TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች መታሰራቸው ተገለፀ። እንዚህ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት ፦ - ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ - ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ - ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተውጣጣ ግብረ-ኃይል ከሙስናና ሕገወጥ ተግባር ጋር በተያያዘ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ ከቆየ በኃላ ነው ተብሏል። ተጠርጣሪዎቹ ፤ ተገልጋዮች በመደበኛ…
#ሙስና #ICS

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ኃላፊ የነበሩት ታምሩ ግንበቶን ጨምሮ 60 የተቋሙ ባልደረቦች 15 የሙስና ወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው።

የተቋሙ ምክትል ዳይሬክተር ከነበሩት ታምሩ ግንበቶ በተጨማሪ የውጭ ዜጎች ቁጥጥር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጅላሉ በድሩ የኬላዎች ማስተባበሪያ ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ቦጋለም ይገኙበታል።

በፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀል ዐቃቤ ሕግ በክሱ የእያንዳንዱ ተከሳሽ የወንጀል ተሳትፎን ዘርዝሯል።

የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ታምሩ ግንበቶ ኃላፊነታቸውን በመጠቀም ፦

* ፎርቲን አቬጋ በተባለ ድርጅት የሚሠሩ 12 ግብፃዊያን ለቪዛ ቅጣት ይከፍሉ የነበረውን 24 ሺህ ዶላር በራሳቸው ትዕዛዝ 14 ሺህ ዶላሩን በመቀነስ በመመሪያው መሠረት ባልተገባ መንገድ የተቀነሰውን በዶላር መክፈል ሲገባቸው በኢትዮጵያ ብር እንዲከፍሉ በማድረግ መንግሥት ላይ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል።

* ሀይንፊን፣ ሀድዙ የተሰኙ የቻይና ኩባንያ ድርጅት ውስጥ የሚሠሩ ብሎም ሻሎም አስመላሽ ኪዳኔ እና ነጃት ዓሊ መሐመድ ለቪዛ ቅጣት በዶላር መክፈል ከነበረባቸው 4 ሺህ ዶላር ያህል መመሪያ በመጣስ እንዳይከፍሉ በማድረግ መንግሥት ላይ ጉዳት አድርሰዋል።

* የማይገባ ጥቅምን ለማግኘት በማሰብ ተገቢ ማጣራት ሳይከናወን ነዋሪነታቸው በሶማሊ ላንድ ሐርጌሳ ለሆኑ 68 ግለሰብ የኢትዮጵያ ፓስፖርት እንዲሰጥ በማድረግ የሀገርን ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል ድርጊት የፈፀሙ በመሆኑ ሥልጣንን ያለ አግባብ በመገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ተከስሰዋል።

1ኛው ተከሳሽ ታምሩ ግንበቶ እና 2ኛ ተካሽ ጅላሉ በድሩ በወንጀል ከሀገር እንዳይወጡ ትዕዛዝ ለተላለፈባቸው 6 ቻይናውያን መካከል ዙ ጂያን እና ዛንግፒንግል የተሰኙ ሁለቱ የተጣለባቸው እግድ ተነሥቶ የመውጫ ቪዛ በአስቸኳይ እንዲሰጣቸው በማድረጋቸው ዐቃቤ ሕግ ሁለቱንም ግለሰቦች በፈፀሙት ሥልጣንን ያለ አግባብ በመገልገል የሙስና ወንጀል ከሷቸዋል።

ዐቃቤ ሕግ የእያንዳንዱን ተከሳሽ የወንጀል ተሳትፎን በመጥቀስ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የሙስና ወንጀል ጉዳይ ችሎት አቅርቧል።

በተከሳሾች ስም ፦

- 14,523,647.36 ብር (14 ሚሊዮን 523 ሺህ 647 ከ36 ሣንቲም)
- አክሲዮን 383,000.00 ብር (383 ሺህ)
- 8 ቤቶች ያሉ ሲሆን በፍትሕ ሚኒስቴር በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል በኩል ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ማፍራት እንዲሁም በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅርብ ወንጀል ምርመራ እየተጣራ እና ምርመራ እየቀጠለ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

ክሱን በንባብ ለማሰማት ፍርድ ቤቱ ለሰኞ ታኅሣሥ 8 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ መሰጠቱን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ICS #Ethiopia

" በአሁን ሰዓት የተጠራቀመ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ አጠናቀናል " - ICS

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት ጉዳዮች አገልግሎት በትግራይ ተቋርጦ የሚገኘውን የኢሚግሬሽን አገልግሎት ለማስጀምር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

አገልግሎቱ ትላንት በሰጠው መግለጫ ነው ይህን ያለው።

በሌላ በኩል ፤ ባለፉት 6 ወራት ከ1.1 ሚሊዮን በላይ የፓስፖርት ቡክሌቶችን ከውጭ ሀገር በማስገባት 640 ሺህ ፓስፓርት ፐርሰናላይዜሽን ህትመት በመስራት ለተጠቃሚዎች ማድረሱን አሳውቋል።

• ለአዲስ አበባ 260,371፣
• በየአካባቢው ላሉ ቅ/ጽ/ቤቶች 269,358፣
• በአስቸኳይ 35,394 እና በውጭ ለሚኖሩ ኢትዬጵያዊያን 81,416 እንደሆነ አመላክቷል።

የውስጥ ህትመት አቅምን በተመለከተ ከዚህ ቀደም በቀን 2 ሺህ ይታተም የነበረው አሁን ወደ 10 ሺህ በላይ ወደማተም ደረጃ መደረሱን ገልጿል።

መ/ቤቱ በአሁን ሰዓት የተጠራቀመ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ እንዳጠናቀቀ በይፋ አሳውቋል።

ከዚህ ባለፈ በእጁ ላይ 80 ሺህ ፓስፖርት ስላለ ያመለከቱና ተራው የደረሳቸው በስልክ በሚደርሳቸው መልዕክት መሰረት እንዲወስዱ ጥሪ ቀርቧል።

ፓስፖርት ለማውጣት ከዚህ ቀደም ይወስድ የነበረው የአንድ አመት ጊዜ ከመጋቢት 16 /2016 በኃላ እንደሚቀረፍ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት ጉዳዮች አገልግሎት ገልጿል።

ከዚህ በባለፈ ፤ ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ፦
➡️ከዋና ቢሮ፣
➡️ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣
➡️ ከቦሌ፣
➡️ከኬላዎች በድምሩ 205 የሚሆኑ ሠራተኞች ውጭ ካሉ #ደላሎች ጋር በመተባበርና የአሰራር ክፍተትን በመጠቀም ከህብረተሰቡ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሰሩ መረጃ ተገኝቶባቸው ለህግ አካላት እንዲቀርቡ እንደየጥፋታቸውም ከስራ እንዲታገዱና የህግ ውሳኔ እንዲሰጣቸው መደረጉን አስረድቷል።

ህብረተሰቡ ፦

* ተመሳስለው ከተሰሩ ዌብሳይቶች ራሱን እንዲጠብቅ
* በግለሰብ አካውንት ምንም አይነት ገንዘብ ገቢ እንዳያደርግ፣
* ዜግነት ማጣራት ጋር በተያያዘ ሂደት ያለው ስለሆነ የሚጠየቁ ሰነዶችን በትዕግስት እንዲያቀርብና እንዲተባበር፣
* ፖስፖርት ውሰዱ ተብለው የጽሁፍ መልዕክት ሲደርሳቸው በተባለው ቀን እና ሰዓት እንዲወስዱ፣
* አስቸኳይ ፓስፖርት በኦንላይን የማይሰጥ ስለሆነ አስቸኳይ የሚያሰጥ ሰነድ ያላቸው ተገልጋዬች በዋናው ቢሮ ብቻ በአካል በመገኘት  መስተናገድ እንዳለባቸው አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#ICS

የሕዝብ ተ/ም/ቤት የሕግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎትን የ9 ወር አፈጻጸም ትላንት ገምግሟል።

ኮሚቴው ከዚህ ግምገማ በፊት ማለትም ሚያዚያ 3/2016 ላይ #ድንገተኛ ምልከታ አድርጎ ነበር።

ቋሚ ኮሚቴው ምን አለ ?

- ምንም እንኳ የተጀመሩ ሥራዎች ጥሩና ተስፋ ሰጪ ቢሆኑም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮችን እና የተገልጋይን ቅሬታ መፍታት አልተቻለም።

- ተገልጋዮች አገልግሎት ለማግኘት ብለው በሚደርስባቸው እንግልትና ስቃይ ምክንያት በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንደሚያቀርቡ በድንገተኛ ምልከታ መመልከት ተችሏል።

- በዋና መ/ ቤቱ ተገልጋይ በተቋሙ ሠራተኞች ፦
➡️ #መሰደብ
➡️ #መመናጨቅ
➡️ #መገፍተር_ጭምር የሚደርስበት በመሆኑ ተገልጋይ በሥነ ምግባር መስተናገድ አለበት።

- በአዲስ አበባ " ካሳንቺስ አካባቢ " የሚገኘዉ የውጪ ዜጎች አገልግሎት ተቋም የሚሰጠው አገልግሎት ኢትዮጵያን የማይመጥን፣ ምቹ ያልሆነ እና የንጽህና ጉድለት ያለው ነው። ይህ መታረም አለበት።

- ዋናው መስሪያ ቤት ለአገልግሎት ምቹ ያልሆነ፣ ሕንፃው የቆየ እና አስፈላጊዉን የማሻሻያ ጥገና ያላገኘ ነው። ሕንፃው ከተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ባህሪ ጋር የማይጣጣም ስሪት ያለው ነው።

- በዋና መስሪያ ቤት ያለው መጨናነቅ እንዲቀንስ በአዲስ አበባ ከተማ ከአምስት ያላነሱ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች እንዲከፈቱ የመፍትሔ ሃሳብ ቢሰጥም አልተፈጸመም። በተለይ በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ የማስፋፋት ሥራዎች መሠራት አለበት።

- የደላላ ሰንሰለት በመለየት ማቋረጥ ያስፈልጋል።

- አሁንም ከደላሎች ጋር የሚመሳጠሩ የተቋሙ #ሠራተኞች በመኖራቸው ትኩረት ሰጥቶ መሥራት አለበት።

- የሠራተኛ ባጅ አለመኖሩም ሊታሰብበት ይገባል።

በምክር ቤቱ የተገኙት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ለተነሱት ጉዳዮች ምላሽ ሰጥተዋል።

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/EPA-04-27-2 #EPA

@tikvahethiopia