#እቴጌጣይቱ

" ብርሃን ዘኢትዮጵያ " እየተባሉ ለሚጠሩት ስመ ጥር የሀገር ባለውለታ እቴጌ ጣይቱ ብጡል በትውልድ ቦታቸውና ለቁምነገር በበቁበት በደብረታቦር ከተማ የመታሰቢያ ሀውልት ቆመላቸው።

ሀውልቱ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ተገንብቶ በዛሬው እለት መመረቁ ተነግሯል።

እቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ ነሀሴ 12 ቀን 1832 ዓ.ም በጌምድር ውስጥ ደብረታቦር ከተማ ነበር የተወለዱት።

ከዳግማዊ አፄ ምንሊክ ጋር ሚያዝያ 25 ቀን 1875 ዓ.ም በአንኮበር መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን ተቀብለው ከተጋቡ በኃላ ንጉሱ ዐፄ ምንሊክ ንጉሰ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም በተቀዳጁ ማግስት ጥቅምት 27/1882 ዓ.ም ወይዘሮ ጣይቱ ብጡል እቴጌ ጣይቱ ተብለው ተሰይመዋል።

እቴጌ ጣይቱ ብጡል ፦

* በሀገር አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።

* የጥቁር ህዝቦች ድል ለተሰኘውና ለዓድዋ ጦርነት ድል መሳካት ሚናቸው ከፍተኛ ነበር።

* ለአዲስ አበባ ከተማ መመስረት መሰረት ጥለዋል።

* የውጫሌ ውል ይሰረዝ ዘንድ ሞግተዋል።

* የዓድዋ ጦርነት አይቀሬ መሆኑ ሲታወቅ " ሴት ነኝ ጦርነት አልፈልግም፤ በሀገሬ ክብር ግን አልደራደርም " በማለት የአዲስ አበባን ሴቶች ሰብስበው ሎጀስቲክስ አዘጋጅተዋል። በአንድ ከፍተኛ የጦር መኮንን ማዕረግ (ራስ) ሆነው 5,000 ጦር በመምራት ወደ ማይቀረው ፍልሚያ ተመዋል። ... ሌሎች ብዙ ያልተዘረዘሩ ሀገራዊ ተግባርን ፈፅመዋል።

እቴጌ ጣይቱ የካቲት 4 ቀን 1910 ዓ/ም ነው  ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።

ፎቶ፦ የደብረ ታቦር ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia