TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ፈረንሳይ iPhone 12ን አገደች። ፈረንሳይ iPhone / አይፎን 12 ከልክ በላይ ጨረራ ያመነጫል በሚል የስልኩ ሽያጭ እንዲታገድ አዘዘች። ትናንት መስከረም 1/2016 ዓ.ም. የሬዲዮ ሞገዶችን የሚቆጣጠረው አካል አይፎን 12 ከሚፈቀደው የኤሌክትሮማግኔቲክ ራዲዬሽን በላይ እያመነጨ ነው ብሏል። ተቋሙ ስልክ አምራቹ አፕል ችግሩን በሚያደርጋቸው ማሻሻያዎች በአስቸኳይ የማይቀርፍ ከሆነ በመላው አገሪቷ…
#ቴክኖሎጂ #iPhone

ፈረንሳይ " አይፎን 12 " ን ከልክ በላይ ጨረራ ያመነጫል በሚል የስልኩ ሽያጭ እንዲታገድ ማዘዟን ተከትሎ የአውሮፓ ሀገራት ጉዳዩን እየተከታተሉ ነው ተብሏል።

ፈረንሳይ አይፎን 12ን ያገደችው ከሚፈቀደው የኤሌክትሮማግኔቲክ ራዲዬሽን በላይ እያመነጨ ነው በማለት ሲሆን ይህን እገዳ ተከትሎ ፦
- ቤልጂየም፣
- ኔዘርላንድስ
- ጀርመን ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ እየተከታተሉት ነው ተብሏል።

የጀርመን ባለሥልጣናት ሁኔታው ወደ አውሮፓ አቀፍ እርምጃዎች ሊመራ ይችላል ብለዋል።

የቤልጂየም መንግስት እ.ኤ.አ. በ2020 ለመጀመሪያ ጊዜ የተለቀቀው አይፎን 12 #የጤና_ጠንቅ መሆኑን እንዲገመግም ለተቆጣጣሪ አካል መመሪያ መስጠቱ ተነግሯል።

የቤልጂየም የዲጂታላይዜሽን ሚኒስትር ማቲዩ ሚሼል ፤ " ዜጎቻችን በሙሉ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ከማንኛውም አደጋ የተጠበቁ እንዲሆኑ ማድረግ የእኔ ኃላፊነት ነው። ጤና መቼም ቢሆን ችላ ሊባል የማይገባ ጉዳይ ነው። " ብለዋል።

ሁሉም የአፕል ሞዴሎችን እንዲመረምር ተቆጣጣሪውን አካል እንደተጠየቀ አመልክተዋል። ሌሎችም ብራንዶች ላይ ተመሳሳይ ስራ ይሰራል ብለዋል።

የኔዘርላንድ ዲጂታል መሠረተ ልማት ኤጀንሲ ፤ በፈረንሣይ ምርመራ ላይ በመመርኮዝ ከልክ በላይ የጨረር መጠን እንደሚያመነጭ ጥርጥር የለውም ያለ ሲሆን አፕልን እንደሚያነጋግር አሳውቋል።

ነገር ግን “ ምንም አጣዳፊ የደህንነት ስጋት የለም ” ብሏል።

የጀርመኑ BNetzA ኔትወርክ ኤጀንሲ ፤ የፈረንሣይ ምርመራ በሁሉም የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ላይ የሚተገበሩ እርምጃዎችን ሊያስወስድ የሚችል ነው ብሏል።

አፕል የፈረንሳዩን እገዳ ከሰማ በኃላ ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ፤ አይፎን 12 የጨረራ መጠኑ በሰዎች ላይ ጉዳት እንደማያስከትል በመላው ዓለም ባሉ ተቆጣጣሪዎች እውቅና ያለው ምርት ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

በሌላ መረጃ ፤ አፕል አዲሱን " አይፎን 15 "  ከነገ ጀምሮ ማዘዝ እንደሚቻል አሳውቋል።

አዲሱ ምርት እንደየአይነቱ በተለያየ የገንዘብ መጠን ለገበያ ቀርቧል።

አይፎን 15 በስንት ዶላር ነው ለገበያ የቀረበው ?

👉 አይፎን 15 ከ$799 እስከ $1,099 (በኢትዮጵያ ብር በባንክ ቢሰላ ከ44,952 ብር እስከ 61,830 ብር ይሆናል)

👉 አይፎን 15 ፕላስ ከ$899 እስከ $1,199 (በኢትዮጵያ ብር በባንክ ቢሰላ ከ50,578 ብር እስከ 67,456 ብር ይሆናል)

👉 አይፎን 15 ፕሮ ከ$999 እስከ $1499 (በኢትዮጵያ ብር በባንክ ቢሰላ ከ56,204 ብር እስከ 84,335 ብር ይሆናል)

👉 አይፎን 15 ፕሮ ማክስ ከ$1,199 እስከ $1,599 (በኢትዮጵያ ብር በባንክ ቢሰላ ከ67,456 ብር እስከ 89,961 ብር ይሆናል)

ገንዘቡ #ዝቅተኛው እና #ከፍተኛውን ጣሪያ የሚያሳይ ሲሆን እንደ ስልኩ GB እና አይነት ይለያያል።

@tikvahethiopia