TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከየመን የባህር ዳርቻ ልዩ ስሙ " #አራ " ከሚባል ስፍራ 77 #ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ ጅቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መገልበጧ መገለጹ ይታወሳል።

በዚህም አደጋ የ5 ዓመት #ሕጻናት እና #ሴቶችን ጨምሮ 16 ኢትዮጵያውያን እንደሞቱ መገለጹ አይዘነጋም።

የIOM የጅቡቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ታንጃ ፓሲፊክ ፤ የሟቾች ቁጥር ቀደም ሲል ከሰጠው መረጃ ማለትም 16 ከፍ ማለቱንና 21 መድረሱን ተናግረዋል።

የሞቱት ሁሉም #ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ገልጸዋል።

23 ሰዎች አሁንም ድረስ የት እንደገቡ እንኳን አይታወቅም ብለዋል።

33 ሰዎች ከአደጋው እንደተረፉ ገልጸዋል።

ይህ አደጋ #38_ኢትዮጵያውን ከሞቱበት አደጋ ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የተከሰተ ነው።

በርካታ ሰዎች በተለይም ወጣቶች ህይወታቸውን ለመቀረ ሲሉ በአደገኛው እና ህገወጥ በሆነው መንገድ ሀገራቸውን ጥለው ይሰደዳሉ ፤ በዚህም ህይወታቸውን ባህር ላይ ያጣሉ ፣ ይታሰራሉ፣ በየበረሃው ይንገላታሉ ፣ በደላሎች ታግተው ይሰቃያሉ ።

ሀገር ጥለው በህወጥ መንገድ የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ አይታይም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ፖሊስ ተጨማሪ 8 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ተፈቀደለት።

ቀሲስ በላይ መኮንን በሃሰተኛ ሰነድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማዘዋወር ሲሞክሩ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል።

በተጠረጠሩበት ወንጀል ዛሬ ለ2ኛ ጊዜ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል።

ከእሳቸው ጋር ሌሎች 2 ግለሰቦች ያሬድ ፍስሃ እና ጣባ ገናና የተባሉ ቀርበዋል።

ከዚህ ቀደም ለፌዴራል መርማሪ ፖሊስ 7 ቀን መሰጠቱ ይታወሳል።

በዚህ ጊዜ መርማሪ ፖሊስ ምን እንደሰራ ለችሎቱ አስረድቷል።

ፖሊስ ምን አለ ?

- " የምስክሮችን ቃል ተቀብያለሁ። "
- " በተጠርጣሪዎች እጅ ላይ የተገኘ ኤሌክትሮኒክስ ምርመራ እንዲደረግ ለሚመለከተው ተቋም ጠይቂያለሁ። "
- " የቴክኒክ ምርመራ እንዲሰጠኝ በደብዳቤ ጠይቂያለሁ። "
- " ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ለአፍሪካ ህብረት የሰነድ ማስረጃዎች እንዲሰጠኝ ጠይቂያለሁ። "
- " ተጠርጣሪዎቹ በስማቸው የሚገኙ ሂሳቦችን ለማጣራት ማረጋገጫ እንዲሰጠኝ በደብዳቤ ጠይቂያለሁ። "
- " በወቅቱ የነበረ የካሜራ ቅጂ ጠይቂያለሁ። "
- " ለወንጀል ተግባር የዋለ ተሽከርካሪ ማረጋገጫ ከሚመለከተው ተቋም ጠይቂየለሁ። "
- " በቀሲስ በላይ ሁለት መኖሪያ ቤቶች ላይ ብርበራ አድርጌ በብርበራ የተገኘ የጦር መሳሪያ ህጋዊነት የማረጋገጥ ስራ እየሰራሁ ነው። " ... ብሏል።

የቀሩ ስራዎች ፦
- " ከተለያዩ ተቋማት የሰነድ ማስረጃ መሰብሰብ። "
- " ተጨማሪ ምስክሮችን ቃል መቀበል። "
- " ግብረአበሮችን ተከታትሎ መያዝ። "
- " ተጨማሪ ሀብት የማፍራት ተግባሮች ላይ የማጣራት ስራ መስራት ሌላም ሰፊ የምርመራ ስራ ስለሚያስፈልግ ተጨማሪ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ " ብሏል።

የተፈጸመው ድርጊት " ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለንን መልካም ግንኙነት ጥላሸት የሚቀባ ተግባር ነው " ብሏል።

ተጠርጣሪው ቀሲስ በላይ መኮንንን ጨምሮ ሌሎቹም ተጠርጣሪዎች በ6 ጠበቆች ተወክለው ነው የቀረቡት።

ጠበቆቻቸው ምን አሉ ?

° " የቀረበው የጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ምክንያቶች ደንበኞቻችን ተጨማሪ በእስር ለማቆየት የሚያስችል አይደለም " ብለዋል።

° " ቀሲስ በላይ የተገኘው የጦር መሳሪያ ህጋዊ ነው። ሀብት ማፍራት ከተጠረጠሩበት ወንጀል ጋር ሊገናኝ አይገባም " ብለዋል።

° " የሃይማኖት አባት መሆናቸው ፣ የልማት ስራ አስተባባሪ በመሆናቸው ፣ ቋሚ አድራሻ ያላቸው በመሆኑ ቢወጡ ከመንግስት ተቋማት የሚመጡ ማስረጃዎችን የማጥፋት አቅም የላቸውም " ብለዋል።

ስለሆነም የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

ቀሲስ በላይ መኮንን ምን አሉ ?

ወንጀል አለመፈጸማቸውን ገልጸዋል።

ለሀገር እንዲሁም ፖሊስ ተባባሪ መሆናቸውን ተናግረዋል።

➡️ " ምሽት ላይ #እቤቴ_እየሄድኩ ጠዋት ላይ ልምጣላችሁ " በማለት ፖሊስን መጠየቃቸውን ለችሎቱ አስረድተዋል።

ከእሳቸው ጋር አብረው የታሰሩት #ሹፌራቸው እና #አጃቢያቸው እንደሆኑ ገልጸው ምንም የወንጀል ተሳትፎ በሌለበት ሁኔታ ከኔ ጋር ተጨማሪ ጊዜ በእስር ማቆየት ተገቢ አይደለም በማለት የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ቢወጡ ማስረጃ ሊሰወር ይችላል በማለት የዋስትና ጥያቄያቸውን ተቃውሟል።

የግራ ቀኝ ክርክሩን የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ለጊዜው በማለፍ ለፖሊስ የ8 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፈቅዷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ ፥ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (#ኤፍቢሲ) መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ዛሬ የብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ፤ በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ መምከሩን አሳውቋል።

ይህ ተከትሎ ዘለግ ያለ መግለጫ አውጥቷል።

በዚህ መግለጫ ፦
- ስለ ሀገራዊ ምክክር
- ስለ ሽግግር ፍትሕ
- ከመንግሥት ውጭ ታጥቀው ስለሚንቀሳቀሱ ኃይሎች
- ስለ ተሃድሶ ኮሚሽን
- ስለ ፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት
- ስለ ህወሓት ታጣቂዎች
- ስለ ተፈናቃዮች መመለስ

...ሌሎችም ጉዳዮች ተነስተውበታል።

ምክር ቤቱ፥ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የሀገረዊ ምክክር ኮሚሽን በክልል ደረጃ የምክክር መድረኮችን ማካሄድ ይጀምራል ብሏል።

ሀገራዊው የምክክር ጉባኤ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚካሄድ ተስፋ ይደረጋል ሲል ገልጿል።

ም/ቤቱ፤ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ መፅደቁን አስታውሷል።

እንደ አግባብነቱ፦
° የወንጀል ምርመራ እና ክስ
° እውነት ማፈላለግ
° ዕርቅ
° በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ምሕረት
° ማካካሻ እና ተቋማዊ ማሻሻያ እንደ ሽግግር ፍትሕ ስልቶች በሀገራችን ተግባራዊ ይደረጋሉ ብሏል።

" የመንግሥት አንዱ መብት በብቸኝነት ኃይልን መጠቀም " መሆኑን ገልጾ በሀገራችን በተወረሰ የፖለቲካ ስብራት የተነሣ የታጠቁ ኃይሎች ተፈጥረዋል ብሏል።

የሀገሪቱን ሰላም የጸና ለማድረግ፣ እነዚህ የታጠቁ ኃይሎች ትጥቅ ፈትተው፣ የተሐድሶ ሂደት ውስጥ መቀላቀል አለባቸው ብሏል። " የፖለቲካ ጥያቄዎቻቸውንም በሀገራዊ ምክክር ሂደት በመሳተፍ መፍታት ይችላሉ " ሲል ገልጿል።

ለዚህም የተሐድሶ ኮሚሽን ተቋቁሟል። ዓላማውም፦
° መሣሪያ ማስፈታት
° የትጥቅ ቡድኖችን ሰላማዊ ማድረግና ከማኅበረሰቡ ጋር መቀላቀል ነው ብሏል።

መንግሥት የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አተገባበር ከሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ጋር የተናበበና የሚመጋገብ እንዲሆን ኃላፊነቱን ይወጣል ብሏል።

ምክር ቤቱ በመግለጫው፤ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ጦርነትን በፖለቲካዊ መፍትሔ የመቋጨት ባህል አምጥቷል ሲል ገልጿል።

የሰላም ስምምነቱ ለትውልድ የአሸናፊ ተሸናፊ ትርክትን ከቂም ጋር ላለማውረስ የተደረገ ውሳኔ እንደሆነ ገልጿል።

የሰላም ስምምነቱ እስካሁን ብዙ ውጤት እና እፎይታ ቢያስገኝም ቀሪ ሥራዎችም አሉ ብሏል።

በተለይ በስምምነቱ መሠረት " የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው " ሲል ገልጿል።

የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች ጉዳይ እልባት ለመስጠት እንዲቻል የተቀመጠው አቅጣጫ ተግባራዊ መደረግ አለበት ብሏል።

" ካለፈ ስሕተተ አለመማር የመጀመሪያውን ስሕተት ከመሥራት የባሰ ነው " ያለው ም/ቤቱ፤ ካለፈው ስሕተታቸው ሳይማሩ ዛሬም ተመሳሳይ ችግር ለመፍጠር የሚከጅሉ አሉ ሲል ጠቁሟል።

እነዚህን ሁሉም ተባብሮ አደብ ማስገዛት ይኖርበታል ብሏል።

" ከትዕግሥት በኋላ የሚከሠት ሕግ የማስከበር ሥራ የሚኖረውን አስከፊ ውጤት ከቅርቡ ታሪካችን ልንማር ይገባል" ሲል አሳስቧል።

ም/ቤቱ፤ መንግሥት በትግራይ ክልል ብዙ ርቄት ሄዶ ቁስልን ለመሻር የሚያስችል ሥራ እየሠራ እንደሆነ ገልጿል።

" ይሄ ግን መንግሥታዊ ኃላፊነት እንጂ ፍርሃት ተደርጎ መወሰድ የለበትም " ብሏል።

" በፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነትና በሕገ መንግሥቱ መሰረት እንደ ሀገር የሚኖረው አንድ የመከላከያ ሠራዊት ብቻ ነው ክልሎች በክልል ከፖሊስ እና ሚሊሺያ ያለፈ የታጠቀና የተደራጀ ሠራዊት ሊኖራቸው አይችልም፤ አይገባምም " ብሏል።

በዚህ መሠረት ትጥቅ መፍታትና ተያያዥ ሂደቶች በተሐድሶ ኮሚሽኑ ዕቅድ መሠረት በፍጥነት ሊተገበሩ እንደሚገባ አሳስቧል።

ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-04-24

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ተፈናቃዮችን ወደ ቤታቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ ነው ፤ ይህም ይቀጥላል " - የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት

የብሔራዉ የደኅንነት ምክር ቤት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ባጋጠመ ግጭት፤ እንዲሁም በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ባጋጠሙ የጸጥታ ችግሮች የተነሣ የተፈናቀሉ ዜጎች እንዳሉ ገልጿል።

" እነዚህ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ እየሠራን ነው " ብሏል።

" የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል አመራሮች በጋራ ሠርተው ብዙዎችን ከመጠለያ ጣቢያ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ተደርጓል " ሲልም ገልጿል።

" በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል፤ #በራያ እና #አላማጣ አካባቢ ከተፈናቀሉ ዜጎች መንግሥትን ሳይጠብቁ በማኅበረሰባዊ መተሳሰብ ብቻ በርካታዎች ወደ ቤታቸው እየገቡ ነው " ሲል አመልክቷል።

በዚህ ሂደት " የተፈናቃዮችን ጉዳይ እንደ ፖለቲካ አጀንዳ አድርገው ሊጠቀሙ የሚፈልጉ አካላት መኖራቸው ታይቷል " ብሏል።

ም/ቤቱ እነዚህ ኃይሎች እነማን እንደሆኑ በግልጽ በስም ጠርቶ ባይገልጽም " ተፈናቃዮቹ ወደ ቤታቸው እንዳይመለሱ ፕሮፖጋንዳና ማስፈራሪያ ይደረድራሉ " ብሏል።

" አንዳንዴም #በኃይል ጭምር የተፈናቃዮችን መመለስ ለማሰናከል ይቃጣቸዋል። " ሲል ገልጿል።

" መንግሥት ካለበት የሞራል እና የሕግ ኃላፊነት የተነሣ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቤታቸውና ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ይቀጥላል " ሲል አሳውቋል።

https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/87168?single

@tikvahethiopia
#ቱርክ #ሶማሊያ

ሶማሊያ እና ቱርክ የካቲት 1/2016 በተለያዩ ወታደራዊ ዘርፎች ትብብር ለማድረግ ስምምነት መፈራረማቸውን ይታወሳል።

ይህንን ስምምነት ተከትሎ የቱርክ ባሕር ኃይል የጦር መርከብ ሞቃዲሾ ወደብ መድረሷን ቢቢሲ ዘግቧል።

የሁለቱ ሀገራት ስምምነት ዝርዝር ይፋ ባይሆንም ቱርክ የሶማሊያን ባሕር ኃይልን #ለማሠልጣን እና #ለማስታጠቅ እንዲሁም በአካባቢው ያለውን የባሕር ላይ ደኅንነት ለማስጠበቅ ተስማምታለች ተብሏል።

በአንጻሩ ቱርክ ከሶማሊያ የባሕር የተፈጥሮ ሃብት ተጠቃሚ እንደምትሆን ሪፖርቶች ይጠቁማሉ።

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

መልካሙን ዜና ከሳፋሪኮም ሰምተዋል?!

🎁ዕለታዊ የዳታ ጥቅል ስንገዛ ቀኑን ሙሉ፣ ሳምንታዊ የዳታ ጥቅል ስንገዛ ሳምንቱን በሙሉ እንዲሁም ወርሃዊ የዳታ ጥቅል በምግዛት ወሩን ሙሉ ከሳፋሪኮም ወደ ሳፋሪኮም መስመር በነጻ እንደዋወል!

ዳታ እንግዛ! በነጻ እንደዋወል!

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ትክክለኛ መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት ቀጥሎ በሚገኙት ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲከታተሉ  እንጋብዛለን።

👉 Facebook

👉Telegram

👉 Twitter

👉Instagram

👉 YouTube
“ ገዳሙ በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛል ” - አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም

አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም በዙራያው በሰፈሩ ሰዎች የታዘ መሬቱን ለማስመለስ የካሳ ክፍያ መጠየቁን አስታወቀ።

በአማራ ክልል የሚገኘው ገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም ከ30,000 እስከ 50,000 የሚሆኑ ፀበልተኞች እንደሚጸበሉበት ይሁን እንጂ የገዳሙ መሬት ሰዎች ስለሰፈሩበት እንኳን ለጸበልተኞች ለመነኮሳቱም እጅግ በመጣበቡ፣ “ ገዳሙ በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛል ” ተብሏል።

የገዳሙ ይዞታ የጠበበው ከበርካታ ዓመታት ጀምሮ ለመፈወስ ወደ ስፍራው የሚሄዱ ፈውስ ያገኙ ጸበልተኞችና አርሶአደሮች ከሕመማቸው ከተፈወሱ በኋላ በገዳሙ መሬት ቤት እየሰሩ እዚያው በመኖራቸው መሆኑን የገዳሙ መነኮሳት አስረድተዋል።

ሰዎቹ በአንዴ ሳይሆን ቀስ በቀስ እዛው መኖር እንደጀመሩ ጠቁሟል።
 
በገዳሙ ይዞታ የሰፈሩ ከ250 በላይ አባውራዎች ይነሱ ዘንድ ለጠየቁት ካሳና ለሌሎች አገልግሎቶች ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ አሳውቋል።

ለዚህም ሚያዚያ 19/2016 ዓ/ም በካፒታል ሆቴል የገቢ ማሰባሰብ መርሀ ግብር እንደተዘጋጀ፣ በመሆኑም በውስጥም በውጪ ያሉ ኢትዮጵያዊያን እርብርብ እንዲያደርጉ ገዳሙ ጥሪ አቅርቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ቀብሪደሃር

ከፊታችን ሚያዚያ 25 ቀን 2016 ጀምሮ ወደ ሶማሌ ክልል #ቀብሪደሃር ከተማ በሳምንት ሁለት ቀን የበረራ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።

አየር መንገዱ በሶማሌ ክልል ከጅግጅጋና ጎዴ ቀጥሎ #ቀብሪደሃር ሶስተኛው መዳረሻው ይሆናል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ድንጋይ እና አፈር ተደርምሶ የ7 ሰዎች ሕይወት አፏል።

አደጋው የደረሰው በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ወረዳ 12 " ጠሮ መስጂድ " አካባቢ ነው።

ለሊት 11 ሰዓት ገደማ ለቤት ግንባታ የተከመረ ድንጋይ እና አፈር ከላይ ወደ ታች (ወደ ቤቱ) ተንዶ 3 ክፍል ያለው ቤት ላይ አደጋ ደርሷል።

በዚህም ቤት ውስጥ ተኝተው የነበሩ 7 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

ሟቾቹ ፦
የ4 ዓመት ህጻን ፣
ሶስት የ11 እና የ12 ዓመት ታዳጊዎች 
ከ25 እስከ 30 ዓመት ያሉ 3 ወጣቶች ናቸው።

ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች የሁለት ቤተሰብ አባላት እንደሆኑ ታውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ አደጋው የደረሰበት ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ ምርመራ ላይ ነው።

መረጃው የአዲስ አበባ እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ነው።

@tikvahethiopia