TIKVAH-ETHIOPIA
" ፍርዱ ለሚዲያ 16 ዓመት ከተባለ በኃላ ወደ 10 ዓመት ዝቅ እንዳለ ሰምቻለሁ " - ጸጋ በላቸው " ጉዳዩ ለቢሮዉም ሆነ ለኔ አዲስ ነው " - ወ/ሮ ወይንሸት ብርሀኑ በሀዋሳ ከተማ የዳሽን ባንክ ሰራተኛ ከሆነችዉ ጸጋ በላቸዉ ጋር በተያያዘ በጠለፋና አስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ  የነበረው ኮንስታብል የኃላመብራት ወ/ማርያም " ለብዙዎች አስተማሪ ይሆናል " በተባለ መልኩ የ16 አመት ጽኑ እስራት…
" ... ሌላዉ ቢቀር እንዴት እግሯን አጎንብሰዉ ያጠቧት ሴት ፖሊሶች ይረሳሉ ? " - የሀዋሳ ፖሊስ

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ስሜን የሚያጠለሹ አካላት ከድርጊታቸው ይታቀቡ ሲል አሳሰበ።

ፖሊስ ፤ " የተለያዩ የሶሻል ሚዲያ በመጠቀም የሀዋሳ ከተማን ገጽታ ለማጠልሸት የሚሰሩ አካላት ከድርጊታቸዉ ሊታቀቡ ይገባል " ብሏል።

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " ከሰሞኑ በተደጋጋሚ እንደሚታየዉ ለሰላም ሌት ተቀን እየደከመ ያለዉን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ በመጥቀስ ስም የማጠልሸት አካሄዶች ውስጥ የገቡ አካላት መኖራቸዉን እየተመለከትን ነው " ብለዋል።

ድርጊቱ አስነዋሪ መሆኑንና የሀዋሳ ከተማን የጸጥታ አካላት ያሳዘነ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢንስፔክተር መልካሙ ፥ " በቅርቡ ' ቲክቶክ 'ን ተጠቅሞ የንግድ ድርጅቴ (የውስኪ ቤቴ) ተዘጋ በማለት ሲከስ የነበረዉ ግለሰብ ልክ አይደለም " ብለዋል።

" ጠጥቶ አልከፍልም ያለዉን አካል ለህግ ማቅረብ ሲቻል የተከበረውን የፖሊስ ስም ማጥፋቱ በፍፁም ልክ አልነበረም ፤ አሁንም ቅሬታ ካለ የቆምነው ህግ ለማስከበር ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ፥ ወይዘሪት ጸጋ በላቸዉ ከተጠለፈችበት ቀን ጀምሮ እሷን ለማግኘት የተንከራቱዉው ወደ ሀዋሳ በመጣችበት ወቅትም ጥበቃና ድጋፍ ባደረገላት የፖሊስ ሀይል ላይ የሰነዘረችዉ ሀሳብ ልክ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

" እሷና ቤተሰቦቿ እንዲያርፉበት ለተፈቀደላቸው ቤትና ለተሰጣቸዉ ጥበቃ ማመስገን ሲገባት እንደእስር ተቆጥሮ ለሚዲያ መጮህ ልክ አይደለም " ብለዋል።

" ሌላዉ ቢቀር እንዴት እግሯን አጎንብሰዉ ያጠቧት ሴት ፖሊሶች ይረሳሉ ? በማለት ለፖሊስ በጎ አድራጎት ምላሹ ይህ ሊሆን አይገባም " በማለት ተችተዋል።

ጨለማ ብርድና ቁር ሳይል በትጋት የሀዋሳ ከተማን የሰላም ተምሳሌት ለማድረግ በሚተጋዉ የጸጥታ ሀይል ላይ የተለያዩ የሶሻል ሚዲያዎችን በመጠቀም የሚሰነዘሩ የስም ማጥፋቶች ልክ አለመሆናቸዉን በመግለጽ ግለሰቦች ከዚህ ድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል።

በቅርቡ በፀጋ በላቸው በቲክቶክ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ አግቶ ጠልፎ ወስዶ ባሰቃያት ግለሰብ ላይ በሚዲያዎች የተገለጸው ፍትህ ከእውቅናዋ ውጭ በሆነ መልኩ የእስራት ፍርዱ ከ16 አመት ወደ 10 መቀነሱን እንደሰማች ተናግራ ያደረባትን ሀዘን መግለጿ ይታወሳል።

ወደ 10 ዓመት ዝቅ እንዲል በተደረገው ፍርድ እጅግ እንዳዘነች የገለጸችው ፀጋ ፤ ካሳለፈችው የስቃይ ሁኔታ ጋር በፍፁም እየሚገባ እንዳልሆነ በእምባ ታጅባ ገልጻ ነበር።

በዚህም ወቅት ህዝብ የማያውቀው ብዙ ነገር እንደተፈፀመ ፤ ከጠለፋው እገታ ከተለቀቀች በኃላ በማታውቀው ምክንያት በፖሊስ ታስራ እንደነበር አሳውቃ ነበር።

መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከዉ የሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia