TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
“ የጤና ባለሙያዎች ወደ ሌሎች አካባቢዎች እየፈለሱ ነው ” - የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ፤ ጤና ባለሞያዎች ወደሌሎች አካባቢዎች እየፈለሱ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

“ የጤና ተቋማት የሥራ ማስኬጃ በጀት ይመደብላቸው ነበር በአሁኑ ሰዓት ግን ይሄ የለም ” ሲልም አመልክቷል።

የቢሮ የፈውስና ተሃድሶ ዋና የሥራ ሂደት ስምኦን ገ/ፃዲቅ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ የጤና ባለሙያዎች ወደ ሌሎች አካባቢዎች እየፈለሱ ነው ” ብለዋል።

አሁን ‘ሁሉም ነገር ወደነበረበት ተመልሷል’ በሚባልበት ሁኔታ መቋቋም እንኳ ስላልቻሉ የፈለሱ የጤና ባለሙያዎችን በቁጥር ለመግለጽ ለጊዜው ባይቻልም አዲስ አበባን ጨምሮ የተሻለ ክፍያ ወዳለባቸው ሌሎች የውጪ አገራት ጭምር እየፈለሱ መሆኑ ነው የተገለጸው።

ስምኦን (ዶ/ር)፣ ለሠራተኞች ፍልሰት ምክንያቱ ፦
* የ17 ወራት ደመወዝ፣
* የትርፍ ሰዓት ክፍያ ስላልተከፈላቸው፣ መሆኑን ገልጸው፣ “ደመወዝ አልተከፈላቸውም ማለት የዕለት ተዕለት ወጪ መሸፈኛ የቤትን ኪራይን ጨምሮ ሲቆይባቸው ነው የቆየው ” ብለዋል።

“ሌላውን ትተን የቤት ኪራይ እንኳ መክፈል አልቻሉም። አሁን የተበጣጠሰ የደመወዝ ክፍያ ቢኖርም በተጨማሪ ደግሞ የትርፍ ሰዓት ክፍያ የላቸውም” ያሉት የሥራ ሂደት ተተኪው፣ “የጤና ተቋማት የሥራ ማስኬጃ በጀት ይመደብላቸው ነበር በአሁኑ ሰዓት ግን ይሄ የለም ” ሲሉ የሁነቱን አሳሳቢነት አስረድተዋል።

“ ጤና ቢሮ፣ የክልል መንግሥትም ከፌደራል መንግሥት በሚያገኘው የደመወዝና የትርፍ ሰዓት ክፍያ ብቻ ሳይሆን የጤና ተቋማት የመድኃኒት መግዣና የሌላ ሥራ ማስኬጃ በጀት ይመድብላቸው ነበር በአሁኑ ሰዓት ይሄ የለም” ብለዋል።

ዶ/ር ስምኦን አክለውም፣ “መበጀት የነበረበት ያለፈው የ17 ወራት ደመወዝና ጥቅማጥቅም፣ የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዳለ ሆኖ ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ ደመወዝ መከፈል ከጀመረበት ጊዜ ወዲህ ያለውም የተበጀተ በጀት የለም” ነው ያሉት።

በመሆኑም ከፌደራል መንግሥት ጀምሮ ያለው ሁሉም የሚመለከታቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ሁሉ እየፈለሱ ያሉት የጤና ባለሙያዎች በቦታቸው እንዲቆዩ ለማድረግ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚጠባ ተጠይቋል።
 
መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከምን ደረሰ ?

" ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታገኝ መንገድ ይጠርጋል " የተባለው የመግባቢያ ስምምነት ከሶማሌለንድ ጋር ከተፈረመ ትላንት 1 ወር አልፎታል።

የመግባቢያ ስምምነቱ እኤአ ጥር 1 ነበር የተፈረመው።

ይህ ስምምነት በተፈረመበት ወቅት በመንግሥት ባለስልጣናት በኩል በተሰጡ ገለፃዎች ፦

* በ1 ወር ውስጥ የስምምነቱ ዝርዝር ይፋ እንደሚደረግ፤

* ስምምነቱ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ሂደቱ ያልቃል / ወደ ተግባር / ስራ እንደሚገባ ተነግሮ ነበር።

እስካሁን ቀጣይ የስምምነቱን ምዕራፎች በተመለከተ / ሂደቱ ምን ላይ እንደደረሰ በይፋ የተሰጠ ማብራሪያ የለም።

ከጥቂት ቀናት በፊት በኢትዮጵያ የሶማሊላንድ ተወካይ አምባሳደር አብዱላሂ ሞሀመድ ፤ ጉዳዩን ለማጠናቀቅ ከሁለቱም ወገኖች የቴክኒክ ኮሚቴ በማዋቀር ላይ እንደነበር መግለፃቸው ይታወሳል።

የስምምነት ፊርማውን ትከትሎም ግንኙነቶች እንደነበሩ፤  የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትርም ጉዳዩን ለማሳለጥና መሰረት ለማስያዝ ኢትዮጵያ ቆይተው መመላሳቸውን ተናግረው ነበር።

የሶማሌላንድ ተወካዩ አምባሳደር አብዱላሂ ሞሀመድ ፤ ይዋል ይደር እንጂ ሁለቱ ኮሚቴዎች ወደ ስራ እንዲገቡ እንደሚደረግ ፤ ይህ በጣም በቅርቡ እንደሚከናወን አመልክተው ነበር።

ኢትዮጵያና ሶማሌላንድ የዛሬ 1 ወር ኢትዮጵያን የባህር በር እንድታገኝ የሚያስችል ፤ ሶማሌላንድ ደግሞ ሉዓላዊ ሀገር እንደሆነች እውቅና ልታገኝ የምትችልበትን ዕድል ይፈጥራል የተባለ ስምምነት ተፈራርመው እንደነበር ይታወሳል።

ስምምነቱ ዓለም አቀፍ ትኩረትን ስቦ የሰነበተ ሲሆን በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል መቃቃርን ፈጥሯል ይህ መቃቃር እስካሁን ያልተፈታ ሲሆን በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ በኩል የስምምነቱ ቀጣይ ሂደት በ1 ወር ውስጥ ያልቃል ፣ ዝርዝሩ ይፋ ይደረጋል ቢባልም እስካሁን ስለጉዳዩ የተባለ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
" ... ለአንድ ሓጅ አጠቃላይ ብር 329,000 እንዲሆን ተወስኗል " - ከኢ/እ/ጉ/ጠ/ም/ቤት

የዘንድሮው የሐጅ እና ዑምራ ምዝገባ ነገ ቅዳሜ ጥር 25 በይፋ የሚጀመር መሆኑ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አሳውቋል።

የዘንድሮው ዓመት የሐጅ ጉዞ መስተንግዶ በባለፈው ዓመት 2015 ከነበሩት 18 የምዝገባ ጣቢያዎች ላይ 9 አዳዲስ ጣቢያዎችን በመጨመር ወደ 27 ከፍ እንዲሉ መደረጉ ለማወቅ ተችሏል።

የምዝገባ ጣቢያዎች ፦
- ስቴዲያም በሚገኘው የኦሮሚያ መጅሊስ ዋና ቢሮ፣
- ጦር ሃይሎች በሚገኘው የአዲስ አበባ መጅሊስ ዋና ቢሮ፣
- በሻሸመኔ፣ በጂማ፣ በሀረር፣ በጂግጂጋ፣ በድሬዳዋ፣ በባህር ዳር፣ በደሴ፣ በሀረሪ፣ በሐዋሳ፣ በቴፒ፣ በአሶሳ፣ በሰመራ፣ በባሌ በሮቤ፤ በወራቤ፤ በጎዴ፣  በሞያሌ የሚገኙ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።

የሐጅ ዋጋ ተመንም ይፋ የተደረገ ሲሆን ወቅታዊ የዓለም ዓቀፍና አገራዊ ተጨባጭ ሁኔታዎችን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ለአንድ ሓጅ አጠቃላይ ብር 329,000.00 (ሦሥት መቶ ሃያ ዘጠኝ ሺህ ብር) እንዲሆን ተወስኗል፡፡

ይህ የዋጋ ተመን ባለበት መልኩ የሚፀናዉ የዶላር ዋጋ አሁን ባለበት የሚቀጥል አሊያም በመደበኛ የአጨማማር ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ ብቻ ነው ተብሏል።

ማንኛዉም የሐጅ ተጓዥ ለምዝገባ በአካል ወደ ምዝገባ ጣቢያዎች ለምዝገባ ሲቀርብ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል ፡-

1.የመኖሪያ አካባቢያቸዉን የሚገልጽ የቀበሌ መታወቂያ
2. የታደሰ የጉዞ ሰነድ ፖስፖርት (የመጠቀሚያ ጊዜው ለመጠናቀቅ ከ11 ወራት በላይ የቀረው መሆን አለበት)
3. አንድ ጉርድ ፍቶ ግራፍ
4. የኮቪድና የቢጫ ወባ ክትባት ካርድ

በዕድሜ መግፋትና በተለያዩ አካላዊ ጉዳቶች ምክንያት እራሳቸዉን ችለው የሐጅ ስርዓቱን መፈፀም የማይችሉ ሁጃጆች አስፈላጊውን መስፈርት ከማሟላታቸው ባሻገር ሊያግዛቸው የሚችል አብሯቸው የሚጓዝ ደጋፊ ሰው የማቅረብ ግዴታ አለባቸው ተብሏል።

ሁጃጆች አስፈላጊ መስፈርቶች ማሟላታቸዉ በምዝገባ ጣቢያ ኃላፊ ሲረጋገጥና የባንክ ክፊያ እንዲከፍሉ ማረጋገጫ ሲሰጣቸው ብቻ የሐጅ መስተንግዶውን ክፍያ ዲፖዚት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
ቀለል ያለ ግምት በመስጠት ይሸለሙ!

ግምትዎን የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል https://publielectoral.lat/GlobalBankEth ይስጡ!

#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #Bank #GBE #ArsLiv #Arsenal #Liverpool #PremierLeague
#እቴጌጣይቱ

" ብርሃን ዘኢትዮጵያ " እየተባሉ ለሚጠሩት ስመ ጥር የሀገር ባለውለታ እቴጌ ጣይቱ ብጡል በትውልድ ቦታቸውና ለቁምነገር በበቁበት በደብረታቦር ከተማ የመታሰቢያ ሀውልት ቆመላቸው።

ሀውልቱ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ተገንብቶ በዛሬው እለት መመረቁ ተነግሯል።

እቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ ነሀሴ 12 ቀን 1832 ዓ.ም በጌምድር ውስጥ ደብረታቦር ከተማ ነበር የተወለዱት።

ከዳግማዊ አፄ ምንሊክ ጋር ሚያዝያ 25 ቀን 1875 ዓ.ም በአንኮበር መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን ተቀብለው ከተጋቡ በኃላ ንጉሱ ዐፄ ምንሊክ ንጉሰ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም በተቀዳጁ ማግስት ጥቅምት 27/1882 ዓ.ም ወይዘሮ ጣይቱ ብጡል እቴጌ ጣይቱ ተብለው ተሰይመዋል።

እቴጌ ጣይቱ ብጡል ፦

* በሀገር አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።

* የጥቁር ህዝቦች ድል ለተሰኘውና ለዓድዋ ጦርነት ድል መሳካት ሚናቸው ከፍተኛ ነበር።

* ለአዲስ አበባ ከተማ መመስረት መሰረት ጥለዋል።

* የውጫሌ ውል ይሰረዝ ዘንድ ሞግተዋል።

* የዓድዋ ጦርነት አይቀሬ መሆኑ ሲታወቅ " ሴት ነኝ ጦርነት አልፈልግም፤ በሀገሬ ክብር ግን አልደራደርም " በማለት የአዲስ አበባን ሴቶች ሰብስበው ሎጀስቲክስ አዘጋጅተዋል። በአንድ ከፍተኛ የጦር መኮንን ማዕረግ (ራስ) ሆነው 5,000 ጦር በመምራት ወደ ማይቀረው ፍልሚያ ተመዋል። ... ሌሎች ብዙ ያልተዘረዘሩ ሀገራዊ ተግባርን ፈፅመዋል።

እቴጌ ጣይቱ የካቲት 4 ቀን 1910 ዓ/ም ነው  ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።

ፎቶ፦ የደብረ ታቦር ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

“ የፍርድ ቤት ማገጃ ጥሰው ዕቃችንን አውጥተው ሜዳ ኮብልስቶን ላይ ጣሉን ” - የቄራ ነዋሪዎች 

“ ከሳሾች ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡና ይህን ቤት ለሌላ ሰው እንዳይሰጥ” - የፍርድ ቤት ደብዳቤ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ቄራ ዶሮ ተራ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የሚገኙ “ የድሃ ድሃ ” የተባሉ የቀበሌ ቤት ተከራይተው የሚኖሩ ሰዎች ፍርድ ቤት እንዳይወጡ የሚያዝ ደብዳቤ ቢጽፍላቸውም የእግዱን ውሳኔ በመጣስ የፓሊስ አባላት ከቤት አስወጥተው ሜዳ ላይ እንደጣሏቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹን ወክለው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ ከባለጉዳዮቹ መካከል አንዱ ፣ ቄራ ዶሮ ተራ 11 አባውራዎች እያንዳንዳቸው የቀበሌ ቤት ተከራይተው ይኖሩ እንደነበር፣ ይሁን እንጂ ከዚያ በኋላ ቤቱ 'የቀበሌ ነው' ተብለው ውጡ እንደተባሉ፣ ይህን ተከትሎም፣ ፍርድ ቤት ክስ መስርተው ማገጃ እንዳስመጡ፣ በዚሁ ጉዳይ ፍርድ ቤት ለሁለት ጊዜያት ያህል ቀጠሮ እንደሰጣቸው አስረድተዋል።

አክለውም፣ “ ፍርድ ቤት ሁከት ይወገድልን ብለን ክስ መስርተን ማገጃ አስመጣን። ከዚያ ‘እናንተ በተከራያችሁት ክፈሉ’ ተብለን መክፈል ጀመርን። በዚያ ሁኔታ እያለን ሳንሰማ፣ ምንም ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ መጡና ‘በሦስት ቀናት ውስጥ ውጡ’ አሉን ” ሲሉ ገልጸዋል።

እኛም ፍርድ ቤት ሂደን ማገጃ አመጣን ያሉት ቅሬታ አቅራቢው፣ “ የፍርድ ቤት ማገጃውን ጥሰው ዕቃችንን አውጥተው ሜዳ ኮብልስቶን ላይ ጣሉን። የእገዳ ወረቀት አምጥተን እራሱ ‘ማንም ኣይከለክለንም፣ እንቀበልም’ ብለው ከቤት አስወጥተው ሜዳ ላይ በትነውን፣ አሽገውት ሄዱ። ውጪ ላይ ነን ” ሲሉ አማረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የፍርድ ቤት ደብዳቤ፣ “ ለን/ስ/ላ/ክ/ ከተማ ወረዳ 06 ቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤት በከሳሽ እነ ኤሊያስ ዘርጋና በተከሳሽ የን/ስ/ላ/ክ/ ከተማ ወረዳ 06 ቤቶች አስተዳደር ባለው ክርክር ከሳሾች ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡና ይህን ቤት ለሌላ ሰው እንዳይሰጥ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ ቁጥር 154 መሠረት ይህ የእግድ ትዕዛዝ እስከ 27/05/2016 ዓ/ም ድረስ ተሰጠ ” ሲል ያረጋግጣል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ ቤት ያስለቀቋቸው የአዲስ አበባና የፓሊስ አባላት መሆናቸውን በገለጹት መሠረት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው አንድ የዶሮ ተራ ቀጠና ፓሊስ፣ ሰዎቹ የቀበሌ ቤት ነው ተብለው እንዲወጡ እንደተደረገ ገልጸው ተጨማሪ ማብራሪያ ከወረዳው ጠይቁ ብለዋል።

ይሁን እንጂ ከወረዳው እስከ ፓሊስ ኮሚሽን የተደረገው ሙከራ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም።

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#ትግራይ

የመኪና አደጋ የአባትና ልጅ ህይወት ቀጠፈ።

ሦስት ተጓዦች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

ዛሬ ጠዋት ጥር  25/2016 ዓ.ም ከዓድዋ ወደ መቐለ 5 ሰዎች ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ባለቤትነቱ የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ የሆነ ትዮታ ዳብል ጋቢና መኪና ተምቤን ልዩ ቦታ " መነወ " በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ በውስጡ የነበሩ ሁሉም ተጓዦች ላይ የሞትና የጉዳት አደጋ አድርሷል።

በመኪናው የነበሩ የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ማርኬቲንግ መምሪያ ሃላፊ ከነልጃቸው ህይወታቸው ሲያልፍ ፤ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው 3 ተጓዦች ደግም በመቐለ ዓይደር ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

የራስ አሉላ አባነጋ የትውልድ ቦታ የሆነው " መነወ " ጠመዝማዛ ቦታና ተደጋጋሚ የመኪና አደጋ የሚከሰትበት በመሆኑ መንገዱ ትኩረት እንደሚያሻው አደጋው አስመልክተው የሚሰጡ የህዝብ አስተያየቶች ያመለክታሉ። 

የመኪና አደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ፓሊስ ትራፊክ ገልጿል።

መረጃውን የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው የላከው።
                                    
@tikvahethiopia