TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ህዝቡ አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳ ለማድረግ እየተፈፀሙ ያሉ ሴራዎችን መታገል አለበት"– የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት
.
.
የተለያዩ የአገሪቱ የፖለቲካ ጉዳዮችን ሌላ መልክ በመስጠት አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳና እርስ በእርሱ እንዲጋጭ ለማድረግ እየተፈፀሙ ያሉ ሴራዎችን መላው ህዝብ እንዲታገል የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ #ለማ_መገርሳ ጥሪ አቀረቡ።

የክልሉ ፕሬዚዳንት ጥሪውን ያቀረቡት በአዳማ ከተማ ዛሬ በተጀመረው 9ኛው የጨፌው ጉባኤ ላይ ከጨፌው አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።

አባላቱ በክልሉ ሰላም፣ የህግ የበላይነትን ማስከበር፣ ህገ-ወጥነትን በመከላከል፣ ክልሉ በአዲስ አበባ ላይ ካለው ጥቅም ጋር የተያያዘ እና ሌሎች በርካታ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጥያቄ አንስተዋል።

የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ በዚሁ ወቅት ህዝቡ ጠረፍ አካባቢ ይፈፀም የነበረውን የፖለቲካ #ሴራ ወደመሃል አገር ለማምጣት እየተደረገ ያለውን ጥረት ሊገታ ይገባል ብለዋል።

ህገ-ወጥነትን ለመከላከል የሚወሰደውን እርምጃ እንደአብነት ያነሱት አቶ ለማ የህዝቡን ጥቅም ማእከል አድርጎ የሚሰራ አመራር እና ህዝቡ ሌሎች በሚቀርፁለት አጀንዳ መመራት እንደሌለበት አስገንዝበዋል።

እንዲያም ሆኖ “ህገ-ወጥ ቤቶች ሲገነቡ ቁጭ ብሎ የሚመለከት አመራር እያለ ቤት እንዲፈርስ መደረጉ በራሱ #ጥፋት ነው” ሲሉም ገልፀዋል።

የቀበሌና የጎጥ አመራር እንዲሁም የከተሞቹ ካቢኔዎች ቤቶቹ ሲገነቡ ያለእነርሱ እውቅና መገንባታቸው፤ ከዚህም አልፎ ግንባታዎቹን በእጅ አዙር ህጋዊ ሲያስደርጉ በመቆየታቸው ግንባር ቀደም ተጠያቂ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ኦሮሞ እና ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላቸውን ጥቅም አስመልክቶ በተነሳው ጥያቄ ላይ ማብራሪያ ሲሰጡም ለውጡን ለመቀልበስ በዳራ አገር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች አሁን በአዲስ አበባ ጉዳይ አንዱን በሌላው በማስነሳት እርስ በእርስ ለማበላላት የሚፈፅሙት ተግባር ስለሆነ ህዝቡ ጉዳዩን በጥንቃቄ ማየት እንዳለበት አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ጉዳይ በታሪክና በህገ-መንግስቱ መሰረት በምክክርና ህግን በተከተለ ሁኔታ ብቻ የሚፈታ እንደሚሆነም ነው አቶ ለማ ያብራሩት።

የልማት ፕሮጀክቶች መጓተት ዋነኛው ምከንያቶች የፋይናንሰ ችግር፣ የተቋራጮች አቅም ማነስ እንደሆነም አነሰተዋል።

የእነዚህ ሁለት ችግሮች ውጤት ተደማምሮ በልማት ፕሮጀክቶቹ ላይ ጫና ማሳደሩን የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ ተናግረዋል።

ከዚሀም በተጨማሪ የክልሉ መንግስት በሰላም ማስከበርና በተፈናቃዮች ጉዳይ ላይ መጠመዱ የልማት ፕሮጀክቶቹ ቁጥጥር እንዲላላ ማድረጉንም አንስተዋል።

በሰላም ማስፈን ተግባር ላይ የክልሉ መንግስት ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ጋር ሰላም ለማውረድ በትእግስት ያከናወነውን ተግባር እንደ ድል መቁጠር ይገባል ሲሉም ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል።

አስከ ነገ የሚቆየው ጉባኤው በአስፈጻሚ አካላት የተከናወኑ ስራዎችን ይገመገማሉ፣ አዋጆችን ይጸድቃል፤ ልዩ ልዩ ሹመቶችን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ህዝቡ አንዱ በሌላው ላይ #እንዲነሳ ለማድረግ እየተፈፀሙ ያሉ #ሴራዎችን መታገል አለበት" – የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት #ለማ_መገርሳ

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አድዋ ላይ #የወደቅነው፤ ሶማሊያን ስንዋጋ #ደማችንን ያፈሰስነው ተከፍሎን አይደለም፤ ቅጥረኞች ሆነን አይደለም። የሞትነው ለአገራችን ነው፤ የሞትነው ለኢትዮጵያ ነው።" ኦቦ #ለማ_መገርሳ (የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሚኒሶታ🔝

ኢትዮጵያ በአሜሪካ ጆርጂያ ካለው ቆንስላ ጽ/ቤቷ በተጨማሪ 2ኛ ቆንስላ ጽህፈት ቤቷን በሚኒሶታ መክፈቷን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል፡፡

ቆንስላ ጽ/ቤቱ የተከፈተው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አምና ነሃሴ ወር ላይ በአሜሪካ ባደረጉት ጉብኝት በገቡት ቃል መሰረት ነው።

በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ #ለማ_መገርሳ እንዳሉት የቆንስላ ጽ/ቤቱ መከፈት ለአካባቢው ብሎም በመላው አሜሪካ የሚኖረውን ዳያስፖራ ለማገልግል የጎላ ፋይዳ ይኖረዋል።

ዳያስፖራው በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው የኢኮኖሚና ፖለቲካ ለውጥ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ የተናገሩት አቶ ለማ፤ ለዚህም መንግስት ከምን ጊዜውም በላይ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

አዲስ የተከፈተው ቆንስላ ጽ/ቤት ቆንሱል ጄኔራል አምባሳደር እውነቱ ብላታ በበኩላቸው የጽ/ቤቱ መከፈት በሚኒሶታ ለሚኖሩ በሺዎች ለሚቆጠሩ የዳያስፖራ አባላት ምቹ ሁኔታና መነቃቃትን እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

የሴይንት ፖል ከተማ ከንቲባ ማልቪን ካርተር በዚሁ ወቅት ሲናገሩ ከቆንስላ ጽ/ቤቱ ጋር ተቀራርቦ ለመስራትና አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። ማርች 2 ቀን በከተማ ደረጃ “የኢትዮጵያ ቀን” ተብሎ እንዲከበርም መወሰኑን ጠቁመዋል።

በመርዓ-ግብሩ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖን ጨምሮ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከቤተ መንግስት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም በርካታ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ አባላት ተገኝተዋል።

ምንጭ፦ የወጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቱ🔝

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ ከኦሮሚያ ክልል ዋና አስተዳዳሪ አቶ #ለማ_መገርሳ ጋር በመሆን ከኢሉባቡር ዞን ነዋሪዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቱ🔝

በኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ እና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት አቶ #ለማ_መገርሳ የተመራውና መቱ ከተማን በመጎብኘት ላይ የሚገኘው ልኡክ በከተማው ወደ 66 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ በ3ሺህ 2 መቶ ሔክታር መሬት ላይ ለሚገነባው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ማዕከል መቱ ቅርንጫፍ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጧል። ልዑኩ በማረሚያ ቤት የተገነባውን የመዝናኛ ማዕከልን በመጎብኘት የመቱ ዩንቨርስቲ መንገድ ፕሮጀክት የመረቀ ሲሆን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋርም ተወያይቷል።

Via waltainfo.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አብይና አቶ ለማ🚁በደሌ🔝

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድና የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ #ለማ_መገርሳ ቡኖ በደሌ ዞን በደሌ ከተማ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ዛሬ ማለዳ ላይ ነው በደሌ ከተማ የገቡት።

በበደሌ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታም ከቡኖ በደሌ ዞን ከተውጣጡ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩ ይሆናል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮምያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ለማ_መገርሳ ለመከላከያ ሚንስትርነት በእጩነት ቀረቡ። #ebc

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ #ተሿሚ ሚኒስትሮች ቃለ መሃላ ፈጽመዋል!

--- አቶ #ለማ_መገርሳ - ሀገር መከላከያ ሚኒስትር
--- አቶ #ገዱ_አንዳርጋቸው - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
--- ኢንጂነር #አይሻ_መሀመድ - የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር

@tsegabwolde @tikvahethiopia