TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቦዴፓ

የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ልኮልናል።

ፓርቲው በላከልን መግለጫ እስካሁን ትጥቃቸውን ያልፈቱ የጉህዴን ታጣቂዎች በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ግልገል በለስ ከተማ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ/ም በፈፀሙት ጥቃት በርካታ ንፁኃን ዜጎች መገደላቸውና በርካቶች መቁሰላቸውን ገልጿል።

ድረጊቱ በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለለው አስነዋሪና አሳፋሪ መሆኑን በመግለፅ አውግዟል።

በንፁሀን ዜጎች  ላይ ይህን የመሰለ ወንጀል የፈጸሙ አካላት በአፋጣኝ ለህግ እንዲቀርቡ ፓርቲው አጥብቆ ጠይቋል።
 
ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ የታጣቂ  ቡድን አባላት በመተከል እና ከማሽ ዞኖች  ትጥቅ ሳይፈቱ በከተሞችና በገጠር ቀበሌዎች በመንግስት ሎጀስትክስ  እየተንቀሳቀሱ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ስጋት እየፈጠሩ ይገኛሉ ሲል አሳውቋል።

ፓርቲው ወቅታዊ የሆነውን ክልላዊ ሁኔታን በማስመልከት ፦

- የመተከልን ህዝብ ማህበራዊ  እረፍት በመንሳት ቀጠናውን የጦረነት ማዕከል ለማድረግ የሚሰሩ አካላት ከድርጊታቸው እንድቆጠቡ ፤ አረሶ አደሩን ለማስራብ በማለም የእርሻና የምርት ወቅት በመጠበቅ የሚደረግ አመራር ፈጠር  ግድያ በእጅጉ እንደሚያወግዝ ገልጿል።

- ጥቅምት 9 ቀን 2015 ዓ/ም ከጉህዴን ጋር የክልሉ መንግስት በደረሰው ስምምነት መሰረት የታጠቁ የጉህዴን ኃይሎች ተሃድሶ ስልጠና ከወሰዱ በኃላ ትጥቅ ፈተው ወደ ህብረተሰቡ ይቀላቀላሉ ቢባልም ትጥቅ ሳይፈቱ ማህበረሰቡ ውስጥ የሚያደረጉት እንቅስቃሴ በተለይም የመንግስት የፀጥታ አካላትን ሚና #ተክተው የሚያደረጉት እንቅስቀሴ በአስቸኳይ እንዲቆምና ትጥቅ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አሳስቧል።

- በመተከል ዞን ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አጀንዳቸውን በኃይል ለማስፈጸም የሚታትሩ #የውስጥ እና #የውጭ ሃይሎች ከድረጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

- ሰሞኑን በግልገል በለስ ከተማ በዜጎች ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ግድያና ከድርጊቱ ጀርባ ያሉ አካላትን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ የክልሉና  የፌደራል ፖሊስ በማጣራት አጥፊዎችን ለህግ እንዲያቀርቡና ለህዝቡ ይፋ እንዲያደረጉ ጠይቋል።

- የክልሉ መንግስት በሰላም ውስጥ ልማትን ማሰብና መፈፀም የማይችሉ፣ በግጭት ውስጥ በህዝብ ደም በስልጣን ላይ ለመኖር የሚፈልጉ ሀሳብና ውጤት አልባ ጊዜ ያለፈባቸው አመራሮችን በአስቸኴይ በማጥራት እንዲያስተካክል ፓርቲው አሳስቧል።

(ከቦዴፓ የተላከው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia