TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኤክሶደስ_የፊዝዮቴራፒ_ልዩ_ክሊኒክ

በውቢቷ ባህርዳር አዲስ ቅርንጫፍ ከፍተናል ፤ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች፦
- ለአንገት፣ ለትክሻ፣ለወገብ ህመም
- ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ   ችግር
- ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር
- ለፊት መጣመም
- ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል
- ለስፖርታዊ ጉዳቶች
- በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች
አድራሻችን፦ ቁጥር 1_ አዲስ አበባ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን ፤ ቁጥር 2_ ባህርዳር ቀበሌ 14 አልዋቅ ሆቴል አጠገብ ስልክ ቁጥር 0979099909 / 0911039377
በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://publielectoral.lat/ExodPhysioClinic
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

- በእስራኤል - ሃማስ ጦርነት ጋዛ ውስጥ የሞቱ ፍልስጤማውያን ቁጥር 2,670 የደረሰ ሲሆን የቆሰሉ 9,600 ደርሰዋል። እስራኤል ውስጥ የሞቱ ደግሞ 1,400 እንደሆኑና የቆሰሉ 3,418 መሆናቸው ተነግሯል።

- የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ሃማስ እስራኤል ላይ የፈፀመውን ጥቃት ለማውገዝ ከፍልስጤሙ ፕሬዜዳንት ሞሃሙድ አባስ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን ገልፀዋል። ባይደን ፤ ሃማስ ለፍልስጤም ህዝብ ክብር እና የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ከቆመ እንዳልሆነ በድጋሚ እንደገለፁላቸው አመልክተዋል። ባይደን " በጋዛ ላሉ ሲቪሎች የሰብአዊ አቅርቦቶች እንዲደርሱ እና ግጭቱ እንዳይስፋፋ ለማድረግ በቀጠናው ካሉ አጋሮች ጋር እየሰራን መሆኑን አረጋግጫለሁ " ብለዋል።

- የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ " የሃማስ ተግባራትና እርምጃዎች እንዲሁም ፖሊሲዎች የፍልስጤምን ህዝብ አይወክሉም " ሲሉ ተናግረዋል። አባስ ከቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት " የፍልስጤም ነፃ አውጪ ድርጅት ፤ የፍልስጤም ብቸኛ ህጋዊ ተወካይ " ነው ብለዋል።

- የማሌዢያ ጠ/ሚ አንዋር ኢብራሂም የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ሃማስን ለማውገዝ በምዕራባውያን የሚደረገውን ግፊት እንደማይስማሙበት ተናግረዋል። አንዋር ማሌዢያ እንደ ፖሊሲ ከሃማስ ጋር ግንኙነት እንዳላት እና ይህም እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

- እስራኤል  ወደ ጋዛ እርዳታ እንዲገባ ፈቅዳለች ተብሏል። ከአሜሪካ እና ከግብፅ ጋር የተደረገ ውይይትን ተከትሎ እስራኤል በመጨረሻ የሰብአዊ እርዳታ ውሃ፣ ምግብ፣ መድሃኒት ወደ ጋዛ እንዲገባ ፈቅዳለች ተብሏል። የውጭ ዜጎችም በግብፅ በኩል እንዲወጡ መንገድ ተመቻችቷል። በጋዛ እና በግብፅ መካከል ያለው የራፋህ ድንበር አቋራጭ ዛሬ እንደሚከፈት ተገልጿል። የተወሰነ ሰዓት የሚቆይ ተኩስ አቁም እንደሚኖር ተመላክቷል። ሃማስ ግን ስለ ሁኔታው የሚያውቀው እንደሌለው ገልጿል።

- ኢራን ፤ እስራኤል ጥቅሟንና ዜጎቿን ለማጥቃት እስካልደፈረች ድረስ ሃይሏ ከእስራኤል ጋር ወደ ጦርነት እንደማይገባ በተመድ ልዑኳ በኩል ገልጻለች። ይህ ከማለቷ ሰዓታት በፊት በውጭ ጉዳይ በኩል በሰጠችው ቃል እስራኤል ጥቃቷን ካላቆመች ሁኔታው እንደሚባባስና ሌሎች ወገኖች እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቃለች።

- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ " ሃማስ " ሁሉንም አግቶ የወሰዳቸውን ሰዎች በአስቸኳይ እንዲፈታ እና እስራኤልም ወደ ጋዛ ሰብአዊ ርዳታ እንዲገባ እንድታደርግ ጠይቀዋል።

- እስራኤል ትላንት ለሊቱን የጋዛ ሰርጥን በቦንብ ስትደበደብ ማደሯ ተነግሯል። ቃላቸውን ለዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የሰጡ የጋዛ ነዋሪዎች እስራኤል ሚሊሻና ተዋጊ በሌለባቸው መንደሮች ንፁሃንን ያለየ ጭካኔ የተሞላበት ጥፋት እያደረሰች ነው ሲሉ ከሰዋል። በእስራኤል በኩል ባለፉት ሰዓታት የሮኬት ጥቃት ከሃማስ በኩል ሲሰነዘርባት የነበረ ሲሆን ግጭቱ ከተጀመረ አንስቶ 6000 ሮኬት ተወርውሮባታል።

- የሃማስ ባለስልጣናት እስራኤል " የጦር ወንጀል እየፈፀመች ነው " ሲሉ ከሰዋል። ንፁሃን፣ ህፃናት፣ ሴቶች በምትፈፅመው ጥቃት ሳይለዩ ተገድለዋል ብለዋል።

Via @BirlikEthiopia

የውጭ ጉዳዮችን፦ https://publielectoral.lat/+LM-bJ8NzZMcxMjA8
TIKVAH-ETHIOPIA
#ወልቂጤ - " በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። ቤቶች ተቃጥለዋል " - የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር - " በቦታው አድማ የመበተን ሥራ እየተሰራ ነው " - የጉራጌ ዞን ፓሊስ ኮሚሽን - " ግጭቱ እንዲባባስ በሚፈልጉ አካላት ንብረት ወድሟል፣ በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል " - የጉራጌ ዞን ኮማንድ ፓስት አዲስ በተዋቀረው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማና ቀቤና…
#Update

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማና በቀቤና ልዩ ወረዳ በተቀሰቀሰው ግጭት ንጹሐን መገደላቸውንና ነዋሪዎችና ባለስልጣናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

ሥሜ ባይጠቀስ ያሉ አንድ የቀቤና ልዩ ወረዳ ነዋሪ " ሰሞኑን ሁለት የቀቤና ወጣቶች ተገድለዋል " ብለዋል።

ሌላኛው የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ ደግሞ " አንድ የወልቂጤ ሰው በወጣቶች ተገድሏል " ሲሉ ገልጸዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ የቀቤና ልዩ ወረዳ ባለስልጣን በሰጡት አጭር ቃል፣ " ሰዎች እየተገደሉ ነው። መንግሥት አስቸኳይ መፍትሄ ይስጥ " ብለዋል።

አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ባለሥልጣን በግጭቱ የንጹሐን ሕይወት ማለፉን አረጋግጠዋል።

ባለሥልጣኑ በሰጡት ቃል፣ " ሁለት ወጣቶች ከጸጥታ ኃይል በተተኮሰ ጥይት ሞተዋል። አንድ ሰው በወጣቶች ተገድሏል " ነው ያሉት።

አክለውም፣ " ቅዳሜ ጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ሁለት የቀቤና ወጣቶች ከጸጥታ ኃይል በተተኮሰ ጥይት ሞተዋል። እሁድ ጥቅምት 4 ቀን 2016 ዓ.ም በአመጹ ከጉራጌ አንድ ሰው በወጣቶች ተግድሏል። ዘረፋ ቤት ማፍረስ ቤት ቃጠሎ በከፍተኛ ደረጃ ቀጥሏል " ብለዋል።

በቁጥር ባይታወቅም የቆሰሉ ሰዎች እንዳሉ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደተቋረጠ፣ የጸጥታ ኃይሉ ግን ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ሌሎች የመረጃ ምንጮች ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ " ከቀቤና ልዩ ወረዳ መጥተው ቤት አቃጥለዋል፣ ንብረት ዘርፈዋል፣ ፌደራል ፓሊስ በመሳሪያ መትተው ገድለዋል። ከተማውና የዞኑ ፓሊስ አቅሙን እንዳይጠቀም ተደርጓል። ልዩ ኃይል እረብሻ ያለበትን ሥፍራ ትቶ መሀል ከተማ ላይ አስለቃሽ ጭስ ማኅበረሰስቡ ላይ ወርውሯል። በተጨማሪም የዞኑን ፓሊስ ኮማንደር ጠጄን አግተውታል፣ ብዙ ወጣቶች ተደብድበዋል" ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ባለስልጣን የኮማንደር ጠጄን እገታ በተመለከተ በሰጡት ምላሽ ፣ " ጉዳት ደርሶበታል መሬት ለመሬት ተጎትቶ በወጣቶቹ ሲደበደብ ነበር። እገታው የሚለው መረጃ እኔ ባለኝ መረጃ ልክ አይደለም " ነው ያሉት።

ለሰው ሕልፈተ ሕይወት ምክንያት የሆነው ግጭት ከምን ጥያቄ የተነሳ እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሲጠየቁም፣ የሚከተሉትን ሦስት ጭብጦቹ ዘርዝረዋል።

- የቀቤና ልዩ ወረዳ ውስጥ በ24 ቀበሌ  የሚኖሩ ብሄራቸው ጉራጌ የሆኑ የሕዝብ ክፍሎች በዚህ አንካለልም ማለታቸው ተከትሎ አለመግባባት አለ።

- የቀቤና ልዩ ወረዳ መቀመጫ ወልቂጤ መሆን የለበትም የሚሉ የጉራጌ ተወላጆች ወልቂጤ ከተማ መስተዳድር  በጉራጌ የሚተዳደር አንድ መዋቅር የዞኑ መቀመጫ ጭምር ነው በማለት ያነሳሉ።

- ቀቤና ልዩ ወረዳ ደሞ የወልቂጤ ከተማ መስተዳድር በዙሪያው ባለው ቀበሌ ላይ የተሠመሰረተ በመሆኑ ከዚህ የትም ወጥቼ የልዩ ወረዳ መቀመጫ አልመሰርትም ብሎ ያምናል።

ከእነዚህ መሠረታዊ ኮዝ በመነሳት በወጣቶች መካከል ግጭት ተነስቶ ነው ለአጠቃላይ ሞት፣መንገድ መዘጋት፣ ንብረት መውደም ዘረፋ እንዲፈፀም  ምክንያት የሆነው " ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ አደረጉት በተባለ ውይይት፣ አራቱ መዋቅሮች የአካባቢያቸውን ሰላምና የሕዝቦችን ደኅንነት ተቀናጅተው በጋራ ማስጠበቅ ሲገባቸው ወደ ሁከትና ብጥብጥ በመግባታቸው ከተጠያቂነት የማያድን በመሆኑ ከድርጊቱ ወጥትው በአስቸኳይ ማስቆም እንዳለባቸው ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ጥቅምት 4 ቀን 2016 ዓ.ም በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል።

https://telegra.ph/Tikvah-10-16

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ #ቻይና

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ቻይና አቅንተው በቻይና ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ናቸው።

ከጠ/ሚ ፅ/ቤት በወጣ መረጃ የቻይናው ጠ/ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ለዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ይፋዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በኃላም የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል። በዚህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የምጣኔ ኃብት ትብብር ግንኙነት ማጠናከሪያ መንገዶች ላይ መክረዋል ተብሏል።

ከሁለትዮሽ ውይይቱ በመቀጠል ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ጠ/ሚ ሊ ኪያንግ በተገኙበት በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ መስኮች 12 ያህል የትብብር ስምምነቶች እና ሁለት የፍላጎት ሰነዶች ተፈርመዋል።

ዶ/ር ዐቢይ በቻይና ይፋዊ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ ከአራት ዓመት በኃላ ሲሆን በቀጣይ በሚካሄደው 3ኛው የቤልት ኤንድ ሮድ አለም አቀፍ ትብብር መድረክ ላይም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፎቶ፦ #PMOffice

@tikvahethiopia
የእህቱ ልጅ በሆነ የሰባት አመት ህፃን ላይ የግብረሰዶም ወንጀል የፈፀመ ተከሳሽ በፅኑ እስራት መቀጣቱ ተገለጸ።

ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸመው በሰኔ ወር 2014 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በተለምዶ ማሪያም ወንዝ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚኖርበት ቤት ውስጥ ነው።

የ37 ዓመት ዕድሜ ያለው ተከሳሹ እና የተከሳሹ እህት በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን ተከሳሹ ሰው የሌለበትን አጋጣሚ ጠብቆ የሰባት ዓመት ዕድሜ ያለው የእህቱን ልጅ በስለት በማስፈራራት የግብረ ሰዶም ወንጀል ፈፅሞበታል።

ፖሊስ በቀረበለት ጥቆማ መነሻነት ተከሳሹን ተከታትሎ በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ አስፈላጊ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ በአቃቤ ህግ ክስ እንዲመሰረትበት አድርጓል፡፡

የተከሳሹን ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ጥፋተኝነቱን በማረጋገጥ ሰሞኑን በዋለው ችሎት በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

ወላጆች ልጆቻቸው ለእንደዚህ አይነት ወንጀል ሰለባ እንዳይሆኑ ዕድሜያቸውን መሰረት በማድረግ አስቀድመው በግልፅ መወያየት እና ተገቢውን ክትትልና ጥበቃ ማድረግ እንደሚኖርባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን ያስተላልፏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የትግራይ አካባቢዎች ከፍተኛ የሃዘን ድባብ ውስጥ ናቸው። ጥቅምት 2 በይፋ የታወጀው የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአት ተከትሎ የክልሉ ከተሞችና ገጠሮች በከፍተኛ የሃዘን ድባብ ውስጥ ይገኛሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በትግራይ ያለው የሃዘንና የመርዶ ስነ-ሰርአትና ተዛማጅ ጉዳዮች አፈፃፀም በሚከተለው ሪፓርታዥ አጋርቶናል።  ዓርብ ጥቅምት 2/2016 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ በክልሉ…
#ትግራይ

የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ስነ-ሰርዓት ከታወጀ ዛሬ 3ኛ ቀኑ ሲሆን ፤ ሌላ ጊዜ በሳምንታዊ የሰኞ ገበያዋ ከመላ ክልሉ ፣  ከዓፋርና የአማራ ክልል አዋሳኝ አከባቢዎች በመጡ ገበያተኞች ትድምቅ የነበረች መቐለ የንግድ ተቋማትዋ ተዘግተው ፣ መኪኖች መንቀሳቀስ አቁመው ጭር ማለትዋ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል። 

በሌላ በኩል ፤ በውጭ አገራት የሚኖሩ የትግራይ ዳያስፓራ ማህበረሰብ የክልሉ የሰማእታት የሃዘንና የክብር ስነ-ሰርአት በማስመልከት ሃይማኖታዊ ፀሎትና ሌሎች ዝግጅቶች ማከናወናቸውን ያገኘናቸው መረጃዎች ያሳያሉ።

በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ፦
- በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ፣
- በኔዘርላንድ ፣
- በጀርመን ሙኒክና ፍራንክፈርት ከተሞች ፣
- በእንግሊዝ ለንደን፣
- በስዊድን ስቶክሆልም ከተማ ፣
- በአሜሪካ ዋሽንግተን ደሲና አከባቢዋ ፣
- በአረብ አገራትና በሌሎች የሚኖሩ የትግራይ ዳያስፓራ አባላት ሰማእታት የሚዘክር የፀሎት ፣ የሻማ ማብራትና የተለያዩ ስነ-ሰርአቶች አከናውነዋል።

በተያያዘ ዓለም አቀፍ የትግራይ ማሕበረሰብ ሙሁራንና ባለሞያዎች ማህበር (GSTS)  የሰማእታት የሃዝንና የክብር ቀን ስነ-ሰርዓት አስመልክቶ ባወጣው የፅሁፍ መግለጫ የተሰማው ጥልቅ ሃዘን በመገለፅ  ሰማእታቱ የተሰውለት የትግራይ ድህንነትና ግዛታዊ አንድነት እንዲከበር ከመታገል ጎን ለጎን የሰማእታቱ ቤተሰቦች ለማቋቋምና ትግራይ መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የበኩሌ እወጣለሁኝ ብሏል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ከሰሞኑን የባህር በር ጉዳይ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።

ጉዳዩ ክብደት እንዲያገኝ ያደረገው ደግሞ በሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ መነሳቱ ነው።

አንዳንዶች ጉዳዩ መነሳቱን እና መነጋገሩን ሲያደንቁ ሌሎች ደግሞ " ጊዜውን የጠበቀ አይደለም ፤ አጀንዳ ለመስጠት ነው ፤ በቅድሚያ የሀገር ሰላምና የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ይቀድማል " በሚል ተቃውመዋል።

ለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምንድነው ያሉት ?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የህዝብ እንደራሴዎችን ሰብሰበው የሰጡት ማብራሪያ በቴሌቪዥን ጣቢያዎች ተሰራጭቶ ነበር።

በዚህም የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አንስተዋል።

- ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ፍላጎትን በግልፅ አስቀምጠዋል።

-  የሕዝብ ቁጥሯ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የሄደው እና ከቀይ ባሕር እና ከሕንድ ውቅያኖስ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ሃሳብ የሕልውና ጉዳይ ነው መሆኑን አመልክተዋል።

- ቀይ ባሕር እና አባይ ኢትዮጵያን የሚበይኑ፣ ከኢትዮጵያ የተቆራኙ ለኢትዮጵያ ዕድገት እና ጥፋት መሠረት እንደሆኑ በመግለፅ ከዚህ ርዕሰ ጉዳይ መሸሽ እንደማይስፈልግ ገልጸዋል።

- ለባህር በር መተላለፊያ መገኘት ኤርትራ፣ ጂቡቲ እና ሶማሊላንድ አማራጮች ሊሆኑ እንደሚችሉ በማንሳት ይህ የኢትዮጵያ ፍላጎት ሊሳካባቸው የሚችልባቸውን #ከግጭት_ውጪ ያሉ አማራጮችን አስረድተዋል።

ይህም ፦

የታላቁ ሕዳሴ ግድብን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮ ቴሎኮም ጨምሮ በትልልቅ የአገሪቱ ተቋማት ውስጥ ድርሻ መስጠት እና የመሬት ልውውጥ ማድረግ እንደሚቻል ነው።

- በአጠቃላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ የባህር በር ጉዳይ ከመነጋገር ከመመካከር መሸሽ እንደማያስፈልግ አስገንዝበዋል።

የሰሞኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ነጥሎ ስለ አንድ ሀገር ትኩረት ያላደረገ ቢሆንም ከኢትዮጵያውን አልፎ #ኤርትራውያንም ስለጉዳዩ አስተያየት ሲሰጡበት ተስተውሏል።

አንዳንዶች ስርዓት ባለው መልኩ ቢሰራበት እና እስካሁን ያልተፈቱ ችግሮች ተፈተው መግባባት ላይ ተደርሶ ቢሰራበት መላው ኤርትራውያንን እና ኢትዮጵያውያንን የሚጠቅም ጉዳይ እንደሆነ ሲያነሱ ሌሎች ደግሞ በፍፁም ይህ ጉዳይ ለውይይትም ሆነ ለንግግር ሊቀርብ አይገባም ባይ ናቸው።

ዛሬ ደግሞ የኤርትራ መንግስት ሰሞነኛው አጀንዳ ስለሆነው የውሃና የባህር በር ጉዳይ " ሰም ያልጠቀሰ " አጭር መግለጫ አሰራጭቷል።

የኤርትራ መንግስት ማስታወቂያ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአስመራ ያወጣው ስም ያልጠቀሰው አጭር መገለጫ " በቅርቡ ጊዚያት ስለ ውሃ እና የባህር በር የመሳሰሉ ርእሰ ጉዳዮች የተባለና ' ተብለዋል ' የተባለው መጨበጫ የለውም። ይህም ያላስገረመው ታዛቢም የለም "  ይላል። 

ስም ያልጠቀሰው ይህ አጭር መግለጫ የኤርትራ መንግስት እንደ ሁልግዜው ይህንን ወደ መሰሉ የባህር በር እና ተያያዥ ጉዳይ መድረኮች የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ገልጿል።

" ይህን መሰል ነገር እንደማንታደም ደጋግመን እናረጋግጣለን " ያለው የኤርትራ መንግስት መግለጫ " ሁሉም አስተዋዮች እና ተቆርቋሪዎች በዚህ እዳይቆጡ " ሲል አክለዋል።

መግለጫው በግልፅ ስለ የትኛው አካልና በየትኛው አካል ስለተነሳ ጉዳይ እንዲሁም ስለየትኛው መድረክ እንደሚያወራ ግልፅ ያለው አንዳች ነገር የለም።

@tikvahethiopia