TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጠንቀቁ ⚠️ ከኦንላይ ዘራፊና አጭበርባሪዎች እራሳችሁን ጠብቁ። ነገሩ እንዲህ ነው ... ገንዘባቸውን ኦንላይን ተጭበርብረው የተበሉ ግለሰቦች መጀመሪያ በማያወቁት የውጭ ሀገር ስልክ ቁጥር በ #ዋትስአፕ / በ #ቴሌግራም መልዕክት ይደርሳቸዋል። ስልካቸውን / username እንዴት እንደሚያገኙት ባይታወቅም። የሚደርሳቸው መልዕክት " ጥሩ የስራ እድል እንደሆነ ፣ በትንሽ ስራም ብዙ ትርፍ እንደሚያገኙ…
#ScamAlert

በርካታ ሰዎች አሁንም በኦንላንይን #አጭበርባሪዎች ገንዘባቸውን የተጭበረበሩ ይገኛሉ።

ዛሬ እንዲሁም ትላንትና " #ተዘረፍን " ሲሉ መልዕክት የላኩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በዋስትስአፕ እና በቴሌግራም  ያነገሯቸው ሰዎች ፤ " ቀለል ያለ ስራ ስሩና ትርፋማ ሁኑ " በማለት ከ150,000 ብር በላይ እንዲልኩላቸው ካደረጉ በኃላ ሰዎቹ የውሃ ሽታ ሆነዋል።

" በእኛ የደረሰ በናተ እንዳይደርስ ለማንም የማታውቁት ሰው መልዕክት አትመልሱ ፤ እንዲሁ ቁጭ ተብሎ ምንም ሳይደክሙ ብቻ ትርፋማ መሆን አይቻልምና ገንዘባችሁ እንዳትበሉ " ብለዋል።

በድጋሚ ማኛውም የማታውቁት ሰው በቴሌግራም ፣ ዋትስአፕ፣ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም ላይ " ትርፋማ ስራ እናሰራችሁ " ወይም ሌላም መልዕክት ሲልክላችሁ አትመልሱ።

ሌላው የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እና ሌሎች የመገልገያ እቃዎችን " #በርካሽ እንሸጥላችኃለን ቅድሚያ የሂሳቡን ግማሽ ላኩ " ለሚሏችሁም ሰዎች መልስ አትስጧቸው / እቃውን ይላኩና ገንዘቡን ላኩላቸው።

አንድ የቤተሰባችን አባል " አዲሱን አይፎን 15 ስልክ ከአሜሪካ በርካሽ እንልክልሃለን ቅድሚያ ግን ግማሹን አስገባ " በማለት 50 ሺህ ብር ካስላኩት በኃላ አድራሻቸውን አጠፋፍተዋል።

ከዚህም ባለፈ ደግሞ ወደ ውጭ ሀገራት ለትምህርት ለስራ እንላካችሁ የሚሉም በዝተዋልና አድራሻሸውን ፣ ህጋዊናታቸውን አጣሩ። በቅድሚያ ምንም አይነት ክፍያ እንዳትከፍላቸው። " ቅድመ ክፍያ የለውም " ካሉም በኃላ በተለያየ መንገድ ጉዳይ መጨረሻ በሚል የሚበዘብዙ አሉና ተጠንቀቁ።

@tikvahethiopia