TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዛሬ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ጠንከር ያለ ዝናብ ዘንቦ ነበር።

በተለይ በዳውሮ ዞን በ " ቶጫ ወረዳ " በተለያዩ ቀበሌዎች ላይ ከቀኑ 7:30 እስከ 8:10 ድረስ በረዶና ንፋስ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በሰብልና በንብረት ላይ መጠነኛ ጉዳት ማድረሱ ተሰምያል።

ወቅቱን ካልጠበቀ ከፍተኛ ዝናብ ጋር ተያይዞ ሊከሰት ከሚችለው አደጋ የወረዳው ህዝብ እራሱንና ወገኑን እንዲከላከል ጥሪ ቀርቧል።

ዝናቡ ቀጣይነት ልኖረው ስለሚችል ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ ተብሏል።

በሌላ በኩል፤ ላለፉት ሳምንታት ከፍ ያለ ሙቀት ስታስተናግድ የነበረችው የሀገራችን መዲና አዲስ አበባ ዛሬ ጠንከር ያለ ዝናብ አግኝታለች።

@tikvahethiopia
#Adwa

በትግራይ ዓድዋ ከተማ የታፈነች / የታገተች ታዳጊን ተማሪ ለማስለቀቅ 3 ሚሊዮን ብር ተጠይቆባታል። አፈናው ከተፈፀመ 5 ቀናት ሆኖታል።

የአፈናው ድርጊት አፈፃፀም እና የጉዳዩ አሳሳቢነት ምን ይመስላል ? 

እሮብ መጋቢ 11 ቀን 2016 ዓ/ም የ16 አመት ታዳጊ ተማሪዋ ማህሌት ተኽላይ ቀን ትምህርት ውላ አመሻሽ ቋንቋ ወደ ምትማርበት ማእከል ብቻዋ በመጓዝ ሳለች ባጃጅ ይዘው በመጡ ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች አፍነው ወሰድዋታል።

ተማሪ ማህሌት ከቋንቋ ት/ቤት እንደልማድዋ በሰአትዋ አለመመለስዋ ቤተሰቦችዋ ተጨንቀው እያለ ወላጅ አባትዋ የልጃቸው የሞባይል ስልክ ጥሪ ይደርሳቸዋል።

በልጃቸው የሞባይል ቁጥር የተደወለባቸው አባት በወላጅ በስስት ' ልጄ ' ብለው ሞባይላቸው ያነሳሉ።

በሞባይል የሰሙት ድምፅ ግን ከዚህ በፊት ሰምተውት የማያውቁ የወንድ ድምፅ ነበር።  ድምፁ በመሃል የልጃቸው ለቅሶ ፣ ፍርሃትና የ 'አስለቅቁኝ ' ልመና አሰማቸው።

ቀጥሎ የልጃቸው ድምፅ በማራቅ " ልጃችሁ በቁጥጥራችን ስር ናት፤ መልሳችሁ በህይወት ልታገኙዋት ከፈለጋችሁ 3 ሚሊዮን ብር ክፈሉ ፤አለበለዚያ እንገድላታለን " የሚል የማስፈራርያ  ድምፅ ካሰሙ በኃላ ስልኩን ይዘጋሉ።

የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተማሪ ማህሌት ተኽላይ የመጥፋት ጉዳይ ወደ አባትዋ ደውሎ ይህ መረጃ እስካዘጋጀበት ቀንና ሰዓት ድረስ ታዳጊዋ ማህሌት ከቤት ወጥታ ከቀረች 5 ቀናት ተቆጥረዋል።

የታዳጊዋን ማህሌት ቤተሰቦች እንባ ለማበስና እንቅልፋቸውን ለመመለስ የዓድዋ ከተማ ፓሊስ ታዳጊዋን አፍነው የወሰዱ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ፍለጋ እያካሄደ ነው።

ጉዳዩ እጅግ ያሳሰባቸው የተለያዩ በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ፥ የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ጉዳይ በማንሳት እየተወያዩበት ይገኛሉ።

" ልጆች አፍኖ ገንዘብ የመጠይቅ ፋሽን መቼ ነው የሚቆመው ? " የሚል ጥያቄ አንስተዋል።

ባለፈው ጥቅምት 2016 ዓ.ም ሚልክያስ ፋኑስ የተባለ የዓዲግራት ከተማ ነዋሪ ህፃን ታግቶ ለማስለቀቅ 4 ሚሊዮን ብር  ተጠይቆበት ፤ በፓሊስ ክትትል ከ12 ቀናት ፍለጋ በኋላ ሊገኝ ችሏል።

በመቐለ ከተማ የዓይደር ክፍለ ከተማ ዓዲሓ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው የ9 አመቱ ሳሚኤል መሓሪ ከበደ ደግሞ ባለፈው ወርሃ የካቲት 2016 ዓ.ም በጠላፊዎች ታግቶ ከተወሰደ በኃላ እንደዲመለስ 4 ሚሊዮን ተጠይቆበታል ቢሆንም ፓሊስና ህብረተሰብ ባደረጉት የተቀናጀ እልህ አስጨራሽ ጥረት ከአንድ ሳምንት በኃላ ተገኝቷል። በድርጊቱ እጃቸው አለበት የተባሉ 5 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው መዘገባችን ይታወሳል።

መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                                               
@tikvahethiopia            
እናንተ ፈንዲሻችሁን ብቻ አዘጋጁ፤ የካናል ፕላስ ክፍያውን በM-PESA  ላይ ጣሉት!

M-PESA ላይ ተመዝግበን፣ በM-PESA እንክፈል!

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://publielectoral.lat/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#FurtherAheadTogether
TIKVAH-ETHIOPIA
" ፍርዱ ለሚዲያ 16 ዓመት ከተባለ በኃላ ወደ 10 ዓመት ዝቅ እንዳለ ሰምቻለሁ " - ጸጋ በላቸው " ጉዳዩ ለቢሮዉም ሆነ ለኔ አዲስ ነው " - ወ/ሮ ወይንሸት ብርሀኑ በሀዋሳ ከተማ የዳሽን ባንክ ሰራተኛ ከሆነችዉ ጸጋ በላቸዉ ጋር በተያያዘ በጠለፋና አስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ  የነበረው ኮንስታብል የኃላመብራት ወ/ማርያም " ለብዙዎች አስተማሪ ይሆናል " በተባለ መልኩ የ16 አመት ጽኑ እስራት…
" ... ሌላዉ ቢቀር እንዴት እግሯን አጎንብሰዉ ያጠቧት ሴት ፖሊሶች ይረሳሉ ? " - የሀዋሳ ፖሊስ

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ስሜን የሚያጠለሹ አካላት ከድርጊታቸው ይታቀቡ ሲል አሳሰበ።

ፖሊስ ፤ " የተለያዩ የሶሻል ሚዲያ በመጠቀም የሀዋሳ ከተማን ገጽታ ለማጠልሸት የሚሰሩ አካላት ከድርጊታቸዉ ሊታቀቡ ይገባል " ብሏል።

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " ከሰሞኑ በተደጋጋሚ እንደሚታየዉ ለሰላም ሌት ተቀን እየደከመ ያለዉን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ በመጥቀስ ስም የማጠልሸት አካሄዶች ውስጥ የገቡ አካላት መኖራቸዉን እየተመለከትን ነው " ብለዋል።

ድርጊቱ አስነዋሪ መሆኑንና የሀዋሳ ከተማን የጸጥታ አካላት ያሳዘነ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢንስፔክተር መልካሙ ፥ " በቅርቡ ' ቲክቶክ 'ን ተጠቅሞ የንግድ ድርጅቴ (የውስኪ ቤቴ) ተዘጋ በማለት ሲከስ የነበረዉ ግለሰብ ልክ አይደለም " ብለዋል።

" ጠጥቶ አልከፍልም ያለዉን አካል ለህግ ማቅረብ ሲቻል የተከበረውን የፖሊስ ስም ማጥፋቱ በፍፁም ልክ አልነበረም ፤ አሁንም ቅሬታ ካለ የቆምነው ህግ ለማስከበር ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ፥ ወይዘሪት ጸጋ በላቸዉ ከተጠለፈችበት ቀን ጀምሮ እሷን ለማግኘት የተንከራቱዉው ወደ ሀዋሳ በመጣችበት ወቅትም ጥበቃና ድጋፍ ባደረገላት የፖሊስ ሀይል ላይ የሰነዘረችዉ ሀሳብ ልክ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

" እሷና ቤተሰቦቿ እንዲያርፉበት ለተፈቀደላቸው ቤትና ለተሰጣቸዉ ጥበቃ ማመስገን ሲገባት እንደእስር ተቆጥሮ ለሚዲያ መጮህ ልክ አይደለም " ብለዋል።

" ሌላዉ ቢቀር እንዴት እግሯን አጎንብሰዉ ያጠቧት ሴት ፖሊሶች ይረሳሉ ? በማለት ለፖሊስ በጎ አድራጎት ምላሹ ይህ ሊሆን አይገባም " በማለት ተችተዋል።

ጨለማ ብርድና ቁር ሳይል በትጋት የሀዋሳ ከተማን የሰላም ተምሳሌት ለማድረግ በሚተጋዉ የጸጥታ ሀይል ላይ የተለያዩ የሶሻል ሚዲያዎችን በመጠቀም የሚሰነዘሩ የስም ማጥፋቶች ልክ አለመሆናቸዉን በመግለጽ ግለሰቦች ከዚህ ድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል።

በቅርቡ በፀጋ በላቸው በቲክቶክ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ አግቶ ጠልፎ ወስዶ ባሰቃያት ግለሰብ ላይ በሚዲያዎች የተገለጸው ፍትህ ከእውቅናዋ ውጭ በሆነ መልኩ የእስራት ፍርዱ ከ16 አመት ወደ 10 መቀነሱን እንደሰማች ተናግራ ያደረባትን ሀዘን መግለጿ ይታወሳል።

ወደ 10 ዓመት ዝቅ እንዲል በተደረገው ፍርድ እጅግ እንዳዘነች የገለጸችው ፀጋ ፤ ካሳለፈችው የስቃይ ሁኔታ ጋር በፍፁም እየሚገባ እንዳልሆነ በእምባ ታጅባ ገልጻ ነበር።

በዚህም ወቅት ህዝብ የማያውቀው ብዙ ነገር እንደተፈፀመ ፤ ከጠለፋው እገታ ከተለቀቀች በኃላ በማታውቀው ምክንያት በፖሊስ ታስራ እንደነበር አሳውቃ ነበር።

መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከዉ የሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
 " ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከተለው ነገር ሁሉ የአማራ ክልል ሙሉውን ኃላፊነት ይወስዳል " - የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ምን አለ
?

" የአማራ ክልል የትግራይ መሬት በካርታው በማስፈር የትምህርቱ ሰርዓቱ አካል በማድረግ እያስተማረበት ይገኛል " ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ከሰሰ።

" ክልሉ የትግራይ መሬት በሚመለከት በስርዓተ ትምህርቱ ያሰፈረው ካርታ ኃላፍነት የጎደለው ብቻ ሳይሆን የትግራይ ህዝብ ከፋፍሎ ለማጥፋት ያወጀው ዘመቻ በማስቀጠል በከፋ መልኩ እየሰራበት እንደሚገኝ ማረጋገጫ መሆኑ ተገንዝበናል " ብሏል።

" የአማራ ክልል መንግስት በህዝባችን ላይ አየፈፀመው የቆየውና አሁንም በሃይል በያዛቸው የትግራይ አከባቢዎች እየፈፀመ የሚገኘው ግፍና መከራ ተሰሞቶት በመፀፀት ፈንታ ወደ ባሰ ታሪካዊ ስህተት መግባቱ በቀጣይነት ዋጋ እንደሚያስከፍለው በማወቅ በአስቸኳይ እርምት ማድረግ አለበት " ሲል አስስቧል።

ካቢኔው ፤ " የፌደራል መንግስት ከአሁን በፊት የፌደራል ተቋማት ዛሬ ደግሞ በአማራ ክልል እየተዘጋጁ ያሉ ኃላፊነት የጎደላቸው ካርታዎች እንዲያርማቸውና በጥፋት ፈፃሚዎች ላይ ተገቢ እርምጃ መውሰድ እየተገባው በዝምታ ማለፉ የጥፋቱ አካል መሆኑ የሚያመላክት ነው " ብሏል።

" የትግራይ ህዝብና ጊዚያዊ አስተዳደሩ የፕሪቶሪያ ውል በተሟላ መልኩ በመፈፀም ሰላም እና መረጋጋት እንዲመጣ በከፍተኛ የኃላፊነት መንፈስ በሚሰሩበት ወቅት ፤ የአማራ ክልል የሰላም ሂደቱ ለማወክ ይህ መሰል ነገር ጫሪ ጥፋት ሆን ብሎ መፈፀሙ ሊሰመርበት ይገባል " ሲልም ገልጿል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ፥ " የአማራ ህዝብም ሆነ ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች በአማራ ክልል መንግስት በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ የቆየውና አሁንም የቀጠለው ግፍና በደል ይቁም ብሎ ከትግራይ ህዝብና ጊዚያዊ አስተዳደሩ ጎኑ  እንዲቆሙ " ብሏል።

" ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከተለው ነገር ሁሉ የአማራ ክልል መሉውን ኃላፊነት እንደሚወስድ ለማስታወቅ እንፈልጋለን " ሲል ገልጿል።

በአማራ ክልል በኩል በጉዳዩ ላይ የተሰጠ መግለጫ እስካሁን የለም። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ክልሉ የሚሰጠው ምላሽ ካለ ተከታትሎ ያቀርባል።
                         
@tikvahethiopia            
#AddisAbaba

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፥ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ በሚገኘው የኮሪደር ፕሮጀክት እና ተያያዥ የልማት ሥራዎች ምክንያት በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ መስመር የማዛወር ሥራዎች እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።

በዚህም ሥራው ሲከናወን ተገቢውን ጥንቃቄ ለማድረግ እንዲሁም አደጋ እንዳይከስት ሲባል ሥራው በሚከናወንባቸው አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ሙሉ ለሙሉ ወይም አልፎ አልፎ ለተወሰኑ ሰዓታት #እየተቋረጠ እንደሚገኝ አመልክቷል።

" የመስመር ማዛወር ሥራዎቹ በጥንቃቄና በፍጥነት ለማከናወንና አገልግሎቱን ለማስቀጠል ከፍተኛ ጥረት እያደረግን ነው " ያለ ሲሆን ነዋሪዎች ይህን ተረድተው በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጥሪ አቅርቧል።

በዚህ ምክንያት ለሚፈጠሩ ለአገልግሎት መስተጓጎሎችም #ይቅርታ ጠይቋል።

በሌላ በኩል፥ ከመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከ4 ኪሎ እስከ ፒያሳ ባለው መስመር የራስ መኮንን ድልድይ እየተሰራ በመሆኑ የመንገድ ግንባታው እስከሚጠናቀቅ በተለይ በስራ መግቢያ እና መውጪያ ሰዓት አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

በዚህም፦
ከ4 ኪሎ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
ከደጎል አደባባይ ትራፊክ መብራት ወደ 4 ኪሎ
ከቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
ከደጃች ውቤ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
ከአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
ከባሻ ወልዴ ችሎት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ እና ከቀበና ወደ ፒያሳ የሚመጡ አሽከርካሪዎች መንገዱ ግንባታ ላይ መሆኑን ተገንዝበው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#አጣዬ

“ የሰው ሕይወት በእነርሱም በእኛም ጠፍቷል። የሟቾች ቁጥር እንደ አጣዬ ከተማ ወደ 10 ደርሷል። በጣም በርካታ ቁስለኞች አሉ ” - የአጣዬ ከተማ ከንቲባ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማና በኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን በታጣቂዎች መካከል ተከፈተ የተባለው የተኩስ ልውውጥ ከሰሞኑ ይልቅ ዛሬ (ሰኞ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም) አንፃራዊ #ሰላም እንዳሳዬ፣ በነበረው የተኩስ ልውውጥ ግን በሁለቱም ወገኖች የንጹሐን ሕይወት እንዳለፈ የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ ተመስገን ተስፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

Q. ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰላሙ ሁኔታ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ፣ የተኩሱ ሂደት ምን ይመስል እንደነበር፣ የጉዳት መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ ለከንቲባው ጥያቄ አቅርቧል።

አቶ ተመስገን ተስፋ፦

“ ተኩሱ ሁለት ቀናት በዙሪያው ሲካሄድ ቆይቷል። ወደ ከተማው ከገባ በኋላ ደግሞ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ውጊያው ተካሂዷል።

መከላከያ ገብቶ ከቆመ በኋላም ተራራ ላይ በመሆን በመተኮሱ የተገደሉ ንጹሐን አሉ። የሰው ሕይወት በእነርሱም በእኛም ጠፍቷል። በጠቅል የሟቾች ቁጥር እንደ አጣዬ ከተማ ወደ 10 አካባቢ ደርሷል። ቁጥራቸው ባይታወቅም እጅግ በጣም በርካታ ቁስለኞች ናቸው ያሉት።

Q. ቲክቫህ ኢትዮጵያ በኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን በኩል “ ፋኖ ታጣቂዎች ጥቃት አደረሱብን ” በአማራ ክልል በኩል ደግሞ “ የሸኔ ታጣቂዎች ጥቃት አደረሱብን ” የሚሉ ሀሳቦችን ነዋሪዎቹ በየፊናቸው እየገለጹ ይገኛሉ። እንደተባለው “ የፋኖ ታጣቂዎች ” ም ሆኑ የሸኔ ታጣቂዎች ናቸው ጥቃት አድራሿቹ ? እውነታው ምንድን ነው? ሲል ጠይቋል።

አቶ ተመስገን ተስፋ፦

“ በከተማችን ላይ የፋኖ ታጣቂ የለም። ከእነርሱም ጋር ግጭት አልፈጠረም። ምናልባት የፋኖ ታጣቂ የሚባለው ችግሩ ከመንግሥት ጋር ነው። መንግሥትን ካልሆነ በስተቀር የኦሮሚያን ብሔር በዚህ ቦታ ሂዶ ተጋጨ የሚል እንደ ከተማችን የለም። ችግሩ የተፈጠረው በእኛ በከተማው ታጣቂዎችና በእነርሱ መካከል ነው።

ዞሮ ዞሮ የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች በአንድ ገበያ የሚገበያዩ፣ ተስማምተው የሚኖሩ፣ በማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ የሚያደርጉ ስለሆኑ፣ አማርኛ ተናጋሪው ኦሮሞው ላይ፣ ኦሮምኛ ተናጋሪውም እንደ ህዝብ ጥቃት ያደርሳል፣ ፈልጎ ይዋጋል ብለን አናስብም።

ልዩ የሆነ ቡድን፣ ፀቡ እንዲነሳ የሚፈልግ (ምናልባት ደግሞ ከዚያ ተጠቃሚ ሊሆን የሚችል) ቡድን አለ። እሱም ደግሞ ኦረምኛ ተናጋሪ ይሆናል ተብሎ የሚታሰበው ‘ሸኔ’ ነው።

ስለዚህ የእኛ ፍረጃ አሁን የኦሮሞ ሕዝብ የአማራን ሕዝብ ወጋው ሳይሆን፣ የኦሮሞ ‘ሸኔ’ አማርኛ ተናጋሪውን በከተማው ላይ መጥቶ ወግቷል የሚል ግምገማ ነው ያለን።

Q. ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እንዲቻል መንስኤውን ማወቅ ያስፈልጋልና የሰሞኑ ተኩስ መነሻው ምን ነበር ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርቧል።

አቶ ተመስገን ተስፋ፦

“ እንደ አጠዬ ከተማ ነዋሪ፣ እንደ ከተማ አመራር መነሻው ይሄ ነው የሚል ነገር የለም። ግጭቶቹ የተካሄዱት በወሰን ብቻ ሳይሆን በከተማው መሀል ላይ ነው። ድንገት ገቡ ተወረረ ከተማው።

ከንጹሐን ሞት በተጨማሪ ሆቴሎች፣ ሱቆች ተዘርፈዋል። አረጋዊያን፣ ሴቶች፣ ህፃናት ከከተማ ወጥተው ወደ ገጠራማው ክፍል ተፈናቅውለዋል። አጣዬ ከተማ ያሉት ወንዶችና የጸጥታ አካላት ብቻ ናቸው።

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ አካባቢውን መከላከያ ተቆጣጥሯል። አንጻራዊ የሆነ ሰላም አለ። ”

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በኩል ስለጉዳዩ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አልተሳካም። ፈቃደኛ ሆነው የሚሰጡት ማብራሪያ ካለ በቀጣይ ይቀርባል።

@tikvahethiopia
#ናይጄሪያ

ናይጄሪያ ውስጥ አንድ ባለሃብት ገንዘብ ለማደል በጠራበት ዝግጅት ላይ በተፈጠረ ግርግር አንዲት የ8 ዓመት ሕፃንን ጨምሮ 7 ሰዎች ተረጋግጠው እንደ #ሞቱ ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

ትላንትና እሁድ አልሃጂ ያኩቡ የተባለ ባለሀብት በሰሜን ምሥራቅ የባውቺ ግዛት ነዋሪዎች ወደ ቢሮው ከመጡ ለእያንዳንዳቸው 5 ሺህ ናይራ (የናይጄሪያ ገንዘብ) ለመስጠት ቃል ይገባል።

5 ሺህ ናይራ ወደ ዶላር ሲመነዘር 3 ዶላር ከ70 ሳንቲም ሲሆን፣ ወደ ብር ሲቀየር 210 ነው።

የባለሀብቱን የገንዘብ እደላ ጥሪ ተከተሎ በርካታ ሰዎች ይወጣሉ በዚህ ወቅት በተፈጠረ ግርግር ዕድሜያቸው ከ8 እስከ 55 የሚሆን 7 ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ አረጋግጧል።

ነዋሪዎች ግን የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከተጠቀሰው ይበልጣል ብለዋል።

ብዙ ጊዜ እንዲህ ያለ እደላ/እርዳታ ላይ ወንዶች የእርዳታ ገንዘብ ሲቀበሉ መታየት  ስለማይፈልጉ ሴቶችን እንደሚልኩ ተነግሯል።

የሀገሪቱ ባለሥልጣናት በዕለቱ የተፈጠረውን ነገር ለማጣራት ምርመራ መጀመራቸውን ተናግረዋል።

ቢሮው አካባቢ የጥሬ ገንዘብ ልገሳ ያሰናዳው ባለሀብቱ አልሃጂ ያኩቡ ማይሻኑ እስካሁን ያለው ነገር የለም።

የናይጄሪያ የምጣኔ ሀብት #መላሸቁን ተከትሎ በርካቶች እርዳታ ጠባቂ ሆነዋል። 5 ሺህ ናይራ አንድን ቤተሰብ ለአንድ ቀን መመገብ ይችላል።

ባለፈው ሳምንት በማዕከላዊ ናይጄሪያ የናሳራዋ ግዛት ዩኒቨርሲቲ ሩዝ ሲታደል ለመቀበል የወጡ የተወሰኑ #ተማሪዎች ተረጋግጠው #ሞተዋል

ባለፈው ወር የናይጄሪያ ገቢዎች አገልግሎት ሩዝ በቅናሽ ዋጋ ሲሸጥ በተፈጠረ ግርግር የተወሰኑ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው አሳውቆ ነበር።

ናይጄሪያ ውስጥ ባለው የኑሮ ውድነት ምክንያት በርካቶች የሚቀበሉት ደመወዝ ከወር ወር ሊያደርሳቸው እንዳልቻለ ቢቢሲ አስነብቧል።

Via https://publielectoral.lat/thiqahEth

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#RUSSIA ሩስያ ባለፈው ሳምንት ማንኛውም የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንቀስቃሴን #ሕገወጥ በማለት ፈርጃለች። የሩሲያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዓለም አቀፍ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የአደባባይ እንቅስቃሴን " #ጽንፈኛ " በማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴዎችን አግዷል። ይህ እገዳ ይፋ ከተደረገ በኃላ ባለፈው አርብ ምሽት የሩስያ ፀጥታ ኃይሎች በሞስኮ ከተማ በሚገኙ ፦ ° የተመሳሳይ ጾታ የምሽት ክበቦች (ክለቦች)…
#ሩስያ

ከዚህ ቀደም ማንኛውም አይነት #የግብረሰዶም እንቀስቃሴን #ሕገወጥ እና #ጽንፈኛ በማለት ፈርጃ የነበረችው ሩስያ አሁን ደግሞ የግብረሰዶም እንቅስቃሴን #የአክራሪነት እና #የሽብር ድርጊት ዝርዝር ውስጥ አካታዋለች።

በዚህም ማንኛውም ዓለም አቀፍ የግብረሰዶም እንቅስቃሴ በሩስያ በአሸባሪነት እና በአክራሪነት ዝርዝር ውስጥ ተካቷል።

ውሳኔው የተደረሰው የሩስያ የፍትህ ሚኒስቴር የቀረበለትን አቤቱታ ተከትሎ የግብረሰዶም ተከራካሪዎች #አክራሪ እና #አሸባሪ ተብለው እንዲጠሩ በህዳር ወር ላይ የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከወሰነ በኋላ ነው።

በቅርቡ የሩስያ ፍርድ ቤት በ " አክራሪ ድርጅት " ውስጥ ሚና አላቸው በሚል በመወንጀል ሁለት የመጠጥ ቤት / ባር ሰራተኞችን በእስር ቤት እንዲቆዩ እና እዛው እስር ቤት ሆነው ፍርዳቸውን እንዲከታተሉ ወሷል።

የሩሲያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ከዚህ በፊት ዓለም አቀፍ የግብረሰዶም የአደባባይ እንቅስቃሴን " #ጽንፈኛ " በማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴዎችን አግዶ ነበር።

በወቅቱም የሩስያ ፀጥታ ኃይሎች በሞስኮ ከተማ በሚገኙ ፦
° የተመሳሳይ ጾታ የምሽት ክበቦች (ክለቦች)
° የተመሳሳይ ፆታ ፓርቲዎችን ያዘጋጃሉ በተባሉ ባሮች
° የወንዶች ሳውና ቤቶች ላይ ዘመቻ አካሂደው ተጠርጣሪዎችን አስረው እንደነበር ይታወሳል።

በሩሲያ የተመሳሳይ ጾታ ጥምረት እውቅና #የለውም

በሩሲያ #ትዳር ማለት የወንድ እና የሴት ጥምረት ማለት ስለመሆኑ ትርጉም ለመስጠት የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ከ3 ዓመታት በፊት ተቀይሮ ነበር።

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ወይም ወደተለያየ ሂሳቦች ያስተላለፉ ግለሰቦች የወሰዱትን ገንዘብ በፍቃዳቸው እንዲመልሱ ያስመቀጠው የመጨረሻ ቀን ዛሬ ቅዳሜ መጋቢት 14 ያበቃል። ባንኩ ሰጥቶ የነበረው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነው። ገንዘቡን በአቅራቢያ ባለው ቅርንጫፍ ወይም በዲጂታል መንገድ ቀድሞ ገንዘቡ ወጪ ወደተደረገበት የባንኩ ሂሳብ ማስገባት ይቻል ነው የተባለው።…
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምን አለ ?

" ... አንድ ሰው ያወጣው ትልቁ ገንዘብ 304 ሺህ ብር ነው ፤ 567 ደንበኞች ጠፍተዋል፤ የጠፉት ደንበኞች 9.8 ሚሊዮን ብር ነው ያወጡት " - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ መግለጫ ሰጥተው ነበር። በዚህም መግለጫቸው ባንኩ አጋጥሞት ከነበረው ችግር ጋር በተያያዘ እስካሁን ስለደረሰበት ደረጃ አብራርተዋል።

ምን አሉ ?

- ችግሩ የት ጋር ነው  ያጋጠመው ? የሚለው ላይ በባለሙያ ጥናት እየተደረገ ነው ገና አላለቀም።

- አርብ መጋቢት 6 በተፈጠረው የሲስተም ችግር ከ801 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ተወስዶበት እንደነበርና 622 ሚሊዮን ያህሉን ወደ ባንኩ ተመላሽ ተደርጓል።

- ቀሪ 567 ግለሰቦች የወሰዱትን 9.8 ሚሊዮን ብር ማግኘት አልተቻለም።

- መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ምሽት ላይ ከ 3 ሰዓት ጀምሮ እስከ 8: 45 ድረስ ባለዉ ጊዜ ነው 25 ሺህ 761 ደንበኞች ብር 801.4 ሚሊዮን ነው የወሰዱት።

- ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በሂደቱ ዉስጥ የተሳተፉ 15 ሺህ ያህል የሂሳብ ቁጥሮች ተገኝተዋል።
 
- የሲስተም ችግር በነበረበት በወቅት 25 ሺህ 761 ደንበኞች ግብይት ፈጽመዋል። በዚሁ ሰዓት ችግር ያለበት 238 ሺ 293 ጊዜ ግብይት ተፈጽሟል። አንድ ደንበኛ በአማካይ ከ9 ጊዜ በላይ ግብይት ፈፅሟል።

- በእለቱ አንድ ወይም ሁለት ግብይት የፈጸሙ ደንበኞች ጥርጣሬ ውስጥ አልገቡም። ያለ አግባብ የተወሰደ ገንዘብ ከሂሳባቸው ተቀናሽ ተደርጎ እንደሚመለስ ተደርጓል።  በአካውንታቸው ላይ በቂ ገንዘብ ከነበራቸው 10 ሺህ ደንበኞች ላይ 44 ሚሊየን ብር ተመላሽ ተደርጓል።

- ቀሪዶቹ 15 ሺህ 8 ደንበኞች 207 ሺህ ግብይት ፈጽመዋል። እያንዳንዱ በዚያ ሌሊት በአማካይ 14 ጊዜ ግብይት ፈፅሟል።

- ሂሳባቸው ላይ ካለው ብር ወስደው ከነበሩ 15 ሺህ 8 ደንበኞች መካከል እስከ ትናንት ማታ ድረስ 372 ሚሊየን ብር ድረስ ተመላሽ ተደርጓል። ከእነዚህ ውስጥ 9 ሺህ 281 ሰዎች ሙሉ በሙሉ ያለባቸውን መክፈላቸውን 5 ሸህ 160 በከፊል መልሰው ቀሪውን ለመክፈል ቃል ገብተዋል።

- እስካሁን በድምሩ ሊጠፋ ከነበረው 800 ሚሊየን ብር ውስጥ 623 ሚሊየን ብር ተሰብስቧል። ቀሪውን የማስመለስ እና የማፈላለግ ስራ እየተከናወነ ነው።

- በህገ ወጥ መንገድ ገንዘብ ከወሰዱት መካከል 567 ደንበኞች ጠፍተዋል። ሙሉ አድራሻውን አለን፤ እየፈለግናቸው ነው። እነዚህ የጠፉት ደንበኞች የወሰዱት አጠቃላይ ገንዘብ 9.8 ሚሊየን ብር  ነው። ከዚህም ውስጥ አንድ ሰው ያወጣው ትልቁ ገንዘብ 304 ሺህ ብር ነው።

- ገንዘብ ያልመለሱ ደንበኞች በባንኩ ቅርንጫፎች በያሉበት ስም ዝርዝራቸው ይለጠፋል። በባንኩ የማበራዊ ትስስር ገጾች ስማቸውን ይወጣል። ከዚህ ባልፉ ስማቸው ከነፎቶዋቸው ጭምር ይወጣል። በዚህም መመለስ ካልቻሉ በህግ ይጠየቃሉ።

- ያለአግባብ የተወሰደ አንድ ብር እንኳ ሳይቀር እናስመልሳለን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን መረጃ የአል አይን ኒውስ እንዲሁም ከካፒታል ጋዜጣ መውሰዱን ይገላጻል።

@tikvahethiopia
#DigitalEthiopia

ዛሬ " የዲጂታል ኢትዮጵያ " የግምገማ መድረክ በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ተካሂዷል።

ጠ/ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ የፌደራል እንዲሁም የክልል ከፍተኛ አመራሮች እና የዘርፉ ተዋናዮች በመድረኩ ተሳታፊ ነበሩ።

የ " ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 " ስትራቴጂ በዋናነት የዲጂታል መሰረተ ልማት በመገንባት እና በማስፋት የአገሪቱን ምጣኔ ኃብታዊ እድገት ማፋጠንን ዓላማ ያደረገ ሲሆን በአምስት ዓመታት ውስጥ ለመተግበር የታቀደ ነው።

ዛሬ ላይ የስትራቴጂውን የ4 አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል።

- ዲጂታል ሊትረሲን ለማስፋት፤
- የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቱን የማሳደግ
- የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፤
- የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትና የሳይበር ጥበቃ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በሚመለከታቸው የመንግሥት ኃላፊዎች ገለጻ ተደርጎባቸዋል።

በዚህ መድረክ በቅርቡ በንግድ ባንክ ላይ ያጋጠመው ጉዳይ በስፋት እንደማሳያ ሲቀርብ ነበር።

ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የብሔራዊ ባንክ ገዢው አቶ ማሞ ምህረቱም አስተያየት ሰጥተው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን አሉ?

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ " በሳይበር ጥቃት በ2022 በዓለም ላይ 9 ትሪሊዮን ዶላር በጠላፊዎች ተመዝብሯል" ብለዋል።

" ይህ ያጋጠመው ችግር ሰዎች አቅደው አምሯቸውን ተጠቅመው ለማለት ያስቸግራል፤ ከውስጥ ያሉ ሰዎች የፈጠሩት ችግር ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ይሄ ማለት [የሳይበር ጥቃት] አይከሰትም ግን ማለት አይደለም። በሺዎች የሚቆጠሩ አታኮች በየቀኑ ተቋሞቻችን ላይ ይፈጸማሉ፤ ኢንሳ ብትመጡ ይሄንን ትመለከታላችሁ " ብለዋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዢው ምን አሉ?

አቶ ማሞ ምህረቱ " የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ችግር በውስጥ ሰዎች የተፈጠረ ነው [ Human Error] ነው " ብለዋል።

" በዚሁ አጋጣሚ የፋይናንስ ሥርዓቱ ግልጽ ነው። ምን አይነት ገንዘብ የት እንደተላከ ከየት እንደወጣ የት እንደገባ ይታወቃል። በእንደዚህ አይነት ስህተቶች የሚጠፋ ገንዘብ አይኖርም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" አሁን ላይ 80 በመቶ የወጣው ገንዘብ ተመላሽ ተደርጋል " ብለዋል።

ብሔራዊ ባንክ የዚህን ክስተት ሙሉ የምርመራ ውጤት በሳምንት ውስጥ ይፋ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

#AddisAbabaTikvahFamily

@tikvahethiopia