TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray
 
ወደ 26 የትግራይ ወረዳዎች ለእርዳታ በመጓጓዝ ላይ ያለ #የተበላሸ የማሽላ እህል ለህዝብ እንዳይከፋፈል ታገደ።

እግዳውን ያስተላለፈው የትግራይ ክልል ምግብና የመድሃኒት ቁጥጥርና ክትትል መ/ቤት ነው።

ከማሽላ እህሉ በተወሰደ የናሙና ምርመራ ውጤት መሰረት ፦
- መጥፎ ሽታ ያለው መሆኑ፤
- በነቀዝ የተበላና ወደ ዱቄትነት የመቀየር ደረጃ የደረሰ በመሆኑ ፤
- በአጠቃላይ የበሰበሰና የተበላሸ በመሆኑ፡
ለምግብነት ቢውል የሚያስከትለው የጤና ጠንቅ እጅግ ከባድ ስለሆነ እህሉ በያለበት መጋዘን እንዲታገድ ተወስኗል።

በመጓጓዝ ላይ ያለውም እንዲቋረጥ ሲል መ/ቤቱ ሰነ 6/2016 ዓ.ም ለወረዳዎቹ በፃፈው የእግድ ደብዳቤ አስታውቀዋል።

እግድ የተጣለበት የማሽላ እህል ' አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ ግብረ ሃይል ' በሚል በክልሉ የተቋቋመው በድርቅ እና በሰብአዊ ቀውስ ለተጎዱ ወገኖች ለማገዝ ከአገር ውስጥና ከውጭ ለጋሾች ባሰባሰው ብር የተገዛ ነው።

ግብረ ሃይሉ ሰነ 5 ቀን 2016 ዓ/ም ለሚድያዎች በሰጠው መግለጫ  እህሉ በግዢ ጊዜ በናሙና ከቀረበው ውጭ የሆነና የተበላሸ ለጤና ጠንቅ መሆኑ ስለተደረሰበት እንዳይከፋፈል ሲል ገልጿል።

መግለጫው ተከትሎ በማሽላ እህሉ ምርመራ ያካሄደው የምግብና የመድሃኒት ቁጥጥርና ክትትል መ/ቤት ፤ እህሉ የተበላሸና ለምግብነት ውሎ የሚያስከትለው አደጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት  በ90 ሚሊዮን ብር በጨረታ የተገዛው የማሽላ እህል #እንዲታገድ ወስኗል።

እግዱን ተከትሎ ' አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ ግብረ ሃይል ' ሰነ 6/2016 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ በሰጠው መግለጫ " እህሉ ከጥቅም ውጭ እንዲሆን ፤ ለመግዣ የተመደበው 90 ሚሊዮን ብር በ26 ወረዳዎች ለሚገኙ ተረጂዎች በጥሬ ገንዘብ እንዲከፋፈል ፤ የጨረታ ሂደቱ ተሰርዞ አህል አቅራቢው ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዘው 9 ሚሊዮን ብር እንዲወረስ ወስኛለሁ " ብሏል። 

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
#መቐለ

@tikvahethiopia