TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ዘይት

ዛሬ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በዘይት አምራች ፋብሪካዎች የመስክ ጉብኝት አድርገው ፤ ከባለሃብቶች ጋርም ውይይት አድርገው ነበር።

ጉብኝቱ የተገደረገው በፊቤላ ዘይት ማምረቻ ኢንዱስትሪ እና በደብሊው ኤ (WA) ዘይት ፋብሪካ ነው።

በዚህም ወቅት በቀን 1 ሚሊዮን 500 ሺ ሊትር ዘይት የማምረት አቅም ያለው ፊቤላ የዘይት ፋብሪካ ፦ በግብዓት አቅርቦት ችግር እና በመብራት መቆራረጥ ምክንያት ካለው የማምረት አቅም ከ40 በመቶ በታች እያመረተ መሆኑን አሳውቋል።

ፊቤላ ዘይት ፋብሪካ ስራ ከጀመረ አንድ አመት ያስቆጠረ ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ከ70 ሚሊዮን ሊትር በላይ ዘይት በማምረት ለህብረተሰቡ እንዳሰራጨ ገልጿል።

በተመሳሳይ የደብሊው ኤ (WA) ዘይት ፋብሪካ በግብዓት አቅርቦት እና በካፒታል እጥረት ምክንያት ካለው የማምረት አቅም እስከ 30 በመቶ ብቻ እያመረተ እንደሆነ አሳውቋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ በፋብሪካው በአካል በመገኘታቸው የችግሮችን ጥልቀት መረዳታቸውን ገልፀዋል።

ሀገር በቀል የሆነ ዘይት እንዲመረት መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንሚያደርግ ተናግረው ፤ የተነሱትን የመብራት፣ የካፒታል እጥረት እና የግብዓት አቅርቦት ችግሮች በአጭር ጊዜ ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ጥረት እንደሚደረግ አሰረድተዋል፡፡

አሁን እየተስተዋለ ያለውን የዘይት እጥረት ለመቅረፍ መንግስት በልማት ድርጅቶች በቀጥታ ተገዝቶ እንዲቀርብ እያደረገ እና 322 ባለሀብቶች በፍራንኮ ቫሉታ ያለቀለት የምግብ ዘይት እንዲያስገቡ እየተደረገ መሆኑንና ፍትሀዊ ስርጭት እንዲኖር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
#ዘይት

የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበት 88.1 ቶን ወይም 4,405 ካርቶን ባላ 5 ሊትር ፈሳሽ የምግብ  የሱፍ ዘይት  ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ሲል በአዳማ መገቢያና መውጫ ኬላ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳወቀ።

በአዳማ መገቢያ መውጫ ኬላ በኩል በቀን 15/12/2015 በተደረገ ቁጥጥር 88.1 ቶን ወይም 4405 ካርቶን ባለ 5 ሊትር ፈሳሽ የምግብ የሱፍ ዘይት

- የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበት ይህም ማለት (የተመረተበት በቀን 04/05/22 የሚያበቃበት ጊዜ ደግሞ በቀን 04/05/2023)፤
- በባለስልጣን መ/ቤቱ ያልተመዘገበ፤
- ከስሪት ሀገሩ የጤና ሰርተፍኬት ያልተያያዘ፤
- የምርቱ ገላጭ በድጋሚ የተጻፈ (relabeled ) የተደረገ፤
- የምርት መለያ ቁጥር (batch number ) የሌለው፤
- በምርት ማሸጊያው ላይ ምርቱ መያዝ ያለበትን ንጥረ ነገር አለመገጹ የተረጋገጠ ነው ተብሏል።

በተደረገው ፍተሻ የተገኙትን ጉድለቶች መሰረት በማድረግ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ጥቅም ላይ እንዳይውል በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳውቋል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ይፋ ባደረገው መረጃ ላይ ይህ ዜጎች ጋር ቢደረስ የጤና ጉዳት የሚያስከትል ዘይት ማን ሊያስገባው እንደነበር / ይዞት ሲንቀሳቀስ እንደነበር ፣ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋለ ግለሰብ ይኖር እንደሆነ የገለፀው ነገር የለም።

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን ማንኛውንም ምርት ስትገዙ እባክችሁ የመጠቀሚያው ጊዜ ያለፈበት መሆን አለመሆኑን አጣሩ።

@tikvahethiopia