TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሙስሊም ሊቃውንት/ #ዓሊሞች ጉባዔ ከትላንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ  እየተካሄደ ይገኛል።

ለሶስት ቀን ይቆያል የተባለው ይኸው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ  ምክር ቤት ሁለተኛው ዓመታዊ የዓሊሞች (የሙስለም ሊቃውንት) ጉባዔ ላይ ፦
- #የትግራይ
- የሶማሊ
- የአፋር
- የአማራ
- የኦሮሚያ
- የጋምቤላ
- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ
- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ
- የደቡብ ኢትዮጵያ
- የሐረሪ
- የሲዳማ
- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ የዑላማ ምክር ቤቶች እተካፈሉ ይገኛሉ።
                          
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶ/ር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ትላንት ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር ፤ " ጦርነት በፈጠረው የሰላም እጦት ችግር ሳቢያ ተለያይተን ከነበርነው የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር ግንኙነታችን ቀጥሎ ዛሬ በአንድ ጉባዔ ላይ መታደማችን የሚያስደስትና የሠላምን ዋጋ ከፍ የሚያደርግ ነው " ብለዋል።

ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ፤ " የሀገራችን ሙስሊም ሊቃውንት በከፍተኛ ችግር ውስጥ ሆነው ዲኑን ለትውልዶች ለማሻገር እና ማኀበራዊ ትስስር እንዲፈጠር ትልቅ ልፋት የሚያደርጉ ታላቅ የሕዝብ ባለውለታና የዲን መሪ ናቸው " ብለዋል።

የሀገር አቀፉ የዑለማ ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢና የፈትዋ ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ጀይላን ኸድር በበኩላቸው፣ " የዑለማው በዚህ ዓይነት ትስስር መፍጠር ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ አንድነት ትልቅ ፋይዳ አለው " ብለዋል።

የዑለማው ጉባዔ የሙስሊሙ ችግሮች እና የሚገኝበት ተጨባጭ ሁኔታ የሚገለጹበት በመኾኑ፣ የሸሪዓ ፍርድ ቤት ቃዲዎቾ፣ የየክልሉ የዑለማ ም/ ቤት እና የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ኃላፊዎች በዚህ መድረክ ላይ ተገናኝተው መምከራቸው መድረኩን ታሪካዊ ያደርገዋል ተብሏን።

የጉባዔው ተሳታፊ የሆኑት ክልሎች የየክልላቸውን ተጨባጭ ሁኔታ አስመልክተው ለጉባዔው ሪፖርት ማቅረባቸውን ለማቀው ተችሏል።

የኢትዮጵያ ሙስሊም ሊቃውንት ሁለተኛው ዓመታዊ ጉባዔ ዛሬም ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ እልምና ጉዳዮች ጠቅላት ምክር ቤት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

​NB. የትግራይ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከቀናት በፊት ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር የነበረውን አለመግባባት በይቅርታ ፈቶ ወደ ቀደመው ግኝኑነት መመለሱ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#መንገድ

ወደ ጅቡቲ ለመጓዝ ሌላ አማራጭ ነው የተባለው የአሳይታ- አፋምቦ-ጅቡቲ ድንበር መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ዋና ስራው ተጠናቆ ለትራንስፖርት ክፍት ሆነ።

ወደ ጅቡቲ ለመጓዝ አገልግሎት በመስጠት ላይ ከሚገኘው የጋላፊ መስመር በተጨማሪ ለወደፊቱ ሌላ አማራጭ ሆኖ የሚያገለግለው የአሳይታ-አፋምቦ-ጅቡቲ ድንበር መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቆ ለትራንስፖርት አገልግሎት ክፍት መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አሳውቋል።

የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ስራዎች ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ ሲሆን፣ የትራፊክ ምልክቶች ተከላ ፤ የቀልም ቅብ ስራዎች እና ሌሎች ጥቃቅን ስራዎች ተገባደዋል ተብሏል።

በአካባቢው ከዚህ ቀደም ደረጃውን የጠበቀ የመንገድ መሰረተ ልማት ያልነበረ በመሆኑ ህብረተሰቡ በትራንስፖርት  እጦት ምክንያት በእግር እና በግመል ከመጓዝ ውጭ ሌላ አማራጭ አልነበረውም።

መንገዱ በዋናነት ኢትዮጵያን በአሳይታ በኩል ከጅቡቲ ጋር በቅርበት ያስተሳስራል። የኢትዮጵያን የገቢ እና ወጪ ንግድ በማቀላጠፍ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንደሚኖረው ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም አሳይታ ከተማን ከአፋምቦ ወረዳ ብሎም በርካታ ቀበሌዎችን በማገናኘት የህዝብ ለህዝብ ትስስሩን ይበልጥ ያጠናክራል ተብሏል።

ይህ አካባቢ የአዋሽ ወንዝ ተፋሰስ የሚገኝበት በመሆኑ በርካታ ምርቶች የሚመረትበት መስመር ነው። ከእነዚህ ምርቶች መካከል ፦
* ከፍተኛ የጨው ምርት፣
* ጥጥ፣
* ቴምር፣
* ሰሊጥ፣
* ቲማቲም፣
* ሽንኩርት፣
* ብርቱካን፣ ሃባብ እና በርካታ ፍራፍሬዎች ይጠቀሳሉ።

የመንገዱ መገንባት እነዚህን ምርቶች በቀላሉ ወደ ማዕከላዊ ገበያ ብሎም ወደ ጀቡቲ ለማድረስ ይበልጥ ያግዛል ተብሎለታል።

ከዚህ ባሻገር በመስመሩ የትምህርት ፣ ጤና እና መሰል ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግልጋሎቶችን በአፋጣኝ አንዲስፋፉ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በተጨማሪም ይህ መስመር አሁን ላይ ያለውን ሚሌ - ዲቼ ኦቶ-ጋላፊ-ጅቡቲ ወደብ ያለውን መንገድ በ30 ኪሎ ሜትር ያሳጥረዋል።

ወደፊት በአካባቢው ሊመረቱ የሚችሉ የፋብሪካ ውጤቶችን (ስኳር ፣ የስንዴ ዱቄት) ወደ ውጪ ገበያ ለማቅረብ ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል።

አጭር መረጃ ስለ መንገድ ፕሮጀክቱ ፦

- የመንገዱን ግንባታ ለማከናወን የተመደበው 1,600,901,379 (አንድ ቢሊዮን ስድስት መቶ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ዘጠኝ ብር) ሙሉ ለሙሉ የተሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው።

- የመንገዱ ርዝማኔ 50.34 ኪሎ ሜትር ነው። የጎን ስፋቱ ትከሻን ጨምሮ በገጠራማ ሥፍራዎች 10 ሜትር ፣ በወረዳ ከተሞች 19 ሜትር እና በዞን 21.5 ሜትር ስፋት አለዉ።

- ፕሮጀክቱ የ3 ድልድዮች ግንባታንም ባካተተ መልኩ ነው የተካሄደው።

- ግንባታውን ያካሄደው ሀገር በቀሉ የስራ ተቋራጭ አሰር ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ነው። የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ይዲዲያ ኢንጅነሪንግ ኮንሰልታንትስ አከናውኗል።

Via ERA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ ትግራይ ክልል ውስጥ በ5 መጠለያ ጣቢያዎች ከ900 በላይ ሰዎች ከምግብ እጦት እና ከመድሃኒት እጥረት ጋር በተያየዝ ሞተዋል ሲል የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አሳውቋል። የተቋሙ የመቐለ ቅርንጫፍ ፤ ረሃብ የሰው ህይወት መንጠቅ ከጀመረ ወራቶች መቆጠሩንም ገልጿል። * በሽረ * አክሱም * በአብይአዲ * በመቐለ * ዓዲግራት ባሉ መጠለያ ጣቢያዎች የሰው ህይወት በረሃብ እና በመድሃኒት እጥረት…
#Update

በአማራ እና ትግራይ ድርቅ ባስከተለው #ረሃብ የሰዎች ህይወት መጥፋቱን እንዳረጋገጠ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ምን ያህል ሰዎች ድርቅ ባስተከተለው ረሃብ ሞቱ ?

በትግራይ ክልል ፤ በማዕከላዊ ዞን 334 ሰው ከድርቁ ጋር በተያያዘ የሞተ ሲሆን ከዚህ ዞን ውስጥ የተቋሙ ቁጥጥር ቡድን ካየው የአበርገሌ ወረዳ 91 ሰው መሞቱን እና ከደቡብ ምስራቅ ደግሞ የኢስራ ወአዲ ወጅራት ወረዳ 17 ሰው መሞቱን ለማወቅ እንደተቻለ ገልጿል።

በአጠቃላይ 351 ሰዎች መሞታቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ ፦
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸው፣
በርካታ እንስሳት መሞታቸው፣
በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ትምህርት ቤት አለመመዝገባቸው፣
በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጣቸው በሪፖርቱ ተገልጿል።

በአማራ ክልል ደግሞ የክልሉ አደጋ መከላክልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኮሚሽን በኩል በድርቅ ምክንያት የሞተ ሰዉ እንደሌለ ቢገለፅም በስልክ መረጃ ከተወሰደባቸው ፦
* በሰሜን ጎንደር ዞን በበየዳ ወረዳ 17 ሰዎች፣
* በዋግኸምራ ዞን በዝቋላ ወረዳ 2 ሰዎች
* በበየዳ ወረዳ 2 ህፃናት በድምሩ 21 ሰዎች ድርቁ ባስከተለው #ረሃብ መሞታቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል።

በአልሚ ምግብ እጥረት ምክንያት በበየዳ ወረዳ 23 ህፃናት ተገቢዉን ዕድገት ባለማግኘታቸዉ ሞተው መወለዳቸውም ተረጋግጧል፡፡

በአማራ ክልል አደጋ መከላክልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኮሚሽን በኩል በድርቅ የተፈናቀለ እና በመጠለያ ካምፕ የሚገኝ ዜጋ የለም በሚል ቢገለጽም ናሙና ተወስዶ በስልክ መረጃ ከተወሰደባቸው ዞኖች እና ወረዳዎች በኩል በተገኘዉ መረጃ በድርቁ ምክንያት ፦
° የመኖሪያ ቀያቸውን የለቀቁ፣
° ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለዉ የሚገኙ
° በቆርቆሮ እና ኬንዳ መጠለያ የሚገኙ የተፈናቀሉ ዜጎች መኖራቸው ተረጋግጣል።

ለአብነት በዋግኸምራ ዞን በአበርገሌ ወረዳ 12270 ሰዎች፣ በሰሜን ጎንደር ዞን 9100 በላይ ሰዎች አሉ።

NB. የፌዴራል መንግሥትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በረሃብ ምክንያት የሰው ህይወት ጠፋ የሚባለው ውሸት መሆኑን እና የድርቅ አደጋ ወደ ረሃብ ተቀይሮ የሰውን ህይወት የሚያጠፋበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ የሀገሪቱ መዋቅራዊ አደረጃጀት የሚፈቅድ እንዳልሆነ መግለፃቸው አይዘነጋም።

(የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ይፋ ያደረገው ዝርዝር ሪፖርት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም

የዘመናችንን መጨረሻውን የ5ኛ ትውልድ ኔትወርክ አገልግሎት በሐረር እና ሀሮማያ ከተሞች በይፋ ማስጀመራችንን ስናበስር እጅግ ደስ ይለናል!

አገልግሎቱን ከትናንት በስቲያ በድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም ቀደም ሲል በአዲስ አበባ፣ አዳማ እና ጂግጂጋ ከተሞች ማስጀመራችን ይታወሳል።

የ5ጂ የሞባይል ኔትወርክ ወሳኝ ለሆኑ፣ በከፍተኛ ቅጽበት፣ ፍጥነትና በተመሳሳይ ወቅት (real-time) መከወን ላለባቸው ማኑፋክቸሪንግ፣ ጤና ፣ ትምህርት፣ ትራንስፖርት፣ ግብርና፣ ስማርት ሆም፣ ለብሮድካስቲንግ፣ በክላውድ ላይ ለተመሰረቱ የ5ጂ ጌሞች እንዲሁም የIOT ቴክኖሎጂዎች እውን ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡

የህዝባችንን ኑሮ በእጅጉ የሚያሻሽል፣ የደንበኞችን ምቾት የሚጨምር፣ የቢዝነስ እንቅስቃሴ እና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ምህዳር በመፍጠር #ዲጂታል_ኢትየጵያን እውን ማድረጋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

አዲስ ፍጥነት፣ አዲስ ምቾት፣ አዲስ አኗኗር!

ለበለጠ መረጃ: https://bit.ly/49uT5WX

#ITU #GSMA