TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና‼️

በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን #ቡራዩ_ከተማ አስተዳደር መልካ ገፈርሳ ቀበሌ ዛሬ በአንድ መዋዕለ ሕጻናት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኝ መጸዳጃ ቤት ተደርምሶ የ4 ሕጻናት ሕይወት አልፏል።

በአደጋው ስምንት ሕጻናት ወደ መጸዳጃ ቤቱ #ጉድጓድ ገብተው እንደነበር የዘገበው ኤፍ ቢ ሲ ከእነዚህ ውስጥም የአራቱ ሕይወት #ወዲያውኑ ማለፉን አመልክቷል።

ቀሪዎቹ አራት ሕጻናት ደግሞ በአደጋው ጉዳት ደርሶባቸው በቤተልና አለርት ሆስፒታሎች የሕክምና #ዕርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የከተማዋ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ በየኑ ረዳ ተናግረዋል።

በአደጋው ሕይወታቸው ላለፉት ሕጻናት ጥልቅ ሐዘን የተሰማቸው መሆኑን በከተማ አስተዳድሩ ስም የገለጹት ወይዘሮ #በየኑ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል። ትምህርት ቤቶች በግቢያቸው ውስጥ የሚገኙ መጸዳጃ ቤቶች ለተማሪዎች ደኅንነት ምቹ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተገቢ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የቡራዩ ከተማ ፖሊስ ምክትል ሳጅን #ሲሳይ_ዓለሙ በበኩላቸው መጸዳጃ ቤቱ የተደረመሰው በነበረበት የጥራት ችግር መሆኑን ተናግረዋል። ጉዳዩን አስመልክቶ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘትም ፖሊስ ምርመራ መጀመሩን ጠቁመዋል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ወ/ሮ ጁዋሪያ መሀመድ ከአንድ የፀጥታ ሀይል አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው አልፏል " - ብልፅግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባል እና የብልፅግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ጁዋሪያ መሀመድ ኢብራሂም በ" ጅግጅጋ ኤርፖርት " ውስጥ ከአንድ የፀጥታ ሀይል አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው ማለፉን ብልፅግና ፓርቲ አሳውቋል። " ጉዳዩ #በህግ_አግባብ ተይዞ እየተጣራ…
#Update

" በአሁኑ ሰዓት ክልሉ በተለይ የጅግጅጋ ከተማ ፍፁም ሰላማዊ ሁኔታ ላይ ትገኛለች " - የሶማሌ ክልል መንግስት

የሶማሌ ክልል መንግስት ጅግጅጋ " ገራድ ዊልዋል ኤርፖርት " የተከሰተውን ድርጊትን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

በዛሬው እለት ከቀኑ 9:00 ላይ በጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አየር ማረፊያ በጥበቃ ላይ የነበረ " የፌደራል ፖሊስ " አባል በከፈተው ተኩስ የ1 ሰው ህይወት ማለፉንና በ4 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ መንግስት አሳውቋል።

" አባሉ በከፈተው ተኩስ የክልሉ ም/ቤት አባልና የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት ወ/ት ጁዌሪያ መሀመድ ኢብራሂም #ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ በተኩሱ የቆሰሉ ሌሎች 4 ዜጎች በህክምና ተቋማት እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል " ሲል ክልሉ አመልክቷል።

ድርጊቱን የፈፀመው ተጠርጣሪ #በክልሉ የፀጥታ ሀይሎች ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ከድረጊቱ በኋላ በኤርፖርት የተፈጠረውን ክስተት ወዳያኑ በቁጥጥር ስር በመዋሉ ኤርፖርቱ ወደ መደበኛው ስራ ተመልሷል ሲል ክልሉ በመግለጫው አሳውቋል።

በአሁኑ ሰዓት ክልሉ በተለይ #የጅግጅጋ ከተማ ፍፁም ሰላማዊ ሁኔታ ላይ እንደምትግኘ የገለፀው የሶማሌ ክልል መንግስት " ጉዳዩ ተመርምሮ ወደፊት ለህዝብ ይፋ ያደርጋል " ብሏል።

@tikvahethiopia
ተጠንቅቃችሁ አሽከርክሩ ⚠️

በዚህ ሳምንት ፤ በሲዳማ ክልል በበንሳ ወረዳ ፤ በንሳ ዋሬ ቀበሌ ልዩ ቦታው " ሬዎ " በሚባል ቦታ በሁለት #ሞተር_ሳይክሎች ግጭት በተከሰተ የሞተር አደጋ የ3 ሰው ህይወት #ወዲያውኑ ሲያልፍ አንድ ሰው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

ከመጠን በላይ ፍጥነትና ከአቅም በላይ መጫን የፈጠረዉ አደጋ መሆኑ የተነገረለት ይህ አሰቃቂ አደጋ ለማህበረሰቡ ታላቅ ድንጋጤ የፈጠረና በአንድ ሞተር ላይ ከሁለት በላይ ሰዉ መጫን ለከፋ አደጋ እንደሚያጋልጥ ያሳየ ነዉ ተብሏል።

በጉዳዩ ላይ ለቲክቫህ ኢትዮጽያ አስተያየታቸውን የሰጡት የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ከበደ ኬኔራ ፤ አደጋዉ በሁለት ሞተር ሳይክሎች ግጭት የተፈጠረ መሆኑን ገልጸዉ የሶስቱ ሰዎች ህይወት ወዲያዉኑ ሲያልፍ አንደኛዉ የከፋ አደጋ ደርሶበት ሆስፒታል እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ኮማንደሩ ፤ አሁን ላይ የትራፊክ ህግን ሳያከብሩ ማሽከርከር በተለይም በሞተረኞች ላይ የሚታይ ችግር መሆኑን ገልጸዉ ይኸውም ህይወት እየቀጠፈ በመሆኑ የሚመለከታቸዉ አካላት ሁሉ ለትራፊክ አደጋ መቀነስ የሚችሉትን እንዲያደርጉና አሽከርካሪዎችም በተፈቀደዉ ፍጥነት ልክ እንዲያሽከረክሩ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia