TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጥቆማ‼️መንግስት ወደሀገር ያስገባቸውን እና ሀገር ውስጥ ያሉትን #ሁሉንም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ክትትል ሊያደርግባቸው ይገባል። ችግሮች ከመፈጠራቸው በፊት አሁን እያታዩ ያሉ መስመር የለቀቁ ከስነ ምግባር የወጡ እቅስቃሴዎች ከወዲሁ ሊገቱ ይገባል።

‼️የሩዋንዳውን እልቂት ማስታወስ ተገቢ ነው‼️

ነፃነት ማለት እንደፈለጉ መሆን፤ ህግ መጣስ፤ ከስነ ምግባር ውጭ መሆን አይደለም። ሁሉም ነገር ገደብ እና ልክ አለው። አሁን መሬት ላይ ያለው ጥብቅ #እርምጃዎችን የመውሰድ እንቅስቅሴ ይበረታታል።


የመንግስት ተቀዳሚ ስራው ህግ እና ስርዓትን ማስከበር ነው‼️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀጫሉ ሁንዴሳ...

“•••እነኚህ ሰዎች ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ሰርተው #ያስደመሙኝ ነገር አለ። ከዚህ በፊት ኦሮሞ እንደ አገር አፍራሽ ተደርጎ ብዙ ተሰርቶበታል። አሁን ግን ኦሮሞ አገር አፍራሽ እንዳልሆነ፣ ትልቅ ሃሳብ ያለው እንጂ የሚያሳስብ እንዳልሆነ፣ ያገሪቱ ጋሻ እንደሆነ ባለም ላይ አስመስክረዋል። በእርግጥ ሁሉም ነገር ተሟልቶ ተጠናቋል ማለት አይደለም። #ለዘመናት የተተበተበብንን ትብታብ በጣጥሶ ነገሮችን ለማስተካከል #አይደለም ስምንት ወር #ስምንት አመትም አይበቃም። አሁን የታሰርንበትን እስራቶችን (ቋጠሮዎችን) በመፍታት ደረጃ ላይ ነው ያሉት። ደግሞም #ሁሉንም ነገር ከነሱ ብቻ መጠበቅ የለብንም። #እኛም እጅ ለእጅ ተያይዘን የምንሰራቸው ነገሮች አሉ።”

ሀጫሉ ሁንዴሳ ከOBN ቴሌቪዝን ጋር በነበረው ቆይታ የተናገረው!

©Daniel Ragassa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቪዲዮ ፦ ከላይ የምትመለከቱት #በአሜሪካ ሀገር ፣ ፊላደልፊያ በአንድ የ " አይፎን ስቶር " ላይ ከቀናት በፊት የተፈፀመ ዘረፋ ነው።

ነገሩ እንዲህ ነው በርካታ #ጭምብል የለበሱ እና ያለበሱ ሰዎች የአፕል ስትሮን በኃይል ሰብረው ይገባሉ።

በኃላ ውስጥ የነበሩ ለእይታ የቀረቡ #ሁሉንም አዳዲሶቹን የ " አይፎን 15 " ምርቶች እና ሌሎች የአፕል ቴክኖሎጂ ውጤቶችን " free iPhone " እያሉ እየጮሁ ይወስዳሉ።

ከአፕል ስቶር ስልኮቹን ይዘው ከወጡ በኃላ አንድ ድምፅ ይሰማሉ ፤ ስልኩ አገልግሎት እንደማይሰጥ እንዲሁም ስልኩን የያዘው ሰው ላይ ክትትል እንደሚደረግ ስልኩ ላይ በተመለኩት ፅሁፍ ይረዳሉ።

በየአፕል ስቶር ውስጥ ለማሳያ የሚቀመጡት አይፎን ስልኮች ለሽያጭ ከሚቀርቡት አይፎኖች ላይ ከሚጫነው ሶፍትዌር በተለየ ልዩ ሶፍትዌር የሚጫንባቸው ናቸው።

ይህን ሲገነዘቡ " አይፎን 15 " ስልኮቹን ጥቅም እንዳይሰጡ አድርገው ወደ መሬት እየጣሉ #ይሰባብራሉ። የውሃ መውረጃ ትቦ ውስጥም ይጨምራሉ።

ፖሊስ ደርሶ በዘረፋው ላይ የተሳተፉትን በቁጥጥር እንዳዋለ ተነግሯል። በርካታ ሰዎች መታሰራቸውን ፖሊስ አሳውቋል።

ድርጊቱ ብዙ የአሜሪካ ዜጎችን በማህበራዊ ሚዲያ እያናጋገረ እና እያወያየ ሲሆን አንዳንዶች በዘረፋ ድርጊት ፈፃሚዎች ላይ ላልቷል ያሉትን ህግ ሲተቹ ታይተዋል።

@tikvahethiopia