TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢትዮ ቴሌኮም

የዘመናችንን መጨረሻውን የ5ኛ ትውልድ ኔትወርክ አገልግሎት በሐረር እና ሀሮማያ ከተሞች በይፋ ማስጀመራችንን ስናበስር እጅግ ደስ ይለናል!

አገልግሎቱን ከትናንት በስቲያ በድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም ቀደም ሲል በአዲስ አበባ፣ አዳማ እና ጂግጂጋ ከተሞች ማስጀመራችን ይታወሳል።

የ5ጂ የሞባይል ኔትወርክ ወሳኝ ለሆኑ፣ በከፍተኛ ቅጽበት፣ ፍጥነትና በተመሳሳይ ወቅት (real-time) መከወን ላለባቸው ማኑፋክቸሪንግ፣ ጤና ፣ ትምህርት፣ ትራንስፖርት፣ ግብርና፣ ስማርት ሆም፣ ለብሮድካስቲንግ፣ በክላውድ ላይ ለተመሰረቱ የ5ጂ ጌሞች እንዲሁም የIOT ቴክኖሎጂዎች እውን ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡

የህዝባችንን ኑሮ በእጅጉ የሚያሻሽል፣ የደንበኞችን ምቾት የሚጨምር፣ የቢዝነስ እንቅስቃሴ እና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ምህዳር በመፍጠር #ዲጂታል_ኢትየጵያን እውን ማድረጋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

አዲስ ፍጥነት፣ አዲስ ምቾት፣ አዲስ አኗኗር!

ለበለጠ መረጃ: https://bit.ly/49uT5WX

#ITU #GSMA
#ካባ

ልጆቾን ማመላለስ በማይመችዎ ቀናት እንዳያስቡ ካባ የልጆች ት/ቤት ሰርቪስ በሰዓቱ ደርሶ ልጅዎን በእንክብካቤ እና በምቾት ከቤት ወደ ት/ቤት ያደርሳል። አሁኑኑ በመመዝገብ የተሻለውን አማራጭ ለልጅዎ ያበርክቱ።
አገልግሎታችን፡
-  የልጆን ጉዞ በቀጥታ የሚከታተሉበት መተግበሪያ
-  ሴት ረዳቶች
-  የተመረጡ አሽከርካሪዎች
- በፈለጉት አማራጭ በግል በቡድን ፣ ቢፈልጉ ሚኒ ባስ ወይም በአውቶሞቢል የተዘጋጀ ነው።

መተግበሪያውን እዚህ ላይ በማውረድ ይመዝገቡ 
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.vintechplc.kabba.parent
ለበለጠ መረጃ 0960009900 ይደውሉ።
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ " በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢሎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት እንደማይቻል ይታወቅ " - የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢሎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ቢከለከልም " ይሄን አልሰማንም " ያሉ ሰዎች የነዳጅ ተሽከርካሪዎችን ገዝተው ወደ ሀገር እያመጡ ይገኛሉ ተብሏል። ይህ የተሰማው የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች…
#AddisAbaba

በህዝብ ትራንስፖርት የሚጠቀሙ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት ፦
* እንዳይቸገሩ ፣
* መንገድ ላይ ሰልፍ ተሰልፈውም ጊዜያቸው እንዳይጠፋ ፣
* ባሰቡበት ሰዓት በህዝብ ትራንስፖርት ያሰቡበት ቦታ እንዲደርሱ በተለየ ሁኔታ ለተወሰነ ሰዓት የግል ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ #ለመገደብ እየተሰራ ይገኛል። ይህ በቅርብ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ምን አለ ?

ዓለሙ ስሜ (ዶክተር) ፦

" በአዲስ አበባ በትራንስፖርት የሚሄደው ህዝብ አገልግሎቱን በአግባቡ የማያገኝበት ፣ ባሰበበት ሰዓት ተነስቶ ባሰበው ሰዓት የፈለገው ቦታ እንዳይደርስ የሚያደርጉ ሶስት ምክንያቶች አሉ።

1ኛ. የህዝብ ትራንስፖርት የተሽከርካሪ እጥረት ነው።

2ኛ. የመንገድ መዘጋጋት ነው።

3ኛ. የስምሪት እና የተሽከርካሪ ማናጅመት አለመዘመን ነው።

በነዚህ ሶስት ጉዳዮች እየሰራን ነው።

የተሽከርካሪ ቁጥር ለመጨመር በየዓመቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአንድ ጊዜ ብዙ ሰዎች የሚጭኑ ማስ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች እየገዛ ወደ አገልግሎት እያስገባ ነው። ዘንድሮም እየተሰራ ነው። በዓለም ባንክ በርካታ ተሽከርካሪዎች ተገዝተው ለአዲስ አበባ ከተማ እንዲሰጡ እየተሰራ ነው።

የመንገድ መዘጋትን በተመለከተ መንገዶቻችን የተወሰኑ ናቸው። ሀገሪቱ ካላት ተሽከርካሪ በአብዛኛው አዲስ አበባ ውስጥ ነው ያሉት። ይሄን ችግር ለመቅረፍ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

አንደኛው ለህዝብ ጭነት ተሽከርካሪዎች የተለየ መንገድ ፣የተለየ መስመር ማበጀት ነው እሱም ተበጅቶ እየተሰራ ነው ያለው። ግን በቂ አይደለም።

ሁለተኛው በተለይ በስራ መውጫና መግቢያ ሰዓት #የተወሰኑ ሌሎች ተሽከርካሪዎችን እንዳይንቀሳቀሱ የመገደብና ህዝብን የሚጭኑ አውቶብስ ቶሎ ቶሎ እንዲመላለስ ማድረግ ነው። ከተሽከርካሪ እጥረት መንገድ ላይ የሚቆመውን ህዝብ ባለው ተሽከርካሪ ቶሎ ለመጫን መንገድ ክፍት የሚሆንበት #ሰዓቶችን መርጠን ጥናቱ አልቋል ወደ ስራ በቅርቡ ይገባል።

ስለዚህ በስራ መውጫና መግቢያ ሰዓት የግል መኪና ተጠቃሚዎች የሚገደቡበት ሁኔታ ይፈጠራል። ይሄም የግል መኪና ተጠቃሚዎች ወደህዝብ የትራንስፖርት አማራጭ እንዲገቡ የማስገደድ ሁኔታ ይመጣል። ይህ ለህዝብ አውቶብስ መንገድ ይከፈታል፣ ነዳጅ ይቆጠባል፣ የአየር ብክለትን ይቀንሳልም። ይህን አሰራር በቅርብ ተግባራዊ እናደርጋለን።

የአውቶብሶች መነሻ እና መድረሻ ሰዓታቸው እንዲታወቅ በቴክኖሎጂ የማስደገፍ ስራ ከዓለም ባንክ ጋር እየተሰራ ነው። ይህም ስራ ካለቀ ከዚህ ጋር ያሉት ችግሮች ይፈታሉ። "

#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
በአዲስ አበባ የመሬት አገልግሎቶች ታገዱ።

በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የመዋቅራዊ አደረጃጀት ጥናት ተከናውኖ በአዳስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ጸድቆ ወደ ተግባር እንዲገባ የተወሰነውን ውሳኔ መሰረት በማድረግ የሠራተኞች የባህሪ እና የቴክኒክ ፈተና ተሰጥቶ ውጤቱ ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

በዚህም አዲስ በተጠናው መዋቅራዊ አደረጃጀት ጥናት መሰረት የሰራተኞች ድልድል ተሰርቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከዛሬ ጥር 21 /2016 ዓ.ም ጀምሮ የመሬት አገልግሎቶች በጊዜያዊነት መታገዳቸውን የአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

አዲሱን ያልተገደበ የኢንተርኔት ጥቅላችንን እንደልብ እየተጠቀምን የእረፍት ቀኖቻችንን ፈታ እንበል::

🔗 የM-PESA Appን በዚህ ሊንክ ያውርዱ: https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#FurtherAheadTogether
#የሥዕል_ውድድር #ጥቆማ

በመቐሌ እና አከባቢው የምትገኙ የሥዕል ችሎታ ያላችሁ ወጣቶች ሪድም ዘጀነሬሽን ከUSAID/OTI ጋር በመተባበር ላዘጋጀው የቡድን የስዕል ውድድር ላይ እንድትሳተፉ ጥሪ አቅርቧል።

ከዚህ ቀደም በሰላም ጉዳዮች ላይ ተከታታይ ውድድሮች ያካሄደው ሪድም ዘጀነሬሽን አሁን ደግሞ በመቐሌ ለሚገኙ ችሎታው ላላቸው እድሜያቸው 13 - 18 ላሉ ታዳጊዎችና 19 - 29 ላሉ ወጣቶች በአጠቃላይ ለ50 ተሳታፊዎች እድሉን አመቻችቷል።

ዘላቂ ሠላም፤ ጽናት፤ እንዲሁም የማኅበራዊ ችግሮችን ማከም በሚችሉ ኃሳቦች ላይ ተወዳዳሪዎች ተመርጠው የሥዕል ውድድሩ ላይ እንዲሳተፉ ይደረጋል። በውድድሩ የተመረጡ ሥራዎች በክልሉ በሚዘጋጁ ፎረሞች ላይ የሚቀርብ ይሆናል።

ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች፥ እስከ ጥር 24 ድረስ ማመልከት የሚችሉ ሲሆን በተከታዩ ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።  https://forms.gle/qYmEMneTagoSgKVQA

ዝርዝር መስፈርቱን ለማግኘት https://telegra.ph/Art-as-a-path-to-Healing-01-29

@TikvahethMagazine
#Sidama #Hawassa

" የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ባለማግኘታችን ከሀገር ወጭ ያገኘነው የስራ እድል ሊያልፍብን ነው " - ወጣቶች

" ያለው አንድ ማሽን ብቻ በመሆኑ ችግሩን ባፋጣኝ መቅረፍ አልተቻለም " -  የሀዋሳ ከተማ ገቢዎች መምሪያ

በሀዋሳ ከተማ እና በአካባቢዉ ያሉ ስራ አጥ ወጣቶች ያገኙትን የውጭ ሀገር የስራ እድል ተከትሎ ማሟላት ካለባቸዉ መስፈርት ውስጥ አንዱ የሆነዉ የግብር መለያ ወይም ቲን ነምበር ለማግኘት ወደ ሀዋሳ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ቢያቀኑም ላለፉት ሰላሳ ቀናት ሊሳካላቸዉ አልቻለም።

እነዚህ ከሀዋሳና አካባቢዋ የተሰባሰቡ ወጣቶች ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት በተለያዬ መልኩ ያገኙትን የስራ እድል ለመጠቀም የጀመሩትን እንቅስቃሴ  የቲን ነምበር ጉዳይ እንቅፋት እንደሆነባቸዉና አሁን ላይ ጭራሹኑ " አናስተናግድም " የሚል ማስታወቂያ መውጣቱን ይናገራሉ።

ከዚህ በተጨማሪም ቢሮዉ " አናስተናግድም " የሚል ማስታወቂያ ካወጣ በኋላ በጎን አገልግሎት ሲሰጥ ይገኛል የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎች በዚህ ምክኒያትም በከፍተኛ  ሁኔታ እየተጉላሉ መሆኑን ያነሳሉ።

ጉዳዩን በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ በሀዋሳ ከተማ ገቢዎች መምሪያ የግብር አወሳሰንና የደንበኞች አገልግሎት ሀላፊዋ ወይዘሮ ሙላት ዮሴፍ እንደገለፁት ፤ በከተማዉ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ስምንት የቲን ነምበር ማሽኖች ስራ ማቆማቸዉን በማንሳት አሁን ላይ በአንድ ማሽን ብቻ እየታገሉ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም " በከተማዉ አገልግሎት እየሰጠ ያለዉ አንድ ማሽን ብቻ በመሆኑ መፍትሄ መስጠት አልቻልንም " ያሉት ሀላፊዋ አገልግሎቱ እስከ ጥር ሰላሳ የታገደው ጫና በመፈጠሩና ወሩ የግብር መሰብሰቢያ ወቅት በመሆኑ ወጣቶችን ማስተናገድ ባለመቻሉ መሆኑን አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ፤ የክልሉ መንግስት እንደሀገር የተጀመረዉን የውጭ ሀገር ህጋዊ  የስራ ስምሪትና ኮታ ተከትሎ የተቀመጠውን የትምህርት ደረጃ እድሜና ፍላጎት የመሳሰሉ መስፈርቶች ያሟሉ ከ900 በላይ ወጣቶች ወደ ሳውዲና መሰል የአረብ ሀገራት መላኩን በመግለጽ  አሁን ላይ የቲን ነምበር ፍላጎት ያላቸዉ ወጣቶች እድሉን በመንግስት በኩል ያገኙ  ሳይሆን ይልቁንም በራሳቸዉ መንገድ ያገኙ መሆናቸዉን የክልሉ የስራ ክህሎት ኢንተርፕራይዞች ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀገረጺዮን አበበ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ኃላፊዋ እንደሚሉት ወደ #ካናዳ እና ሌሎችም ሀገራት በራሳቸዉ ጥረት ለመሄድ ቲን ነምበር የሚያስፈልጋቸው ወጣቶችን ለመርዳት ጥረት ላይ መሆናቸውን በመግለጽ መምሪያዉ ያለዉ አንድ ብቻ የቲን ነምበር ማሽን ግን ችግር መፍጠሩን አመልክተዋል።

ችግሩ የሚፈታበትን መንገድ ለመፍጠር ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር እየተወያዩ መሆኑን አስረድተዋል።

አሁን ላይ እስከ ጥር 30 አገልግሎት እንደማይኖር የሚገልጸዉን ማስታወቂያ የሰሙ ወጣቶች ጭንቀት ዉስጥ ሲሆኑ የሚመለከተዉ አካል አስፈላጊዉን መፍትሄ እንዲሰጣቸዉ ጠይቀዋል።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ጥያቄ ብናቀርብም አስተያዬት ከመስጠት ተቆጥቧል።

መረጃውን የላከው የሀዋሳዉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነዉ።

@tikvahethiopia
#አሜሪካ

" የዋሽንግተን አጠቃላይ የመሳሪያ ሽያጭ መጠን 238 ቢሊየን ዶላር ደርሷል " ተባለ።

አሜሪካ በፈረንጆቹ 2023 ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ሽያጭ አስመዝግባለች።

" የዋሽንግተን አጠቃላይ የመሳሪያ ሽያጭ መጠን 238 ቢሊየን ዶላር ደርሷል " የተባለ ሲሆን፤  ይህም በ2022 ከነበረው የ50 በመቶ ብልጫ ማሳየቱ ተመላክቷል።

ለሽያጩ መጨመር የሩሲያ ዩክሬን #ጦርነት ከፍተኛ ድርሻ አለው የተባለ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ የአሜሪካ መከላከያ ኩባንያዎች ለውጭ ሀገራት በቀጥታ ያደረጉት ሽያጭ እንደሆነ ነው።

ፖላንድ የአሜሪካን የጦር መሳሪያ በመግዛት ቀዳሚ ሀገር እንደሆነች ለተቀናጀ የአየር እና የሚሳኤል መከላከያ የውጊያ ትዕዛዝ ስርዓትም 4 ቢሊየን ዶላር ማውጣቷ ተመላክቷል።

"አሜሪካ ለውጭ ያቀረበችው የጦር መሳሪያ ሽያጭ ባለፈው ዓመት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ሲል ፖለቲኮ ዘግቧል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን በዚህ ይከታተሉ ፦ https://publielectoral.lat/+LM-bJ8NzZMcxMjA8

@ThiqaMediaEth
#ሽረ

" የነቀዘ ፣ የተበላሸና መጥፎ ጠረን ያለው የአርዳታ ዱቄት እየተሰጠን ነው " - ተፈናቃዮች

" ጉዳዩን ደርሼበት የታደለው የተበላሸ ዱቄት እንዲሰበሰብ የሚያስጠነቅቅ ደብዳቤ ፅፊያለሁ "  - የእንዳስላሰ ሽረ ከተማ አስተዳደር

በትግራይ ክልል፣ ሰሜን ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ ሽረ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች ለድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፤ የተበላሸ ፣መጥፎ ጠረን ያለው እና የነቀዘ ዱቄት ከለጋሽ ደርጅቶች መታደላቸውን ገልጸዋል።

ላለፉት 13 ወራት የረባ ሰብአዊ እርዳታ ባለማግኘታቸው በከባድ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ የገለፁት ተፈናቃዮቹ ፤ ከረጅም ጊዚያት በኃላ ጥር 20/2016 ዓ.ም መሰጠት የተጀመረው ዱቄት ጥራት የሌለው ፣ የተበላሽ ፣ የነቀዘና መጥፎ ጥረን ያለው መሆኑ በማስረጃ አስደግፈው አቅርበዋል። 

የቴሌቪዥን ጣቢያው " ለተፈናቃዮቹ የተሰጠው ዱቄት ለምግብነት ቢያውሉት ለጤናቸው ጠንቅ እንደሚሆን የምግብ ባለሙያዎች አረጋግጠውልኛል " ብሏል።  

ዱቄቱ በእርዳታ ያከፋፈሉ ለጋሽ ድርጅቶች 'ተበላሸ' ስለተባለው እህል ምላሽ እንዲሰጡ የተደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም።

ጉዳዩ በጥብቅ እየተከታተለው መሆኑ የገለፀው የእንዳስላሰ ሽረ መንግስታዊ አገልግሎት ፅህፈት ቤት ፤  ዱቄቱ ያከፋፈሉ ለጋሽ ድርጅቶች ያደሉት እንዲሰበስቡና ማደል እንዲያቆሙ የሚጠይቅ ደብዳቤ መፃፉን አስታውቋል።

ፅህፈት ቤቱ ለለጋሽ ድርጅቶች በፃፈው ደብዳቤ በመጋዝን የተከማቸውና ለተፈናቃዮች የታደለው ዱቄት ተዘዋውሮ መመልከቱንና የተበላሸ መሆኑ ማረጋገጡ ገልጿል።

ስለሆነም ዱቄቱ በላፕራቶሪ ተጨማሪ ምርመራ እስኪደረግለት ድረስ Lot No. 1 MFD March 2023 & Exp. /Best Before February 2024 በሚል የሚታወቅ የተከማቸና ወደ ተፈናቃዮች የደረሰ ዱቄት እንዲሰበሰብና እንዲከለከል በፃፈው ደብዳቤ ማስጠንቀቁን የድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ዋቢ በማድረግ የመቐለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል መረጀውን አጋርቷል።
                  
@tikvahethiopia