TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Humanity❤️

ይህ የሆነው በአሜሪካ ሀገር ሚኒሶታ ነው።

በሚኒሶታ በሚገኝ #ፈጣን_መንገድ ላይ አንድ አሽከርካሪ መንገድ ስቶ ወጥቶ ከመብራት ፖል ጋር ተጋጭቶ እዛው መኪና ውስጥ እያለ መኪናው በከፍተኛ እሳት መያያዝና መንደድ ይጀምራል።

በመንገዱ ሲጓዙ የነበሩ አሽከርካሪዎች ይህን አይተው አላለፉም።

መኪናቸውን አቁመው ከሚነደው መኪና ውስጥ አሽከርካሪውን ለማውጣትና ለማዳን ርብርብ ጀመሩ።

ከእሳት ነበልባል ጋር #እየታገሉ ፤ በሹፌሩ በር በኩል ያለውን መስታወት ሰብረው ከብዙ እልህ አስጨራሽ ትግል በኃላ አሽከርካሪውን በእሳት ተያይዞ ከሚነደው መኪና ውስጥ በህይወት አወጡት።

በኃላም ወደ ሆስፒታል እንዲወሰድ አደረጉ።

አሽከርካሪው ላይ ምንም አይነት የከፋ ጉዳት አልደረሰበትም ተብሏል።

ከከፍተኛ እሳት ጋር ተጋፍጠው የሰው ህይወት ለማትረፍ ርብርብ ሲያደርጉ ከነበሩት አንዱ ከድር ቶላ ይባላል። (ጥቁር ጁንስ ሱሪ በነጭ ጫማ ያደረገው)

ወደ ስራ እየሄደ በነበረበት ሰዓት ነው ይህ ክስተት ያጋጠመው።

ከድር የነፍስ አድን ስራውን ፥ " በህይወቴ እጅግ በጣም አስፈሪው ቅጽበት ነበር። ይህንን መቼም ቢሆን አልረሳውም ሁሌም ቢሆን አስታውሰዋለሁ " ሲል አስረድቷል።

አሽከርካሪው በህይወት እንዲተርፍ ቦታው ላይ የነበሩ ሁሉም ሰዎች ላደረጉት ፍጹም #ሰብዓዊ ተግባርና ርብርብ ፈጣሪን አመስግኗል።

የነበረውን የህይወት አድን ርብርብ የሚያሳይ ቪድዮ ከድር ቶላ መኪና ላይ በነበረ የዳሽቦርድ ካሜራ የተቀረጸ ነው።

Video Credit : Kadir Tolla / ከድር ቶላ

#TikvahFamily

@tikvahethiopia