TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#አስቸኳይ “ አጋቾቹ ወደ ታች ዘቅዝቀው እየገረፉት ቪዲዮ ላኩልኝ። ‘1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን #ገድለን ቪዲዮ እንልክልሻለን’ አሉኝ ” - የታጋች እናት በሊቢያ ደላሎች የታገተው የሀዋሳው ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ወጣት ጌድዮ ሳሙኤል፣ በአጋቾቹ ልዩ ልዩ ድብደባዎች እየተፈጸሙበት እንደሚገኝ ፣ አጋቾቹ ወጣቱን ለመልቀቅ 1.7 ሚሊዮን ብር እንደጠየቁ፣ ገንዘቡ በፍጥነት ካልገባ “ እንገድለዋለን ”…
“አጋቾቹ እያሰቃዩት ነው። ዱብ እዳ ወረደብኝ። ወደ 950 ሺሕ ጠይቀዋል። ልጄ ‘በአንድ መጋዘን ወደ 200 ሰዎች ታጎርን’ ነው የሚለው ” - የታጋች አባት

በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ካሜራ ማን ሆኖ ሲሰራ ነበር የተባለው ወጣት አብርሃም አማረ #በሊቢያ በአጋቾች #ታግቶ በየቀኑ ስቃይ እየደረሰበት መሆኑን ፣ አጋቾቹ ታጋቹን ወጣት ለመልቀቅ 950 ሺሕ ብር እንደጠየቁ፣ ይህን ገንዘብ ማሟላት እንዳልተቻለ የታጋች አባት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የታጋች አባት አቶ አማረ ዓለም ገረመው ምን አሉ ?

- “ አጋቸቹ እያሰቃዩት ነው። ዱብ እዳ ወረደብኝ። ወደ 950 ሺሕ ተጠይቀዋል። ልጄ ‘ከአንድ መጋዘን ወደ 200 ሰዎች ታጎርን’ ነው የሚለው። እኛ ኑሯችን ዝቅተኛ ነው። ፈተና ላይ ነኝ። ምን አይነት ደላላ አታሎ እንደወሰደው ፈጣሪ ይወቅ። ”

- “ ሌሎችም ታጋቾች ‘ነፍስ ውጪ የፍስ ግቢ፣ ስቃይ’ ላይ እንደሆኑ ልጄ ነግሮኛል። ”

- “ በጥቅም የተሳሰረ ምን አይነተ ጊዜ ላይ እንደደረስን ፈጣሪ ይወቅ። ልጄ በዚህ ደረጃ ላይ ይጠብቀኛል ብዬ አላሰብኩም ነበር። ”

-  “ አጋቾቹ ገንዘቡን በፍጥነት አስተላልፉ እያሉ እያጣደፏን ነው። እስካሁን ወደ 450 ሺሕ ብር ቢገኝም ቀሪው 500 ሺሕ ብር ገና አልተሟላም እየታገልኩ ነው። ”

-  “ ልጄ ለዚህ እገታ የተዳረገው፣ ሕይወቱን ለማሻሻል ወደ ሌላ አገር እየሄደ ሊቢያ ሲደርስ ነው። ”

-  “ ከዚህ በፊት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ይከታተል የነበረ ቢሆንም በኮረና ወቅት እንደተቋረጠ፣ በዚህም አጋጣሚ ካሜራ ማን ሰልጥኖ በተለያዩ ተቋማት ተቀጥሮ 1,000 ብር እየተከፈለው ይሰራ ነበር። ”

-  “ ዲግሪውን በግል እንዲማር እየጎተጎትኩት ነበር። ሆኖም ግን በደላሎች ተታሎ አሁን እሱም በስቃይ፣ ቤተሰብን በጭንቀት ላይ ወድቋል። ”

- “ አጋቾቹ ቀረጻውን ይልካሉ፣ የሱን ግን ድምጹን ነው የሚያሰሙኝ። ‘ስቃይ ነው እስከ 2 ወራት ታግተው የቆዩት በየቀኑ ነው የሚገረፉት ብር አምጡ እየተባሉ’ ብሏል። ”

የታጋች አባት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አሁንም ፦
- የዓለም ባንክ፣
- የቄራና የሌሎች አካባቢ ወጣቶች በህገወጥ መንገድ ወደ ውጪ እየሄዱ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ይህ ደግሞ ለወጣቶቹም ለወላጅም፣ ለአገርም ፈተና ስለሆነ ትኩረት እንዲሰጠው መክረዋል።

“ ይሄ ነገር ይገጥመኛል ብዬ አልጠበኩም። ” ያሉት አባት አቶ አማረ “ ልጆቼ እንዳይርባቸው፣ እንዳይጠማቸው፣ ከቁም ነገር እንዲደርሱ ነበር የምጥረው። አቅም ያላችሁ ሁሉ እርዳታ አድርጉልኝ ” ሲሉ ተማጽነዋል።

+251911388792 የታጋቹ አባት አቶ አማረ ዓለም ገረመውን በዚህ ስልክ ማግኘት ይቻላል። መርዳት ለምትፈልጉ 1000030178638 አቶ አማረ ዓለም ገረመው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፥ ከትላንትና በስቲያ #በሊቢያ ደላሎች የታገተ የሀዋሳ ከተማ ተወላጅ ወጣት ጌድዮ ሳሙኤል፣ በአጋቾቹ ልዩ ልዩ ድብደባዎች እየተፈጸሙበት እንደሚገኝ ፣ አጋቾቹ ወጣቱን ለመልቀቅ 1.7 ሚሊዮን ብር እንደጠየቁ፣ ገንዘቡ በፍጥነት ካልገባ “ #እንገድለዋለን ” በማለት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደሰጡ የታጋችን እናት በማነጋገር መረጃ እንደላከላችሁ ይታወሳል።
 
መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ  ነው።

@tikvahethiopia
#DStv

🔥ደማቁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወደ ሜዳ ተመልስዋል🔥

🏆አስተማሪው ከ ተማሪው ጋርለዓመቱ የመጨረሻ ጊዜ ይገናኛሉ!

👉ዛሬ እሁድ መጋቢት 22 ከምሽቱ 12፡30 ሰዓት ማን ሲቲ ከ አርሰናል በኢትሃድ ስታዲየም የሚያረጉትን እስገራሚ ፍልሚያ በቀጥታ በSSPremier League እና በSS Liyu ቻናል በቀጥታ ይከታተሉ!

👉 መድፈኞቹ 3 ነጥብይዛው የሊጉን መሪነታቸውን ይቀጥላሉ?

🎉ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃትእስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ይከታተሉ!
🎉ከጥር 6 እስከ መጋቢት 22 ደንበኝነትዎን ሲያሳድጉ... እኛም ቀጣዩን ፓኬጅ ለአንድ ወር እንጋብዝዎታለን!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ! https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#PremierLeagueAllonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET #StepUp
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሶማሌክልል በሶማሌ ክልል በተከሰተው የጎርፍ አደጋ እስካሁን 28 ሰዎች ሲሞቱ ከ300,000 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተጠቆመ። በሶማሌ ክልል ከ33 ወረዳዎች በላይ ተከሰተ የተባለውን የጎርፍ አደጋ በተመለከተ ተጎጂዎችና ተፈናቃዮች በምን ሁኔታ እንደሚገኙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቦታው እርዳታ እያደረገ የሚገኘውን Save the Childrenን ጠይቋል። የድርጅቱ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ አብዲራዛቅ…
“ ከተጎጂዎች መካከል 30,427 ህፃናት ናቸው። የሟቾች ቁጥር ከ40 በላይ ደርሷል ” - ሴቭ ዘ ቺልድረን

በሶማሌ ክልል ከተከሰተ የወራት ያለፈው የጎርፍ አደጋ የውሃ መጠኑ እየቀነሰ የመጣ ቢሆንም ትንበያዎች የሚያመለክቱት በመጪው የዝናብ ወቅት ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንዲሚችል ስለሆነ፣ ህብረተሰቡም አሁንም ካለፈው የጎርፍ አደጋ ገና እያገገመ በመሆኑ፣ ትልቅ ፈተናና ስጋት መፍጠሩን በቦታው የሚገኘው የህፃና አድን አድን ድርጅት (Save the children) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

የድርጅቱ ሶማሌ ክልል ምሥራቅ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ አብዲራዛቅ አህመድ ምን አሉ ?

- “ ጎርፉ ከቀነሰ በኋላ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ። በሚመለሱ ጊዜ ግን ቤታቸውን ለመጠገን፣ እንደገና ለመገንባት፣ ቁሳቁሶችን ለማሟላት ድጋፍ ይፈልጋሉ። ሆኖም ይህ ድጋፍ በሚፈለገው መጠን አልተሰጠም። ”

- “ በክልሉ በጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ40 በላይ ደርሷል። ” (ከወራት በፊት የሟቾች ቁጥር 23 እንደነበር ይታወሳል)

- “ አደጋው በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን አፈናቅሏል። በሶማሌ ክልል ብቻ ከ1,000,000 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል። 400,000 የሚሆኑ ተፈናቅለዋል። ”

- “ በተለይ የሸበሌ ዞን ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን፣ በዞኑ የሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች ከሞላ ጎደል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ”

- “ በጎርፍ አደጋው ላይ በተደረገው የጋራ ዳሰሳ ፦ 84, 800 አባውራዎች (490, 000 ሰዎች) ተጎድተዋል። ከእነዚህም መካከል 34, 441 የሚሆኑ አባውራዎች (206, 646 ሰዎች) በሸበሌ ዞን በሚገኙ 8 ወረዳዎች ተፈናቅለዋል። ከተጎጂዎች መካከል 49, 430 ሴቶች፣ 30, 427 ህጻናት እና 25, 253 አረጋውያን ናቸው። ”

- “ ከብቶች በጎርፍ አደጋው በጣም ተጎድተዋል፣ እንደሚታወቀው ለበርካታ ተጎጂ ማህበረሰቦች ወሳኝ የገቢ ምንጭ ናቸው። በጎርፉ አደጋው ከ19, 822 በላይ እንስሳት ሞተዋል። መተዳደሪያቸው የነበረ ከ94,000 ሄክታር በላይ የሚሸፍን ሰብልም ወድሟል። በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ሙሉና በከፊል ወድመዋል። ”

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-03-31

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስቴር በንግድ ማዕከልነት የሚያገለግሉ ሕንፃዎችን በጋራ ገንብተው በባለቤትነት የሚያስተዳድሩ አክሲዮን ማኅበራት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የዲቪደንድ (የትርፍ ድርሻ) ታክስን ጨምሮ የተለያዩ የግብር ዓይነቶችን እንዲከፍሉ ወስኗል።

በንግድ ማዕከልነት የሚያገለግሉ ሕንፃዎችን ገንብተው በባለቤትነት የሚያስተዳድሩ አክሲዮን ማኅበራት የሕንፃውን ሱቆች በማከራየት ከሚያገኙት ገቢ ላይ ለሚገኙበት ከተማ ወይም የአካባቢ አስተዳደር የኪራይ ገቢ ግብር ብቻ ሲከፍሉ ቆይተዋል።

ሚኒስቴሩ በአክሲዮን ማኅበራት ባለቤትነት ሥር የሚገኙና የሚተዳደሩ የንግድ ማዕከላት ላይ ጥናት ያካሄደ ሲሆን የጥናቱ ግኝትም ፣ አክሲዮን ማኅበራቱ በሕግ የተጣለባቸውን ግብር በተገቢው መንገድ እየተወጡ አለመሆናቸው ያረጋገጠ ነው ተብሏል።

ገቢዎች ሚኒስቴር በጥናት የደረሰባቸውን ግኝቶች መሠረት በማድረግ ሊወሰዱ ይገባል ያላቸውን የማስተካከያ ዕርምጃዎች የተመለከተ ምክረ ሐሳብ ለመንግሥት አቅርቦ በቅርቡ ተቀባይነት ማግኘቱ ተጠቁሟል።

በዚህም መሠረት ፥ በአክሲዮን ተደራጅተው የተገነቡና በንግድ ማዕከልነት የሚያገለግሉ ሕንፃዎች ባለቤት አክሲዮን ማኅበሩ በመሆኑ፣ የንግድ ማዕከሉን የሚመለከቱ የግብር ግዴታዎች ላይ ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ እንዳለበት ተወስኗል።

በመሆኑም በንግድ ማዕከልነት በሚያገለግለው ሕንፃ ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን በማከራየት የሚገኘው ገቢ ላይ በግብር አዋጁ መሠረት የሚጣለውን የኪራይ ገቢ ግብር እንደ ከዚህ ቀደሙ በከተማ አስተዳደሮች እንደሚሰበሰብ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

ይሁን እንጂ ሚኒስቴሩ ባካሄደው ጥናት አክሲዮን ማኅበራቱ በሚያስተዳድሯቸው የንግድ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙ የንግድ ሱቆች ኪራይ ተመን ፦
- ከወቅታዊ ገበያው በእጅጉ አነስተኛ መሆኑ፣
- በርከት ያሉ ማኅበራትም በንግድ ማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን በርካሽ ዋጋ ለማኅበሩ አባላት እንዳከራዩ ፣
- ሌሎች በርከት ያሉ አክሲዮን ማኅበራት ደግሞ የባለቤትነት ማስተላለፍ ሥርዓቶችን ሳይከተሉ በንግድ ማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን እንደ አክሲዮን ድርሻ ለማኅበሩ አባላት አከፋፍለው መገኘታቸው ተመላክቷል።

በመሆኑም ፣ ከ2016 ዓ.ም. የግብር መክፈያ ወቅት ጀምሮ በንግድ ማዕከላቱ ውስጥ የሚገኙ ሱቆች የኪራይ ተመን በገበያ ዋጋ ተሰልቶ የኪራይ ገቢ ግብር እንዲከፍሉ መወሰኑን ሪፖርተር ጋዜጣ ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘውን መረጃ ዋቢ በማድረግ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#CBE የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምን አለ ? መጋቢት 7 / 2016 ዓ/ም ባጋጠመው የሲስተም ችግር ምክንያት ያለአግባብ የገንዘብ ልውውጥ እንደነበር ፤ በዚህም በርካታ ግለሰቦች በጥሬ ገንዘብ እንዲሁም በዲጂታል የክፍያ አማራጮች የወሰዱትን የገንዘብ ልክ እየመለሱ እንደሆነ ገልጿል።  ነገር ግን አንዳንድ ግለሰቦች የወሰዱትን ገንዘብ ወደ #ቤቲንግ (የስፖርት ውርርድ) ተቋማት በማዛወራቸው መመለስ እንደተቸገሩ…
" የመጨረሻ ተጨማሪ 3 ቀን ሰጥተናል " - ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 222 ግለሰቦች እስካሁን የወሰዱትን ገንዘብ መመልስ እንዳለጀመሩና እነዚህ ግለሰቦች ጋር ያለው ገንዘብ 4,034,979 ብር ከ75 ሳንቲም መሆኑን ገልጿል።

ባንኩ አሁንም ገንዘብ ተመላሽ ለማድረግ የመጨረሻ የ3 ቀናት ስለመስጡትን አሳውቋል።

ባንኩ ከዚህ ቀደም ሙሉ በሙሉና በከፊል ገንዘብ ያለመለሱ እንዲመልሱ 2 ጊዜ የመጨረሻ ያለውን ቀነ ገደብ አስቀምጦ እንደነበር ይታወሳል። የስም ዝርዝርም ይፋ አድርጎ ነበር።

ባንኩ አስተላልፎ የነበረውን ጥሪ ተከትሎ ፦

ያለ አግባብ ከተወሰደው ገንዘብ ውስጥ ከባለፈው ሳምንት ተጨማሪ ብር 117,612,000 ብር ከ59 ሳንቲም በመሰብሰቡ የተከፈለ አጠቃላይ ገንዘብ 86% መድረሱን እና ያልተመለሰ ገንዘብ ወደ ብር 112,389,455 ብር ከ12 ሳንቲም ዝቅ ማለቱን ገልጿል።

ያለባቸውን ገንዘብ አጠናቀው ክፍያ የጨረሱ ግለሰቦች ቁጥር ወደ 10,857 ከፍ ማለቱን ገልጿል።

የወሰዱትን ገንዘብ መመለስ ያልጀመሩ ግለሰቦች ቁጥር ወደ 222 ዝቅ እንዳለና ከነዚህ ግለሰቦች የሚጠበቅ ገንዘብም ወደ ብር 4,034,979 ብር ከ75 ሳንቲም ዝቅ ማለቱን ጠቁሟል።

ባንኩ ፥ አንድ አንድ ግለሰቦች ወደ ተለያዩ ተቋማት ያስተላለፉትን ገንዘብ ተመላሽ ለማድረግ ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጣቸው ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑን ገልጿል።

ይህ ተከትሎ ከነገ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ተጨማሪ 3 ተከታታይ ቀናት እንደተሰጠ አሳውቋል።

ባንኩ ፤ የወሰዱትን ገንዘብ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ  ወደ ከፈቱት የዲጂታል ሒሳቦች አስተላልፈው አሁን ላይ ወደ ባንኩ ለመመለስ የተቸገሩ ግለሰቦችም ካሉ ወደ ማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፎች ቀርበው ዝርዝር ሁኔታውን እንዲያሳውቁ ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ታዳጊዋ የት ናት ? በትግራይ ዓድዋ ከተማ የታገተችውና ለማስለቀቅ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባት ታዳጊዋ ማህሌት ተኽላይ እስካሁን እንዳልተገኘች እና ድምጿም እንዳልተሰማ ቤተሰቦቿ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። እገታው ከተፈፀመ 7 ቀናት ሆኖታል። የ16 አመቷ ታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ መጋቢት 11 ባጃጅ ይዘው በመጡ ' ማንነታቸው አልታወቀም ' በተባሉ ሰዎች ታፍና ከተወሰደች በኃላ በራሷ ስልክ ለአባቷ…
#ትግራይ

ታጋቹ ከ3 ወር መሰወር በኃላ የማስለቀቂያ ክፍያ ተጠየቀባቸው። 

"አጋቾች ነን" ባዮች የጠየቁት ገንዘብ በ1 ሳምንት ጊዜ ካልተከፈላቸው ታጋቹን እንደሚገድሉት እንደዛቱ የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

እገታው እንዴት እና መቼ ተፈፀመ ? 

የሰዎች እገታ ከህፃናት አልፎ እድሜያቸው በገፉት ላይም በመቀጠል በህብረተሰቡ ውስጥ ቀውስን ማቀጣጠል መቀጠሉ እየተገለፀ ይገኛል።

ታጋቹ ሃለቃ ኣከቦም መሓሪ ኣባይ በትግራይ ፤ ምስራቃዊ ዞን ጉለመኻዳ ወረዳ የፍረዳሽም ቀበሌ ነዋሪ ናቸው።

ከ3 ወራት በፊት ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ / ም ከቤት እንደወጡ አለመመለሳቸው ያሳሰባቸው ቤተሰቦቻቸው ወደ አቅራቢያ ፓሊስ አመልክተው ራሳቸውንና ሌላውን በማሳተፍ በፍለጋ ቢታክቱም ሳይሳካላቸው ቆይተዋል።

የታጋቹ ሃለቃ ኣኮቦም ቤተሰቦች በከፍተኛ የተስፋ መቁረጥና የሀዘን ስሜት ውስጥ ባሉበት ሁኔታ ታድያ መጋቢት 15/2016 ዓ.ም የሞባይል ስልክ ጥሪ ይደርሳቸዋል።

የታጋቹ ቤተሰቦች የተደወለላቸው የሞባይል ስልክ ቁጥር የወንድማቸው ሃለቃ ኣከቦም ቢሆንም  ሞባይሉን ሲያነሱት የሰሙት ድምፅ ግን ከዛ በፊት ሰምተውት አያውቁም።

ይህ ማንነቱ ያልታወቀው ደዋይ በወንድማቸው የሞባይል ቁጥር በመጠቀም ፥ "...ወንድማችሁ ኣከቦም በህይወት ለማትረፍና በአካል ለማግኘት ከፈለጋችሁ 350 ሺህ ብር ክፈሉ። " የሚል ትዕዛዝ ያስተለልፋል።

የታጋቹ ወንድም ግደይ መሓሪ አባይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል በሰጠው ቃል ፥ ስልክ ደዋዩ ከአጋቾቹ አንዱ መሆኑን በማሳወቅ የተጠየቀው ብር እንዲከፍሉ የአንድ (1) ሳምንት ጊዜ ብቻ እንደሰጣቸውና ብሩን ካልከፈሉ ወንድማቸውን እንደሚገድሉባቸው እንደ ዛተ ተናግረዋል።

የታጋቹ ሃለቃ ኣከቦም መሓሪ ኣባይ በማህበራዊ ሚድያ ተሰራጭቶ ያነበቡ አስተያየት ሰጪዎች ፦ " ይህንን ያልተለመደና መጤ የእገታ ተግባር እጅግ አሳስቦናል !፤ ይህ እገታ ማቆምያው የት ይሆን ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

" አስከፊው ተግባር ወደየ ቤታችን ከመድረሱ በፊት መፍትሄ ያሻዋል " ያሉ አስተያየት ሰጪዎች " ከህግ አካላት በቅንጅት መስራት ሲቻል ችግሩ መፍትሄ ሊያገኝ ይችላል " ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዓድዋ ከተማ መጋቢት 11/2016 ዓ.ም የታገተችውና እንድትለቀቅ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባት ታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ 12 ቀናት ቢያልፋትም ደብዛዋ ሊገኝ አልቻለም።

መረጃው የተዘጋጀው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

ፎቶ 1 ፦ ሃለቃ ኣከቦም መሓሪ ኣባይ
ፎቶ 2 ፦ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ

@tikvahethiopia            
#Puntland #Somalia

ፑንትላንድ ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ዕውቅና መስጠት ማቆሟን ይፋ አድርጋለች።

ከፊል ራስ ገዝ የሆነችው #ፑንትላንድ በሞቃዲሾ ለሚገኘው ለሶማሊያ የፌደራል መንግሥት ከዚህ ቀደም ሰጥታው የነበረውም ዕውቅና አንስታለች።

የፑንትላንድ መንግሥት ካቢኔ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዶ ፑንትላንድ የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ተቋማት ላይ የነበራትን መተማመን በማጣቷ ትሰጥ የነበረውን ዕውቅና እንዳነሳች አሳውቋል።

ምክንያቱ ምንድነው ?

የሶማሊያ መንግሥት ፓርላማ ብዙ ባወዛገበ ሂደት በአገሪቱ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።

የሕገ መንግሥት ማሻሻያው ፕሬዝዳንቱ የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር የማሰናበትን ሙሉ ሥልጣን የሚሰጥ ሲሆን ‘ አንድ ሰው አንድ ድምጽ ’ የሚለውን ዓለም አቀፍ የምርጫ መርህ ተግባራዊ እንዲሆን የሚያደርግና ሌሎችም ማሻሻያዎች አሉበት።

NB. በሶማሊያ #ውስብስብ የሆነውን እና በጎሳ መሠረት የሚደረገውን ምርጫ ከ50 ዓመታት በላይ ስትጠቀምበት ቆይታለች፡፡ አሁን ' አንድ ሰው አንድ ድምፅ ' የሚለው ማሻሻያ በፑንትላንድ ባለልስጣናት ተቃውሞ ገጥሞታል።

በአጠቃላይ የፌዴራል መንግሥት ያካሄደው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ በፑንትላንድ አልተወደደም ውድቅም ተደርጓል።

ፑንትላንድ ፤ " በጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት ሕገ መንግስታዊ ሂደት እስከሚፈጠር ድረስ የፑንትላንድ አስተዳደር ለፌዴራል ተቋማት እውቅና አይሰጥም፣ ተቋማቱ ላይም እምነት የለውም " ብላለች።

ሕዝበ ውሳኔ (#ሪፈረንደም) የሚደረግበት ሕገ መንግስት እስከሚወጣ ድረስ፣ ፑንትላንድ የራሷ የሆነ መንግስታዊ ስልጣን እንደሚኖራት አስታውቃለች፡፡

ከአሁን በኋላ ፍላጎቷን ለማስጠቅ ከማዕከላዊ የሶማሊያ መንግሥት እውቅና ውጪ በራሷ አማካይነት #የውጭ_ግንኙነቶችን እንደምታደርግ ገልጻለች።

ይህ የፑንትላንድ ውሳኔ ከሶማሊያ ተነጥሎ ነጻ አገርነትን ከማወጅ ጋር ሊስተካከል እንደሚችል በመጥቀስ #ከሶማሊላንድ ቀጥሎ ለፌደራል መንግሥቱ ሌላ ራስ ምታት እንደሚሆን ተንታኞች እየገለጹ ነው።

ፑንትለንድ በተፈጥሮ ሃብቶችና #በቦሳሶ_ወደቧ በመተማመን እ.አ.አ 1998 ነው ከፊል ራስ ገዝ መሆኗን ያወጀችው። እራሷን እንደ ነጻና ሉኣላዊ ሀገር የምትቆጥረው የሶማሊላንድ ጎረቤትም ናት።

መረጃው ከቪኦኤ እና ቢቢሲ የተውጣጣ ነው።

@tikvahethiopia
#ሶልኤል

ልክ እንደ ክት ልብስ....

የድርጅቶን ስምና የብራንድ ደረጃ የጠበቁ የሥራ ልብሶችን በተመጣጣኝ ዋጋና ጥራት በሶልኤል ጋርመንት ያገኛሉ።

በመስቀል ፍላወር የሚገኘው ከ200 በላይ ባለሙያዎችን ይዞ የሚገኘው ማምረቻችን የእርሶን ትእዛዝ ይጠብቃል።

▪️ለሆስፒታል እና ለተማሪዎች የሚሆኑ ዩኒፎርሞች፤
▪️የፋብሪካ ቱታዎች እና የጥበቃ የደንብ ልብሶች፤
▪️ለሆቴሎች እና ለመስተንግዶ የሚሆኑ ደረጃውን የጠበቁ የሥራ ልብሶች ከእኛ ዘንድ ያገኛሉ።

በተጨማሪም በዘመናዊ ማሽኖቻችን የተለያዩ የኢምብሮይደሪ ወይም የክር ጥልፍ አግልግሎት እንሰጣለን። 👉 የተለያዩ የ ስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞችን ለሚያሰሩ ኤጀንሲዎች የዱቤ አገልግሎት ማመቻቸታችንን ስንገልጽ በደስታ ነው።

ይደውሉልን 📞 +251911236545 / 📞 +251992303030

በብዛት፤ በጥራትና በፍጥነት ማቅረብ የታወቅንበት ነው። ይምጡ እና ይጎብኙን።
ሰኞን በስጦታ!

ከባንክ ሂሳባችሁ ወደ M-PESA 1,000 ብር እና ከዚያ በላይ በማስተላለፍ እስከ 50 ብር ስጦታን አግኙ!

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://publielectoral.lat/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#FurtherAheadTogether
“ 1.2 ቢሊዮን የምስኪን ሕዝብን ገንዘብ 4 ዓመታት ሙሉ ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ እየተጠቀመበት ነው። በውላችን መሠረት መኪና አላስረከበንም ” - የቱሪስት ታክሲ ማኀበራት

በስራቸው ከ2,800 በላይ አባላት ያሏቸው ከ40 በላይ የሚሆኑ ሕጋዊ የቱሪስት ታክሲ ማኀበራት ከ3 ዓመታት በፊት " ከኦክሎክ ትሬዲንግ/ኃላ/የተ/የግ/ ማኀበር " መኪና እንዲቀርብላቸው ቢዋዋሉም መኪናው ሳይቀርብ የውል ገደቡ እንዳለፈ፣ ከ3 ጊዜ በደብዳቤ ቢጠይቁትም መፍትሄ እንዳልሰጣቸው፣ በመሆኑም መንግሥት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ኃላፊዎቹ እና እያለቀሱ ቅሬታ ያቀረቡ ቆጣቢዎች ጠይቀዋል።

ኃላፊዎቹና በእንባ የታጀቡት ቆጣቢዎቹ ይህን ያሉት ባለፈው ቅዳሜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ የተፈጠረውን ቅሬታ መነሻና ሂደትና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ ለማኀበሩ ጥያቄ አቅርቧል።

የቱሪስት ታክስ ማኀበራት ኃላፊ አቶ ግዑሽ መብራህቶም ምን አሉ ?

➡️ “ ከ2012 ዓ/ም መጨረሻ አካባቢ ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ በሚባል ድርጅት መኪና ያስገባል ወይም ገጣጥሞ ይሰጠናል በሚል ነው የነበረን ሂደት። ነገር ግን በዚህ መሠረት መኪናውን ማስረከብ አልቻለም። ይህም ብቻ አይደለም ‘መኪናውን ካላስረከበ ገንዘባችን ይመለስን’ ብለው የሚሄዱ አባላት ለሦስትና አራት ወራት እየተጉላሉ ነው። ”

➡️  “ በ2012 ዓ/ም መጨረሻ አካበቢ መኪና እናስመጣለን ብለው ማኀበራት ሲመዘግቡ እንሰጣለን ብለው ያሰቡትን ዋጋ በአማካኝ ብጠቀስ፣ 520 ሺሕ ብር ነበር። 520 ሺሕ ብር የነበረው መኪና አሁን ወደ 2 ሚሊዮን ብር አካባቢ ደርሷል። ”

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው ቱሪስት ታክሲ ማኀበራት ለኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ የጻፈው ደብዳቤ ምን ይላል ?

- የቱሪስት ታክስ ማኀበራት በሄሎ ታክስ መዝጋቢነት፣ በኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ መኪና አቅራቢነት የመኪና ሽያጭ ውል እንደተፈራረሙ፣ 

- የኦክሎክ ጀነራል ትሬዲግ በውሉ አንቀጽ 2 የውል ትርጉም መሠረት የመኪና አቅራቢ በመሆን ውሉ እንደተፈረመ፣ 

- በውሉ መሠረት እያንዳንዱ አባል ቅድመ ክፍያ እንደዬ መኪናዎቹ ሞደል 60 ሺሕ ብር እንደተከፈለ፣ በተጨማሪ ከውሉ ጋር የመኪናውን የ25% በመክፈል ከኦክሎክ የመኪናውን የቻንሲና የሞተር ቁጥር በውሉ መሠረት እንልተረከቡ ያስረዳል።

ቆጣቢዎች ምን አሉ ?

ኦክሎክ ትሬዲንግ ቢበዛ በአንድ ዓመት ውስጥ መኪናውን እንደሚያስረክባቸው በወቅቱ ገልጾላቸው እንደነበር፣ ይሁን እንጂ “ ከዛሬ፣ ነገ ይመጣል” እየተባለ በወቅቱ ሳይመጣ ዓመታት እንዳስቆጠረ፣ “ይባስ ብሎ” መኪናውን በማስረከብ ፋንታ “አዲስ ውሎ ፈርሙ” እያለ መሆኑን በቁጣ ገልጸዋል።

የቱሪስት ታክስ ማኀበር ኃላፊ በበኩላቸው ኦክሎክ ፈርሙ ያለውን አዲሱን ውል በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያብራሩ ፦ “ የማኀበራት ኃላፊዎች ባሉበትም አይደለም አዲሱን ውል እንዋዋል የተባለው። ዝም ብለው በዬማኀበራት ግለሰቦችን እየጠሩ ነው። በወሬ ወሬ ሰማነው፣ ከዚያ የሆነ አካል ፓስት አድርጎ በቴሌግራም አደረሰን። ከዚያ ሕዝቡ/ቆጣቢው ተንጫጫ። ስናየው አዲሱ ውል ከ85 በመቶ በላይ ለድርጅቱ የሚያደላ ነው ” ብለዋል።

አክለውም ፣ “ እውነትም አቅም ካለው ውሉ መሠረት መኪናውን ያስረክብ። አቅም ከሌለው በሚመጥን ዋጋ ገንዘቡን ኳልኩሌት አድርጎ ይመልስ ” ሲሉ በአባላቱ ሥም ጥሪ አቅርበዋል።

“ እኔ 1.5 ሚሊዮን ብር ነው የተጨመረብኝ። እውነት ድርጅቱ ጨምሮበት ነው ወይስ የድሃ እንባ ፈልጎ ነው?” ሲሉ እያለቀሱ ቅሬታ ያቀረቡ ቆጣቢ እናትን ጨምሮ የሌሎቹን ቆጣቢዎች የቅሬታ ቃል በቀጣይ እናቀርባለን። #TikvahFamilyAA

@tikvahethiopia
#አዲስአበባ #ነዳጅ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር ፥ በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ዕጥረት መከሰቱንና ምክንያቱ ደግሞ ጅቡቲ ላይ የዘነበ ከባድ ዝናብን ተከትሎ የመንገድ መቆራረጥ በመፈጠሩ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪም አስቀድሞም ከቦታዉ በበቂ ሁኔታ ነዳጅ እየተጫነ ባለመሆኑ መሆኑን አመልክቷል።

የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ደሳለኝ አበባየሁ ፥ እነዚህ ምክንያቶች ከነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች የተነገራቸዉ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ችግሩ ለመስተካከል ጊዜ ይወስድ እንደሆን የተጠየቁት አቶ ደሳለኝ " ጉዳዩ ትልቅ ነዉ፤ እንደ ቀላል የሚታይ አይደለም ያሉን ሲሆን፤ በእርግጠኝነት መንግስትም ሌት ተቀን ርብርብ አድርጎ ነገሮችን ያስተካክላል ብለን ተስፋ እናደርጋለን " ብለዋል።

ከጅቡቲ ከሚመጣዉ በተጨማሪ ክምችት ውስጥ ነዳጅ አልነበረም ወይ ? የተባሉት አቶ ደሳለኝ፤ " ቤንዚን ከአዋሽ ፣ ከሱሉልታ ዲፖዎች ነው እየተጫነ ያለዉ ፤ አሁን ላይ ግን ከክምችት ለመጫን ያልፈለጉበት የራሳቸዉ ምክንያት ይኖራቸዋል ፤ መንግስትም ይህንን አይቶ መፍትሄ ይሰጣል ብለን እንጠብቃለን " ብለዋል።

" አንድ ያለን መንገድ የጅቡቲ ብቻ ነዉ " ብለው " መንገዱ የተበላሸ በመሆኑ ደግሞ የመቆራረጥ ችግር ያጋጥማል ከባድ ዝናብ ሲዘንብ ደግሞ ችግሩን ከፍ ያደርገዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" እንደዚህ ዓይነት ችግሮች የሚያግጥሙ በመሆኑ ለተወሰነ ጊዜ በትዕግስት ማለፍ አስፈላጊ ነው " ብለዋል።

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ረጃጅም የነዳጅ ሰልፎች እየተስተዋሉ ይገኛል።

ይህ መረጃ የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia