TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ለተሽከርካሪዎች ዋስትና የሚያስከፍሉት የዓረቦን መጠን ጨመረ።

የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከወቅታዊ #የዋጋ_ንረት ጋር በተያያዘ የዋስትና ሽፋን ለሚሰጧቸው ንብረቶች የሚያስከፍሉትን የዓረቦን መጠን እየጨመሩ መሆኑን ሪፖርተር አስነብቧል።

ኩባንያዎቹ በተለይ በሞተር ኢንሹራንስ ዘርፍ ለተሽከርካሪዎች የመድን ሽፋን ይጠይቁ የነበረውን የዓረቦን መጠን ከመቼውም ጊዜ በላይ መጨመራቸው ታውቋል ብሏል ጋዜጣው።

ኩባንያዎቹ ለሚሰጡት የመድን ሽፋን ይጠይቁ ከነበረው ዋጋ እስከ እጥፍ ጭማሪ እየጠየቁ መሆኑን የኩባንያዎቹ ደንበኞች እየገለጹም ነው፡፡

ደንበኞቹ የተሽከርካሪ የመድን ሽፋን ሲያሳድሱ በወቅቱ የተሽከርካሪዎች ዋጋ መሠረት ዓመታዊ የዓረቦን ክፍያቸውን እንዲፈጽሙ እየተደረገ ነው፡፡

የኩባንያዎቹ ደንበኞች እንደሚገልጹት ከሆነ ፣ የተሽከርካሪዎቻቸውን የኢንሹራንስ ሽፋን ለማሳደስ ሲቀርቡ ከዚህ ቀደም ሲከፍሉ ከነበረው የዓረቦን ዋጋ በላይ እየተጠየቁ ነው፡፡ ከኩባንያዎቹ የተገኘው መረጃም ፣ ጭማሪ ሳይሆን ወቅቱን ያገናዘበ ማስተካከያ እየተገረገ ነው፡፡

ይህ የተለመደ አሠራር ሲሆን፣ የአሁኑን የሚለየው ከሌላው ጊዜ በተለየ የተሽከርካሪዎች ዓረቦን ዋጋ ጭማሪ ከፍተኛ መሆኑ ነው፡፡ 

አንዳንድ ደንበኞችም አደጋ ደርሶባቸው የጉዳት ካሳ በሚጠይቁበት ወቅት የኢንሹራንስ ሽፋናቸው በወቅታዊው ተሽከርካሪዎች ዋጋ መሠረት ገቢ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውንም እያመለከቱ ነው፡፡

የሪፖርተርን ዘገባ ያንብቡ : telegra.ph/Reporter-08-22

@tikvahethiopia
#ቫት

መንግስት በመሰረታዊ ፍጆታ በሆኑ #ምግቦች ላይ #ቫት እንዲያስቀር ተጠየቀ።

መንግሥት ከድጎማ ይልቅ መሠረታዊ የዜጎች ፍጆታ በሆኑ ምግቦች ላይ የሚጣለውን የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲያስቀር ፐርፐዝ ብላክን ጨምሮ ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት መንግሥትን ስለመጠየቃቸው ሪፖርተር አስነብቧል።

የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ፍስኃ እሸቱ በሰጡት ቃል ፤ ለኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴና ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጥያቄው በአካል መቅረቡን የገለፁ ሲሆን የጉዳዩ ዋነኛ ባለቤት የሆነው የገንዘብ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ተገቢውን ምልክታ እንዲያደርግ ጥያቄ ለማቅረብ በሚቀጥለው ሳምንት ቀጠሮ መያዙን ገልፀዋል።

ዶ/ር ፍስኃ እሸቱ ለሪፖርተር የሰጡት ቃል ፦

" ለዋጋ ግሽበት አንዱና ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ያለው ጉዳይ በተለይ በምግብ ውጤቶች ላይ የሚጣለው የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ጉዳይ ነው።

ዝቅተኛ ገቢ ያለው ኅብረተሰብ ክፍል በሚመገበው ምግብ ላይ 15 በመቶ ታክስ መጨመር ትልቅ ተፅዕኖ አሳድሯል።

ከወር በፊት ይኸው ጥያቄ ለሚመለከታቸው አካላት ቀርቧል። የገንዘብ ሚኒስትሩን ለማግኘት ጥረቶች እንደተደረጉ ነው፤ ምናልባት በሚቀጥለው ሳምንት ዕድሉ የሚሳካ ከሆነ ጥያቄውን በግምባር ለማቅረብ እየተሰራ ነው።

ጥያቄውን በአዋጅ ሳይሆን በመመርያ ደረጃ መመለስ የሚቻል ነው። የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ይሁንታ ካገኘ መስተካከል የሚችል ነው።

አነስተኛ የሆነ ገቢ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚጠቀሟቸው በተለይም የአትክልት እና የፍራፍሬ ውጤቶች (ሽንኩርት ፣ ቲማቲም እና ሌሎችም) ከታክስ ነፃ ናቸው ከሚባሉት እንቁላልና ሥጋ በበለጠ ተዘውታሪ በመሆናቸው፣ መንግሥት ከእነዚህ ምርቶች የሚሰበሰበው ቫት እንዲቀር ተጠይቋል።

ፐርፐዝ ብላክ የምርት ውጤቶቹን ቫት በማከል ነው ለሸማች የሚያቀርበድ ይህም ምርቶችን በጣም በረከሰ ዋጋ እንዳያቀርቡ አንዱ እንቅፋት ሆኗል።

ኢትዮጵያ ውስጥ #የዋጋ_ንረት_መባባስ የጀመረው #የተጨማሪ_እሴት_ታክስ አሠራር ከመጣ ወዲህ መሆኑን ጥናት ያስረዳል።

መንግሥት ለሚያከናውናቸው ሥራዎች #ገንዘብ እንደሚያስፈልገው ሳይረሳ ነገር ግን በሁሉም ምግብ ፍጆታዎች ላይ ሳይሆን ኅብረተሰቡ በመሠረታዊነት የሚጠቀምባቸውን ምርቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ማድረግ ይገባዋል። "

🍏🥬🫑🥕🍋🍌🍇🍎🍓🍍🧄🥔🍅🌶

#ቫት ፦ የገንዘብ ሚኒስቴር ከሃያ (20) ዓመታት በፊት ያወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) አዋጅን የሚተካ ረቂቅ ማዘጋጀቱ ይታወሳል።

ረቂቅ አዋጁ መንግሥት ከቫት ታክስ የሚሰበስብበትን መሠረት የሚያሰፋ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሥራ ላይ ያለው አዋጅ በ1994 ዓ.ም. ከወጣ በኋላ በ2001 ዓ.ም. እና በ2011 ዓ.ም. ለሁለት ጊዜያት መጠነኛ ማሻሻያዎች ተደርጎበት የቀጠለ ሲሆን ፣ አዲስ እየወጣ ያለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ሲፀድቅ የበፊቱን ይሽራል ተብሏል፡፡

በረቂቅ አዋጁ በሰንጠረዥ ሁለት አንቀጽ ስምንት ከታክስ ነፃ የሆኑ አቅርቦቶች መዘርዝር ሥር የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመርያ ላይ ዝርዝራቸው የሚወሰን የምግብ አቅርቦቶች እንደሚኖሩ የተደነገገ ሲሆን የትኞቹ ናቸው በሚለው ላይ ምንም ተጨማሪ ማብራሪያ አለመስፈሩ ታውቋል፡፡

Credit : ሪፖርተር ጋዜጣ (www.Ethiopianrepoter.com)

@tikvahethiopia
#የዋጋ_ንረት📈

መስከረም 2015 መጀመርያ ላይ ከ6 ሺሕ ብር በታች ይሸጥ የነበረ አንድ ኩንታል ነጭ ጤፍ ለመጀመርያ ጊዜ ከ10 ሺሕ ብር በላይ ዋጋ ያወጣው ሊጠናቀቅ ሰዓታት በቀሩትና አሮጌ ብለን ልንሸኘው በተዘጋጀው 2015 ዓ.ም. ነው፡፡ የጤፍ ዋጋ ነሐሴ 2015 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ እስከ 15 ሺሕ ብር ሲደርስ ይኸው የዋጋ ጭማሪ 1 ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከዕጥፍ በላይ እንደደረሰ ያመለክታል።

#የስንዴ_ገበያም በተመሳሳይ ከፍተኛ የሆነ ዋጋ የተመዘገበበት ዓመት ይኼው 2015 ዓ.ም. ነው፡፡

በአጠቃላይ ከጤፍና ስንዴ በተጨማሪ በሌሊችም ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ባለሆኑ ሸቀጦች ላይ በዚህ ልንሸኘው ጥቂት ሰዓታት በቀረን 2015 ከፍተኛ የሆነ ዋጋ ተመዝግቧል።

የኢኮኖሚው ባለሙያ አቶ አወት ተክኤ ምን ይላሉ ?

" በሀገሪቱ ከፀጥታና አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች የዋጋ ንረትን በማባባስ ዓይነተኛ ሚና ነበራቸው። አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች እንዳይስፋፉ ጭምር አድርገዋል።

በ2015 ዓ/ም በጀት ዓመት ለዋጋ ንረቱ መባባስ በተደጋጋሚ ከሚጠቀሱ ምክንያቶች ባሻገር፣ መንግሥት የወሰዳቸው የፖሊሲ ዕርምጃዎች ለዋጋ ንረቱ አስተዋጽኦ ነበራቸው።

ለአብነት የኢኮኖሚ የነዳጅ ጭማሪ እና ሌሎች የመንግሥት የፖሊሲ ውሳኔዎች ለዋጋ ንረቱ የራሳቸው አስተዋጽኦ አድርገዋል።

ይህ የዋጋ ንረት በቀጣይ ዓመትም እንዳይተላለፍ ለችግሩ መንስዔ የነበሩት፣ ለምሳሌ የፀጥታና ያለ መረጋጋቶች መፍትሔ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

በቅርቡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ውሳኔዎችን በአግባቡ መተግበር ለዋጋ ንረት መርገብ መፍትሔ ሊሆኑ ይገባል፡፡ "

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Ethiopianreporter-09-11

#ሪፖርተር_ጋዜጣ

@tikvahethiopia