TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ ተስፋዎች👆

#ሰውነት ያስተሳሰራቸው፤ #ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች #የተሰባሰቡ፤ ሀገራችንን ከገባችበት አዘቅት ውስጥ ለማውጣት በየዩኒቨርሲቲው እየተጓዙ የሚገኙት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት #ኑ ኢትዮጵያን #ከጥላቻ አላቀን #ታላቅ እናድርጋት የሚል #ሀገራዊ ጥሪ አቅርበዋል።

ፎቶ: የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት #ለእንግዶቹ ያደረገው #የእራት እና #የምሳ ግብዣ #WKU

Photo: @Dura_pic

ደማችን #አንድ ነው!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀገራዊ_ምክክር 🇪🇹

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕ/ር መስፍን አርአያ ለኤፍ ቢ ሲ በሰጡት ቃል የተናገሩት ፦

" በሀገራዊ ምክክሩ #ሁሉም ኢትዮጵያዊ አጀንዳ የሚያስይዝበት አሰራር ይዘረጋል።

የውይይት ሃሳቦች ከታች ወደ ላይ ነው የሚሰበሰቡት።

በውይይቱ ይህ ይነሳ ያ አይነሳ የሚባል ነገር የለም ። ኮሚሽኑ በአጀንዳዎች ላይ ጣልቃ አይገባም።

ምክክሩ ልሂቁ ላይ ብቻ የተንጠለጠለ ባለመሆኑ ሁሉም ዜጋ ሐሳቡ በጥቂቶች እንዳይጨናገፍ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ እናቀርባለን።

በቀጣይ በየክልሉ እንደ አመቺነቱ ጽሕፈት ቤቶች ይቋቋማሉ ፤ የኮሚሽኑ ምክር ቤት መርሃ ግብር ያዘጋጀ ሲሆን ስትራቴጂክ ዕቅዱን ለባለድርሻ አካላት በማቅረብ ግብዓት ይሰበሰባል።

አጀንዳ የመሰብሰብ ሥራ በገጽ ለገጽ ማህበረሰቡ በሚረዳው ቋንቋ ስለ ኮሚሽኑ በማስረዳት ሃሳቡን እንዲገልጽ ይደረጋል። በሌሎች አማራጮችም በስልክ፣ ኢሜይል እና ፖስታ በመሳሰሉት ማቅረብም ይቻላል።

ማሕበረሰቡ ሃሳቡን ከማቅረብ በተጨማሪ በማዕከል ደረጃ ለሚደረገው ምክክር ወኪሎቹን እንዲመርጥ ይደረጋል።

የአጀንዳ ሃሳቦች መሰብሰብ የሚጀመርበት ጊዜ #በቅርቡ_ይፋ ይደረጋል። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የትምህርት ሚኒስቴር የብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ ፦ (ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ - የትምህርት ሚኒስትር) - የፈተና ንክኪው በእጅጉ ተቀንሷል። - ከዚህ በፊት በፈተና አሰጣጥ ወቅት የነበረውን " የኔ አካባቢ ሰው ፣ የኔ ዘመድ " የሚለውን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ማንኛውም የአንድ አካባቢ ተወላጅ እዛው አካባቢ ያሉ ተማሪዎችን አይፈትንም። ማንኛውም የአንድ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ እራሱ የሚያስተምርበት ዩኒቨርሲቲ…
የፈታኝ መምህራን ጉዳይ !

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚፈትኑ መምህራንን ምደባ አካሂዷል።

መምህራኑ ወደ ተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ወዳሉ የመፈተኛ ማዕከላት የተመደቡ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ሚቀርቡ ማንኛውም አይነት ጥያቄዎችን እንደማያስተናግዱ ዩኒቨርሲቲዎች እያሳወቁ ይገኛሉ።

በሚኒስተሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 260/2004 አንቀፅ 9(2) በተሰጠው ሥልጣንና እንዲሁም በሀገር አቀፍ የፈተና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1/2012 መሰረት ፈተና ለመፈተን ወደ ሌላ መፈተኛ ማዕከል የተመደበ መምህር በተዘጋጀው የፈተና አሰጣጥ እና አፋጻጸም ማንዋል 01/2014 መሰረት የፌደራል ት/ሚ/ር እና ፈተናዎች አገልግሎት ኤጄንሲ ወደ ተመደበበት ቦታ የመገኘት ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ይገልጻል፡፡

በመመሪያው መሰረት የዩኒቨርሲቲ መምህራን ወደ ተመደቡበት አካባቢ ሄደው የተጣለባቸው #ሀገራዊ_ኃላፊነት የመወጣት ግዴታ ያለባቸው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከጉዞ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ማንኛውንም ጥያቄ እንደማያስተናግዱ ዩኒቨርሲቲዎች ከወዲሁ እያሳወቁ ይገኛሉ።

ትላንት የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሰጡት መግለጫ ፤ " ከዚህ በፊት የነበረውን የኔ አካባቢ ሰው ፣ የኔ ዘመድ የሚለውን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ማንኛውም የአንድ አካባቢ ተወላጅ እዛው አካባቢ ያሉ ተማሪዎችን አይፈትንም። ማንኛውም የአንድ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ እራሱ የሚያስተምርበት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አይፈትንም " ሲሉ አሳውቀዋል።

(ከላይ የተያያዘው ደብዳቤ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከፈታኝ መምህራን ምደባ ጋር በተያያዘ ማንኛውም አይነት ጥያቄ እንደማያስተናግድ ያሳወቀበት ነው)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ማዳበሪያ . . . " ማዳበሪያ በወቅቱ ስላልቀረበልን የዘር ስራችን እየተደናቀፈብን ነው " - በደብረ ብረሀን ከተማ ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች " የማዳበሪያ አቅርቦት ችግር  ከአቅሜ በላይ ነው " - የደብረብርሃን ከተማ ግብርና መምሪያ በደብረብርሃን ከተማ ዙሪያ በጫጫ ክፍለ ከተማ የጨፋንን ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ካሳየ ሄየ ፦ " በበጋ መስኖ ስንዴ ስናለማ መንግስት ሰው ሰራሽ ማዳበሪያና…
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምን አለ ?

በአማራ ክልል በ2015/16 የመኸር የእርሻ ዘመን 5 ሚሊዮን ሔክታር ማሣ በዘር በመሸፈን 160 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት ሰፊ የቅድመ ዝግጅትና የትግበራ ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።

ነገር ግን የማዳበሪያ አቅርቦት እንዲሁም ስርጭቱ በሚፈለገው ፍላጎትና ቢሮው በአስቀመጠው የዕቅድ መጠን ልክ እንዳልሆነ አልሸሸገም።

ይህም ካለው የሀገሪቱ አጠቃላይ ወቅታዊ ችግርና ማዳበሪያ በሀገር ውስጥ የሚመረት እና እንደ ምርጥ ዘር በራሳችን የሚቀርብ አለመሆኑን ሁሉም መገንዘብ ይኖርበታል ብሏል።

ቢሮው  ፤ " ከፌደራል ግብርና ሚኒስቴር ጋር በቅርበትና በቅንጅት በመስራት ማንኛውንም የሚቻለንን ሁሉ እየሠራን ነው "  ሲል ገልጾ " ችግሩን ይበልጥ #ማጯጯህ ሳይሆን ይህም ችግር እንደማንኛውም ችግር የሚያጋጥምና ችግሩን መወጣትም አንዱ የትግል አካል በመሆኑ በመተባበርና በመቀናጀት መስራት ይገባል " ብሏል።

ቢሮው ፦

1ኛ. ቀድሞ የገባን ማዳበሪያ ቀድመው ለሚዘሩ ሰብልና አካባቢዎች በመተሳሰብ ማሰራጨት፤

2ኛ. ማንኛውም የሚቀርቡ ግብአቶች ከብልሹ አሰራርና ህገወጥ ድርጊት መከላከል፤

3ኛ. የተፈጥሮ ማዳበሪያ ኮምፓስት፣ ቨርሚ ኮምፓስትና ሌሎችንም ቢሮው ሲከታተለው የከረመ በመሆኑ በዞኖች በሪፓርት የተላከውን ኮምፓስት መጠቀም መቻል፤

4ኛ. የመረጃ ቅብብሎሽ በትክክለኛና በተመጠነ አኳኃንና እንዲሁም የአርሶአደሩን ሞራልና ስሜት የሚያበረታታና የሚያጠነክር መሆን አለበት ብሏል።

ቢሮው በአሁኑ ሰዓት በክልሉ በሁሉም የሰብል አይነትና መጠን የምርጥ ዘር ችግር በአንጻራዊነት ችግር እንደሌለ ገልጿል።

ከግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት አማራ ቅርንጫፍ በተገኘው መረጃ መሠረት አማራ ክልል በነዚህ በተዘረዘሩት ሰብሎች የሚከተለውን " #ሀገራዊ_ድርሻ " የያዘ ክልል ነው።

- ጤፍ  👉 40% ሀገራዊ ድርሻ አለው።

- ሰሊጥ 👉 80% ሀገራዊ ድርሻ አለው።

- ስንዴ 👉 32% ሀገራዊ ድርሻ አለው።

- አኩሪአተር 👉 85% ሀገራዊ ድርሻ አለው።

- ሩዝ 👉 63% ሀገራዊ ድርሻ አለው።

- በርበሬ 👉 45% ሀገራዊ ድርሻ አለው።

- እጣንና ሙጫ 👉 60% የማምረት ድርሻ አለው።

መረጃው ከአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#ባልደራስ

ከዚህ ቀደም ጠቅላላ ጉባኤውን እንዳያደርግ ተከልክሎ እንደነበር የገለፀው ባለደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ዛሬ ጠቅላላ ጉባኤውን አድርጓል።

ፓርቲው በጠቅላላ ጉባኤው ፥ አቶ አምሃ ዳኜው ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟል።

አቶ አማሃ ዳኜው ፤ ፓርቲውን በም/ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ ነበሩ። ዛሬ በአብላጫ ድምፅ አቶ ለቀጣይ 3 አመታት በፕሬዝዳንትነት እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፤ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ዛሬ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ #ሀገራዊ_ፓርቲ ለመሆን ውሳኔ አሳልፏል።

ባልደራስ ፓርቲ ፤ ምንም እንኳን ኢትዮጵያዊ ሀሳቦችን እያነሳው የታገልኩኝ ቢሆንም ባለኝ ፍቃድ መሰረት ግን መንቀሳቀስ የቻልኩት አዲስ አበባ ላይ ብቻ ነው ብሏል።

የዛሬው ጉባኤ ፓርቲው ሀገር አቀፍ ፓርቲ ለመሆን የሚያስፈልጉ ቅድመ ተግባራትን እያከናወነ እንዲቆይ እና ከወራት በኋላ በሚደረገው ጉባኤ ወደ ሀገር አቀፍነት እንዲያድግ ያለ ተቃውሞ እና ድምፀ ታቅቦ መፅደቁ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ ጠቅላላ ጉባኤው ፓርቲው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ከውህደት-መለስ አብሮ እንዲሰራ ፈቅዷል።

ነገር ግን ከፓርቲዎች ጋር የሚኖረውን ግንኙነት የፓርቲው ምክር ቤት እንዲወስን ጉባኤው ፍቃድ ሰጥቷል።

በዚህ መሰረት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከፓርቲዎች ጋር የሚኖረውን ግንኙነት መርምሮ እና አጥንቶ ለፓርቲው ምክር ቤት እንዲያቀርብ፤ እንዲሁም ም/ቤቱ ስራ አስፈፃሚ የሚያቀርብለትን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንዲያፀድቅ ወስኗል።

መረጃው ከፓርቲው ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ሀገራችን ኢትዮጵያ በቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመጨረሻዋ ውድድር የሆነውን የሴቶች 3000ሜ መሰናክል ውድድር ማድረግ ጀምራለች። በውድድሩ ሀገራችን ፦ - በአትሌት ሲምቦ አለማየሁ - በአትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ - በአትሌት ሎሜ ሙለታ ተወክላለች። መልካም ዕድል ! @tikvahethiopia
#ተጠናቋል

በዚህም ድል አልቀናንም !

በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል ኢትዮጵያ ድል አልቀናትም።

ዘርፌ ወንድማገኝ 4ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

ሎሜ ሙለታ 12ኛ ፣ ሲምቦ አለማየሁ 13ኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።

ሀገራችን በሀንጋሪ፣ ቡዳፔስት ስታካሂድ የነበረውን ውድድሮች ሁሉ #አጠናቃለች

ኢትዮጵያ በሜዳሊያ ብዛት ከዓለም 6ኛ ደረጃ፣ ከአፍሪካ ደግሞ ኬንያን በመከተል 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች። ኢትዮጵያ 2 የወርቅ፣ 4 የብር እና 3 የነሐስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን ነው ያገኘችው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዋና ገፅ / @tikvahethiopia ስፖርት በተለይ አትሌቲክስ #ሀገራዊ ስሜትን ፣ አብሮነትን ፣ አንድነትን ያጠነክራል የሚል እምነት ስላለው የሀገራችን ልጆች የተካፈሉባቸውን ውድድሮች ሁሉ #ከስፍራው ከፎቶ ጋር ሲያደርስ ቆይቷል።

ስፖርታዊ መረጃዎችን በ @tikvahethsport መከታተል ትችላላችሁ።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia