TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሀዋሳ

ካለፉት ሁለት ቀናት የተሻለ ሰላም እና መረጋጋት በዛሬው ዕለት ነበር። ከተማዋ ወደቀደመው እንቅስቃሴዋ እየገባች ነው። የተወሰኑ ባጃጆች እና ታክሲዎች ሲንቀሳቀሱ ነበር/ከመናኸሪያ ሞቢል-ፒያሳ የታክሲ እንቅስቃሴ ነበር/። ብዙሃኑ የንግድ ቤቶች ተዘግተው ነው የዋሉት። አብዛኞቹ ባንክ ቤቶችም ዝግ ነው የዋሉት። በየሰፈሩ ያሉ ሱቆች ተከፍተው ደምበኞቻቸው ሲያስተናግዱ ነበር። እንደሰማሁት ከሆነ በሸቀጦች ላይ መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል። ከሁከቱ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎችን አሁንም የፀጥታ አካላት እያሰሩ እንደሆነ ከከተማው ነዋሪዎች ሰምቻለሁ። ከትላንት ምሽት ጀምሮ የመጠጥ ውሃ ተመረዘ ተብሎ ሲናፈስ የነበረው ወሬም ሀሰትና ህዝቡን ለማሸበር የተደረገ እንደሆነ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በሚዲያ ገልፀዋል።

#ይርጋለም

ባለፉት ሁለት ቀና ከፍተኛ የፀጥታ ችግር የነበረባት እድሜ ጠገቧ ይርጋለም ከተማ ዛሬ ፀጥ ረጭ ብላ ውላለች። በከተማው ምንም አይነት እንቅስቃሴ አልነበረም። ሱቆች፣ ባንኮች፣ ሆቴሎች ዝግ ነው የዋሉት። በከተማይቱ ውስጥ የመከላከያ እና የፌዳራል የፀጥታ ሃይላት በመኪና ሲዘዋወሩ እንደነበር የከተማው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

#አለታወንዶ

ባለፉት ሁለት ቀናት በአለታ ወንዶ የነበረው የፀጥታ ችግር ዛሬ መጠነኛ መሻሻል አሳይቷል። ከተማዋ ሙሉ በሙሉ ከእንቅስቃሴ ውጭ ሆናለች። ሰዎች አልፎ አልፎ ካልሆነ አይንቀሳቀሱም። አንዳንድ ሱቆች ተከፍተው ነበር። ልክ እንደሀዋሳ በአለታ ወንዶ ከተማ የዋጋ ጭማሪ ነበር። ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች እንደገለፁልን ከተማውን ወደቀደመው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ስራዎች እየተሰሩ ነው። ካለፉት ሁለት ቀናት ዛሬ ከተማዋ ትሻላለች።

ይቀጥላል👇
#ሀዋሳ

የሀዋሳ ከተማ ሰላም ቀድሞ ወደነበረበት እየተመለሰ ይገኛል። በከተማይቱ የንግድ እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴም እየተጀመረ ነው። ካለፉት ቀናት በእጅጉ የተሻለ መረጋጋት እና ሰላም በከተማዋ መስፈኑን በስልክ ያነጋገርናቸው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል።

#ወንዶገነት

በወንዶ ገነት ከተማ አርብ ዕለት ተከስቶ በነበረው ግጭት ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን የሚታወስ ሲሆን ትናንት ቅዳሜም በወንዶ ገነት ውጥረት ነግሶ ነው የዋለው። ይሁን እንጂ ዛሬ እሑድ በከተማው መረጋጋት እንደሚታይ አንድ የአይን እማኝ ለቢቢሲ ገልፀዋል “የትራንስፖርት አገልግሎት ጀምሯል። ሱቆችም ከሞላ ጎደል ተከፍተዋል። የጸጥታ ኃይል አስከባሪዎች በስፋት በከተማዋ ሲንቀሳቀሱ ነው የዋሉት።
/BBC/

#ይጋለም

ከተማዋ ወደ ቀድሞ እንቀስቃሴ አልተመለሰችም፤ ሆኖም ግን ካለፉት ሁለት ቀናት የተሻለ #መረጋጋት አለ። ዛሬ ላይም ቢሆን በይርጋለም ከተማ የደህንነት ስጋት መኖሩን ለBBC የተናገሩ የከተማዋ ነዋሪ፤ በዚሁ ምክንያት በርካታ የንግድ ተቋሟት በራቸውን ዝግ አድርገው እንደዋሉ ገልፀዋል።

#ሀገረሰላም

በስልክ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ዛሬ ካለፉት ሁለት ቀናት የተሻለ ሰላም እና መረጋጋት እንደታየ ገልፀዋል፤ ስጋቶች ግን አሁንም አሉ ብለዋል። የመከላከያ ሰራዊት በከተማው ይገኛል በየቦታውም ቅኝት ሲያሰርግ ውሏል ሲሉ የዛሬውን ሁኔታ አስረድተዋል።

#አለታወንዶ

የዛሬው ዉሎ ከትላንትና እና ከትላንት በስቲያ ከነበረው እጅጉ የተሻለ እና መረጋጋት የታየበት እንደነበር ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል።

በሲዳማ ዞን የኢንተርኔት አገልግሎት አልተጀመረም!

@tsegabwolde @tikvahethiopia