TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ATTENTION🚨

" አንዳንድ ወጣት ሴቶች ከቫይረሱ በላይ #እርግዝናን_ይፈራሉ "

ስለኤች አይቪ/ኤድስ ስርጭት የሚሰጠው የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ ከጊዜ ወደጊዜ እየተቀዛቀዘ መሆኑን በጤና ሚኒስቴር የኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ገልጿል።

ችግሮች ከመባባሳቸው በፊት ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ አሳስቧል።

ቫይረሱ ኢትዮጵያ መግባቱ ከተረጋገጠበት ጊዜ አንስቶ በተሰራው እንቅስቃሴ ብዙ ለውጦች መመዝገባቸውን አስታውሷል።

ይሁን እንጂ የተመዘገቡት ለውጦች በተወሰነ ደረጃም ቢሆን መዘናጋት እንደፈጠሩ ፤ የሚዲያዎች ተሳትፎም መቀዛቀዙን ጠቁሟል።

በአሁኑ ወቅት ኤች አይ ቪ ቫይረስን በተመለከተ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች ትኩረት የሚሹና በይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ ብቻ ትኩረት ያደረጉ ናቸው ብሏል።

እነዚህም ፦
- ሴተኛ አዳሪዎች፣
- አደንዛዥ እፅ የሚጠቀሙ ሰዎች፣
- የረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች፣
- አፍላ ወጣቶች በተለይ (ከማኅበራዊ ሚዲያ ጋር በተያያዘ)፣
- የቀን ሠራተኞች፣
- ከማኅበራዊ ችግሮች ጋር ተያይዞ ተጋላጭ የሆኑት እንደሆኑ አመልክቷል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የስርጭት መጠኑ ከ1 በመቶ በላይ ቢሆንም ከቦታ ቦታ በፆታ፣ በኅብረተሰብ ክፍል፣ በገጠርና በከተማ ከፍተኛ ልዩነት አለው ብሏል።

በከተሞች ያለው ስርጭት በገጠር ካለው በሰባት እጥፍ እንደሚበልጥም ጠቁሟል።

ይህንን ልዩነት መሠረት ያደረገ አጠቃላይ ማኅበረሰቡን ተደራሽ የሚያደርግ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ እየተከናወነ አይደለም ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፦
° የመጠጥ ቤቶች ፣
° የጫት ቤቶች
° በሺሻ ቤቶች መስፋፋት ሌላ ተግዳሮቶች እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጿል።

" አንዳንድ ወጣት ሴቶች ከቫይረሱ በላይ እርግዝናን ይፈራሉ። የወጣቶች አዲስ የመያዝ ምጣኔ ጨመረ ባይባልም እየቀነሰ አይደለም፤ ይህ በራሱ ችግር ለመኖሩ አመላካች ነው "ም ብሏል።

በተለይ በወጣቶች በኩል ሁሉን አቀፍ ሥራ ባለመሠራቱ እንደ ሀገር ዋጋ ሊያስከፍሉ የሚችሉ አጋላጭ ባሕሪያት እየተስተዋሉ መሆኑን አመልክቷል።

የኤች አይ ቪ ቫይረስን በተመለከተ ጠንካራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን እንደሀገር ማከናወን እንደሚጠበቅ አሳስቧል። #ኢፕድ

@tikvahethiopia