TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሁሉንም በአንድ ላይ ማከናውን የሚችል ስማርት ስልክ እየፈለጉ ከሆነ፣ ‘ቴክኖ ፋንተም ቪ ፍሊፕ 5ጂ’ ለእርሶ ነው!

የ5ኛው ትውልድ ወይም 5ጂ ዓለም የደረሰበት የመጨረሻው ፈጣን የሞባይል ኔትዎርክ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም፣ እንከን የለሽ አገልግሎት እንዲስጥ ታስቦ በኦክታ ኮር ሲፒዩ(Octa Core CPU) በመታጀብ በፍጥነቱ የተመሰከረለት ሚዲያቴክ ዲምነሲቲ 8050 (Mediatek Dimensity 8050) ፕሮሰሰር የተገጠመለት፣ ማንኛውንም አይነት መተግበሪያ በፍጥነት እና ያለእንከን እንዲሰራ የሚያረገው 256 ጂቢ ሜሞሪ ከ(8+8) virtual RAM ያካተተ እንዲሁም እነዚህን ሁሉ ደግፎ ለረጅም ጊዜ ያለ ማቋረጥ አገልግሎት ማስጠቀም የሚያስችል 45ዋት የፍጥነት ቻርጅ በመጠቀም 45 ደቂቃ ብቻ ሙሉ ቻርጅ የማድርግ አቅም ያለው ባለ4000 ሚሊአሚፒር ባትሪ ያካተተ ነው ።

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#PhantomVFlip#TecnoMobile #TecnoEthiopia
🔹 " እስከ 90 በመቶ የሚሆነው ሙስና የሚፈጸመው #በኮንስትራክሽን ዘርፍ ነው " የመ/ግ/ን/ባ

በመንግሥት የግዥ ሒደት እስከ 90 በመቶ የሚሆነው ሙስና የሚፈጸመው በኮንስትራክሽን ዘርፍ መሆኑን፣ የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

ባለሥልጣኑ ይህን ያስታወቀው ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም. በዘንድሮ በጀት ዓመት በ169 የፌዴራል ተቋማት የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሲስተም ተግባራዊ ተደርጎና አፈጻጸሙን ለማሳደግ፣ ከንግድ ማኅበረሰቡ ጋር በተደረገ ውይይት ላይ ነው፡፡

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሐጂ ኢብሳ ምን አሉ ?

- በመንግሥት በግዥ ሥርዓት ውስጥ፣ ከ80 እስከ ከ90 በመቶ በላይ ሙስና የሚፈጸመው በኮንስትራክሽን ዘርፍ ነው ብለዋል።

- ስሙን መጥቀስ ያልፈለጉት የመንግሥት ተቋም #በጨረታ አንደኛ የወጣ ድርጅት እያለ ሦስተኛ ከወጣው ጋር ውል መግባቱን፣ በዚህም ምክንያት ባለሥልጣኑ እስከ ፍርድ ቤት በመሄድ ሒደቱ እንዲቋረጥ ማደረጉን ገልጸዋል፡፡

- ከኮንስትራክሽን ጋር ተያይዞ ጨረታ የሚያወጡ የመንግሥት ተቋማት #የሚፈልጉዋቸው ተጫራቾች ካልመጡ እስከ #መሰረዝ እንደሚደርሱ አመልክተዋል።

- የመንግሥት ተቋማት ተጫራቾችን ሆን ብለው ከጨረታ ውጪ እንዲሆኑ ሕጎችን እንደ ምክንያት እንደሚጠቀሙ፣ ያሸነፉ ተጫራቾችንም #እንዲሰላቹ በማድረግ ከጨረታ ውጪ እንዲሆኑ እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል፡፡

- በመንግሥት የግዥ ሥርዓት ምክንያት የሚመጡ ክሶች መኖራቸውን ገልጸው በዓመት እስከ 150 የሚደርሱ ክሶች እንደሚስተናግዱ ተናግረዋል። በአብዛኛው ጨረታ የማውጣትና የሚገመገምበት መሥፈርት በመለያየቱ ምክንያት በርካታ ተጫራቾች ክስ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የኢጋድ አባል አገሮችና የነጋዴ ሴቶች ማኅበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ እንግዳዬ እሸቴ ምን አሉ ?

- በኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ከታዩ ክፍተቶች አንዱ በጠቅላላ የመንግሥት ግዥ መባሉ ትክክል እንዳልሆነ ተናግረዋል።

- የመንግሥት ግዥ ተብሎ ስያሜ ቢሰጠውም የመንግሥት ተቋማትና የንግዱ ማኅበረሰብ የሚገናኙ በመሆናቸው ከስያሜ ጀምሮ ማስተካከያ ይፈልጋል ብለዋል።

- የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ሙስናን ለመቅረፍ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጻዋል። ከዚህ ቀደም #በዩኒቨርሲቲዎች በሚደረጉ ግዥዎች ጥራታቸውን ያልጠበቁ ምርቶች እየቀረቡ እንደነበርና ሥርዓቱ መዘመኑ በተወሰነ መንገድ ችግሩን መቀረፉን አስረድተዋል፡፡

- በኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ለሚታዩ የሙስና ብልሹ አሠራርን ከሥሩ ማድረቅ እንደሚገባ፣ በተለይ ተጫራጮች ወደ ተቋማት ሲሄዱ #ሲስተም_የለም የሚለው ቋንቋ የችግሩ መጀመርያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

- ተጫራቾች ወይም የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ለሙስና እንዳይጋለጡ መብቶቻቸውን ለማስጠበቅ ሞጋችና ተከራካሪ መሆን አለባቸው ብለዋል።

የመንግሥት ግዥ የንብረት ባለሥልጣን የመንግሥት ግዥ የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ ከበደ ምን አሉ ?

- የነባሩ የወረቀት የግዥ ሥርዓት የሙስና ተጋላጭነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት እየተደረገበት ነው ብለዋል።

- የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት መኖሩ የሚቀርፏቸው ችግሮች ሰፊ ከመሆናቸው ባሻገር፣ ለብዙ ተጫራቾች ዕድል ከመስጠት አኳያ ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

- የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት በ2015 ዓ.ም. ሲጀመር የተመዘገቡት የንግድ ማኅበረሰብ አባላት 100 ብቻ የነበሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በጥቅሉ ከ15‚000 በላይ ተሻግረዋል።

- ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ በጀቷ 70 በመቶ የሚውለው ለግዥ ሥርዓት መሆኑን ገልጸው ይህም በገንዘብ ሲቀየር 560 ቢሊዮን ብር ለግዥ እንደሚውል ተናግረዋል።

#ReporterNewspaper

@tikvahethiopia
" የቤት አከራዮች የተከራዮቻቸውን ማንነነት እና የሚሰሩትን ስራ በደንብ ማረጋገጥ አለባቸው " - ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ ሀሰተኛ የውጪ ሀገራትና የኢትዮጵያን ገንዘብ በማተም የተጠረጠሩ የውጪ ሀገር ዜጎች መያዙን አሳወቀ።

በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ እንዲመሰረት መደረጉንም ገልጿል።

ሀሰተኛ ገንዘብ በማዘጋጀት ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች የተያዙት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው " ቦሌ አዲስ ትምህርት ቤት " አካባቢ መሆኑን ፖሊስ አመልክቷል።

የውጪ ሀገር ዜግነት ያላቸው 3 ግለሰቦች #ሙሉ_ግቢ የመኖሪያ ቤት በመከራየት  ሀሰተኛ ብር እና የውጭ ሀገር  ገንዘቦችን በማተም  እንደሚያሰራጩ እና የከበሩ ማዕድናትን በህገ-ወጥ መንገድ እንደሚያዘዋውሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው ክትትልና ባሰባሰበው ማስረጃ ያረጋግጣል።

ህጋዊ አሰራሩን ተከትሎ በተደረገ ብርበራም ተጠርጣሪዎቹ ፦
- ሀሰተኛ ገንዘቦችን ለማዘጋጀት የሚገለገሉባቸውን መሳሪያዎች ፣
- ልዩ ልዩ ኬሚካሎችን  ፣
- በሀሰተኛ መንገድ የታተሙ ገንዘቦች ፣
- በገንዘብ ልክ ተቆራርጠው የተዘጋጁ ወረቀቶች
- የዘንዶ ቆዳዎችን በኤግዚቢትነት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ሀሰተኛ ገንዘብ ከማዘጋጀት በተጨማሪ የፀና የመኖሪያ ፍቃድ ሳይኖራቸው እየኖሩ ያሉና በህገ-ወጥ መንገድ የከበሩ ማእድናትን እንደሚዘዋውሩ በምርመራ ማረጋገጡን ገልጿል።

ፖሊስ የምርመራ መዝገብ በማደራጀትና በማጠናቀቅ ለሚመለከተው የፍትህ አካል በመላክ ክስ ተመስርቶባቸዋል ብሏል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ክ/ከተሞች ውስጥ በተመሳሳይ መንገድ ሀሰተኛ ገንዘቦችን ሲያትሙ የተገኙ ግለሰቦች እንደተያዙ አስታውሷል።

" መሰል የወንጀል ድርጊቶች በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ ናቸው " ያለው ፖሊስ መኖሪያ ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች ለወንጀሉ መስፋፋት ምቹ ሁኔታን እየፈጠሩ መሆናቸውን በመረዳት  የተከራዮቻችውን ማንነነት እና የሚሰሩትን ስራ የማረጋገጥ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
በቴክኖ ‘‘ፋንተም ቪ ፍሊፕ 5ጂ’ ካሜራ እያንዳንዱ ፎቶ ልዩ ነው !

ለአያያዝ እና አጠቃቀም ምቹ ከሚያደርገው ልዩ ዲዛይን በተጨማሪ 64-ሜጋ ፒክስል  (RGBW sensor) እና ባለ 13-ሜጋ ፒክስል እጅግ ሰፊ አንግል( ultra-wide-angle) የታገዘ ካሜራ በ120 ዲግሪ ሰፊ የእይታ ሽፋን ያለው  ዋና ካሜራዎች እንዲሁም ባለ 32 ሜጋ ፒክስል የፊትለፊት ካሜራ ከሁለት ኤል ኢዲ ፍላሽ መብራት የተገጠመለት ቴክኖ ‘ፋንተም ቪ ፍሊፕ 5ጂ’ የሚያስደንቁ ፎቶዎችን ከየትኛውም ርቅት በጥራት እና ቀለማትን ቁልጭ አድርጎ ማንሳት የሚያስችለው አቅሙ ተመራጭ ያደርገዋል። 

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#PhantomVFlip#TecnoMobile #TecnoEthiopia
#Kenya

የጎረቤት ኬንያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ብሔራዊ መታወቂያ ካርድ ለማውጣት ዜጎች ክፍያ እንዲፈጽሙ መንግሥት ያወጣውን መመሪያ #አገደ

የኬንያ መንግሥት ይህን መመሪያ ማውጣቱን ተከትሎ ዜጎች ቅሬታቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ማጋሬ ጊኬንይ የተባሉ ሐኪም ናቸው መንግሥት አዲሱን መመሪያ ያወጣው “ድንገተኛ እና ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ” ነው ሲሉ የሕዝብ ድምፅ በማሰባሰብ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የወሰዱት።

የተሰበሰበው የሕዝብ ድምፅ እንደሚለው በአዲሱ መመሪያ መሠረት፤ በርካታ ዜጎች መታወቂያ ካርድ በቀላሉ ማግኘት አይችሉም።

ከዚህ ቀደም በነፃ ይሰጥ የነበረው ብሔራዊ መታወቂያ ካርድ አሁን 1 ሺህ ሺልንግ [370 ብር ገደማ] እንዲሆን መንግሥት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አዟል።

መታወቂያ ለማሳደስ ደግሞ ኬንያዊያን 2 ሺህ ሺልንግ እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል።

ኬንያዊያን እያሻቀበ ባለው የኑሮ ግሽበት ምሬታቸውን እየገለጡ ባሉበት ወቅት ነው መንግሥት ገቢውን ለማሳደግ ሲል ዜጎች ከዚህ ቀደም በነፃ አሊያም በርካሽ የሚያገኟቸውን አገልግሎቶች በበለጠ ክፍያ እንዲሆን ያደረገው።

በርካታ ኬንያዊያን በሚከፍሉት ግብር አማካይነት ተግባራዊ እየሆኑ ላሉ የመንግሥት ግልጋሎቶች ተጨማሪ ክፍያ መጠየቃችን ተገቢ አይደለም እያሉ ናቸው።

አዲሱ መመሪያ መታወቂያ ካርድ ብቻ ሳይሆን ፓስፖርት፣ የጋብቻ ወረቀት፣ የሥራ እና የመኖሪያ ፈቃድ እንዲሁም የልደት እና ሞት ምስክር ወረቀት ለማውጣትም ክፍያ ይጠይቃል።

አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት አሊያም ለማሳደስ ይጠየቅ የነበረው ክፍያ 50 በመቶ ሲያድግ የልደት እና ሞት ወረቀት ለማውጣት የሚጠየቅ ክፍያ በአራት እጥፍ አድጎ 200 ሺልንግ ገብቷል።

መንግሥት በተጨማሪ ዜግነት አሊያም የመኖሪያ ፈቃድ ለማስጠት የሚጠይቀውን ክፍያ እጥፍ አድርጎታል።

ከኬንያዊያን ዜጎች በውጭ ሃገር የተወለዱ ልጆች የኬንያ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት የሚጠየቁት ክፍያ 1 ሚሊዮን ሺልንግ ሆኗል።

በደንገት የተጫኑት የክፍያ መመሪያዎች አቅም የሌላቸው ዜጎች የመንግሥትን ግልጋሎት ተጠቅመው አስፈላጊ ወረቀት ለማግኘት ሊቸገሩ ይችላሉ የሚል ስጋት ጭሯል።

ባለፈው ዓመት መስከረም ወደ ሥልጣን የመጡት የፕሬዝደንት ሩቶ መንግሥት በርካታ የግብር ዓይነቶችን ዜጎች ላይ የጣለ ሲሆን የነዳጅ ዋጋ ከፍ እንዲልም አድርጓል።

የብሔራዊ ፓርክ መግቢያ ዋጋን ጨምሮ በርካታ የመንግሥት አገልግሎቶች ክፍያ ከፍ እንዲልም ሆኗል።

ባለፈው ሳምንት የገቢዎች መ/ቤት ባለሥልጣናት ወደ ኬንያ የሚመጡ ዜጎችም ሆኑ ጎብኝዎች ከ500 ዶላር በላይ ተመን ያለው ዕቃ ይዘው ከተገኙ ይቀረጣሉ ብሏል።

ፕሬዝደንት ሩቶ እስካሁን ስለ ዋጋው ጭማሪ ያሉት ነገር ባይኖርም ሐሙስ ዕለት ለሃገሪቱ ዜጎች ባስተላለፉት መልዕክት ኬንያዊያንን ከዕዳ ጫና ለማላቀቅ " ቀላል ያልሆኑ ግን አስፈላጊ " ውሳኔዎችን ለመውሰድ ተገድጃለሁ ብለዋል።

#BBC

@tikvahethiopia
" የቢሮዉ ቁልፍ በመቀየሩና አካባቢዉ አስጊ በመሆኑ ስራ መስራት አልቻልንም " - የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ

" በተቀነባበረ ድራማ ቢሯችን ከነዶክመንቱ ተቀምተናል " ሲል የሲዳማ ፌደራሊስት ፖርቲ የክልሉን መንግስት ከሰሰ።

የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አት ገነነ ሀሳና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ባሰሙት ቅሬታ እንደገለጹት ከሆነ ፤ ከወራት በፊት በዲስፕሊን ግድፈት ከፓርቲዉ የታገዱት አቶ ጴጥሮስ ዱቢሶ በክልሉ ፖሊስ ድጋፍ ወደቢሮዉ በመግባት የቢሮዉን ቁልፍ ቀይረውና ፋይሎቹን ይዘው መውጣታቸውን ገልጸዋል።

አቶ ገነነ አክለዉም በወቅቱ ቢሮ ዉስጥ የነበረዉ የፓርቲዉ አባል አቶ ሳሙኤል ላንቃሞ በአቶ ጴጥሮስ መደብደባቸውን እንዲሁም ለእስር መዳረጋቸውን አመልክተዋል።

አሁን ላይ ፓርቲውን እየመሩ ያሉትን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ደሳለኝ ደምሴን ጨምሮ ሁሉም የፓርቲው አመራሮች የቢሮዉ ቁልፍ በመቀየሩና አካባቢዉ አስጊ በመሆኑ ስራ መስራት አልቻሉም ሲሉ ቅሬታቸዉን ገልጸዋል።

በቅርቡ በክልሉ መንግስት ጫና እየደረሰብኝ በሚል ምክኒያት የፓርቲዉ ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ተሰማ ኤልያስ ከሀገር መዉጣታቸዉ ይታወቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የፓርቲውን ቅሬታ በተመለከተ የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮን እንዲሁም የሀዋሳ ከተማ ፖሊስን ለማነጋገር ጥረት ቢያደርግም ስልክ ባለመነሳቱ ሊሳካ አልቻለም።

ክልሉ በየትኛውም ሰዓት ለፓርቲው ወቀሳ ምላሽ የሚሰጥ ከሆነ ተከታትለን እናቀርባለን።

መረጃው የሀዋሳው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Oromia ምንም እንኳን እስካሁን ድረስ በመንግሥትም ሆነ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ኦነግ ሸኔ እያለ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን) በኩል ይፋዊ መግለጫ ሆነ ማብራሪያ ባይሰጥም በታንዛኒያ፣ ዳሬሰላም ውስጥ ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር መጀመሩን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገልጸዋል። ዲፕሎማቲክ ምንጮች እንደገለፁት ድርድሩ እየተመራ ያለው በጦር አዛዦች ነው። የመንግሥት የተደራዳሪ ቡድን የሚመራው በሀገር…
#Update

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

መግለጫውን የሰጡት የክልሉ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው አቶ ኃይሉ አዱኛ ሲሆኑ ታንዛኒያ ውስጥ እየተካሄደ ነው ስለተባለው የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድር ተጠይቀው ቀጥተኛ ምላሽ ሳይሰጡ አልፈዋል።

አቶ ኃይሉ ፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አሁንም በክልሉ ዘላቂ ለሰላም እና ደህንነት እንዲሰፍን ፅኑ አቋም እንዳለው አሳውቋል።

ያሉ ማንኛውም ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉት በድርድር እና በንግግር ብቻ ነው ያሉት ኃላፊው የክልሉ መንግሥት ልክ እኛ ቁርጠኛ እንደሆነው ሌላውም ወገን ተመሳሳይ አቋም መያዝ አለበት ብለዋል።

ለሰላም የተዘረጋው ክንዳችን ዛሬም አልታጠፈም ሲሉ አሳውቀዋል።

አቶ ኃይሉ በታይንዛኒያ ፣ ዳሬ ሰላም መካሄድ ጀምሯል ስለተባለው ሁለተኛ ዙር የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራው) እና የመንግሥት የሰላም ድርድር በቀጥታ አስተያየት እና ማብራሪያ ሳይሰጡ አልፈውታል።

እንደ ዲፕሎማቲክ ምንጮች መረጃ ከሆነ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በታንዛኒያ፣ ዳሬሰላም ውስጥ ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር እያካሄዱ ነው።

የሰላም ድርድሩ እየተመራ ያለውም በጦር አዛዦች ነው።

የመንግሥት የተደራዳሪ ቡድን የሚመራው በሀገር መከላከያ ሰራዊት የምዕራብ ዕዝ አዛዥ በነበሩት ጄነራል ጌታቸው ጉዲና ሲሆን በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በኩል ደግሞ በኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) ነው።

ጃል መሮ ከወለጋ ጫካ በኢጋድ፣ በአሜሪካ፣ በኖርዌይ መንግሥታት አስተባባሪነት በአውሮፕላን ወደ #ኬንያ ከዛም ታንዛኒያ የገቡ ሲሆን የታጣቂ ቡድኑ የደቡብ ኦሮሚያ አዛዥ ገመቹ ረጋሳ (ጃል ገመቹ አቦዬ) ከነበሩበት ቦረና አካባቢ በኬንያ አድርገው ወደ ዳሬሰላም እንዲገቡ ተደርገው የሰላም ድርድሩን እያካሄዱ ነው።

እንደ ዲፕሎማቲክ ምንጮች ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር እንዲሳካ ኢጋድ፣ አማሪካ፣ ኖርዌይ፣ ኬንያ ድጋፍ እና የማመቻቸት ስራን እየሰሩ ናቸው።

የፌዴራል መንግሥትም ይሁን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት / መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራው / እስካሁን በይፋ ያሉት ነገር የለም።

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የጎረቤት ሀገራት እንዲሁም የሌሎችም በርካታ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ ይገኛሉ።

መሪዎቹ ሳዑዲ ዓረቢያ ያቀኑት በመጀመሪያው የ " ሳዑዲ-አፍሪካ ጉባዔ " ለመሳተፍ ነው።

በሳዑዲ አረቢያ እየተካሄደ በሚገኘው ጉባኤ ላይ እየተካፈሉ ከሚገኙት መሪዎች መካከል፦
🇪🇹 የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ
🇪🇷 የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ
🇩🇯 የጂቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌህ
🇸🇴 የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼህ ሞሃመድ
🇸🇸 የደቡብ ሱዳን ፕሬዜዳንት ሳልቫኪየር ማያርዲት
🇰🇪 የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶክተር ዊሊያም ሩቶ ይጠቀሳሉ።

በሌላ በኩል ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከሳዑዲ - አፍሪካ ጉባኤ ጎን ከጂቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌህ እና ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼህ ሞሃመድ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንዳደረጉ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia