያላትን ፖሊሲ በተመለከተ ምን አሉ ?

- በትጥቅ ግጭት ውስጥ የገቡ አካላት፣ ግጭት አቁመው በንግግር ሰላምን ሊያሰፍኑና የሰብአዊ መብቶችን ማክበር አለባቸው።

- የታጠቁ ቡድኖች ፖለቲካዊ ዓላማዎቻቸውን በአመፅ ለማሳካት እየገፉ ናቸው ፤ መንግስትም ይህን ለመከላከል የሚወስዳቸው ርምጃዎች፣ በፖለቲካ ምኅዳሩ ላይ የማይካድ ተጽእኖ አለው። ውይይትን ወደ ጎን ያለው ይህ አካሔድ የመብት ጥሰቶች እንዲቀጥሉ አድርጓል።

- ሰላማዊ ዜጎች፣ በተለያዩ ኀይሎች ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የዘፈቀደ እስራት፣ አስገዳጅ ስወራ፣ ከግጭት ጋራ የተያያዘ ጾታዊ ጥቃት እና ሌሎችም ጥቃቶች እየተፈጸሙባቸው መሆኑን የሚገልጹ ዘገባዎችን ማየቱ እጅግ ያሳዝናል።

- የተፈጸሙ ጥፋቶች እውነተኛና ግልጽ የሽግግር ፍትሕ ሒደት በተከተለ የተጠያቂነት አሰራር በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል።

- ሽፍታዎች፣ የታጠቁ ቡድኖች፣ አንዳንዴም የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች፤ በህይወት የመኖር፣ የሰብዓዊ ክብርን፣ መከበርን በመሰሉ መብቶች ላይ ያለምንም ተጠያቂነት ጥሰቶች ይፈጽማሉ።

- በጦርነት እና ግጭት ወቅት እንኳ የሰብዓዊ መብቶች ሊረሱ አይገባም።

- ሁሉም ሀገር ራሱን የመከላከል ህጋዊ መብት አለው፤ ሆኖም ሀገራት ራሳቸውን የሚከላከሉበት መንገድ ያለምንም ጥርጥር የወደፊት ግጭቶችን አካሄድ የሚወስን ነው።

- ሀገር የመከላከያ መንገዶቹ በዛሬው እና በወደፊቱ የማህብረሰብ ትስስር ላይ ይበልጡኑ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነው።

- የታጠቁ ወገኖች የፖለቲካ ግባቸውን ከውይይት ይልቅ በግጭት ለማሳካት ሲሞክሩ፤ ለሚፈጸሙ በደሎች ሁኔታዎች የተመቻቹ ይሆናሉ።

- በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ታጣቂ ቡድኖች ንግግር / ድርድር አንቀበልም ማለታቸው እራሳቸውን ነው የሚጎዳቸው። በአማራ ያሉ በርካታ ሰዎች " የቆሙለት ዓላማ ፍትሃዊ ነው " የሚል እምነት/አላቸው ይህንኑ መከራከሪያቸውን ከግጭት ይልቅ በውይይት ማቅረብ አለባቸው።

- በአማራ ክልል ውጊያዎች የሚቀጥሉ ከሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች እንዳለው በውጤቱ የሚሰቃዩት ሰላማዊ ሰዎች ናቸው።  

- ህወሓት በኀይል ወሰን ለማስመለስ ከሚደረግ እንቅስቃሴ መቆጠብ አለበት።

- የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ኃይሎች በድርድር ተስፋ ሳይቆርጡ መተማመን ለመገንባት የሰላም ውይይትን ሊቀጥሉ ይገባል።

- ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በውስጣዊ ግጭቶች እየታመሰች ትገኛለች።

- የኢትዮጵያ መንግስት የአገሪቱን ችግሮች በኀይል ለመፍታት ከሚያደርገው ጥረት መቆጠብ አለበት። በእስር ላይ የሚገኙ ቁልፍ የፖለቲካ ሰዎችን መፍታቱ ጠቃሚ ነው፤ ያን ተፈጻሚ ማድረግ ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን የፖለቲካ ውይይት ሊያግዝ ይችላል።

- ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ስምምነት ሊፈጸም ይገባል።

- ሁሉም የታጠቁ ተዋናዮች፣ በመላ አገሪቱ አዲስ የሕዝብ መፈናቀልን ጨምሮ ለሰዎች ስቃይ ምክንያት ከመሆን መገታት አለባቸው።

- የታጣቁ ኃይሎች ት/ቤቶችን፣ ጤና ተቋማትንና የውኃ መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ማድረግ ማቆም አለባቸው። የተሟላና ያልተገደበ ሰብአዊ አቅርቦት ሊኖር ይገባል። ይህም ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ማድረግን ይጨምራል።

- ግጭት የኢትዮጵያውያንን ሥቃይ ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የለውም። ውይይት ትኩረት ሊደረግበት ይገባል።

- ምንም እንኳን ፍጹም ሊሆን ባይችልም፣ ሁሉም ወገኖች የአገራዊ ምክክሩን ዕድል ሊጠቀሙበት ይገባል።

#USEmbassyAddisAbaba
#VOA
#EthiopiaInsider

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #TPLF የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የዛሬውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔን አወደሱ። አቶ ጌታቸው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ሰላምን ለማጠናከር በትክክለኛው አቅጣጫ አንድ እርምጃ የተራመደ ነው ብለውታል። ዛሬ የሚኒስትሮች ም/ቤት ያሳለፈው " የኢትዮጵያ የምርጫ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ…
#Update

ፓርላማው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( #ህወሓት ) ዳግም ህጋዊ እውቅና ሊያገኝ የሚችልበትን / በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚፈቅድለትን የአዋጅ ማሻሻያ አጽድቋል።

" የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅን " የሚያሻሽለው የህግ ረቂቅ የጸደቀው በ2 የፓርላማ አባላት ተቃውሞ፣ በአንድ ድምጸ ተዐቅቦ፣ በአብላጫ ድምጽ ነው።

" በአመጽ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበሩ " የፖለቲካ ፓርቲዎችን " በልዩ ሁኔታ " እንዲመዘገቡ የሚያስችለው የህግ ማሻሻያ፤ የፖለቲካ ቡድኖቹ ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶችን እና የምርጫ ቦርድን ኃላፊነት የዘርዘረ ነው።

የጸደቀው የአዋጅ ማሻሻያ ፥ " ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ ተሰማርቷል " በሚል " ህጋዊ ሰውነቱ እንዲሰረዝ " የተደረገው ህወሓት #በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚያስችሉ አንቀጾችን በውስጡ ይዟል።

" አንድ የፖለቲካ ቡድን ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጽ ተግባር ውስጥ የተሳተፈ እንደሆነ እና ይህንን ተግባር ማቆሙን እና ሕገ መንግስታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን አክብሮ ለመንቀሳቀስ መስማማቱ በሚመለከተው የመንግስት አካል ከተረጋገጠ፣ የፖለቲካ ቡድኑ በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ሊመዘገብ ይችላል " ሲል አዋጁ ደንግጓል።

#EthiopiaInsider
#TPLF

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia : ከማከሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎቹ ዋና ዋና የፖሊሲ ርምጃዎች መካከል አንዱ በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓትን የሚመለከት ነው። ይህ የውጭ ምንዛሬ ግብይት በገበያው አማካኝነት እንዲበየን የማድረግ ሂደት እንደሆነ ተገልጿል። መንግሥት " በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመንን ማረጋገጥ በአቅርቦት እና በፍላጎት መካከል ያለውን የውጭ ምንዛሪ መዛባት ለማስተካከል…
#ETHIOPIA

መንግስት " በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት " ተግባራዊ ሊያደርግ እንደሆነ አስታውቋል።

ውሳኔው በመንግስት ቁጥጥር ሲከናወን የቆየውን የውጭ ምንዛሬ ግብይት " በገበያው አማካኝነት እንዲበየን " የሚያደርግ ነው።

ውሳኔው ተግባራዊ ሲሆን ብር፤ ዶላር እና ፓውንድን ከመሳሰሉ ዋና ዋና የመገበያያ ገንዘቦች አኳያ ያለው የምንዛሬ ተመን ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል።

አሁን በስራ ላይ በሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ተመን ስርዓት፤ ባንኮች አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ54 ብር ከ50 ሳንቲም ገደማ ገዝተው በ58 ብር ከ64 ሳንቲም ገደማ ይሸጣሉ።

በተለምዶ " ጥቁር " እየተባለ በሚጠራው ትይዩ ገበያ በአንጻሩ፤ ይህ የምንዛሪ ተመን ከእጥፍ በላይ ልዩነት አለው።

የውጭ ምንዛሬ ግብይት ስርዓትን ጨምሮ የኢትዮጵያ መንግስት ተግባራዊ በሚያደርጋቸው የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎች እና እርምጃዎች " ተጋላጭ " የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ የሚያስችሉ ተግባራት እንደሚከናወኑ መንግስት ገልጿል።

ለዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች የማክሮ ኤኮኖሚ ማሻሻያዎቹ ሊያስከትሉ ከሚችሉት የአጭር ጊዜ አሉታዊ ተጽዕኖዎች ለመጠበቅ አስፈላጊ የደመወዝ ድጎማ እና ማሻሻያዎች ለተወሰኑ ጊዜያት ይደረጋሉ ተብሏል።

በነዳጅ ዋጋ ላይ የሚከተለውን ጭማሪም መንግስት በከፊል #እንደሚደጉም አሳውቋል።

#EthiopiaInsider #Ethiopia #MacroEconomicReform

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እና የተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አበባው ደሳለው ፦ " የመንግስት ኃላፊዎች በተለያየ ጊዜያት በተደጋጋሚ ስለ ሀገራዊ ምክክር እና ስለ ሽግግር ፍትህ ሲያነሱ ይደመጣል። ነገር ግን ከሀገራዊ ምክክር እና ከሽግግር ፍትህ በፊት መቅደም ያለባቸው ነገሮች አሉ። ከነዚህ ውስጥ አንደኛውና ዋነኛው የእምነት ግንባታ ነው። መንግስት በህዝብ…
" መኖሪያ ቤታቸው የገቡት ትላንት ከምሽቱ 4 ሰዓት ገደማ ነው " - ቤተሰቦች

ከ6 ወራት በፊት " ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታፍነው " መወሰዳቸው የተነገረላቸው የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ሀብታሙ በላይነህ ትላንት ተይዘው ከነበረበት መለቀቃቸውን ቤተሰቦቻቸውን ዋቢ በማድረግ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

የአብን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ ሀብታሙ፤ ደብዛቸው የጠፋው ከየካቲት 22፤ 2016 ጀምሮ ነበር።

በዕለቱ በአዲስ አበባ 4 ኪሎ አካባቢ " ሰው ላግኝ ብሎ ከቤት እንደወጣ አልተመለሰም ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ለ6 ወራት ያህል ያለበት ሳይታወቅ ቆይተዋል " ሲሉ አንድ የቅርብ ምንጭ  አስረድተዋል።

የአማራ ክልል የምክር ቤት አባሉ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አያት አካባቢ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው የገቡት ትላንት ከምሽቱ 4 ሰዓት ገደማ መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።

አቶ ሀብታሙ በላይ እስካሁን ድረስ የት እንደቆዩና የነበሩበትን ሁኔታ በተመለከተ ግን በዚህ ጊዜ መናገር እንደማይፈልጉ ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የአቶ ሀብታሙን መለቀቅ አረጋግጣል።

የቆዩበት እና ሌሎችንም ዝርዝር ጉዳዮች በተመለከተ " ገና ቃላቸውን እንዳልሰጡ " አስረድቷል።

ሰኔ መጨረሻ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ምንም እንኳን ምላሽ ባይሰጥበትም የአቶ ሀብታሙ ጉዳይ በአብን የምክር ቤት ተመራጭ አቶ አበባው ደሳለው ተነስቶ እንደነበር ይታወሳል።  #EthiopiaInsider

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF በሊቀመንበሩ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የተመራው የህወሓት ጉባኤ አቶ ጌታቸው ረዳን ከምክትል ሊቀመንበርነት አነሳ። ዶ/ር ደብረጽዮን በድጋሚ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ተነግሯል። በአቶ ጌታቸው ረዳ ምትክ አቶ አማኑኤል አሰፋ ምክትል ሊመንበር ሆነው ተመርጠዋል። ሌሎች የስራ አስፈጻሚና የማእከላይ ኮሚቴ ሆነው የተመረጡ የድርጅቱ አባላት ከላይ ስማቸው ተያይዟል። ምርጫ ቦርድ ከጉባኤው ቀደም…
#TPLF #Tigray

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለመምራት ህወሓት " የራሱን ሰዎች መመደብ ይችላል " ሲሉ የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ።

አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ቡድን " አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም ” ብለዋል።

ሊቀመንበሩ ፤ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት ትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር " ህወሓትን ወክሎ ነው የገባው። አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም " ሲሉ ተናግረዋል።

በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር " የህወሓት ሰዎች መመደብ አለባቸው " ብለው በጉዳዩ ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩን " ካቋቋሙ ወገኖች ጋር ውይይት ያስፈልጋል " ብለዋል።

በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ ከህወሓት በተጨማሪ የትግ ራይ ሠራዊት፣ ምሁራን እና ተቃዋሚው ባይቶና ድርሻ አላቸው።

በጉዳዩ ዙሪያ ከፌድራሉ መንግስት ጋር ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመው ፥ " እኛ ትግራይ ውስጥ ብቻ የምንጨርሰው አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል።

ከሰሞኑን ህወሓት " የድርጅቱን አመራሮች የከፋፈለ ነው " የተባለለትን 14ኛ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጎ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን በድጋሚ ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑትን አቶ ጌታቸው ረዳን በማንሳት አቶ አማኑኤል አሰፋን እንዲሁም ሌሎችንም አዳዲስ የማዕከላዊና የስራ አስፈጻሚዎችን መምረጡ ይታወቃል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግን ቀደም ብሎ ጉባኤው ሳይጀመር የቦርዱን አሰራር ላልተከተለ ጉባኤ እና በጉባኤው ለሚተላለፉ ማንኛውም ውሳኔዎችና ለውጦች እውቅና እንደማይሰጥ በይፋ አሳውቋል።

#TPLF #EthiopiaInsider

@tikvahethiopia