TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#OROMIA #Peace

" . . . እርቁ በምንፈልገው ፍጥነት አለመምጣቱ ቢያሳዝንም ተስፋ መቁረጥ ግን አያስፈልግም " - አቶ ጃዋር መሀመድ

አቶ ጃዋር መሀመድ የኢፌዴሪ መንግሥትና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLA) በታንዛኒያ ዳሬሰላም ያደረጉት የሁለተኛው ዙር ድርድር ያለ ስምምነት ከተበተነ በኃላ ድርድሩን በተመለከተ ሰፋ ያለ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አቶ ጃዋር መሀመድ ምን አሉ ?

- መንግስትንና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (WBO-OLA) ለማስታረቅ የተደረገው 2ኛው ዙር ሙከራ አለመሳካቱ በህዝቡ ዘንድ ትልቅ ሀዘን የፈጠረ ነው።

- በሕዝቡ በኩል ቢያንስ ሁለቱም ወገኖች በዚህ ዙር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንደሚደርሱ ተስፋ ተደርጎ ነበር። በተለይ የጦር አዛዦች ከጦር ሜዳ ለውይይት መምጣታቸው እርቀ ሰላሙን ያሳካል የሚል ተስፋ ፈጥሮ ነበር።

- ድርድሩ አለመሳካት እንደ ትልቅ ውድቀት ሲቀርብ እናያለን ነገር ግን ውይይቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ብዙ ርቀት ተጉዟል። እርቅ ከማያስፈልግበት ወይም ከማይቻልበት ደረጃ ተነስተን የሁለቱም ወገን አመራሮች ፊት ለፊት ተገናኝተው መወያየት ደረጃ ደርሰናል።

- ይህ እርቅ በምንፈልገው ፍጥነት አለመምጣቱ ቢያሳዝንም ተስፋ መቁረጥ ግን አያስፈልግም። ተስፋ ልንቆርጥም አንችልም። ሌላ መፍትሄ የለንምና። ስለዚህ የሰላም ድርድሩ እንደሚቀጥል ተስፋ እናደርጋለን።

🕊አቶ ጃዋር መሀመድ በሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር ላይ ከተሳተፉት አካላት እና ከተለያዩ ምንጮች ተረዳሁት ያሉትንና ለቀጣይ ዙር የሰላም ድርድር ያግዛሉ ያሏቸውን ሃሳባችን በዝርዝር አቅርበዋል።

➜ በሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር ሁለቱም ወገኖች በእውነት #እርቅ/#ሰላም ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ።

በዚህ የተነሳ ሁለቱም ወገኖች ልክ እንደ ህዝቡ ይህ ምዕራፍ በእርቅ ስምምነቱ ይጠናቀቃል የሚል ተስፋ (expectation) ይዘው ነበር የቀረቡት።

ሁሉም ተሳታፊዎች (WBO / የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ፣ መንግስት እና አሸማጋዮች) በሰላም፣ በእርቅ ይጠናቀቃል የሚል ተስፋ ይዘው ስለሄዱ ግባቸው ላይ ባለመድረሳቸው የመናደድ ስሜት ውስጥ ገብተዋል። በዚህ ምክንያት ለቀጣዩ የሰላም ውይይት በር ከመክፈታቸው በፊት ተለያይተዋል።

➜ ሁለቱም ወገኖች በቅን ልቦና ለመታረቅ ቢሄዱም፣ አንዱ ከአንዱ የሚፈልገውን (demands/concessions) ለመስጠት እና ለመቀበል ሙሉ በሙሉ የተዘጋጁ አይመስሉም።

በመጀመሪያው ዙር እርስ በርሳቸው የሚፈልጉትን ነገር ተረድተው ተለያይተዋል። በሁለተኛው ዙር ደግሞ አንዳቸው ለሌላው መስጠት የማይችሉትን ያወቁ ይመስለኛል።

አሁንም ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኝነት ካላቸው፣ ቀጣዩ እርምጃ ሁለቱም ወገኖች ጥያቄዎቻቸውን ለማስተካከል (modifying demands) መዘጋጀት አለባቸው። ይህ ማለት እንዱ መቀበል የማይችላቸው ነገሮች ላይ በመግፋት መጋጨት መተው አለባቸው።

በሰላም ድርድር ውስጥ የሚፈልጉትን እና ይገባኛል ብለው የሚያስቡትን ሁሉ ማግኘት አይቻልም። ይገባኛል ብለው የሚያስቡትን ሁሉ ማጣትም አይቻልም። ሁለቱም ወገኖች ወደ መካከለኛው አቋም መምጣት ይጠበቅባቸዋል።

➜ የሰላም ድርድሩ ዋነኛው #እንቅፋት እየሆነ ያለው ዋና ምክንያት አንዱ ከአንዱ የሚፈልገው ነገር ላይ ተራርቀው ነው ብዬ አላስብም። ትልቁ እንቅፋት #አለመተማመን ነው። በሁለቱ ወገኖች በታሪክ ካለው ግንኙነት እና ከአገራችን የፖለቲካ ባህል አንፃር አለመተማመናቸው ይጠበቃል። የውጪው አካል ያስፈለገበትም ምክንያት ይሄ ችግር ስለተረዳ ነው። እነዚህ አስታራቂዎች የእርቅ ስምምነት ላይ መድረስ ብቻ ሳይሆን የስምምነቱ አፈጻጸምን ለማረጋገጥ ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ይህንን አሻሚ የሆነ ችግር ለማሻሻል ይጠቅማል።

➜ ከውስጥ ከውጭ " እርቅ ሊመጣ ነው " ብለው እያዘኑ የነበሩት ወገኖች አሁን በመፍረሱ በደስታ እየፈነደቁ ነው። ሌላ ዙር ድርድር እንዳይደረግም እያሴሩ ነው። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLA) እና የመንግስት አመራሮች አሁንም ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል አቋም ካላቸው እነዚህ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ወደ ውስጥ እንዳይገቡ ሁሉንም ክፍተቶች መዝጋት አለባቸው። በተጨማሪም የሚቀጥለውን ዙር እድሎች ከሚያጠብ ወይም ከሚያርቁ ድርጊቶች እና ቃላት መቆጠብ አለባቸው። ይህም የሚዲያ ፕሮፓጋንዳ እና የመስክ ውጊያን አለማባባስን ያካትታል።

➜ እኔ እስከተረዳሁት ድረስ ከ2ቱም ወገን ደጋፊዎች በኩል የነበረው የ " #ምታ - #ስበር - #አጥፋ " ዘመቻ ባለፉት አመታት በጣም መቀነሱን ነው። የእርቅ ሀሳብ መደገፍ እና ሰላም እንዲወርድ ያላቸው ምኞትም ከየትኛውም ጊዜ በላይ እያደገ መጥቷል።

➜ አሁንም የሁለተኛው ዙር ሙከራ ስላልተሳካ እርስ በርስ ጣት መቀሳሰር እና መደማማት ምንም ፋይዳ እንደሌለው መረዳት ያስፈልጋል። የሚጠቅመው የሚደግፉትን ወገኖች ወደ ድርድሩ እንዲመለሱ እና የሚጠበቅባቸውን እንዲሰጡ ማበረታታት እና ጫና ማድረግ ነው።

➜ በመጨረሻም ፤ ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ይሄ የሰላም ድርድር የጦር ሜዳ ውጤቶች አይደለም።

ሁለት የሚዋጉ ወገኖች ለእርቅ ድርድር የሚቀመጡት በሁለት ሁኔታዎች ውስጥ ነው።

የመጀመሪያው ፦ በጦር ሜዳ ላይ አንደኛው የበለጠ የበላይነት አግኝቶ ወደ ድል ሲቃረብ እና ሌላኛው ወገን ሙሉ በሙሉ ከመሸነፉ በፊት ለመታረቅ ሲወስን ነው።

ሁለተኛው ፦ ከረዥም ጊዜ ጦርነት በኋላ ሁለቱም ወገኖች መሸናነፍ ካልቻሉ ነው። በWBO-OLA እና በመንግስት መካከል ያለው ጦርነት የመሸናነፍ ወይም የመድከም ደረጃ ላይ አልደረሰም። በአጭር ጊዜ ውስጥም እዚህ ደረጃ ላይ ይደርሳል ብዬ አላስብም። ይህ ውይይት የመጣው በህዝብ እና በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ግፊት ነው።

በተለይም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሀገራችን ሰላም እንዲሰፍን ያሳየው ትኩረት ያልተጠበቀ እና ትልቅ እድል ነው።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት በፍጥነት እየተቀየረ ነው። ስለዚህ ፤ ጉዳያችን ትኩረት ባገኘበት በዚህ ወቅት በፍጥነትና በብልሃት መጠቀም አስፈላጊ ነው። ይህንን እድል መጠቀም ካልቻልንና የሚባክን ከሆነ ለረጅም ጊዜ እንቆጫለን።

#JawarMohammed

Via https://publielectoral.lat/tikvahethAFAANOROMOO

#TikvahEthiopiaAFAANOROMOO

@tikvahethiopia