TIKVAH-ETHIOPIA
#ወልቂጤ - " በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። ቤቶች ተቃጥለዋል " - የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር - " በቦታው አድማ የመበተን ሥራ እየተሰራ ነው " - የጉራጌ ዞን ፓሊስ ኮሚሽን - " ግጭቱ እንዲባባስ በሚፈልጉ አካላት ንብረት ወድሟል፣ በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል " - የጉራጌ ዞን ኮማንድ ፓስት አዲስ በተዋቀረው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማና ቀቤና…
#Update

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማና በቀቤና ልዩ ወረዳ በተቀሰቀሰው ግጭት ንጹሐን መገደላቸውንና ነዋሪዎችና ባለስልጣናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

ሥሜ ባይጠቀስ ያሉ አንድ የቀቤና ልዩ ወረዳ ነዋሪ " ሰሞኑን ሁለት የቀቤና ወጣቶች ተገድለዋል " ብለዋል።

ሌላኛው የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ ደግሞ " አንድ የወልቂጤ ሰው በወጣቶች ተገድሏል " ሲሉ ገልጸዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ የቀቤና ልዩ ወረዳ ባለስልጣን በሰጡት አጭር ቃል፣ " ሰዎች እየተገደሉ ነው። መንግሥት አስቸኳይ መፍትሄ ይስጥ " ብለዋል።

አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ባለሥልጣን በግጭቱ የንጹሐን ሕይወት ማለፉን አረጋግጠዋል።

ባለሥልጣኑ በሰጡት ቃል፣ " ሁለት ወጣቶች ከጸጥታ ኃይል በተተኮሰ ጥይት ሞተዋል። አንድ ሰው በወጣቶች ተገድሏል " ነው ያሉት።

አክለውም፣ " ቅዳሜ ጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ሁለት የቀቤና ወጣቶች ከጸጥታ ኃይል በተተኮሰ ጥይት ሞተዋል። እሁድ ጥቅምት 4 ቀን 2016 ዓ.ም በአመጹ ከጉራጌ አንድ ሰው በወጣቶች ተግድሏል። ዘረፋ ቤት ማፍረስ ቤት ቃጠሎ በከፍተኛ ደረጃ ቀጥሏል " ብለዋል።

በቁጥር ባይታወቅም የቆሰሉ ሰዎች እንዳሉ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደተቋረጠ፣ የጸጥታ ኃይሉ ግን ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ሌሎች የመረጃ ምንጮች ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ " ከቀቤና ልዩ ወረዳ መጥተው ቤት አቃጥለዋል፣ ንብረት ዘርፈዋል፣ ፌደራል ፓሊስ በመሳሪያ መትተው ገድለዋል። ከተማውና የዞኑ ፓሊስ አቅሙን እንዳይጠቀም ተደርጓል። ልዩ ኃይል እረብሻ ያለበትን ሥፍራ ትቶ መሀል ከተማ ላይ አስለቃሽ ጭስ ማኅበረሰስቡ ላይ ወርውሯል። በተጨማሪም የዞኑን ፓሊስ ኮማንደር ጠጄን አግተውታል፣ ብዙ ወጣቶች ተደብድበዋል" ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ባለስልጣን የኮማንደር ጠጄን እገታ በተመለከተ በሰጡት ምላሽ ፣ " ጉዳት ደርሶበታል መሬት ለመሬት ተጎትቶ በወጣቶቹ ሲደበደብ ነበር። እገታው የሚለው መረጃ እኔ ባለኝ መረጃ ልክ አይደለም " ነው ያሉት።

ለሰው ሕልፈተ ሕይወት ምክንያት የሆነው ግጭት ከምን ጥያቄ የተነሳ እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሲጠየቁም፣ የሚከተሉትን ሦስት ጭብጦቹ ዘርዝረዋል።

- የቀቤና ልዩ ወረዳ ውስጥ በ24 ቀበሌ  የሚኖሩ ብሄራቸው ጉራጌ የሆኑ የሕዝብ ክፍሎች በዚህ አንካለልም ማለታቸው ተከትሎ አለመግባባት አለ።

- የቀቤና ልዩ ወረዳ መቀመጫ ወልቂጤ መሆን የለበትም የሚሉ የጉራጌ ተወላጆች ወልቂጤ ከተማ መስተዳድር  በጉራጌ የሚተዳደር አንድ መዋቅር የዞኑ መቀመጫ ጭምር ነው በማለት ያነሳሉ።

- ቀቤና ልዩ ወረዳ ደሞ የወልቂጤ ከተማ መስተዳድር በዙሪያው ባለው ቀበሌ ላይ የተሠመሰረተ በመሆኑ ከዚህ የትም ወጥቼ የልዩ ወረዳ መቀመጫ አልመሰርትም ብሎ ያምናል።

ከእነዚህ መሠረታዊ ኮዝ በመነሳት በወጣቶች መካከል ግጭት ተነስቶ ነው ለአጠቃላይ ሞት፣መንገድ መዘጋት፣ ንብረት መውደም ዘረፋ እንዲፈፀም  ምክንያት የሆነው " ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ አደረጉት በተባለ ውይይት፣ አራቱ መዋቅሮች የአካባቢያቸውን ሰላምና የሕዝቦችን ደኅንነት ተቀናጅተው በጋራ ማስጠበቅ ሲገባቸው ወደ ሁከትና ብጥብጥ በመግባታቸው ከተጠያቂነት የማያድን በመሆኑ ከድርጊቱ ወጥትው በአስቸኳይ ማስቆም እንዳለባቸው ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ጥቅምት 4 ቀን 2016 ዓ.ም በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል።

https://telegra.ph/Tikvah-10-16

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia