TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እነሆ የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓልን ይበልጥ የሚያደምቅ ልዩ አድዋ የሞባይል ጥቅል አሰናድተን እስከ 20% በሚደርስ ቅናሽ በአርዲ ቻትቦት፣ በማይ ኢትዮቴል እና *999# እንዲሁም በቴሌብር http://onelink.to/fpgu4m ከተጨማሪ 10% ቅናሽ ጋር አቅርበናል።

ጥቅሉን ለራስዎ በመግዛትና በስጦታ በማበርከት በዓሉን በደስታ ያሳልፉ!

መልካም የድል በዓል!

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
#Adwa128

የሀገር መከላከያ ሠራዊት የዘንድሮው 128ኛው የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ ስነስርዓቶች እንደሚከበር አሳውቋል።

በዓሉ በአ/አ ፒያሳ በሚገኘው የ " ዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም " እንደሚከበር ገልጿል።

የዓድዋ ጀግኖችን የሚዘክር የ34 ደቂቃ ዶክመንታሪ ፊልም፣ ቢል ቦርድ፣ በራሪ ወረቀቶች፣ ሎጎ፣ መሪ ቃል እና ሠራዊቱ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ሆኖ የሚወያይበት ፅሁፍ ተዘጋጅቷል ተብሏል።

በዕለቱ የካቲት 23 ቀን ወታደራዊ የሰልፍ ትርኢት እና ድሉን የሚያስታውሱ ልዩ ልዩ ትርኢቶች ፒያሳ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ይቀርባል ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የሟቾች ቁጥር ከ8 ወደ 11 ከፍ ብሏል " - ኢስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ ወደ ሐዋሳ ጉዞውን እያደረገ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር 11 መድረሱን የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። ትላንት ማምሻውን መነሻውን ከአርባ ምንጭ አድርጎ ወዘ ሐዋሳ እያመራ የነበረ ተሽከርካሪ በዎላይታ ዞን በዱጉና ፋንጎ ወረዳ ፋንጎ ኮይሻ ቀበሌ ልዩ ቦታው " ዞንጋ " በተባለው ቦታ አስከፊ…
#ሀዋሳ🕯

በቅርቡ ከአርባ ምንጭ ወደ ሐዋሳ ሲመለሱ በዎላይታ ዞን ውስጥ በመኪና አደጋ ህይወታቸዉ ላለፈ የሐዋሳ ከተማ ወጣቶች የሻማ ማብራትና የገቢ ማሰባሰቢያ  ፕሮግራም በከተማ ደረጃ ከንቲባዉ በተገኙበት ተካሄደ።

በድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይዎታቸዉ ያለፉ የጤና ቡድን አባላትን ለመዘከር ያለመ የሻማ ማብራትና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የተጎጅ ቤተሰቦች ፣ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሲዳማ ባህል ሽማግሌዎች በተገኙበት ተካሂዷል።

በሻማ ማብራት ፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ መኩሪያዬ መርሻዬ ፤ " እንደሀዋሳ ብቻ ሳይሆን እንደሀገር አልቅሰናል  " ብለዋል።

ከዚህ አይነት አስከፊ የትራፊክ አደጋ ለመዉጣት ጥንቃቄ ብቻ ሳይሆን ጸሎትም ያስፈልገናል ሲሉ ገልጸዋል።

የተጎጅ ቤተሰቦችን ለመደገፍ ለተሰናዳዉ ፕሮግራም በከንቲባዉ ቢሮ 3 መቶ ሺህ ብር እንዲሁም በግላቸዉ 10 ሽህ ብር በማበርከት ድጋፉን አስጀምረዋል።

ፕሮግራሙን ለመካፈል ተደግፎ የመጣዉና ከአደጋዉ የተረፈዉ ወጣት ፋሲል በበኩሉ ሀዘኑን መቋቋም ከባድ መሆኑን በመግለጽ በእንባ ታጆቦ ወደቦታዉ ተመልሷል።

በእለቱ ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ  በጎፈንድሚና ለዚህዉ ተብሎ በተከፈተዉ የባንክ አካዉንት መሰብሰብ ተችሏል።

የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙን ያዘጋጀዉ ኮሚቴ  " በድንገት ያጣናቸዉ ጓደኞቻችን ልጆችና ቤተሰቦች ለመርዳት ሁሉም ወጣት ድጋፍ እንዲያደርግ " ሲል ጠይቋል።
 
ለዚህ ሲባል የተከፈተዉ የባንክ አካዉንት ቁጥር 1000610475667 መሆኑን ገልጿል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#Amahra

በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት በላይ ጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን 11 የቅኔ ተማሪዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በሜጫ ወረዳ ብራቃት ቀበሌ በሚገኘው በላይ ጋፊት  ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 11 የቅኔ ተማሪዎች  እንዲሁም 1 በግብርና የሚተዳደር የአካባቢው ነዋሪ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተገድለው እንደሞቱ ተነግሯል።

የሟች ቤተሰቦች በሰጡቅ ቃል የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 6:00 ገደማ እንደሆነ ተማሪዎቹ በጎጇቸው ሳሉ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ፦

- " ፋኖን ታስጠልላላችሁ " ፣

- " ለፋኖ አባላት ጥይት የማያስመታ መድኃኒት ትሰጣላችሁ "

- " እናንተም የፋኖ አባላት ናችሁ " በማለት 11 ተማሪዎች እንዲሁም የጩኸት ድምፅ ሰምቶ ወደ ጉባኤ ቤቱ ሲሄድ የነበረን የአካባቢው ነዋሪ መግደላቸውን ገልጸዋል።

አሁን የተገለጸው የሟቾች ቁጥር በዛሬው ዕለት በትክክል የተገኘ እንደሆነ እና በሰዓቱም በጉባኤ ቤቱ የነበሩ በርካታ ተማሪዎች ወደተለያየ አቅጣጫ ስለተበታተኑ የሟቾች ቁጥር አሁን ከተጠቀሰው ቁጥር ሊልቅ እንደሚችል ተጠቁሟል።

ከጥቂት ጊዜያት በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ ከ12 ያላነሱ የአቋቋም ተማሪዎች በአዴት ፍልሰታ ደብር ተገድለው እንደነበር ተገልጿል።

የዞኑ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ስለ ጉዳዩ እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም። #ተሚማ

@tikvahethiopia
የወልዲያ ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ ካሳሁን በጥይት ተመተው መገደላቸው ተነግሯል።

ኃላፊው ትናንት ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን የቅርብ ጓደኞቻቸውን ዋቢ በማድረግ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

ቃላቸውን የሰጡ ከጓደኞቻቸው አንዱ ፤ " ትናንት ጠዋት 2 ሰዓት አካባቢ ሆርማት በተባለ የከተማው አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በጥይት ተመትተው ተገድለዋል። አጥቂዎቹ ሸሽተው አምልጠዋል " ብለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በባለሦስት እግር ተሸከርካሪ (ባጃጅ) ሆነው ጥቃቱን መፈፀማቸው ነው የተነገረው።

ጓደኞቻቸው ፤ ከዚህ ቀደምም መኖሪያ ቤታቸው ላይ ከዚህ በፊት ቦምብ ተወርውሮ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በወልዲያ ገቢዎች ጽ/ቤት ይሰሩ እንደነበርና በነበራቸው የስራ ትጋት በክልል ደረጃ ተሸላሚ እንደነበሩም ግልጸዋል።

አቶ ዓለማየሁ የከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት ኃላፊ ሆነው ሲሰሩም ከመሬት ወረራ ጋር በተያያዘ በርካታ ሥራዎችን ሲሰሩ እንደነበር ፤ ግድያውም ከዚህ ሥራቸው ጋር ሳይያያዝ አይቀርም የሚል ግምት እንዳላቸው አመልክተዋል፡፡

ሬድዮ ጣቢያው ጉዳዩን በተመለከተ ለከተማው ፖሊስ ጽ/ቤት ሲደውል " መረጃ በስልክ አልሰጥም "  የሚል ምላሽ እንደተሰጠው በዘገባው ጠቅሷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ተመስገን_ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን “ትክክለኛ ፍትሕ ይሰጣሉ ብዬ ስለማላምን ይነሱልኝ” ያሏቸው ዳኛ “ #አልነሳም” አሉ።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጥር 7 ቀን 2016 ዓ/ም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰሚ ችሎት ቀርበው በነበረበት ወቅት፣ “የግራ ዳኛ የሆኑት ክቡር አቶ አሕመድ መሐመድ ትክክለኛ ፍትህ ይሰጣሉ ብዬ ስለማላምን በዚህ ጉዳይ ከችሎት እንዲነሱልኝ ምክንቻቶቼን አቀርባለሁ” ብለው ያዘጋጁትን ምክንያታዊ ፅሑፍ በዝርዝር አቅርበው ነበር።

ችሎቱም የጋዜጠኛውን አቤቱታ ካደመጠ በኋላ፣ የዳኛውን ከችሎት መነሳትና አለመነሳትን ጉዳይ ለመወሰን፣ ጋዜጠኛ ተመስገን በዋናው ክሳቸው ይሰጣሉ ተብሎ የሚጠበቀውን መለስ ለመቀበል ለጥር 28 ቀን 2016 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ አይዘነጋም።

ይሁን እንጂ ለጥር 28 ቀን 2016 ዓ/ም ተሰጥቶ የነበረው ቀጠሮ፣ “አቤቱታ የቀረበባቸው ዳኛ ስልጠና ላይ ስለሆኑ ውሳኔ አልሰጠንም” በሚል ለየካቲት 21 ቀን 2016 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶበት ተራዝሞ ቆይቷል።

በየካቲት 21 ቀን 2016 ዓ/ምቱ ችሎት ደግሞ፣ ጋዜጠኛው ከችሎቱ እንዲነሱ አቤቱታ ያቀረቡባቸው ዳኛ “አልነሳም” ብለዋል።

ጋዜጠኛው ያቀረቡት የዳኛውን “ከችሎት ይነሱልኝ” አቤቱታ ችሎቱ ወድቅ ያደረገው፣ “እንዲነሱ የተጠየቁት ዳኛ መልካም ስብዕና ያላቸው መሆኑን” በመጥቀስ ነው።

ጋዜጠኛ ተመስገን፣ የተሳሳተ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ዋቢ አድርገው በመጥቀስ “ዳኛው ይነሱልኝ” ብለው ባቀረቡት አቤቱታ ሳቢያ የ1,000 (አንድ ሺሕ ብር) ቅጣት ተፈርዶባቸው ክፍያውን ፈጽመዋል።

ጋዜጠኛው ተመስገን፣ ፍርድ ቤቱ ‹ዳኛው ስህተት ሰርተዋል ወይስ አልልሩም?› ወይም ‹ከሳሽ ያለአግባብ ጠቅመዋል ወይስ አልጠቀሙም?› በማለት የቀረበውን ቅሬታ መመርመሩን ወደ ጎን በመተውና የቀድሞ ስብእናቸውን መነሻ በማድረግ ቅሬታዬን ውድቅ ማደረጉ እጅጉን አስደንግጦኛል” ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም፣ “የፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እኔን ስጋት ላይ የጣለ ነው” ያሉ ሲሆን፣ ጋዜጠኛው ላይ የቀረበውን የይግባኝ መልስ ለመስማትም ለመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም ቀጠሮ ተስጥቷል።

መረጃውን አዘጋጅዮ የላከው የአ/አ ተክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#Amahra

በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም " ማንነታቸው አልታወቀም " የተባሉ #ታጣቂዎች አንድ መነኩሴ ሲገድሉ የገዳማት ንብረት ተዘርፏል።

በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በሚገኙ ሁለት ገዳማት " ማንነታቸው ያልታወቀ  ታጣቂዎች " ባደረሱት ጥቃት አንድ መነኩሴ ሲገደሉ የገዳማቱ ንብረቶች እንደተመዘበሩ ተገለጸ።

ሀገረ ስብከቱ ስለጉዳዩ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ፅ/ቤት በፃፈው ደብዳቤ ምን አለ ?

- በሀገሪቱ ላይ የተከሰተውን ወቅታዊ ችግር እንደ ትልቅ አጋጣሚ በመጠቀም በሀ/ስብከቱ በሚገኙት በተለያዩ ወረዳዎች ሥር በሚተዳደሩ አድባራትና ገዳማት በተካሄደው ጦርነትና እየተፈጠረ ባለው ግጭት ብዙ ጉዳት ደርሷል።

- በማቻክል ወረ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው በዋሻ አምባ አቡነ ተ/ሃይማት አንድነት ገዳም ታህሳስ 27 / 2016 ዓ.ም ሌሊት ማንነታቸው ያልታወቁ 8 ግለሰቦች ከገዳሙ ውስጥ በመግባት፡-

1ኛ. የገዳሙን አመሰራረትና የገዳሙን ሙሉ ታሪክ የያዘ የፊልም ዶክሜንት

2ኛ. የገዳሙ መጠበቂያ የሆኑ 2 ዘመናዊ ክላሾች ከእነ ሙሉ ተተኳሹ፤

3ኛ. በጥሬ ገንዘብ ከ100,000 /ከአንድ መቶ ሺህ ብር/ በላይ፤

4ኛ. ወርቅ በግራም 20 ግራም የሚመዝን

5ኛ. ለመነኮሳቱ በየጊዜው የሚሰፋላቸውን ሙሉ ጣቃ ልብስ

6ኛ. ዘመናዊ ተች የእጅ ስልኮች ብዛት 5

7ኛ. አምስት ጠገራ ብርና የአንገት ጌጣ ጌጦች

8ኛ. የጥበቃ ክፍሉን መጽሐፍና ብር 2000.00 በአጠቃላይ የተዘረዘሩትን የገዳሙን ንብረቶች ከመዘረፋቸውም በላይ ገዳማውያኑን በማንገላታትና የገዳሙን አበምኔት እማሆይ ወለተ ማርያም ገላውን አፍነው /አግተው/ በመውሰድ ከፍተኛ እንግልት አድርሰውባቸዋል።

- በአዋባል ወረዳ ቤተክህነት ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው በመካነ ቅዱሳን ጣቢያ ቅ/ጊዮርጊስ አንድነት ገዳም የተፈጠረ ችግር ጥር 27 ለ28 አጥባህ ከሌሊቱ በ6፡00 ሰዓት ማንነታቸው ያልታወቁ በቁጥር 5 የሆኑ ታጣቂዎች ገዳሙ ውስጥ ገብተዋል።

2 ክላሽ ጠበንጃ ፣ 1 ገጀራ ፣ 1 ሽጉጥ ፣ 1 አለንጋ የያዙ ታጣቂዎች የገዳሙን አበምኔት ቤት እንዲያሳዩአቸው ዘበኞችን በማፈን ይዘው መ/ሃይማኖት ቆ/አባ ሊባኖስን ፀበልተኛ እንደታመመ አስመስለው " ክፈቱ " ሲሏቸው " እኔ አልከፍትም " ወደ አባ ገ/ሕይወት ሂዱ ሲሉ ይነግሯቸዋል።

አባ ገ/ሕይወትም ጋር ሄደው በመሳሪያ አስገድደው ወደ ገዳሙ አባት መጋቢ ሃይማኖት ቆሞስ አባ ሊባኖስ አስታጥቄ በድጋሚ ሄደው " ክፈቱ " ሲሏቸው " ያለ ሰዓት አይከፈትም " የሚል ምላሽ ሲመልሱ የቤቱን በር በ5 ጥይት ደብድበዋል።

በድጋሚ የካቲት 20 ለ21 አጥቢያ ከምሽቱ በግምት 3፡00 ሰዓት ሲሆን ከገዳሙ ገብተው የእቃ ቤቱን በማንኳኳት የእናቶችንና የአባቶች7 ገዳም ቤቶችን በር ሲመቱ ቆይተው፦

👉  አባ ገ/ሥላሴ ታመነ የተባሉትን በገጀራ መተው #ገድለዋቸዋል

👉 ዲ/ን ዮሐንስ እና አብርሃም አያና ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርሰውባቸዋል።

👉 15 የሞባይል ስልክ ከፀበልተኛው ወስደዋል።

በቁጥር ያልታወቀ ገንዘብና ንብረት ወስደዋል።

በዚህም በ2ቱም ገዳማት ላይ ከፍተኛ የግድያ ፣ የድብደባና የንብረት ዝርፊያ እየተፈጸመ ስለሆነ ለወደፊቱም በቤተ ክርስቲያኗ፣ በገዳማት ላይ ከፍተኛ ችግር እየገጠመን ስለሆነ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥ ሲል አሳስቧል።

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ የዘንድሮው 128ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ዋዜማ በታሪካዊቷ ከተማ ዓድዋ በድምቀት ሲከበር ውሏል።

የበዓሉ ዋዜማ ከጥዋት አንስቶ እስከ ምሽት ድረስ በተለያዩ የአደባባይ እና ሌሎች ስነስርዓቶች በድምቀት ተከብሯል።

የዓድዋ በዓል በተለይ ባለፉት ዓመታት በትግራይ ጦርነት ወቅት እጅግ ተቀዛቅዞ እንደነበር ፤ ሰዎችም በከፍተኛ ሀዘን ምክንያት በዓሉን በድምቀት ሲያከብሩት አልነበረም። ቱሪስቶችም በጦርነት ምክንያት ወደ ስፍራው መጓዝ አይደፍሩም ነበር።

ዘንድሮ ከተማው ሰላም መሆኑን ተከትሎ የበዓሉ ዋዜማ እጅግ በደመቀ በተለይም በአደባባይ ስርዓቶች ሲከበር ውሏል። በነገው ዕለትም የተለያዩ ዝግጅቶች ይኖራሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

ወደ ዓድዋ የተጓዘው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል መረጃዎችን የሚያጋራን ይሆናል።

@tikvahethiopia