TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አቢሲንያ_ባንክ

በማንኛውም ዓይነት ስልኮች ያለ ኢንተርኔት *815# በመደወል የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ። አገልግሎቱን ለማስጀመር አቅራቢያዎ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ።

#BankofAbyssinia #BankingService #BankinginEthiopia #SavingAccount #815 #EducationSaving #boamobile  #TheChoiceForAll #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#መነሻዬ

ለልጆቻቸው ምርጥ ምርጡን መሸመት የፈለጉ ወላጆች ወደ መነሻዬ እየተመሙ ነው! እርሶስ ምን ይጠብቃሉ ታዲያ?!

አድራሻ፦
📍 ጉርድ ሾላ ሆሊ ሲቲ ሴንተር 3ኛ ፎቅ
የልጅዎን መነሻ ያቅልሉ!
ይደውሉ 0989939393 ወይም 0930323334

Telegram > http://publielectoral.lat/meneshayeofficial
Tiktok > http://tiktok.com/@meneshayeofficial
Facebook > http://facebook.com/@meneshayeofficial
#ደሴ

የደሴ ፖሊስ መምሪያ ፤ በውሸት " ታግቻለሁ " በማለት ቤተሰቦቹን  500 መቶ ሺህ ብር የጠየቀ ግለሰብ ከወንጀል ተባባሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

ሳይታገት ታግቻለሁ በማለት ቤተሰቦቹን 500 መቶ ሽ ብር የጠየቀው ግለሰብ አልጋ ቤት ውስጥ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው።

ተጠርጣሪው ግለሰብ ከደቡብ ወሎ ዞን ከመካነሰላም ወደ ደሴ በመምጣት ደሴ ከተማ ቧንቧ ውሀ ክፍለ ከተማ በ " ካራ ጉቱ " ከሚባለው አካባቢ ጫካ ውስጥ በመግባት ከጓደኛው ጋር በመመካከር  ጓደኛው የታገተ በማስመሰል እራሱን  በገመድ ዛፍ ጋር በማሰር ፎቶውን ለቤተሰቦቹ በመላክና በስልክ 500 መቶ ሽ ብር ላኩልኝ በማለት ይነግራቸዋል።

ቤተሰቦቹም ደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊሰ መምሪያ 2ኛ/ዋ/ፖ/ጣቢያ ያመለክታሉ።

ፖሊስ ባደረገው ክትትል ግለሰቡ ታግቻለሁ እያለ ሲያወራና ቤተሰቦቹንና የአካባቢውን ሰው እያስጨነቀ እያለ ከሌሊቱ 07:00 ስዓት በህብረተሰቡ ጥቆማ መነኸሪያ አካባቢ አልጋ ቤት  ውስጥ ከወንጀል ተባባሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር ሊያውለው ችሏል።

መረጃው የደሴ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#እገታ

ከሰሞኑን ጎንደር ላይ አንድ እስራኤላዊ ዜጋ ታግቷል ተብሎ መረጃ ሲሰራጭ ነበር።

ይህን ተከትሎ የሀገሪቱ መንግሥት ዜጋውን ለማስለቀቅ ፍለጋ ጀምሮ ነበር።

ነገር ግን ጎንደር ላይ ታግቷል ተብሎ የተነገረው ኤስራኤላዊ ጉዳይ ውሸት ሆኖ በመገኘቱ የእስራኤል ባለስልጣናት ፍለጋቸውን እንዳቋረጡ የእስራኤል ጋዜጦች ዘግበዋል።

ጋዜጦቹ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሳምንታት በፊት ወደ ትውልድ ሀገራቸው ያመሩት የ79 ዓመቱ ፍራንሲስ አደባባዪ በውሸት " ታግቻለው " በማለት የማስለቀቂያውን ገንዘብ በመፈለግ ድርጊቱን እንደፈፀሙ #እንደሚያምን ፅፈዋል።

ባለፈው ሳምንት የፍረንሲስ አደባባዪ ዘመዶች እንዳስታወቁት ከሆነ ፍረንሲስ እጅ እና እግራቸውን ታስረው በታጠቀ ሰው ሲጠበቁ የሚያሳይ የተቀዳ መልእክት፣ ምስሎች እና አጭር ቪዲዮ ክሊፕ አጋቾቹ ልከውላቸዋል።

ታጋቾቹ ከእስር እንዲፈቱ 2.5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ወይም 45,000 ዶላር እየጠየቁ ነበር ተብሏል።

በተቀዳው መልዕክት ላይ ፍራንሲስ " እርዱኝ ወንድም እና እህቶቼ ፤ በጫካ ውስጥ ነኝ፤ ታግቻለሁ ፤ ከባድ ዝናብ እየዘነበ ነው ... ይህንን ችግር በጠላቶቼም ላይ እንዲሆን አልመኝም " ሲሉ ተደምጠዋል።

የእስራኤል ባለስልጣናትም ከ #ኢንተርፖል ጋር በመሆን በጉዳዩ ላይ እየሰሩበት ነበር።

ነገር ግን ፍራንሲስ አደባባዪ ከእስራኤል የሚደወሉ የስልክ ጥሪዎችን እመለሱ መሆኑን ካወቁ በኋላ ባለስልጣናት ፍለጋውን ማቋረጣቸውን ጋዜጦቹ ዘግበዋል።

ዘመዶቻቸው ግን አሁንም ድረስ ፍራንሲስ አደባባዪ መታገታቸውን እና ለደህንነታቸው  አጥብቀው እንደሚሰጉ ተናግረዋል። ለእስራኤል መንግሥት አቤት እንደሚሉም አሳውቀዋል።

ፍራንሲስ የ79 አመት የእድሜ ባለፀጋና ባለትዳር እንዲሁም የ8 ልጆች አባት መሆናቸውን የገለፁት ቤተሰቦቻቸው እገታውን ያቀነባበረ አካል ስለመኖሩ ምልክት እንዳላገኙ  በእርግጠንኘት ደግሞ እገታውን እሳቸው (ፍራንሲስ) እንዳላቀነባበሩ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው ተማሪዎች ምን ያህል ፐርሰት ተማሪዎቸው አለፉ ?

(እስካሁን ድረስ ይፋ ያደረጉ)

- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ 👉 89.35 በመቶ
- አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ 👉 87.04 በመቶ
- ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ 👉 84.7 በመቶ
- ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ 👉 81 በመቶ
- ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ 👉 81 በመቶ
- ቀብሪድሃር ዩኒቨርሲቲ 👉 80.69 በመቶ
- ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ 👉 80.6 በመቶ
- ወልድያ ዩኒቨርሲቲ 👉 80.3 በመቶ
- አርሲ ዩኒቨርሲቲ 👉 79.66 በመቶ
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ 👉 79.2 በመቶ
- ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ 👉 77.6 በመቶ
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ 👉 72.2 በመቶ
- ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ 👉 71 በመቶ
- ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ 👉 70.62 በመቶ
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ 👉 65.7 በመቶ
- መቱ ዩኒቨርሲቲ 👉 53.00 በመቶ
- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ 👉 41 በመቶ ተማሪዎቻቸው ዘንድሮ የተሰጠውን የመውጫ ፈተና #ማለፍ እንደቻሉ አሳውቀዋል።

እስካሁን በተቋማቸው ያለፉ ተማሪዎችን በፐርሰት ይፋ ካደረጉት ከላይ ከተዘረዘሩት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከ50 በመቶ በታች (ማለትም ያለፉት 41 በመቶ ብቻ) በማስመዝገብ ዝቅተኛው ሲሆን በተቋሙ የሶስት አካዳሚክ ፕሮግራም ተፈታኞች ሙሉ በሙሉ ፈተናውን ማለፍ እንዳልቻሉ ታውቋል።

የተመዘገበውን ውጤት ቀድሞውንም የተገመተና በሞዴል ፈተና ወቅትም ከተመዘገበው ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ተመላክቷል።

ውጤቱ ወደ ትክክለኛ የተጠጋ ነው ያለው ተቋሙ ይህ ያረጋገጠው ከየትኛውም ስርቆት እና ኩረጃ ነፃ በሆነ መንገድ ፈተናው እንዲሰጥ የተያዘውን የማያወላዳ አቋም ነው ብሏል።

የተቋሙ ማኔጅመት የተመዘገበው ከግማሽ ብታች ውጤት እንደ ዩኒቨርሲቲ የታመነበት እውነተኛ ችግር ያለ በመሆኑ ውጤቱ ዝቅተኛ የሆነበትን ምክንያት የሚያጠና ኮሚቴ እንዲዋቀር ወስኗል።

ኮሚቴው የችግሩ መነሻዎችና ችግሩ ያደረሰውን ጉዳት በማጥናት ችግሮቹን ለመፍታት የሚያስችሉ ምክረ ሃሳቦችን ያቀርባል ተብሏል፡፡

#tikvahethiopia

@tikvahethiopia
በአንድ ፍሌክሲ ሁሉንም የሞባይል አገልግሎት!

በተለያየ የጊዜ አማራጮች በቴሌብር ሱፐርአፕ፣ በማይ ኢትዮቴል እና *999# ከቀረቡት የፍሌክሲ የሞባይል ጥቅሎች መርጠው በአንድ ጥቅል የሞባይል ድምጽ፣ ዳታ እና አጭር መልዕክት አገልግሎቶችን እንዳሻዎ ይጠቀሙ!

በቴሌብር ሲገዙ ተጨማሪ 10% ስጦታ ያገኛሉ

(ኢትዮ ቴሌኮም)
" የ10 በመቶ የተርን ኦቨር ታክስ ተነስቷል "

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢዎች ቢሮ የሜትር ታክሲ አገልግሎት ከሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ይሰበስብ የነበረውን አሥር በመቶ የተርን ኦቨር ታክስ (ቲኦቲ) ማንሳቱን ሪፖርተር አስነብቧል።

ቢሮው ከገንዘብ ሚኒስቴር አገኘሁት ባለው ማብራሪያ መሠረት፣ በኮድ 03 የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጡትን ተሽከርካሪዎች ነው የተጨማሪ እሴት ታክስና ተርን ኦቨር ታክስ ተግባራዊ እንዳይሆንባቸው የወሰነው፡፡

ተሽከርካሪዎቹ በንግድ ሥራ ፈቃዳቸው ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ቢልም፣ ሊብሬያቸው የኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ እንደሆኑ በመጥቀሱ አሥር በመቶው የአገልግሎት ሰጪዎች ተርን ኦቨር ታክስ ተግባራዊ ይደረግባቸው ነበር፡፡

ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በታክስ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ታዬ ማስረሻ ተፈርሞ ለአሥራ አንዱም ክፍላተ ከተሞችና ለአምስት ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የተላከው ደብዳቤ፣ አገልግሎቱን የሚሰጡ የሜትር ታክሲ ተሽከርካሪዎች ከሁለቱ ታክሶች ነፃ እንዲሆኑ አስታውቋል፡፡

ደብዳቤው ላይ " የሚሰጡት አገልግሎት የትራንስፖርት በመሆኑ የንግድ ሥራ ገቢ ግብርን በተመለከተ ግብር ከፋዮች የሚያቀርቡት የሒሳብ መዝገብ፣ የሒሳብ መዝገብ ካልያዙ ደግሞ በመረጃ እንዲስተናገዱ "  ይላል።

በገቢዎች ቢሮ የግብር አወሳሰንና አሰባሰብ ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኘሁ ካሳዬ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ፥

" የሜትር ታክሲዎች የብቃት ማረጋገጫቸው የመኪና ኪራይ የሚልና ኮድ 3 ሰሌዳ የሚወስዱ ቢሆንም፣ በኮድ 1 ተሽከርካሪዎችም ተመሳሳይ አገልግሎት ይሰጣል፡፡

ይህ ደግሞ ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጡትን የተለያየ የታክስ አከፋፈል ስለሚተገበርባቸው ቅሬታ ሲያስነሳ ነበር።

የኅብረተሰቡን የትራንስፖርት ጫና በማየትና ተሽከርካሪዎችን እንደ ኮድ 1 በመቁጠር፣ ቢሮው ታክሱን አንስቷል።

በኮድ 3 የኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን ከታክሱ ነፃ መሆን ዕድል ተጠቃሚ እንዳይሆኑ፣ እነሱን ለመለየት በሲስተሙ ላይ እየሠራ ነው።

የሜትር ታክሲ አገልግሎት ከሚያቀላጥፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችም መረጃ እየሰበሰብን ነው። "  ሲሉ አስረድተዋል፡፡

Credit : #ሪፖርተር

@tikvahethiopia
#ምርቃት

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከነገ ረቡዕ ጀምሮ ተማሪዎቻቸውን ያስመርቃሉ።

ተቋማት ለዓመታት ያስተማሯቸውን ተማሪዎች ቤተሰቦቻቸው ፣ የክብር እንግዶች በተገኙበት ነው የሚያስመርቋቸው።

ዘንድሮ ከተሰጠው የመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ በምርቃት መርሃግብር ላይ ከመሳተፍ ጋር በተገናኘ በተመራቂዎች ዘንድ ጥያቄዎች የነበሩ ቢሆንም ትምህርት ሚኒስቴር ይህ ጉዳይ የተቋማቱ #የሴኔት ውሳኔ ጉዳይ መሆኑን ገልጾ ነበር።

በዚህም መሰረት በተቋማት ሴኔት ውሳኔ ለምርቃት ብቁ የሆኑ / የምረቃ ፎርማሊቲ የሚያሟሉ ተማሪዎች የምርቃት ስነሥርዓት ላይ ይሳተፋሉ ፤ ነገር ግን ጊዜያዊ የትምህርት ማስረጃቸውን የሚወስዱት የመውጫ ፈተና ያለፉት ብቻ ናቸው።

የተቋማት የምረቃ ቀን መቼ ነው ?

ነገ ረቡዕ ተማሪዎቻቸውን ከሚያስመርቁ ተቋማት መካከል ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ይገኝበታል።

የፊታችን ሐሙስ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ/ም ፦

- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ ካምፓስ) ፤ ጊምቡ እና ሻምቡ በነጋታው።
- ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (በዋናው ግቢ) ፤ በ15/2015 (ቡሬ ካምፓስ)
- ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ
- አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ) ፤ በነጋታው በሳውላ ካምፓስ
- ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ
- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ
- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
- ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
- ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ
- ዲላ ዩኒቨርሲቲ
- እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
- ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ (በዋናው ግቢ)  በነጋታው (ዱራሜ ካምፓስ)
- መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ
- ቀብሪ ድሃር ዩኒቨርሲቲ
- ወራቤ ዩኒቨርሲቲ
- መቱ ዩኒቨርሲቲ
- አምቦ ዩኒቨርሲቲ
- ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻቸውን ያስመርቃሉ።

ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ካስመረቁ በኃላ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ከሐምሌ 16 ጀምሮ ይቀበላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

#tikvahethiopia

@tikvahethiopia
#አማራ_ባንክ

አማራ ባንክ የኅብረተሰቡን የመገናኛ ብዙኃን አጠቃቀም ልምድ እና ፍላጎት ላይ ያተኮረ ጥናት እያደረገ ይገኛል፡፡ በመሆኑም እርስዎም ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጫን ይህን መጠይቅ እንዲሞሉ ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

https://docs.google.com/forms/d/1oGb8jFYvXVn5Z4GHxYjljGs9F4anGLrBiuZ1CaNgEhs/edit

እናመሰግናለን!

አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!

የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Telegram: https://publielectoral.lat/Amhara_Banksc
Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1
Website: https://amharabank.com.et/

#አማራባንክ #AmharaBank
#ፓስፖርት

ከዓለም አገራት ፓስፖርቶች ሁሉ ሴንጋፖር ፓስፖርት " ጠንካራው " ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ፓስፖርት ደግሞ ከነበረበት ደረጃ መሻሻል አሳይቷል።

ከዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር / ሄንሌይ እንደተገኘው መረጃ የሲንጋፖር ፓስፖርትን የያዙ ሰዎች ከ227 መዳረሻዎች 192 ወደሚሆኑት ያለ ቪዛ ለመጓዝ በማስቻል ከሁሉ ልቆ ተገኝቷል።

በዓለም ካሉ ደካማ ፓስፖርቶች መካከል የሚመደበው የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከዚህ ቀደም ከነበረበት 97ኛ ደረጃ ጥንካሬው ተሻሽሎ ወደ 89ኛ ከፍ ብሏል።

የሀገራት የፓስፖርት ደረጃ ምን ይመስላል ?

- በጥንካሬው አንደኛ ደረጃ የተቀመጠው የሲንጋፖር ፓስፖርት ነው። ከ227 መዳረሻዎች ወደ 192ቱ ያለ ቪዛ ማስገባት ይችላል።

-  የጀርመን፣ የጣሊያን እና የስፔን ፓስፖርትን የያዙ ተጓዞች ወደ 190 መዳረሻዎች ያለ ቪዛ መጓዝ ይችላሉ።

- ጃፓን ለበርካታ ዓመታት ቁጥር አንድ ባለ ጠንካራ ፓስፖርት የነበራት ሲሆን አሁን ላይ ከኦስትሪያ፣ ከፊንላንድ፣ ከፈረንሳይ፣ ከላክሰመበርግ፣ ከደቡብ ኮሪያ እና ከስዊድን ጋር በእኩል 189 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

- ዩናይትድ ኪንግደም 4ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጠ አሜሪካ ደግሞ 8ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

የኢትዮጵያ ፓስፖርት ደረጀ . . .

ከዚህ ቀደም ድርጅቱ ባወጣው የደረጃ ሰንጠረዥ የኢትዮጵያ ፖስፖርት ከ109 ፓስፖርቶች ጋር ተነጻጽሮ በ46 ነጥብ 97ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ነበር።

በ2023 ሦስተኛ ሩብ ዓመት ሪፖርቱ ላይ የኢትዮጵያ ፓስፖርት በ47 ነጥብ 14 ደረጃዎችን አሻሽሎ ከ103 ፓስፖርቶች 89ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ይህ ማለት የኢትዮጵያን ፓስፖርት የያዙ ተጓዦች አሁን ላይ ቀድሞ ቪዛ ሳያስፈልጋቸው ወደ 47 መዳረሻዎች መጓዝ ይችላሉ ማለት ነው።

ደካማዎቹ ፓስፖርቶች የትኞቹ ናቸው ?

አፍጋኒስታን፣ ኢራቅ፣ ሶሪያ፣ ፓኪስታን እና የመን አምስቱ እጅግ ደካማ ፓስፖርት ያላቸው አገራት ሆነዋል።

ከአፍሪካ ደካማ ፓስፖርት ያላቸው 10 አገራት፦
- ሊቢያ
- ሱዳን
- ኤርትራ
- ደቡብ ሱዳን
- ናይጄሪያ
- ኢትዮጵያ
- ጅቡቲ
- ላይቤሪያ
- ኮንጎ ሪፓብሊክ እና ቡሩንዲ ናቸው።

ሄንሌይ ደረጃው እንዴት ነው የሚያወጣው ?

ሄንሌይ የፓስፖርቶችን ጥንካሬ የሚለካው፤ ተጓዦች በያዙት ፓስፖርት ምክንያት ቪዛ ቀድመው ሳያስፈልጋቸው ወደ ስንት አገራት መጓዝ ይችላሉ የሚለውን በማጤን ነው።

ቀድሞ ቪዛ አለማስፈለግ ማለት ወደ መዳረሻ ለመጓዝ ቪዛ አለመጠየቅ አልያም በመዳረሻ ቪዛ የማግኘት መብት ማለት ነው።

ተቋሙ የፓስፖርት ደረጃን የሚያወጣው ያለ ቪዛ ለሚደረግ የጉዞ መዳረሻ አንድ ነጥብ በመስጠት ነው።

የፓስፖርት ጥንካሬ የሚወሰነው በምንድን ነው ?

የዓለም ባንክ እንደሚለው የአንድ አገርን የፓስፖርት ጥንካሬ ከሚወስኑ ዋነኛ ጉዳዮች መካከል እነዚህ ይጠቀሳሉ።

- ዜጎች የሚያገኙ የነፍስ ወከፍ ገቢ መጠን ፤ ከፍተኛ የነፍስ ወከፍ ገቢ ያላቸው አገራት ከደሃ አገራት በተሻለ ወደ በርካታ አገራት ቪዛ ቀድሞ ማግኘት ሳይጠበቅባቸው መጓዝ ይችላሉ።

- የአንድ የአገር #ሁለንተናዊ_ሰላም ከአገሪቱ የፓስፖርት ጥንካሬ ጋር በቀጥታ ይገናኛል። በአንድ አገር የሽብር ጥቃቶች እና የውስጥ ግጭቶች የበረከቱ ከሆነ እንዲሁም በተደራጁ ቡድኖች የሚፈጸሙ ወንጀሎች ካሉ የዚያች አገር ዜጎች ዓለም አቀፍ ጉዟቸው የተገደበ ይሆናል።

- ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት የሌላቸው እና ከፍተኛ ተፈናቃይ ያለባቸው አገራት ዜጎችም በተመሳሳይ ቪዛ የሚጠየቁባቸው መዳረሻዎች ከፍተኛ እንዲሆኑ አድርጓል።

ሪፖርቱን በዚህ ይመልከቱ ፦ www.henleyglobal.com/passport-index/ranking

Via BBC

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

የወላጆችን ጊዜ ቆጥቦ፤ ተማሪዎችን ከእንግልት ገላግሎ፤ የትምህርት ቤቶችን አሰራር ያዘመነውን ዘመናዊ ፤ቀላል እና ቀልጣፋ የብርሃን ስኩል ፔይ (school pay) አገልግሎት ይጠቀሙ!
#schoolpay #berhanbank #bank #finance #Stressfreebanking #bankinethiopia
#ብርሃን_ባንክ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
#MyWish

አስተማማኝ የሆነውንና ቱርክ ሰራሹን ኢሳን ሲልድ ባትሪን በተለያዩ አማራጮች ማለትም በ12V35AH፣ በ12V45AH፣ በ12V55AH፣ በ12V60AH፣ በ12V70AH፣ በ12V90AH፣ በ12V100AH፣በ12V120AH እና በ12V150AH በጅምላና በችርቻሮ በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡
0910041280  0911135133  0921612272  0911159234   0984733988  0941473413
ዋና መስሪያ ቤት፡ ሀይሌ ጋርመንት ወደለቡ መብራት በሚወስደው መንገድ ቅርንጫፍ፡ ወሎ ሰፈር ጎርጎሪዮስ አደባባይ አጠገብ
ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ 
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://publielectoral.lat/MYWISHENT
" ፕሬዜዳንቱ በጣም ስራ ስለሚበዛባቸው ማታ፣ ለሊትም ቢሆን ቤታቸው ሲቀመጡ ፣ ዜና ሲያዩ የህዝባቸውን ስቃይ ይመለከታሉ " - የናይሮቢ ነዋሪ

ዛሬ በጎረቤት ሀገር ኬንያ በተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ በትንሹ 4 ሰዎች መቁሰላቸውና ትምህርት ቤቶችም ተዘግተው መዋላቸው ተሰምቷል።

ሰዎች የተጎዱት በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ፣ ማታሬ አካባቢ መንግሥት የኑሮ ውድነትን ዝቅ እንዲያደርግ ለመጠየቅ አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር በመጋጨታቸው ነው።

ፖሊስ ሰልፈኞችን ለመበተን ውሃ እና አስለቃሽ ጭስ ሲጠቀም መዋሉ ተነግሯል።

ከኑሮ ውድነት ጋር በተያያዘ በኪሱሙ፣ ሚጎሪ፣ ኪሲሊም ጨምሮ በተለያዩ የኬንያ አካባቢዎችም ሰልፍ ስለመደረጉ ተሰምቷል።

የኬንያ ትምህርት ሚኒስቴር ባዘዘው ትዕዛዝ መሰረት በናይሮቢ እና ሞምባሳ ከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ውለዋል።

ተቃዋሚዎሽ የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ለኑሮ ውድነት መፍትሄ እንዲፈልጉ ለማስገደድ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ቀን የሚካሄድ የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ አድርገዋል።

ፍሬድ አንዜሪ የተባለ ስራ አጥ በሰጠው ቃል ፤ ሰልፉ ለውጥ ያመጣል ብሏል።

" በየሳምንቱ የምንናደርገው የተቃውሞ ሰልፍ ለውጥ ያመጣል።

ምክንያቱም በፕሬዜዳንቱ ዙሪያ ያሉ አማካሪዎች እውነቱን አይናገሩም።

ፕሬዜዳንቱ በጣም ስራ ስለሚበዛባቸው ማታ፣ ለሊትም ቢሆን ቤታቸው ሲቀመጡ ፣ ዜና ሲያዩ የህዝባቸውን ስቃይ ይመለከታሉ " ሲል ተናግሯል።

ዛሬ በናይሮቢ የንግድ ሱቆች ተዘግተው የዋሉ ሲሆን ነጋዴዎቹ ሱቃቸውን የዘጉት የፀጥታ ዋስትና ስለሌላቸው በመፍራታቸው ነው ተብሏል።

አንድ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ገለሰብ እየተካሄደ ያለው ተቃውሞ እንዲቆምና ፕሬዜዳንቱ የገቡትን ቃል እንዲፈፅሙ ጊዜ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ገልጸዋል።

ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ በሀገሪቱ ምንም አይነት የተቃውሞ ሰልፍ አይደረግም ሲሉ የዛቱ ሲሆን ሰልፉን የጠሩት ቀንደኛ ተቃዋሚያቸውን ራይላ ኦዲንጋን ተጠያቂ እንዲሚያደርጉ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia