TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአለታ ወንዶ፣ ሀገረ ሰላም፣ ይርጋለም ከተሞች ዛሬም #ሁከት#ዘረፋ እና የንብረት #ውድመት መታየቱንና በርካቶችም መታሰራቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡ ሀዋሳ ዛሬ ተረጋግታ ውላለች።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከትግራይ ህዝብ ጋር ተከባብረን የምንኖርበት እንጂ ለጦርነትና እልቂት የምንፈላለግበት ጉዳይ ሊኖር አይገባም " - ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት የአማራ ክልል መንግስት በመደበው በጀት በጦርነት ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የወደሙ መሰረታዊ አገልግሎት መስጫ ፕሮጀክቶች መልሶ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ዛሬ በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ እየተካሄደ እንደሚገኝ የብሄራዊ ቴሌቪዥን…
#Amhara

ዛሬ በአማራ ክልል፣ ሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ እየተካሄደ ባለ የመልሶ ግንባታ ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ስዩም መኮንን የተናገሩት ፦

- በጦርነቱ ከደረሰው ሰብአዊ ጉዳት ባሻገር 👉 291 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ቁሳዊ #ውድመት መድረሱ በጥናት መረጋገጡን ተናግረዋል።

- በክልሉ የደረሰውን ውድመት መልሶ ለማቋቋም የክልሉ መንግሥት የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ፅ/ ቤት አቋቁሞ እየሰራ መሆኑ ገልፀዋል።

- ዛሬ የመልሶ ግንባታ የማስጀመሪያ መርሀግብር እየተካሄደ በሚገኝበት ራያ ቆቦ ወረዳ ብቻ ወደ 👉 9 ቢሊዮን ብር የሚገመት #ውድመት መድረሱም ጠቁመዋል።

- በዚህ አመት ብቻ 12 ቢሊዮን ብር በማሰባሰብ የመልሶ ግንባታ ለማከናወን የታቀደ ሲሆን የክልሉ መንግስት ለዚሁ ስራ 1 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አሳውቀዋል።

- ሶስት ሺህ (3000) የግለሰብ መኖሪያ ቤቶች፣ 21 ትምህርት ቤቶች፣ 10 ጤና ጣቢያዎች፣ 1 ሆስፒታል፣ 31 የንፁህ መጠጥ ውሀ ተቋማትና ሌሎችም ፕሮጀክቶች እንደሚገነቡ ገልጸዋል።

- ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት ለመልሶ  ግንባታው የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ካሰራጨው ዘገባ የተወሰደ።

(በጦርነት የወደመው ህንፃ ፎቶ - ፋይል)

@tikvahethiopia
#AxumUniversity

አክሱም ዩኒቨርስቲ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሳቢያ የደረሰበት ጉዳት 15 ቢሊዮን ብር እንደሚገመት ማስታወቁን " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።

ላለፉት 19 ወራት ትምህርት መስጠት አቁሞ የቆየው ዩኒቨርስቲው፤  ሊያከናውነው ላቀደው ዳግም ግንባታ የድጋፍ ጥሪ አቅርቧል።

የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ገብረእየሱስ ብርሃነ የሰጡት ቃል ፦

- ዩኒቨርስቲው በጦርነቱ ሳቢያ በደረሰበት #ውድመት እና #ዘረፋ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር የሚያስችሉት ቁሳቁሶች እና መሳሪያዎች አጥቷል።

- ሙሉ ለሙሉ የተዘረፉ እና ከወደሙ የዩኒቨርስቲው ንብረቶች ውስጥ ኮምፒውተሮች፣ የላብራቶሪ መሳሪያዎች፣ ሰርቨሮች እና የቢሮ በሮች ይገኙበታል።

- ዩኒቨርስቲው ከጦርነቱ በፊት የነበሩት 60 ገደማ ተሽከርካሪዎች ተዘርፈው እና ተቃጥለው አሁን በስራ ላይ የሚገኘው #አንድ_መኪና ብቻ ነው።

- በጥር ወር ላይ በተደረገ ዳሰሳ የደረሰው ውድመት 15 ቢሊዮን ብር ይደርሳል።

- ጉዳት የደረሰባቸውን ንብረቶች በተወሰነ መልኩ በመተካት ወደ ስራ ለመግባት ታቅዷል።

- ለሚያከናውነው ዳግም ግንባታ እና ጥገና ስራ የገንዘብ እና የማቴሪያል ድጋፍ እንዲደረግልን  ጠይቀናል። የድጋፍ ጥሪው ለዓለም አቀፍ እና ለሀገር በቀል አጋር ድርጅቶች፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ነው።

- ዩኒቨርስቲው የሚያገኘውን ድጋፍ በፌደራል መንግስት ከሚመደበለት በጀት ጋር በማጣመር በአጭር ጊዜ ውስጥ የመማር ማስተማር አገልግሎቱን ለመስጠት ታቅዷል። 

- ቁሳቁሶችን በተወሰነ መልክ ቅድሚያ እየሰጠን ካስገባን፤ የግዢ ሂደቱ ፈጣን ከሆነ፤ ተማሪዎችን #በሶስት_ወር ውስጥ ማስገባት እንችላለን። በትግራይ ክልል የሚኖሩ እና ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት ያቋረጡ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን ትምህርት ማስጨረስ ላይ ትኩረት ይደረጋል።

አክሱም ዩኒቨርሲቲ እስካሁን ከፌደራል መንግስት በጀት ባይለቀቅለትም፤ በስሩ ለሚገኘው የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 43 መምህራንን ለመቅጠር ከ2 ሳምንት በፊት ማስታወቂያ አውጥቷል።

የቅጥር ሂደቱ የሚፈጸመው በትምህርት ሚኒስቴር ተፈቅዶ፣ በጀት ሲለቀቅ መሆኑ ተገልጿል።

ከፌደራል መንግስት የሚለቀቀው በጀት፤ ለዩኒቨርስቲው ሰራተኞች ደመወዝ ለመክፈል እና ትምህርት ለማስጀመር ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

#አራት_ሺህ ገደማ የሚሆኑት የዩኒቨርስቲው መምህራን እና ሰራተኞች ከሐምሌ 2013  ዓ.ም. ወር ጀምሮ #ደመወዝ_አለማግኘታቸውን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል።

Credit : www.ethiopianInsider.com

@tikvahethiopia
" ዳግም #ሞት እና #ውድመት ውስጥ መግባቱ ይቅርብን " - የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ፤ በሀገራችን እየተካሄደ ያለው ጦርነት ባስቸኳይ እንዲቆምና ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ ተማጸነ።

" ዳግም ሞት እና ውድመት ውስጥ መግባቱ ይቅርብን " ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

ጉባኤው በላከልን መግለጫ ጦርነት ለየትኛውም አይነት የፖለቲካዊ ችግር መፍትሔ ሆኖ አያውቅም ብሏል።

" ፖለቲካዊ ችግር መፈታት ያለበት መከባበር ባለበት የጋራ ጥቅም በሚያስቀድም ሁኔታ በሚደረግ የፖለቲካ ውይይት ነው " ያለው ጉባኤው ፤ " ውይይቱ ፦
- ብሶት የወለዳቸውን ምሁራንን፣
- የሀገር ሽማግሌዎችን፣
- የሃይማኖት አባቶችን፣
- ወጣቶችን እና ሴቶችን ጭምር ያካተተ ቢሆን የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን ሙሉ እምነታችን ነው " ሲል ገልጿል።

ይህ እንዲሆን የመንግሥት #የፖለቲካ_ፈቃደኝነት በጣም አስፈላጊ እንደሚሆን አመልክቷል።

ምክንያቱም " መንግስት ከሁሉም በላይ እኛ በብዙ መልኩ ወንድማማችና እህትማማች የሆነውን ኢትዮጵያውያንን በጋራ የማምጣት አቅም አለው ብለን ስለምናምን ነው " ሲል ገልጿል።

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ በዚሁ መግለጫው ፤ በሀገራችን እየተካሄደ ያለው ጦርነት ባስቸኳይ እንዲቆምና በውይይት ችግሮች እንዲፈቱ መንግስትንና ተፋላሚ ወገኖችን አጥብቆ ተማጽኗል።

" በዚህ በፍልሰታ ጾም ጸሎት ወቅት ልቦናችንን ወደ እግዚአብሔር እንድንመልስ ፤ ስለ ሰላም ፣ ፍትህ፣ ውይይት እንድንጸልይ ለምዕመኖቻችንና በጎ ፊቃድ ላላቸው ወገኖቻችን ሁሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን " ብሏል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia