TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EMA

የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝዳንትና የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለሚዲያዎች የሰጡት ቃለምልልስ ከምርጫ በፊት እንዳይሰራጭ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አሳሰበ።

ቃለምልልሱ በዚህ በጥሞና ወቅት መተላለፍ የለበትም ብሏል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ እድሪስ ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፥ ምንም እንኳን ቃለ መጠይቁ የመንግስት የስራ ክንውኖች ላይ ያተኮረና የምርጫ ቅስቀሳ እንዳልሆነ ቢታወቅም በዚህ ጥሞና ወቅት ሊተላለፍ አይገባም ብለዋል።

የቃለ መጠይቁ መተላለፍ ብዥታ እንዳይፈጥር ሲባል ከምርጫው በፊት መተላለፍ እንደሌለበት አቶ መሀመድ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ቃለ መጠይቁ እንዳይተላለፍ የተፈለገው መንግስት በዚህ ዓመት የተሻለ ምርጫ እንዲካሄድና ፍትሀዊ እንዲሆን ፍላጎት ስላለው መሆኑን ተናግረዋል።

ስለዚህ ቃለ መጠይቁን ለማስተላለፍ ማስታወቂያ እየሰሩ ያሉ መገናኛ ብዙሃንም ሆኑ ለማስተላለፍ የተዘጋጁ ከወዲሁ #እንዲያቆሙ አሳስበዋል።

በተመሳሳይ የማሕበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የምርጫ ቅስቀሳ የሚመስሉ መልዕክቶችን እያስተላለፉ ያሉ አካላትም ከድርጊታቸው መታቀብ አለባቸው ብለዋል።

መገናኛ ብዙሃንም ቢሆኑ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት በመጠናቀቁ ቅስቀሳ መሰል ዘገባዎችን ከማስተላለፍ ሊጠነቀቁ ይገባል ሲሉ ማሳሰባቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ይገልፃል።

@tikvahethiopia
#EMA

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን (ኢመብባ) በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰሩ ሁሉም መገናኛ ብዙሃን የሀገሪቱን ሉዓላዊ ግዛት ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ስያሜዎችን ከመጠቀም እንዲቆጠቡ አሳሰበ።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል የሚደረገውን ኦፕሬሽን ጋር ተያይዞ በመደበኛም ሆነ በበየነመረብ የሚሰሩ ዜናዎች እና ፕሮግራሞች ላይ ክትትል ማድረጉን የገለፀ ሲሆን በክትትሉ ወቅት ህግን ያላከበሩ አዘጋገቦችን ተመልክቻለሁ ብሏል።

በዋነኝነት በኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀውን ህወሓትን የትግራይ መከላከያ ሰራዊት / ኃይል / የሚል ስያሜ መጠቀም መሆኑን አንስቷል።

በክልል ደረጃ "የመከለከያ ሰራዊት" የሚባል ኃይል አለመኖሩን የገለፀው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እንዲህ አይነት ስያሜ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ የሀገር ደህንነትን እና የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም የሚጎዳ ነው ብሏል።

የህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት ጥቅምት 2013 ዓ/ም የቀድሞው የትግራይ ክልል መንግስት በህገ - መንግስት ሽሮ አዲሱን ግዚያዊ አስተዳደር አቋቁሟል ሲል ያስታወሰው ኢመብባ ምርጫ ቦርድ በክልሉ ምርጫ አካሂዱ ክልሉን የሚያስተዳድረው አካል እስኪመረጥ ድረስ በአንዳንድ ሚዲያዎች ዘገባ ውስጥ እምደሚታየው "የትግራይ ክልል መንግስት" የሚባል አካል የለም ብሏል።

በክልሉ ምርጫ እስኪካሄደ ድረስ ትግራይን እንዲመራ ስልጣን የተሰጠው ጊዜያዊ አስተዳደሩ ነው ሲልም አክሏል።

የኢመብባ ፥ መደበኛ ሆኑ የበየነ መረብ ሚዲያዎች "የትግራይ መከላከያ ሰራዊት/ኃይል/" እንዲሁም "የትግራይ ክልል መንግስት" የሚል ስያሜ ከመጠቀም ተቆጠቡ ሲል አሳስቧል።

መ/ ቤቱ ስያሜዎቹን ሲጠቀም በተገኘ የመገናኛ ብዙሃን ተቋም ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
#EMA

የኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ትላንት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ "አሸባሪዎችን ከእነአስተሳሰባቸው ቀብረን ኢትዮዽያን እናስቀጥላለን" በሚል ርዕስ ያሰፈሩትን ጹሑፍ ተንተርሶ አዲስ ስታንደርድ ሚዲያ ወደ እንግሊዝኛ ሲተረጉመው በዋና ዳይሬክተሩ ያልተባለ እና ከፍተኛ የደኅንነት አንድምታ ያለው መልዕክት ጨምሮ መዘገቡን የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ገልጿል።

ባለሥልጣኑ ለጃክሊን ፐብሊኬሽን (አዲስ ስታንዳርድ) በጻፈው ደብዳቤ

''...ነውረኛ ድርጊቶች እንኳን ሊገስፁ ቀርቶ እንዲያውም ቀለብ ከመስፈር ጀምሮ የህክምና መድሀኒቶችና የመገናኛ መሳሪያዎችን እያመቻቹ መገኘታቸው ሳያንስ መንግስትን ሲተቹ፤ ሲጎነትሉና ሲያስፈራሩ ማየት ልብን ያደማል፤ ጨጏራ ይመልጣል፤ ቆሽትን ያሳርራል።'' የሚለውን የዋና ዳይሬክተሩን ጹሑፍ

“Let alone condemning, these countries are helping the T.P.L.F. including feeding it, providing medicine, communication equipment and providing arms ” በሚል መተርጎሙ ሀሰተኛ ያልተባለና የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም የሚጎዳ እንደሆነ ያነሳል።

ባለሥልጣኑ ሚዲያው አንባቢውን እና የደኅንነት ተቋሙን ይቅርታ እንዲጠይቅና ለፈጸመው ከባድ ጥፋትም በአስቸኳይ እርማት እንዲያደርግ ያዛል።

አዲስ ስታንደርድ በድረገጹ ላይ ዘገባው ላይ ለነበረው የትርጉም ስህተት በኤዲተሮቹ በኩል ይቅርታ ጠይቋል።

ስህተቱ ''በትርጉም ወቅት የተፈጸመ ስህተት መሆኑን እና የዋና ዳይሬክተሩን መግለጫ በተሳሳተ መንገድ ለማቅረብ የተደረገ ሙከራ አለመሆኑን ለአንባቢዎቻችን ማረጋገጥ እንፈልጋለን'' ብሏል።

telegra.ph/EBA-08-26

@tikvahethiopia
#EMA

ከዛሬ ጀምሮ በአገር ውስጥ የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች የውጭ አገር ፕሮግራሞችን ሊንክ አድርጎ ማስተላለፍ ከዛሬ ጀምሮ መከልከሉን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሃመድ እድሪስ አሳውቀዋል።

አቶ መሃመድ ይህ ያሳወቁት ለኢዜአ በሰጡት ቃል ነው።

አቶ መሃመድ ፥ በውጭ አገራት የሚሰሩ የሬዲዮ ጣቢያዎች የሚተላለፉ ፕሮግራሞች የአገር ውስጥ ህግና ስርዓትን ተከትለው አይካሄዱም ብለዋል።

በተጨማሪ የአገሪቷን ፖለቲካዊ ነበራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያላስገቡ ፕሮግራሞችም ሲተላላፉ እንደነበርም አስታውሰዋል።

እነዚህ አካላት በአገር ውስጥ ፈቃድ ያላገኙ በመሆናቸው የሚተላለፉ መርሃ ግብሮችን በመከታተል ግብረ መልስና የማስተካከያ ሃሳብ ለመስጠት የሚቻልበት ሁኔታ አለመኖሩን ገልጸዋል፡፡

በአገር ውስጥ የሚያስተላልፉ የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች ፕሮግራሞቹ ላይ የሚያደርጉት ቁጥጥር አነስተኛ መሆኑን አቶ መሃመድ ተናግረዋል።

"በፕሮግራሞቹ የአንዳንድ አገራት አቋም መግለጫ ሲተለለፍ የሚታይበት እና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ግምት ውስጥ ያላስገ ሲሆን ተስተውሏል" ሲሉም አስረድተዋል።

የተጠቀሱትን ሃሳቦች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ባለስልጣኑ ከዛሬ ጀምሮ ከውጭ ሚዲያዎች ወደ አገር ውስጥ የኤፍ ኤም ጣቢያዎች ሊንክ አድርጎ ማስተላለፍን ከልክሏል ሲሉ አሳውቀዋል።

በአገር ውስጥ ፈቃድ ያልተሰጣቸው የውጭ አገር የሬዲዮ ጣቢያዎች ፈቃድ ባላቸው የአገር ውስጥ የኤፍ ኤም ማሰራጫ ጣቢያዎች አማካኝነት ፕሮግራሞቻቸውን ሲያስተላልፉ ቆይተዋል።

@tikvahethiopia
#EMA : ሲኤንኤን ፣ ቢቢሲ ፣ ሮይተርስ እና ኤፒ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ለአራት የውጭ ሚዲያዎች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ፅፏል።

እነዚህ ሚዲያዎች ሲኤንኤን (CNN)፣ ቢቢሲ (BBC)፣ ሮይተርስ (Reuters) እና አሶሺየትድ ፕሬስ (AP) ናቸው።

በማስጠንቀቂያ ደብዳቤው ላይ ሚዲያዎቹ ፦

- TPLFን ዓላማ ለማገዝ በኢትዮጵያ ላይ የሀሰት ዜናዎች እና የዜና ትንታኔዎችን ማዘጋጀታቸው እና ማሰራጨታቸው ፥

- የህግ ማስከበር ዘመቻውን የዘር ማጥፋት (Genocide) ዘመቻ አድርገው ሪፖርት ማድረጋቸው ፥

- በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ሰብዓዊ ቀውስ ለመፍታት መንግስት የሚያደርገውን ጥረት የሚያበላሽ ዘገባዎችን መስራታቸው፣

- በትግራይ ክልል መንግስት ረሃብንን እና አስገድዶ መድፈር እንደጦር መሳሪያ እንደተጠቀመበት ሪፖርት ማድረጋቸው ፤

- በሀገሪቱ መሪ ተቋማት ላይ የስም ማጥፋት ሪፖርቶችን ማዘጋጀታቸው፤

- የሀገሪቱን መሪ በዓለም አቀፍ መድረክ ለማጣጣል እና ሀገሪቱን ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጫና ውሥጥ የሚከቱ ዜናዎችን ማዘጋጀታቸው ተገልጿል።

ተቋማቱ የጋዜጠኝነት መርህን አክብረው እንዲሰሩ መደበኛ እና መደበኛ ባልሆነ መልኩ ተደጋጋሚ ምክርና ማሳሰቢያ ሲሰጥ መቆየቱን የጠቀሰው ባለስልጣኑ፤ መገናኛ ብዙኃኑ ከድርጊታቸው ከመታቀብ ይልቅ አባብሰው መቀጠላቸውን አስታውቋል።

ለኢትዮጵያዊያን ደህንነት ሲባል የሚዲያ ተቋማቱ በቀጣይ ከዚህ ድርጊታቸው የማይታቀቡ ከሆነ ባለስልጣኑ በተሰጠው ስልጣን እና ሃላፊነት በመጠቀም የሰጣቸውን የሥራ ፈቃድ ለመሰረዝ እንደሚገደድ አስጠንቅቋል።

በኢመብባ ዋና ዳይሬክተር መሀመድ ኢድሪስ ተፈርሞ የወጣው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#EMA

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፤ " የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃን አስከፊነት እንዲረዱ እና መከላከያ መንገዶችንም እንዲያውቁ ያግዛቸዋል " ያለውን ስልጠና ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ ከ11ዱም ክ/ከተሞች ከሚገ ኙ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተወጣጡ የሚኒ ሚዲያ አባላት ተማሪዎች መስጠቱን ገለጸ።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ፤ ከቴክኖሎጂ መስፋፋት ጋር ተያይዞ በርካታ መገናኛ ብዙኃን እየተበራከቱ መሆናቸውንና በዚህም በርካታ የተሳሳቱ፣ ሀገርን የሚያፈርሱ እንዲሁም ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ ሐሰተኛና የጥላቻ ንግግሮች ሲሰራጩ እንደሚስተዋሉ ተናግረዋል።

መ/ቤታቸው የሰጠው ስልጠናም ታዳጊዎች መገናኛ ብዙኃንን ሲጠቀሙ ፤ የትኛው መረጃ ትክክል እንደሆነ እና እንዳልሆነ እና የትኛው መረጃ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ነው የሚለውን በመለየት እና ባለማሰራጨት፣ ባለማጋራት እንዲሁም ተሰራጭቶ ሲያገኙ ለባለሥልጣኑ በመጠቆም ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ታስቦ መሆኑን አስረድተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ፤ ስልጠናው ተማሪዎቹ ከወዲሁ የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃን አስከፊነት እንዲረዱ እና መከላከያ መንገዶችንም እንዲያውቁ እንደሚያግዛቸው ገልጸዋል።

" ወጣቶች ነገ የሚረከቧት ሀገር ከጥላቻ የፀዳች እንድትሆን ጥላቻን በመፀየፍ የሀገርን አንድነትና የህዝቦችን አብሮነት ለማፅናት የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን በመከላከል ረገድ የበኩላቸውን ዛሬ ላይ መወጣት ይኖርባቸዋል " ሲሉም አሳስበዋል።

ይህ ስልጠና የማስጀመሪያ ነው ያለው ባለስልጣን መ/ቤቱ ወደፊት በአዲስአበባ ከተማ በሚገኙ ሁሉም 2ተኛ ደረጅ ት/ቤቶች እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚገኙ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መሰል ስልጠና ለመስጠት ውጥን መኖሩን አመልክቷል።

@tikvahethiopia
#EMA

ከ600 በላይ የሕክምና ባለሙያዎችና ውሳኔ ሰጪዎች ውይይት ሊያደርጉ መሆኑን የኢትዮጵያ ሕክምና ማኀበር ገለጸ።

የማኀበሩ ራዕይ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ማግኘት የሚችል ጤናማና የበለጸገ ማህበረሰብ እውን ለማድረግ ይረዳ ዘንድ ከሚመለከታቸው የመንግሥት መ/ቤቶች የጤና ሚኒስትርን ጨምሮ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከስፔሻሊቲ ሶሳይቲዎች፣ ከማኀበሩ አባላት ጋር በመሆን ምክክር የሚያደርግበት ዓመታዊ ጉባዔ ያካሂዷል።
      
በዚሁ መሠረት ዘንድሮ 60ኛውን ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ የጤና አውደ ርዕይ ከየካቲት 29 እስከ 30/2016 ዓ/ም በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ለማካሄድ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን አስታውቋል።

በዓመታዊ የሕክምና ኮንፈረንሱ (AMC፣ በውስጥ እና ውጭ ሀገራት የሚኖሩ እውቅ የህክምና ባለሙያዎች ያላቸውን እውቀት፣ የምርምር ግኝቶችን፣ የሕክምና ልምዶችን ለመለዋወጥ የሚረዳ መድረክ መሆኑንም አመላክቷል።

በጉባዔው የዓመቱን መሪ ቃል መነሻ በማድረግ የፓናል ውይይቶች እንደሚካሄዱ፣ CEU የሚያስገኙ የሙያ ማሻሻያ ስልጠናዎች እንደሚሰጡ እንዲሁም የሳይንሳዊ ግኝቶች የሚቀርቡበት ክፍለጊዜም እንደተዘጋጀ ተጠቁሟል።

በማህበሩ 60ኛው ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ የጤና አውደ ርዕይ፦ 

* ከ600 በላይ የተከበሩ የሕክምና ባለሙያዎች
* ከሁሉም ክልል የሚመጡ የማህበሩ አባላት ተወካዮች፣ 
* ከተለያዩ የጤና ባለሙያዎች ማኀበራት፣
* ከስፔሻሊስቶች ማኀበራት የተውጣጡ ተወካዮች፣
* የሕክምና ኮሌጅ ኃላፊዎች
* የመንግሥት አካላት
* የጤና አውደ ርዕይ ከ100 በላይ ድርጅቶች 
* ከ2,000 በላይ ሰዎችም ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል። 

በተጨማሪም በየዓመቱ ተጠባቂው የኢትዮጵያ ሕክምና ማኀበር የሽልማት መርሀ ግብር ግብርም በ2016 ዓ/ም በአራት ዘርፍ ማለትም ፦

• “የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የአመቱ ምርጥ የህክምና ተማሪዎች
• የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የሕይወት ዘመን 
• የኢትዮጵያ ሕክምና ማኀበር ተፅዕኖ ፈጣሪ እና ምርጥ ወጣት ሀኪም
• የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የ2016 የዓመቱ ምርጥ ተቋም ሽልማት የሚሰጥ ይሆናል” ተብሏል።

የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር ከተመሰረተ 1954 ዓ/ም ጀምሮ በሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፣ በታካሚዎች ደኀንነት እና በአጠቃላይ በሕክምናው ዘርፍ ቁልፍ ሚና በመጫዎት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ማኀበር ነው፡፡ 

#AddisAbabaTikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EMA ከ600 በላይ የሕክምና ባለሙያዎችና ውሳኔ ሰጪዎች ውይይት ሊያደርጉ መሆኑን የኢትዮጵያ ሕክምና ማኀበር ገለጸ። የማኀበሩ ራዕይ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ማግኘት የሚችል ጤናማና የበለጸገ ማህበረሰብ እውን ለማድረግ ይረዳ ዘንድ ከሚመለከታቸው የመንግሥት መ/ቤቶች የጤና ሚኒስትርን ጨምሮ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከስፔሻሊቲ ሶሳይቲዎች፣ ከማኀበሩ አባላት ጋር በመሆን ምክክር የሚያደርግበት ዓመታዊ…
#EMA

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ አባል ፤ ከኢትዮጵያ ሕክምና ማኀበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ትዕግስት መኮንንን ጋር ቆይታ  አድርጎ ነበር።

በዚህም ወቅት መሰረታዊ የሚባሉ ጥያቄዎችን አንስቷል።

1ኛ. በጤና ተቋማት እየታዩ ያሉና ትኩረት የሚሹ ችግሮች ምንድን ናቸው ?

ወ/ሮ ትዕግስት መኮንን ፦

" አሁን በስፋት በዋነኝነት እንደተግዳሮት ሆኖ የሚታየው የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት መኖር ነው።

የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት በሚፈለገው ልክ ተቋማት  የሚጠበቅባቸውን ሥራ ለመስራት ትልቅ ተግዳሮት እየሆነ ነው። "

2ኛ. ማህበሩ #የጤና_ባለሙያዎችን ጉዳዮች ተደራሽ ማድረግ አንዱ ዓላማው እንደመሆኑ መጠን በደመወዝ እጥረት የጤና ባለሙያዎች ወደ ውስጥም ሆነ ውጪ አገራት እየፈለሱ (የትግራይ ክልል) መሆኑን በተመለከተ ማኅበሩ እንደማኀበር ምን እየሰራ ነው ?

ወ/ሮ ትዕግስት መኮንን ፦

" እርግጥ ነው ይሄ ነገር ማኀበሩ እውቅና የሚሰጠው ጉዳይ ነው። ከሥራ ማጣት ጋርም ተያይዞ፣ ከተለያዩ ችግሮች አንፃር የባለሙያዎች ፍልሰት እንዳለ እሙን ነው። ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ እንደዚህ ነው የሚል ጥናታዊ ፅሑፍ አልሰራንም።

ግን ችግሩ እንዳለ፣ በጥልቀት አትኩሮት መሰጠት እንዳለበትም ለተለያዩ አካላት ግብዓት ስንሰጥ ቆይተናል።

ይሄ አገሪቱም ካለችበት የኢኮኖሚ ጉዳይ፣ ለጤና ሴክተሩ ከሚሰጠው ትኩረት አንፃር እጥረት አለ፣ መድረስ ያለብን ደረጃ ላይ አልደረሰንም። ይህ ባለበት ሁኔታ የመፍለሱ፣ ሥራ የማጣቱ ጉዳይ እየታዬ ስለሆነ እንደ አገር ያለው ችግር ነው ለዚህ የዳረገው። "

3ኛ. የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ጤና ተቋማት የሚሄዱ ሕሙማን መጉላላት፣ የቀጠሮ መንዛዛት ስለሚገጥማቸው በወቅቱ መታከም ሲገባቸው ከሕመማቸው ጋር ለመቆየት እንደሚገደዱ ሕሙማን በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያነሱ ይደመጣል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ ማኀበሩ ምን እየሰራ ነው ?

ወ/ሮ ትዕግስት መኮንን ፦

" የታካሚዎች መጉላላት፣ በወቅቱ የሚፈለገውን የሕክምና አገልግሎት አለማግኘት አጠቃላይ የሥርዓት ችግር ቢሆንም፣ ችግሩን ምን አመጣው ? በሚለው ጉዳይ ብዙ ነገሮች ሊጠቀሱ ይችላሉ።

ለምሳሌ፦ የሕክምና መሣሪያዎች ግብዓት እጥረት መኖር፣ ለጤና ሴክተር የሚሰጠው የበጀት እጥረት፣ ከዶላር ጋር ተያይዞ ያለው ችግር በቀጥታ ለዚህ ችግር አስተዋጽኦ ያደርጋል።

ቁጥሩን ለመግለጽ ለጊዜው ባላስታውሰውም ማህበረሰቡ የጤና አገልግሎት ፍላጎቱ እየጨመረ መጥቷል።

እንደ አጠቃላይ በታካሚዎች፣ በሐኪሞች፣ በዘርፉ ያለውን ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል ውይይት የማኀበሩ 60ኛ ዓመታዊ ጉባኤ በዚህ ወር ሲደረግ ይነሳል። ይበልጥ ትኩረት ይሰጠዋል ተብሎ ይጠበቃል። "

#TikvahEthiopiaAA

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

“ ሀኪሞች ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ችግር አለባቸው። ኩሽና ተከራይተው ነው የሚኖሩት፤ ቤት እንኳ የላቸውም። በአውቶብስ ተጋፍተው ነው እየመጡ የሚሰሩት። ይህ ችግር ግን የጤና እከል የደረሰበትን ማህበረሰብ ከማገልገል አልከለከላቸውም ፤ ያንን እያደረጉ ግን ሲታመሙ እንደ ሞያተኛ ሳይሆን ለምነው ነው የሚታከሙት። ” - ዶክተር በሀሩ በዛብህ (የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር የቦርድ አባል - ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)

#EMA
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ “ ሀኪሞች ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ችግር አለባቸው። ኩሽና ተከራይተው ነው የሚኖሩት፤ ቤት እንኳ የላቸውም። በአውቶብስ ተጋፍተው ነው እየመጡ የሚሰሩት። ይህ ችግር ግን የጤና እከል የደረሰበትን ማህበረሰብ ከማገልገል አልከለከላቸውም ፤ ያንን እያደረጉ ግን ሲታመሙ እንደ ሞያተኛ ሳይሆን ለምነው ነው የሚታከሙት። ” - ዶክተር በሀሩ በዛብህ (የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር የቦርድ አባል - ለቲክቫህ…
#EMA

“ ሀኪሞች ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ችግር አለባቸው፤ ኩሽና ተከራይተው ነው የሚኖሩት ” - የኢትዮጵያ ህምክምና ማህበር

የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር (EMA) በየዓመቱ ሰኔ 25 ቀን የሚከበረውን “ 7ኛውን የሀኪሞች ቀን ” በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተከብሮ ነበር።

በዚህም በዘንድሮው ' የሀኪሞች ቀን ' ከጌራ የቤት ለቤት ህክምናና የሀኪሞች ቢሮ ተቋም ጋር በመሆን 2,000 ለሚጠጉ የማህበረሰብ ክፍሎች የቤት ለቤትና የጎዳና ላይ ነጻ የህክምና ለመስጠት ማቀዱን አመላክቷል።

ይኸው የነጻ ህክምና ከሐምሌ 1 /2016 ጀምሮ ነው የሚሰጠው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በተመለከተ፣ ከ34 ዓመታት ጀምሮ በአጥንት ቀዶ ህክምና እያገለገሉ የሚገኙትን የማኀበሩ የቦርድ አባልና የአባላት ጉዳይ የሚከታተሉት ዶ/ር በሀሩ በዛብህን ጠይቋል።

እሳቸው በሰጡት ቃል፣ “ ሀኪሞች ከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር አለባቸው፤ ኩሽና ተከራይተው ነው የሚኖሩት። ቤት እንኳ የላቸውም። በአውቶብስ ተጋፍተው ነው መጥተው የሚሰሩት ” ብለዋል።

“ ይህ ችግር የጤና እከል የደረሰበትን ማህበረሰብ ከማገልገል አልከለከላቸውም ” ያሉት ዶ/ር በሀሩ፣ “ ያን እያደረጉ ግን ሲታመሙ እንደ ሞያተኛ ሳይሆን ለምነው ነው የሚታከሙት ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ መብራት ኃይል ለአባላቱ መብራት፣ ቴሌ ለአባላቱ የአየር ሰዓት፣ ውሃና ፍሳሽ ለአባላቱ ውሃ ይሰጣሉ። የእኛ ጤና ሲታወክ እንኳ ምንም አይሰጥም። በህግም የተቀመጠ ነገር የለም ” ሲሉ አማረዋል።

“ የሥራ ሁኔታዎች ራሱ አልተመቻቹም ፤ ከሌላ አገር ጋር ሲገጻጸር እየሰራን የሚከፈለን እራሱ ውስን ነው ” ብለዋል።

“ መሬት እንኳን ቢሰጠን ምን ችግር አለው ? መኖር ነው ያቃተን። የሚከፈለን ገንዘብ በጣም ውስን ነው ” ሲሉ አክለዋል።

በዘርፉ የበዙ ችግሮች ከመኖራቸው አንጻር በርካታ ሀኪሞች ከአገር ለመውጣት እየተገደዱ መሆኑን ገልጸው፣  መንግስት ልቦና ሰጥቶት ለሚስተዋሉ ችግሮች ሁሉ መፍትሄ እንዲሰጥ በማኀበሩ ስም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ህክምና ማኀበር / EMA ከተመሠረተ 75 ዓመታትን እንዳስቆጠረ፣ በኢትዮጵያ ከ15,000 እስከ 20,000 ሀኪሞች እንዳሉ ተመላክቷል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia