TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ግድያውን የፈፀመው የፖሊስ አባል ነው " - የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

በአዲስ አበባ ከተማ ፤ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አባቸው አሞኜ የእለት ከእለት ተግባራቸውን በማከናወን ላይ እንዳሉ ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ/ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ #በፖሊስ አባል መገደላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳወቀ።

ግድያውን የፈፀመው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የካሳንቺስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የቀጠና ኦፊሰር የሆነ አባል መሆኑን ፓሊስ ገልጿል።

እንደ ፖሊስ መረጃ ግድያውን የፈፀመው ግለሰብ ፤ የግል ጉዳዩ እንዲፈፀምለት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ  ለወረዳ 8 አስተዳደር ጽ/ቤት ያመለክታል፡፡

ወረዳው ጉዳዩን ተመልክቶ ምላሽ እንደሚሰጠው የተገለፀለት ቢሆንም " ጥያቄዬ እንዳይፈፀም የከለከልከው አንተነህ " በሚል ምክንያት የወረዳውን ዋና ስራ አስፈፃሚ ቢሯቸው ውስጥ በስራ ላይ እንዳሉ በታጠቀው ሽጉጥ ገድሏቸዋል።

ወንጀሉን የፈፀመው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" ኮንስታብል ማክቤል ሮባ የተባለ የፖሊስ አባል ለስራ በታጠቀው ታጣፊ ክላሽ በተኮሰው ጥይት ነው የዶ/ር እስራኤል ጥላሁን ህይወት ያለፈው " - ፖሊስ

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ዶ/ር እስራኤል ጥላሁን የተባለ የጤና ባለሞያ በተተኮሰበት ጥይት ተመቶ #ተገድሏል

ግድያው የተፈፀመው #በፖሊስ_አባል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።

ፖሊስ ስለጉዳዩ ምን አለ ?

የአዲስ አበባ ፖሊስ ሰሞኑን " ቦሌ አትላስ " አካባቢ ዶ/ር እስራኤል ጥላሁን በተባለ ግለሰብ ላይ ተፈፅሟል ከተባለው የግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል።

ፖሊስ ምርመራ መዝገቡን ዋቢ አድርጎ እንዳስረዳው በቀን 28/3/2016 ዓ.ም ከንጋቱ 11:20 ሰአት ላይ ነው ዶ/ር እስራኤል ጥላሁን ወንጀሉ የተፈጸመበት።

ወንጀሉ የተፈፀመው ወረዳ 4 ልዩ ስሙ " አዲስ ህይወት ሆስፒታል " አካባቢ ነው ብሏል።

ዶክተር እስራኤል ያሽከረክራት የነበረችው ተሽከርካሪ ኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥር 36734 አ.አ ሲሆን፤ በወቅቱ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥር 28177 የሆነ #ቪትስ ተሽከርካሪ የያዘ ግለሰብ የመኪና " መስታወት - ስፖኪዮ ገጭቶ አመለጠኝ " በሚል ከፍተኛ ድምጽ እያሰማ ከኋላ ይከተለው ነበር፡፡

ወደ 11፡20 አካባቢም " ፋሲካ የመኪና መሸጫ " የሚባል ቦታ ሲደርስ፤ በአካባቢው ያሉ ኑሯቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ዜጎች " ያዘው ያዘው " የሚል ድምጽ በማሰማት ከፍተኛ ግርግርና ወከባ ሲፈጥሩ፤ በዚያን ሰአት #ኮንስታብል_ማክቤል_ሮባ የተባለ የፖሊስ አባል፤ ለስራ በታጠቀው ታጣፊ ክላሽ " የመኪናውን ጎማውን መትቼ ለማስቆም " በሚል በተኮሰው ጥይት የዶ/ር እስራኤል ህይወት ሊያልፍ ችሏል ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስረድቷል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ አንዳንድ ግዜ ወዲያውኑ መረጃ የማይሰጠው #ከምርመራ_ሂደቱ ጋር በተያያዘ የሚበላሹ ነገሮች ስለሚኖሩ ነው ያለ ሲሆን ቀጣይ የምርመራ መዝገቡ እየታየ መረጃዎችን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የትርታ ኤፍ ኤም 97.6 ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ መሆኑን ያሳውቃል።

* በጉዳዩ ላይ ከሟች ቤተሰቦች / ከቅርብ ጓደኞች መረጃ የሚገኝ ከሆነ ተከታትለን እናቀርባለን።

@tikvahethiopia