TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፎቶ ⬆️ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ደረጃ እያካሄደው የሚገኘውን የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት 3ኛ ቀን መርሀ ግብር ዛሬ አከናውኗል። ዛሬ በከተማ ደረጃ " #ታዋቂ ፣ #ተጽዕኖ_ፈጣሪ " ናቸው የተባሉ ግለሰቦች ተገኝተው በኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ስለ ሂደቱ ገለጻ ተደርጎላቸዋል ተብሏል። በተመሳሳይ በተለየ ቦታ ላይ ከ112 ወረዳዎች ከ11 የህብረተሰብ የተወጣጡ ተሳታፊዎች በየማኅበረሰብ ክፍላቸውን…
#Update

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ለ7 ቀናት ሲያደርገው የነበረውን የአጀንዳ ማሰባሰብ መርሐ ግብር ዛሬ አጠናቋል።

በማጠቃለያው መርሐ ግብር ላይ የተገኘው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዬ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርቧል።

Q. የ7ቱ ቀናት በአ/አ ደረጃ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደትና ውጤቱ ምን ይመስላል ?

ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ፦

“ ትኩረቱ የነበረው 3 ነጥቦች ላይ ነው።

የመጀመሪያው ትኩረት በቅንነት ፣ ያለአንዳች መከልከል ፣ ያለመሸማቀቅ ሕዝባችን እንዲወያይ ነበር።

ሁለተኛው ደግሞ የአካባቢን ሁኔታ መሠረት ያደረገ ከጀንዳ ማቅረብ ነበር። 

ሦስተኛው ተወካይ መምረጥ ነበር። በአጠቃላይ ሁሉም የተሳካ ነበር። ”

Q. በአ/አ ደረጃ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች ምንድን ናቸው ? 

ዶክተር ዮናስ አዳዬ ፦

“ አጀንዳዎቹን በሙሉ ሰብስበን፣ ኮሚሽኑ ካጠናቀረ በኋላ እነዚህ የአዲስ አበባ እነዚህ የእነዛ ብሎ መናገር ይሻላል።

አሁን ባለበት ሁኔታ ግን መናገሩ አስፈላጊ አይደለም። ምክንያቱም ሌሎች የሚያስቡትን ማበላሸት ስለሚሆን። ”

Q. በአዲስ አበባ የተደረገው የተወካዮች መረጣ ከኃይማኖትና ፆታ ስብጥር አንፃር ምን ይመስላል ?

ዶክተር ዮናስ አዳዬ ፦

“ እኛ እስከገባን፣ እስካደረግነው ሥራችን ድረስ ፦
° ፆታን፣
° አካል ጉዳተኝነትን፣
° ሃይማኖትን
° የማህበረሰብ ክፍሎችንም፣ ሌላው ቀርቶ የብሔር ስብጥርን የወከለ ይመስላል።

ሴቶችን ለማካተት ተብሎ የታቀደው 30 በመቶ ነው።

በአገራችን የሴቶቻችን ብቃት ምን ያህል ነው? ምን ያህሉ ተማሩ ? በተለያዩ ዘርፎች ሴቶቻችን ብዙ አልተማሩም። ስለዚህ 50 በመቶ ብንል እንዋሻለን። ”

Q. ኢሕአፓ ከምክክሩ እንዳገለለ፣ ኦፌኮና ኦነግ በምክክሩ ዙሪያ ቅሬታ አላቸው። ከጅምሩ የሚስተዋሉ እንዲህ አይነት ተቃርኖዎች ምክክሩን አያደናቅፉትም ? ኮሚሽኑ ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየሰራ ነው ? 

ዶክተር ዮናስ አዳዬ ፦

“ ስንጀምር ከ60 ፓርቲዎች አብረውን ለመስራት የተስማሙት 2 ወይም 3 ፓርቲዎች ነበሩ። አሁን ደግሞ የቀሩት 3 ወይም 4 ናቸው። 50 ፓርቲዎች ከእኛ ጋር እየሰሩ ነው።

ለምን ? ከተባለ አካሄዳችንን አይተዋል። አካታች፣ ለማንም ያልወገንን ግን ለኢትዮጵያ የወገን፣ ለእውነት የቆምን መሆናችንን ተገንዝበው መጥተዋል።

አሁንም #ለኦፌኮም #ለኦነግም ደብዳቤ ጽፈን ሰጥተናል እንዲመጡ። እና እነርሱ ባይመጡም ሌሎቹ አብረዋቸው የነበሩ እየመጡ እንዳሉ ማዬት ይቻላል።

እንደዚህ አይነት አለመግባባቶች ካሉ፣ ቢኖሩም ብዙም አይገርመንም። ምክክሩም ያስፈለገው እንዲህ አይነት መከፋፈል ስለነበረ ነው። ”

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia