TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" የሃሳብ ልዩነቱ ወደ ግጭት አያመራም " - አቶ ጌታቸው ረዳ ዓመታዊው የ2016 ዓ/ም የአሸንዳ በዓል ዛሬ ነሃሴ 16/2016 ዓ/ም በመላ ትግራይ መከበር ጀምሯል። በዓሉ እስከ ነሃሴ 24/2016 ዓ.ም አንደሚቀጥል የወጣው መርሃ ግብር ያመለክታል። በሌላ በኩል ፕሬዜዳንት ጌታቸው በ2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር የተገነባ የ10.2 ኪሎ ሜትር  የአስፋልት መንገድ ሲመርቁ ፤ የአሸንዳ አደባባይ ግንባታ መሰረተ…
#ኣሸንዳ

ከሰሞኑን በፖለቲካ ትኩሳት ውስጥ የከረመችው ትግራይ በደማቅ ሁኔታ የዘንድሮውን የኣሸንዳ በዓል እያከበረች ነው።

በዓሉን ለማክበር በርካታ እንግዶች ትግራይ ይገኛሉ።

በዓሉ እስከ ነሃሴ 24 ቀን 2016 ዓ/ም በተለያዩ ስነስርዓቶች እየተከበረ ይቀጥላል።

በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የሚከበረው የኣሸንዳ በዓል ፍቅር፣ ይቅር ባይነትና መልካም ተግባቦት በተግባር የሚንጸባረቅበት በዓል ሲሆን በዓሉ በልጃገረዶች ይበልጥ ትኩረት ተሰጥቶት ይከበረል።

ልጃገረዶች አደባባይ ወጥተው ይህን በዓልን በድምቀት ያከብራሉ።

የበዓሉ ይዘት በዋናነት ህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ መልካም ተግባቦቶች፣ ፍቅርንና ይቅር ባይነት ላይ ያነጣጠረ ነው።

የሌሎች ሃሳቦች፣ ጭፈራዎች እና ትእይንቶች እንዲታዩ የሚጋብዝ በዓል ከመሆኑም ባለፈ የሃይማኖትና የብሔር ልዩነት አይንፀባረቅበትም።

ፎቶ፦ ትግራይ ቲቪ (ኖርዘርን ስታር ሆቴል፣ መቐለ ነሐሴ 17)

#Ashenda #Tigray

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF #Tigray የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለመምራት ህወሓት " የራሱን ሰዎች መመደብ ይችላል " ሲሉ የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ። አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ቡድን " አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም ” ብለዋል። ሊቀመንበሩ ፤ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት ትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር " ህወሓትን ወክሎ ነው የገባው። አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም…
#Tigray

የትግራይ ጊዜያዊ አስተደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የስልጣን ሽምሹር አደረጉ።

ፕሬዜዳንቱ በህወሓት የፓሊት ቢሮ አባልዋ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ምትክ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ክርስቶስ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ በማድረግ ሾመዋል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ ተፈርሞ ነሃሴ 14/2016 ዓ.ም የወጣው ደብዳቤ ፤ ፀጋይ ገብረተኽለ የዞኑ አስተዳዳሪ በመሆን የሚገባቸው ጥቅም ተጠብቆላቸው ሃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጡ አደራ በማለት ያሳስባል።

አዲሱ ተሿሚ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ኽርስቶስ ቀደም ሲል በዞኑ የእንደርታ ወረዳ አስተዳዳሪ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል። 

ወ/ሮ ሊያ ከቀናት በፊት የህወሓት ስራ አስፈጻሚ በመሆን መመረጣቸው ይታወሳል።

ህወሓት ባካሄደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ያልሰጠው ፤ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር የሚገኙባቸው 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን " ህጋዊ አይደለም " ያሉት ጉባኤ ካልተሳተፉት መካከል  ፦
- የምዕራባዊ
- የማእከላዊ
- የምስራቃዊ
- የደቡበዊ ዞኖች አስተዳዳሪዎች ይገኙበታል። 

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው የስልጣን ሹምሽር ያደረጉበት የደቡባዊ ምስራቅ ዞን ኣስተዳዳሪ ፀጋይ ገ/ተኽለ ህወሓት ባካሄደው ጉባኤ የፓሊት ቢሮ አባል ሆነው የተሸሙት ወ/ሮ ሊያ ካሳ የተኩት አምስተኛ የእነ ዶ/ር ደብረፂዮን አካሄድ የሚቃወሙ የዞን አስተዳዳሪ ናቸው።

በትግራይ ካሉ 7 የዞን አስተዳደሮች አምስቱ የእነ ዶ/ር ደብረፂዮን አካሄድ በሚቃወሙ የሚመሩ ሲሆኑ ሁለት ዞኖች ማለትም የሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በተካሄደው ጉባኤ የፓሊት ቢሮ አባል ሆነው በተመረጡት  ተኽላይ ገ/መድህን የመቐለ ከተማ ደግሞ በተካሄደው ጉባኤ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ሆኖው በተመረጡት ይትባረክ ኣማሃና ኤልያስ ካሕሳይ ዋናና ምክትል በመሆን በመመራት ላይ ይገኛሉ።

ቀሪዎቹ የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን አካሄድ የሚደግፉ የሁለት ዞን አስተዳዳሪዎች በያዙት ሃላፊነት የቆዩ ይሆን ? የብዙዎች ጥያቄ ነው። 

የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከቀናት በፊት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን ለመምራት ህወሓት " የራሱን ሰዎች መመደብ ይችላል " ሲሉ ተናግረው ነበር።

ሊቀመንበሩ ፤ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር " ህወሓትን ወክሎ ነው የገባው። አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም " ነበር ያሉት።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ጊዜያዊ አስተደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የስልጣን ሽምሹር አደረጉ። ፕሬዜዳንቱ በህወሓት የፓሊት ቢሮ አባልዋ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ምትክ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ክርስቶስ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ በማድረግ ሾመዋል። በአቶ ጌታቸው ረዳ ተፈርሞ ነሃሴ 14/2016 ዓ.ም የወጣው ደብዳቤ ፤ ፀጋይ ገብረተኽለ የዞኑ አስተዳዳሪ በመሆን የሚገባቸው ጥቅም ተጠብቆላቸው ሃላፊነቱን በአግባቡ…
#TPLF #Tigray

በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ማንኛውም አይነት የስልጣን ሹምሽር አልቀበልም አለ።

በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " በማንኛው የሃላፊነት እርከን በራስ ፍላጎት የሚደረግ የስራ ምደባና ሹምሽር ተቀባይነት የለውም " ብሏል።

የእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ለሁሉም የዞንና የወረዳ የድርጅቱ ፅህፈት ጠቅሶ ባሰራጨው ደብዳቤ ፥ " ከሰርዓታዊና ተቋማዊ አሰራር ውጪ የሚካሄዱ የስራ ምደባዎች ኢህጋዊ ብቻ ሳይሆኑ ተጠያቂነትን ያስከትላሉ " ሲል አስጠንቅቋል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ነሃሴ 17/2016 ዓ.ም በህወሓት የፓሊት ቢሮ አባልዋ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ምትክ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ክርስቶስ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ በማድረግ መሾማቸው ዘግበናል።

ነሃሴ 18/2016 ዓ.ም የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ደግሞ በሰሜናዊ ምዕራብ ዋና አስተዳዳሪና በቅርቡ ህወሓት ባካሄደው ጉባኤ የፓሊት ቢሮ አባል ሆነው በተመረጡት ተክላይ ገ/መድህን ምትክ የክልሉ የስፓርት ኮሚሽን ኮምሽነር የነበሩት ተኽላይ ፍቓዱ ተሹመዋል።

ትግራይ ካሉዋት ሰባት የዞን አስተዳደሮች በአሁኑ ጊዜ ስድስቱ የእነ ዶ/ር ደብረፂዮን አካሄድ በሚቃወሙ የሚመሩ ሲሆኑ የመቐለ ከተማ ብቻ በቅርቡ  በተካሄደ ጉባኤ  የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ሆኖው በተመረጡት ይመራል። 

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
#Tigray : በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤቨን ማሲንጋ ዛሬ መቐለ ገብተዋል።

ማሲንጋ መቐለ ሲደርሱ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ እና ምክትል ፕሬዜዳንት ጄነራል ታደሰ ወረደ ተቀብለዋቸዋል።

በቆይታቸው በወቅታዊ የትግራይ ሁኔታ፣ በወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ፣ በተፈናቃዮች መመለስ ጉዳይ ላይ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር ይመክራሉ ተብሏል።

ፎቶ፦ ድምጺ ወያነ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

አሜሪካ በህወሓት እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መካከል ያለው ውጥረት እንዲረግብ ጠየቀች።

ትላንት ትግራይ ፣ መቐለ የገቡት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህም ወቅት በህወሓትና በጊዚያዊ አስተዳደሩ መካከል የተፈጠረው ውጥረት መርገብ እንዳለበት አሳስበዋል። 

አምባሳደሩ ውጥረቱ እንዲረግብ ከሰጡት ማሳሰብያ በተጨማሪ ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ በማድረግ ጉዳይ ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ተወያተዋል።

@tikvahethiopia
#Tigray

በትግራይ የክረምቱ ሃይለኛ ዝናብ ባስከተለው አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አልፋዋል።

በበርካታ የክልሉ አከባቢዎችም ከአሁን በፊት ታይቶ በማያውቅ መልኩ የመሬት መደርምስ አደጋ እየተከሰተ ነው።

ነሃሴ 17 እና 19/2016 ዓ.ም በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የሓውዜንና ብዘት ወረዳዎች የጣለ ሃይለኛ ዝናብና በጥልቅ ጉድጓድ በተጠራቀመ ውሃ የ7 እና 9 ዓመት እድሜ ህፃናት የሚገኙባቸው 4 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

የሓውዜን ወረዳ ነዋሪ የሆኑ ህፃናቱ በአከባቢያቸው በሚገኘው በጥልቅ ጉድጓድ በተጠራቀመ የዝናብ ውሃ ሊዋኙ ሲሉ ነው ለህልፈት የተዳረጉት። 

በዞኑ ብዘት ወረዳ ነዋሪ የሆኑ የአንድ ቤተሰብ አባላት በሃይለኛ ዝናብ ምክንያት ቤታቸው በላያቸው ላይ ፈርሶ የ5 ልጆች አሳዳሪ የሆኑ ባልና ሚስት ወድያውኑ ህይወታቸው አልፏል።

ልጆቻቸው እቤት ስላልነበሩ የሟቾች ቁጥር ሊቀንስ እንደቻለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከወረዳው ያጋኘው መረጃ ያሳያል።

ልጆቹ ወላጅ እናት አባታቸውን አጥተው በፈረሰ ቤት ሜዳ ላይ መውደቃቸው ተገልጿል።

ከአሁን በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በክልሉ የተለያዩ አከባቢዎች የመሬት መደርመስ አደጋ ተከስቷል።

በአላጀና ሰለዋ ወረዳዎች በሚገኙ አራት የቀበሌ ገበሬ ማህበራት ፣ በእንደርታና ሕንጣሎ ወረዳዋች ፣ በዓዴትና ፀለምቲ ወረዳዎች የመሬት መደርመስ አደጋ መከሰቱ ከአከባቢዎቹ የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF #Tigray በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ማንኛውም አይነት የስልጣን ሹምሽር አልቀበልም አለ። በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " በማንኛው የሃላፊነት እርከን በራስ ፍላጎት የሚደረግ የስራ ምደባና ሹምሽር ተቀባይነት የለውም " ብሏል። የእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ለሁሉም የዞንና የወረዳ የድርጅቱ ፅህፈት ጠቅሶ ባሰራጨው ደብዳቤ…
#Tigray

" በቅርቡ ሁሉም ተቀባይነት ያላቸው ህጎችና አሰራሮች በመጣስ ጉባኤ አድርጊያሎህ የሚለው ህገ-ወጥ ቡድን በትግራይ ስርአት አልበኝነት እንዲስፋፋ እየሰራ ነው " ሲል የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሷል።

አስተዳደሩ ፥ ህዝብ ለማገልገል የሚያካሂዳቸው የመዋቅራዊ አደረጃጀት ማስተካከያዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

የመንግስት ውሳኔና ተግባር የሚያደናቅፍ ማንኛውም አካል ሆነ ሃይል አልታገስም ብሏል።

" ህግና ስርዓት የሚጥስ አካል ሆነ ሃይል ህጋዊ አሰራር የተከተለ ተጠያቂነትና እርምጃ እንደሚወሰድበት ሊታወቅ ይገባል " ሲል አስጠንቅቋል።

በአሁኑ ወቅት ማንኛውም የስልጣን ጥያቄ አለኝ የሚል ቡድን በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ጠያቄውን ለሚመለከተው አደራዳሪ አካል   በሰላማዊ አግባብ የማቅረብ መብቱ ዝግ እንዳልሆነ ጠቁሟል።

" ጊዚያዊ አስተዳደሩ እንዲዳከም ሳያለሰልስ የሰራ ቡድን አሁን የሚደረጉት የስራ ምደባዎች ' ህጋዊ አይደሉም ' ብሎ በመቃወም ለዓመታት እስከ ታች በሰፋው ኔትወርክ እንቅፋት እየፈጠረ ይገኛል " ብሏል።

" ቡድኑ በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተመደቡ አመራሮች ህጋዊ አይደሉም ተቀባይነት የላቸውም ' ከማለት አልፎ ባደራጀው ኔትወርክ እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ በመውረድ ' እንዳትቀበሉዋቸው ' በማለት ህግ አልበኝነት እንዲነግስ በመንቀሳቀስ ላይ ነው " ሲል ከሷል።

" ህዝቡ ህገ-ወጥቶች ሃይ ሊላቸው ሊያስታግሳቸው ይገባል " ሲል አስገንዝቧክ።  

" ህዝቡ ተገቢውን  መንግስታዊ አገልግሎት እንዲያገኝ አልሞ የሚከናወነው የመዋቅር ማስተካከያ እርምጃ ተጠናክረው ይቀጥላሉ ፤ መንግስታዊ የመዋቅር ማስተካከያ እርምጃ በሚቃደናቅፍ አካል ሆነ ሃይል እርምጃ እንደሚወሰድ ህዝባችን ሊያውቀው ይገባል "  ሲል በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚመራስ ጊዜዊ አስተዳደር አሳውቋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia 
#Tigray

ዛሬ በአክሱም ከተማ የብዙዎች መነጋገሪየ የሆነ ፓለቲካዊ ክስተት ተከስቷል።

በመካከላቸው በተፈጠረው ፓለቲካዊ ልዩነት በርቀት በመግለጫዎች ሲጎነታተሉ የከረሙት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እና የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በዓመታዊው አክሱም ከተማ የዓይኒ ዋሪ በዓል አከባበር ላይ ተገናኝተዋል።

በመድረኩ በቅደም ተከተል ንግግር ያደረጉት ሁለቱ መሪዎች ከምር ይሁን ከአንገት በላይ በማይታወቅ የእጅ ሰላምታ ተጨባብጠዋል።

ከአክሱም ከተማ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከንግግራቸው በላይ አነጋገሪ የሆነው " በዓሉ ላይ እኔ ነኝ መገኘትና መሳተፍ ያለብኝ " የሚል ክርክርና ሰጣ ገባ መነሳቱ ነው።

ክርክርና ሰጣ ገባቸው የሃይማኖት አባቶች መሃል ገብተው አስማምተው ሁለቱም በመድረኩ እንዲገኙና ንግግር እንዲያደርጉ ለማሳመን የወሰደው ጊዜ ፕሮግራሙ ሳይጀመር ለሰዓታት እንዲራዘም ሆኗል።

ሁለቱ መሪዎች ያደረጉት ሰጣ ገባ ደጋፊዎቻቸው ደረስ ዘልቆ እስከ አሁን ድረስ በማህበራዊ የትስስር ገፆ እያከራከረ ይገኛል።

ቀድመው ንግግር ያደረጉት ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ድርጅታቸው በቅርቡ ባካሄደው 14ኛው ጉባኤ ያሳለፋቸው ውሳኔዎችና አተገባበራቸው ያተኮረ ሲሆን ቀጥለው የተናገሩት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በንግግራቸው የጊዚያዊ  አስተዳደሩ የስራ አቅዶችና አንድነትን የሚመለከት ነበር። 

ፕሬዜዳንት ጌታቸው በስም ያልገለፁዋቸው " የውጭ  ጠላቶች " የሚያደርጉት ሙከራ ከትግራይ አቅም በላይ አይደለም ፤ ስለሆነም ከጨለማ ለመውጣት በአንድነት መጓዝ አለብን ብለዋል።

ለሦስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ትግራይ የነበሩት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በህወሓትና በጊዚያዊ አስተዳደሩ መካከል የተፈጠረው ውጥረት መርገብ እንዳለበት ማሳሰባቸው መዘገባችን ይታወሳል። 

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

" በችግር ላይ ሌላ ችግር  በህዝቡ ላይ የመጫን ፍላጎት የለንም ፤ አሁን የገጠመን ፈተና እናልፈዋለን። አባቶች በፀሎትና ምክር አግዙን !! " - ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)

የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) ነሃሴ 24 ቀን 2016 ዓ/ም ከአበው ጳጳሳት እና የአገር ሽማግሌዎች ጋር በኣክሱም ከተማ መወያየታቸውን የሚገልጽና አንድ ንግግር ሲያደርጉ የሚታይበት ቪድዮ ተሰራጭቷል።

ቪድዮው በትግራይ ፐብሊክ ሚዲያ (TPM) የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ነው የተሰራጨው።

ሊቀመንበሩ የ5 ደቂቃ ርዝማኔ ባለው ንግግራቸው  ፥ " እኔ ለድርጅትና ለህዝብ ደህንነት ስል ብዙ ታግሻለሁ ፤ ትዕግስትና ዝምታዬ ግን መልካም ነገር ሳይሆን አደጋ ነው ያስከተለው ፤ ስለሆነም ከአሁን በኋላ መታገስ ሳይሆን ተመጣጣኝ ሰላማዊ ትግል ነው የሚያዋጣው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" እኛ የውጭ ጠላት አለብን የውስጥ ጉዳይ አናቆየው በማለታችን በውስጣችን ብዙ ችግሮች እንዲፈጠሩ ሆኗል " ያሉት ደብረፅዮን (ዶ/ር) ፥ " ከአሁን በኋላ የጎራ መደበላለቅ አይኖርም አቋማችን በግልፅ በማንፀባረቅ ሰላማዊ ትግል ማካሄዳችን እንቀጥላለን " ብለዋል።

" በሃይል ፍላጎቴን አሳካለሁ የሚል አካል ሃይ ሊባል ይገባዋል ፥ በትግራይ በጉልበት እሰራለሁ ማለት አያዋጣም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከአሁን በኋላ ከህዝብ የሚደበቅ ሚስጥር አይኖርም " በማለትም ተናግረዋል።

ሊቀመንበሩ ፤ " የተፈጠረውን ልዩነት በሰላም እንጨርሰው ፤ የማይሳካ ከሆነ ግን ሉአላዊነታችንን አሳልፈን አንሰጥም ፤ አቋማችን ግልፅ በማድረግ እንታገላለን " ብለዋል።

" አንድ በማያደርገን አንድ ሁኑ አትበሉን  በፓለቲካ አንድ በማያደርግህ አቋም አንድ መሆን አይቻልም ፤ ተከባብሮ በሰላም መስራት ግን ይቻላል ፤ ትግራይ ለሁሉም በቂ ናት " ሲሉም ደብረጽዮን (ዶ/ር) አክለዋል።

ህዝቡ ላይ በችግር ላይ ሌላ ችግር መጫን  እንደማይፈልጉ የተናገሩት ሊቀመንበሩ ፥ የተፈጠረው ሁኔታ ተስፋ የሚያስቆርጥ እንዳልሆነና በሰላማዊ አግባብ እንደሚፈታ በማመላከት የሃይማኖት አባቶች በፀሎትና በምክር እንዲረዱዋቸው ጠይቀዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያመቐለ #TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TIGRAY

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በዓዲግራት ምን አሉ ?

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዋና ከተማ ዓዲግራት ህዝባዊ ውይይት አካሂደዋል።

" ህዝቡ ስጋት ላይ የሚጥል ሁኔታ ለመቅረፍ ከናንተ መሃል ተገናኝተናል " ብለዋል።

" የትግራይ መልሶ ግንባታ ጋሃድ እንዲሆን በመደጋገፍ መስራት ይገባናል " ሲሉ አስገንዝበዋል።

" በውስጣች በተፈጠረው መፎካከር መስራት የሚገቡን አልሰራንም " ያሉት አቶ ጌታቸው " አብዛኛው ጊዚያችን በጭቅጭቅና በጎሪጥ በመተያየት ነው ያሳለፍነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ በማህበራዊ አገልግሎት መልሶ ግንባታ ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገናል ፤ ጅምሮቻችን ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በውስጣችን የታዩ ድክመቶችን ማረምና የጋራ መፍትሄ ለመሻት መስራት ይጠበቅብናል " ብለዋል።

" በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ሁሉም በጠላት ስር የሚገኙ አከባቢዎች  ወደ ነባር አስተዳደራቸው መመለስ አለባቸው ብለን እየሰራን ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው " የሰላም ስምምነቱ በተሟላ መልኩ እንዲተገበር እንደ መንግስት ጠንክረን እንሰራለን " ሲሉ ተናግረዋል።

" የህዝባችን ሰላም በማረጋገጥ በኩል ዓለም ከኛ ጋር ናት ይህንን እንዲቀጥል ግን ውስጣዊ አንድነታችን እንዳይላላ ያለማቋረጥ መስራት አለብንም " ብለዋል።

በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ዓዲግራት ሲደርሱ በልዩ አጀብ በፈረሰኞች የተደገፈ አቀባበል ነበር የተደረገላቸው።

በአቀባበሉ የተገኙ የዓዲግራት ከተማ ወጣቶች ፦
👉 የጥይት ድምፅ እንጠየፍ !! 
👉 መሰረታዊ ለውጥ እንፈልጋለን !!" 
👉 ተፈናቃዮች ይመለሱ ግዛታዊ አንድነት ይከበር !!
👉 ትግራይ በሳይንስና ጥበብ እንጂ በጥይት አፈሙዝ አትመራም !!
👉 ጊዚያዊ አስተዳደሩ እንደግፋለን !!
የሚሉና ልሎች መፈክሮች በመያዝ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በተመራ የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች ቡድን ምክትል ፕሬዜዳንት ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ ነበሩበት።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia