TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል⬆️

በቤንሻንጉል ጉምዝ ካማሼ ዞን በተለይ በበሎይ ጅጋንፎይ ወረዳ በተባባሰ ግጭት ከ72 ሺህ ሰዎች በላይ ተፈናቅለው #ነቀምት እንደሚገኙ የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ #ታከለ_ቶሎሳ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

በደንብ #የተደራጀና የታጠቀ ኃይል በተለይ ትላንት ከፍተኛ ጥቃት ከፍቶ በኦሮሚያ በኩል የሟቾች ቁጥር 23 መድረሱን ገልፀዋል።

የቤንሻንጉል ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #አበራ_ባይታ በበኩላቸው ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልፀው "ቁጥሩ የተጋነነ ነው" ብለውታል። በቤንሻንጉል ጉምዝ በኩልም 31 ሰዎች ሞተዋል ይላሉ።

በከተማው ውስጥ ዘጠኝ ሰላማዊ ሰዎች #መገደላቸውን አረጋግጠዋል።

ከሁለቱ ክልል VOA ባገኘው አጠቃላይ መረጃ መጀመሪያ ላይ አራት ተገደሉ የተባሉ አመራሮችን ጨምሮ በአምስት ቀናት ውስጥ የ67 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች መኖራቸውና ብዙ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውና ሁለቱም ክልሎች ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia